
እንደ ሰው ፤ ሰፊውን ተፈጥሮዋዊ ፍላጎቶቾቻችንን በግላችን ጥረት ብቻ ማሙዋላት ስለ እማንችል ከሌሎች ሰዎች ጋር የተለያዩ ይዘት የአላቸው ትስስሮችን መፍጠር ፤ ተፈጥሮዋዊ የሆነ የውዴታ ግዴታችን ነው ። ይኽም ተፈጥሮዋዊ ባሕሪያችን ነው ፤ “ሰው ማሕበራዊ ወይንም ፖለቲካዊ ፍጥረት ነው” የአስባለን ።
እኛም እንደ ሰው ወይንም እንደ ማሕበራዊ ፍጥረት ፤ ማሕበራዊ ፍጥረት በአደረገን በእዚኽ ሰብዓዊ ባሕሪያችን እየተነዳን ፤ ከቤተሰብ እስከ ሐገር ያሉትን ትልልቅ ማሕበራት[1] መስርተናል።
ይኽ ትስስርን የመፍጠር ኹኔታ ግን በግለሰብ ደረጃ ብቻ የተወሰነ ሰአይሆን እንደ ማሕበረሰብም የእምናሳየው ባሕሪ ነው ።
ራሱን ሙሉ በሙሉ የቻለ ምንም ዓይነት ማሕበረሰብ በአለ መኖሩ ወይንም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በአላቸው ተነፃፃሪ ብልጫ ምክንያት ፦ ማሕበረሰባትም የጥንካሬያቸውን ምርት በመስጠት እና ደካማ በሆኑበት ከእነርሱ የጠነከረውን ማሕብረሰብ ምርት በመቀበል እርስ በእርሳቸው ትስስር ይፈጥራሉ ።
ስለ እዚኽ ሰብዓዊነታችን በግል በዜጎች መካከል ከእሚመሠረተው ሕብረት ጀምሮ ፤ እንደ ሐገር እና ሉላዊነትን ላሉት ኹሉ የሰው ልጅ ማሕበረሰባት በሙሉ መሠረት ነው።
በታሪክ እንደ እምናውቀው ፤ እነ እዚኽ ሰውን ማሕበራዊ ወይንም ፖለቲካዊ ፍጥረት የአስባሉት እና ለሰው ጥቅም በሰው ተፈጥሮዋዊ ባሕሪ እየተነዱ የእሚፈጠሩ ግለሰባዊም ሆኑ ማሕበራዊ ትስስሮች ወይንም በግለሰብም ሆነ በማሕበረስባት መካከል ያሉ ትስስሮች ፤ የዛሬው ሰብዓዊው ሰው ከተፈጠረበት እና እንደ ማሕበር አብሮ መኖር ከጀመረበት አንስቶ የነበሩ ክስተቶች ናቸው ።
ማሕበረሰብ እና ሉላዊ ትስስር ከጥንትም የነበረ ቢሆንም ቅሉ ፤ ትስስሮቹ እንደ ማንኛውም ታሪካዊ ክስተት የራሳቸው የዝግመት እና የእድገት ታሪክ የአላቸው ናቸው።
በዘመናዊ የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች ምክንያት በግለሰቦች እና በተለያዩ ማሕበረሰባት መካከል የአለው ግንኙት በእጅጉ በመቀላጠፉ እና በመሻሻሉ ፤ በእዚኽ ዘመን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በግለሰቦች እና በማሕበረሰባት መካከል የአለው ግንኙነት ፤ በሐገራት ፖለቲካዊ ፣ ኢከነሚያዊ እና ባሕላዊ ስረዓት ላይ የእሚጫወተው ሚና እጅግ እንዲ ያይል የአደረገ ስለሆነ ፤ ይኽ የእምኖርበትን ዘመን ፤ ዘመነ ሉላዊነት (the age of globalisation) ወይንም ዓለም ዓቀፋዊ ግኑኝነት ሚናው የአየለበት አስብለውታል ።
እንደ አልነው ፤ ግለሰባዊም ሆኑ ማሕበራሰባዊ ትስስሮች ፤ የእዚኽ ዘመን አዲስ ክስተቶች አይደሉም ። መጠኑ እና ይዘቱ ይለያይ እንጂ ግለሰባዊም ኾነ ማሕበራዊ ትስስር ከጥንትም የነበረ ነው ። በግለሰቦች ትስስር የእሚፈጠሩ ቤተሰብ ፣ መንደር ፣ ነገድ ፣ ወዘተ ፤ ብንተዋቸው እንኳን ፤ ቢያንስ ከዛሬ 3,500 ዓመታት ገደማ ጀምሮ ፤ ሐገር አቋራጭ ፥ የባሕር እና የየብስ ንግድ ፣ ረዥም ርቀት ተጉዞ ፥ ባሕር ተሻግሮ ወታደራዊ ዘመቻ ማድረግ ፣ ወዘተ ፤ የተለመዱ ክስተቶች መሆን ጀምረዋል ፤ ምንም እንኳን የግንኙነቱ አድማስ እንደ አኹኑ ዘመን ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ በአይዘልቅም ።
ይኽን የአኹኑ የእምንገኝበትን ዘመን ፤ ከእዚኽ ቀደም ከነበሩት ዘመናት ለየት የእሚያደርገው ፤ የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች ባለፉት ከ150 ዓመታት በአነሰ ግዜ የደረሱበት ደረጃ ፤ ትስስሮቹን በጣም በመአቀላጠፍ እና በመአመቻቸት ፤ የግንኙነቱን አድማስ እጅግ በማስፋታቸው ፤ በዓለም ላይ የእሚኖር ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ማሕበረሰብ ፤ ይኽ ዓለም ዓቀፋዊ ትስስር የእሚያደርስበትን በጎም ሆነ መጥፎ ተጽኖ ከቀን ወደ ቀን የጎላ እንዲሆን በማድረጉ ነው።
የጉዞን ኹኔታ ብንወስድ ፤ የእዚኽ ዘመኑ ሰው ርቀት ወይንም የጉዞ እንግልት ገድቦት ፤ ሳይደርስበት የእሚቀረው የዓለም ክፍል የለም ።
በአየር ጉዞ ፤ ከአንድ የዓለም ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ ፤ ቢበዛ በኹለት ቀን የእምንደርስበት ሆኗል ።
ከእዚኽ ቀደም የእማይደፈሩ ወይንም መንፈቅ እና ከእዚያኽ በላይ የእሚፈጁ የባሕር ላይ ጉዞዎች ፤ አኹን ፦ በሺ የእሚቆጠሩ ሰዎችን ወይንም ቁሳቁሶችን ጭነው ፤ በምቾት እና በፍጥነት በሳምንታት እድሜ የእሚከወኑ ሆነዋል ።
የየብሱንም ብንወስድ ፤ መኪኖች እና ባቡሮች የርቀትን ወሰን በእሚያስገርም ኹኔታ እያስቀሩት ነው ። ጥይት የእሚባሉት ባቡሮች ፤ ሰዎች መኖሪያቸው እና የሥራ ቦታቸው በመቶ ኪሎሜትሮች የተራራቁ እንዲ ሆኑ አስችለዋል ። በዓለም ዓቀፍ ደረጃም ብዕንመለከት ፤ ለምሳሌ ፦ አንድ ጎዳና በአንድ ቀበቶ (One Road One Belt) ፤ በእሚል ዕሳቤ በባሕር እና በየበስ ፤ ያለብዙ ማቆራረጥ (Transit) ዓለምን ለማስተሳሰር እየተሰራ ነው ።
የመገናኛ ቴክኖሎጂ ፤ በመጓጓዣ መስኩ ብቻ ሳይሆን ፤ ስፍራን ሳይለቁ የእሚደረጉ ፤ የድምፅ ፣ የምስል እና የጽሑፍ ግንኙነቶችን ፤ በላቀ ኹኔታ በመአቀላጠፉ ፤ የድምፅ ፣ የጽሑፍ እና የቪድዮ ግንኙነቶች ፤ በሞያው ቋንቋ “Real Time” ወይንም አኹን በአኹን የእሚደረጉበት እና ከአንዱ የዓለም ጫፍ ወደ ሌላው የዓለም ጫፍ ፤ ያለ ምንም እክል ፤ አጠገባችን እንደ አለ ያኽል የእምናወራበት ግዜ ላይ ነን ።
ይኽ የመገናኛ ቲክኖሎጂ የአስቻለው ቅልጥፍና ደግሞ ፤ የዓለምን ሕዝብ በከፍተኛ ኹኔታ በማስተሳሰር ፤ ኢከነሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ባህላዊ ቁርኝታችንን እጅግ በማቆላለፉ ፤ ይኽ በእዚኽ መልክ መተሳሥራችን የአለው ተፅኖን እጅግ አጉልቶት ፤ ክስተቱ የዘመኑ ዓይነተኛ መገለጫ ኾኗል ።
ይኽ የዘመናችን ሉላዊነት እንደ ማንኛውም መልካም ታሪካዊ አጋጣሚ ፤ ለእሚጠቀሙበት ሰዎች ወይንም ማሕበረሰባት ፤ የተመቻቸ የፖለቲካዊ እና ኢከነሚያዊ ምህዳር (platform) ሲሆን ፤ በተለያዩ ውስጣዊ እና ውጫዊ እክሎች ፤ ሉላዊነትን ማቀብ (Harness) ያልቻሉ ማሕበረሰባት ደግሞ ፤ በተለያየ አግባብ ሰለባ የእሚሆኑበት ነው ።
ልክ ኢንደስትራላይዜሽንን መቀበል እና መጠቀም የእሚያስችል ኢከነሚያዊ ፣ ማሕበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ መሠረት ኖሩዋቸው በግዜ ኢንደስትራላይዝድ የሆኑ ሐገራት እንደ ተጠቁመት እና ይኽን ማድረግ የአልቻሉ ሐገራት የኢንደስትሪያላይዝድ ዓለሙ ሸቀጥ ማራገፊያ እና ተመፅውዋች እንደ ሆኑት ፤ የሉላዊነትም ውጤት ተመሳሳይ ነው እየሆነ የአለው ።
የሉላዊነት አሉታዊ ተፅኖ ሰለባ በሆኑ አከባቢዎች ወይንም ሐገሮች ፤ አንደኛው እና ዋነኛው ክስተት ደግሞ የፅንፈኛ ፖለቲካ አንድ ዘውግ የሆነው ፤ ዘረኝነት ወይንም ብሔራዊ ጽንፈኝነት ነው ።
ይኽ ዘረኝነት ወይንም ብሔራዊ ጽንፈኝነት ፤ የዘመናዊ ሉላዊነት አሉታዊ ትሩፋት የሆነበትን አግባብ ለመረዳት ፤ የዘመናዊውን ሉላዊነት ፤ አኹን ወደ ደረሰበት ደረጃ እንዲ ደርስ ምክንያት የኾኑ ፤ ነባሪያዊ ፖለቲካዊ እና ኢከነሚያዊ ጉዳዮችን መመልከት አለብን ።
አስቀድመን እንደ አልነው ፤ በግለሰብም ይሁን በማሕበር ደረጃ ፤ የእሚደረጉ ትስስሮች በሺ የእሚቆጠር እድሜ የነበራቸው ክስተቶች ቢሆኑም ፤ ዓለም የሉል ቅርጽ ነው ያላት እና ወደ ምዕራብ በመጓዝ ምሥራቅ መድረስ ይቻላል በእሚል ፤ ከደቡባዊ አውሮፓ ፥ የኢቤሪያ ሰርጥ በስተምዕራብ በመጓዝ ፤ ቻይና እና ኅንድ መድረስ ይቻላል በእሚለው ፤ አዲስ የሕዳሴው ዘመን የመልክዓ ምድር ሳይንስ ፤ በስፔን ነገሥታት ድርጎ በክርስቶፈስ ከለምቦስ (Christopher Columbus) የተደረገው የባሕር ላይ ጉዞ ፤ ለዘመናዊ ሉላዊነት መጀመር ፈር ቀዳጅ ነው ።
ምንም እንኳን ፤ በእዚኽ እሳቤ የተነሳው ፤ ክርስቶፈር ከለምበስ ፤ ኅንድ እና ቻይና ሰአይሆን የዛሬዎች ደቡብ እና ሰሜን አሜርካ ደሴቶች ወደ ሆኑት የካረቢያን ደሴቶች ቢሆንም የደረሰው እና ይኽንንም በስህተት ኅንድ እንደ ደረሰ አስቦ ፤ አከባቢውን የቀያይ ኅንዶች መኖሪያ ቢለውም ፤ ያስመዘገበው ስኬት በእዚያኽ ዘመን ፤ ከሜድትራኒያን ባሕር በስዊዝ ወሽመጥ ከእዛያኽም በቀይ ባሕር ወደ ኅንድ ከእሚያደርሰው ብቸኛ የባሕር መንገድ ተለዋጭ መንገድ ለእሚፈልጉት የአውሮፓ ክርስቲያኖች አንድ ወሳኝ እርምጃ ነበር።
አሜሪጎ[2] ቫስፑቺ የተባለው ሰው ፤ ክርስቶፈር ከለምበስ የአገኘውን ይኽን አዲሱን ዓለም ፤ ኀንድ አይደለም እስኪል እና በእርሱም ኃሳብ መሠረት አዲስ የዓለም ካርታ እስኪ ዘጋጅ ፤ መላው አውሮፓ ፤ ዛሬ ደቡብ እና ሰሜን አሜሪካ ብለን የእምናውቃቸውን የከለምበስ ግኝት የሆኑትን አዲሱ ዓለም ፤ ኀንድ ብሎ ነበር የእሚያውቃቸው ።
ከእዚኽ የክርስቶፈር ከለምበስ ኅንድ የመድረስ “ከፊል ስኬት” በኋላ ፤ እ.አ.አ. በ1498 ዓ.ም. የስፔን አጎራባች በሆኑት በፖርቹጋል ነገሥታት ድርጎ ፤ ከምዕራባዊ አውሮፓ የኢቤሪያ ሰርጥ በመነሳት ፤ በምዕራብ አፍሪካ ጥግ ጥግ አድርጎ ወይንም አፍሪካን በመዞር ፤ በኅንድ ውቂያኖስ አድርጎ በርግጥ ኅንድ የደረሰው ወይንም አዲስ ወደ ኅንድ የእሚያደርስ የባሕር ላይ መንገድ የአገኘው የፖርቹጋሉ የባሕር ላይ አሳሽ ቫስኮ ደጋማ ነው።
የቫስኮ ደጋማ ጉዞ ለፍሬ መብቃት የቻለው ደግሞ ፤ በወቅቱ በነበረው ፤ ዓለም ዓቀፋዊ የፖለቲካ ኃይላት አሰላለፍ አስገዳጅነት ፤ በአውሮፓ ለብዙ ዓመታት ፥ የፖርቹጋል ዜግነት የአለው እና እ.አ.አ. 1394 – 1460 ዓ.ም. የኖረው ፤ አሳሹ ልዑል ሔነሪ (Prince Henry the Navigator) እና መሰል ሰዎች ፤ ይኽን መሰሉን ጉዞ ለመአካኼድ የእሚያስፈልጉ የእውቀት ፣ የኃብት ፣ የቴክኖሎጂ ክምችት ሲፈጥሩ እና የዲፕሎማሲ ጥረት ሲያደረጉ በመቆየታቸው ነው ።
በታሪክ አጋጣሚም ሐገራችን ኢትዮጵያ ፦ በእዚያኽን ወቅት ፤ ተስፋፊው የእስልምና መንግሥት አውሮፓ ላይ የጋረጠውን አደጋ ለመቀልበስ ለእሚደረገው ትግል እገዛ ማቅረብ የእሚችል ታላቅ አቅም ያላት ፥ የክርስቲያን ሐገር እንደ ሆነች በአውሮፓዊያኖች እምነት ተይዞ ስለ ነበር ፤ በእዚኽ አዲስ መንገድ የማፈላለግ ታሪክ ውስጣ ወሳኝ ሚና አላት ። ምክንያቱም ፦ የእነ ቫስኮ ደጋማን ስኬት የአስቻለው የእነ ልዑሉ ሔነሪ ዋነኛ የመንገድ ፍለጋ አንደኛው ምክንያት ኢትዮጵያ ለመድረስ ነበር ። ይኽም ማለት ፤ ዘመናዊ ሉላዊነትን ለማስጀመር ኢትዮጵያ ለዓለም ሕዝብ የተስፋ ኮከብ ሆና አገልግላለች ማለት ነው ። ስለ ጉዳዩ ማቲዮ ሳልቫዶር የተባለ ተመራማሪ እንደ እዚኽ ይላል ፦
“በአሳሹ ልዑል ሔነሪ (እ.አ.አ. 1394 – 1460 ዓ.ም.) መሪነት የተጀመረው ፤ የፖርቹጋሎች አህጉረ አፍሪካን በባሕር መዞር የተነሱበት ዓላማ ወደ ኢትዮጵያ በመድረስ ፤ እያየለ ከመጣው የእስልምና አደጋ ስጋት የእሚከላከል እርዳታ ከቀሲስ ዮሐንስ ለማግኘት ነበር ።”
“One of the primary purposes behind the Portuguese circumnavigation of Africa, started under the leadership of Prince Henry the Navigator (1394 - 1460) in the early fourteenth century, was to identify a path to Ethiopia, and secure Prester Jhon's support against the growing Islamic threat. [32]“
ምክንያቱም ፦ የእስልምና ኢምፓየር ፤ ሰሜናዊ አፍሪካን ፣ የሜድትራኒያን ባሕር እና መካከለኛው ምሥራቅ ላይ ተቀናቃኝ የሌለው ብቸኛ ኃይል ስለ ነበረ እና ይኽም የእስልምና የበላይነት ፤ ወደ ሰፊው የሩቅ ምሥራቅ ገበያ የእሚያደርሱትን ፤ የወቅቱን የየብስ እና አንድ የባሕር መንገድ (ወደ ስዊዝ ካናል የተጠጋውን ቀይ ባሕር እና የደቡብ አረብያ እና የፐርዤያ ወደቦች) በብቸኝነት በመቆጣጠር ፤ በእዚኽም ራሱን በመንግሥታዊ ሽፍትነት ብቸኛው የዓለም ዓቀፍ ንግድ መተላለፊያ መንገዶች ኢፍትሓዊ ዳኛ በማድረግ ፤ ከእስልምና ውጭ በአሉ ሐገራት ላይ ብዙ መቶ ዓመታት የቆየ ኢከነሚያዊ ጫና እያደረሰ የነበረ በመኾኑ ፤ አውሮፓዊያኖች ይኽን በደል ለመታገል ኢትዮጲያ ታግዘናለች ብለው አምነው የነበሩ በመሆኑ ነው ።
ይኽ የትብብር ፍላጎት ግን የአንድ ወገን እና የአውሮፓዊያን ብቻ ሳይሆን ፤ የኢትዮጲያም ፍላጎት ነበር። ምክንያቱም ፦ ኢትዮጵያም ፤ እንደ አውሮፓ አቻዎቿ የክርስቲያን ሐገር በመሆኗ እና ይኸው የእስላማዊ ዓለም ዓቀፋዊ ‘ማዕቀብ’ እና በወታደራዊ ኃይል የመስፋፋት አካኼድ ተጠቂ የነበረች በመሆኗ ፤ በእዚኽ ዓለም ዓቀፍነት በአለው እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፍ ፥ ይኽንን ኢፍትሐዊ ማዕቀብ እና ግፊያ ለማስወገድ ፍላጎት የነበራት በመሆኑ ፤ ዘመናዊ ሉላዊነትን ለማስጀመር ወሳኝ ክስተት በሆነው የባሕር አሰሳ ላይ ኢትዮጲያም ንቁ ተሳታፊ ነበረች።
ይኽም በመሆኑ ፤ አውሮፓዊያንን እና ኢትዮጲያዊያን ፤ በወታደራዊ ኃይል ተስፋፊ ከነበረው የእስልምና ኢምፓየር ሊታደጋቸው የእሚችል የጋራ መከላከያ ግንባር ለመመሥረት እና ይኸው የእስልምና ኢምፓየር በዓለም ዓቀፍ የየብስ እና የባሕር መንገዳት ላይ በኢፍትኃዊነት የአስቀመጠውን ማዕቀብ ለማንሳት የነበራቸው የጋራ ፍላጎት ፤ አውሮፓዊያን ይኽን ለማድረግ ከፍተኛ ወታደራዊ አቅም አላት ብለው ወደ አሰቧት ኢትዮጲያ ለመድረስ እንዲነሱ ስለ አደረገ ፤ ኹኔታው የዘመናዊ ሉላዊነት ፍም የተለኮሰበት እንዲሆን አድርጎታል።
ኢትዮጵያም በእዚኽ መልኩ አውሮፓዊያን ፤ ከነበሩበት የፍርኃት እና የውስንነት አጥር ወጥተው ፤ ዓለምን በመሠረታዊነት የለወጠውን የባሕር ላይ አሰሳ እንዲያደርጉ በማድረጓ ፤ ልትሰጥ ትችል ከነበረው ወታደራዊ እገዛ በላይ ኃሳባዊዋ ኢትዮጵያ የፈጠረችው ተስፋ የዓለምን ታሪክ የቀየረውን የቫስኮ ደጋማ ጉዞ አስችሏል ። አንድ አውሮፓዊ አጥኚ እንደ አለውም ፦
“በአባቶቻችን የታሰበው ቀሲስ ዮሐንስ ፤ በትክክል ቢገኝ እንኳን የእማይሰራውን ሥራ በአለመኖሩ መሥራት ችሏል !”
“Had the prester John visualised by our ancestors really existed he could have hardly done a better job than he did by simply not being there ! [33]“
በታሪክ እንደ እምናውቀው ግን በእዚኽ እንቅስቃሴው ውስጥ ኢትዮጵያ ልትጫወት የእምትችለው ሚና ያሳሰባቸው የወቅቱ የእስልምና ግዛት የበላዮች ፥ ዖቶማን ተርኮች ፤ የግራኝ አህመድን ጦርነት በገንዘብ ፣ በመሳሪያ እና በወታደራዊ ኃይል በማገዝ እና እርሱም ሳይሳካ ሲቀር ፤ በወቅቱ በነበራቸው የባሕር ኃይል የበላይነት የቀይ ባሕርን ወደቦች በኃይል በመያዝ ፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በደቡብ እና በሰሜን አከታትለው በከፍተኛ ደረጃ በማጥቃት ፤ እንደ እሚታወቀው ፥ ብዙ ኪሳራ በኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት ላይ ያደረሱ በመሆኑ ፤ የነበራት አቅም ተንኮታኩቶ በውስጣዊ ችግር ስለ ተጠመደች ፤ ለእዚኽ ፍትሐዊ ዓለም ዓቀፍ ትግል በነበራት አቅም ልክ አስተዋፆ ማድረግ ሳትችል መቅረት ብቻ ሰአይሆን ፤ ቀድማ በመመታቷ ፤ አንዳንዶቹ ፥ እስከ ዛሬም የአላገገመችባቸው ፖለቲካዊ ፣ ኢከነሚያዊ እና ሰብዓዊ ኪሳራ ያደረሰባት ሆኗል ክስተቱ ።
ሪቻርድ ፓንክረስት ፤ በተባባሪ ተርጓሚነት ከአረብኛ ወደ እንግሊዘኛ በተረጎሙት ፤ በግራኝ ዜና መዋዕል ጸሐፊ ሲኃብ አድአዲን የተጻፈው እና ሐበሻን መቀራመት (The Conquest of Abyssinia) በእሚለው መጽሐፍ መግቢያ ላይ ፤ የግራኝ ወረራ ከእዚኽ ዓለም ዓቀፍ ትግል ጋር ስለ ነበረው ተያያዥነት ይኽን ብለዋል ፦
“ከኢማሙ(ግራኝ) ጋር የተያያዘው ሰልፍ ፤ እጅግ ወሳኝ ዓለም ዓቀፍ ደርዝ የአለው በመሆኑ ፥ በቀጣይነት በክርስቲያኖቹ ፖርቹጋሎች እና በሙስሊሞቹ ዖቶማን ተርኮች መካከል ከእሚካኼደው ዓለም ዓቀፍ ጦርነት ጋር እየተጠላለፈ ነበር ።”
“The warfare associated with the imam, which had an important international dimension, became increasingly enmeshed in the global conflict between the Christian Portuguese and the Muslim Ottoman Turks. [34]“
ኢትዮጵያን ያናወጠው አዲሱ የሉላዊነት ማዕበል ፤ በዖቶማን ተርኮች የተልዕኮ እና የቀጥታ ጦርነት ተወስኖ አልቀረም ። በአጋርነት የተጀመረው የፖርቹጋል እና የኢትዮጵያ ግንኙነት ፤ በተወሰኑ ዕቡያን ፖርቹጋሎች ምክንያት ቃናውን ለውጦ የአሰልጣኝ እና የሰልጣኝ ግኑኙነት ከአልሆንኩ በማለቱ ፤ የባሕል ግጭቱ በኢትዮጵያ ተጨማሪ ማሕበራዊ ቀውስ ምክንያት ሆኖ ነበር። ፖል ሔንዝ የተባለ የኢትዮጵያ ታሪክ ጸሐፊ ስለ ኹኔታው እንዲኽ ይላል ፦
“ፖርቹጋሎቹ ኢትዮጵያን ከሙስሊሞች ማዳን ብቻ ይበቃል ብለው አልረኩም ፤ ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ እንዲኖራቸው ፈለጉ ። ሐገሪቱን የሮማዊ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ምሽግ አድርጎ የመቀየር ተስፋ ይዘው ነበር ።”
“The Portuguese were not content with rescuing the Ethiopians--- from the Muslims; some aspired to political influence. They hoped to transform the country into a bastion of Roman Catholicism. [35]“
ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በእዚኽ አዲስ ዓለም ዓቀፋዊ የስረዓት ለውጥ ውስጥ ስትሳተፍ ፤ ትልሟ የነበረው የአውሮፓን ቴክኖሎጂ ወደ ሐገር ውስጥ ማስገባት እና ታሪካዊ የባሕር በሮቿን በነፃነት የመጠቀም እድል የማግኘት ፍላጎት ቀዳሚው ቢሆንም ፤ በተደራራቢ አሉታዊ ምክንያቶች ፤ ይልቁንም ኺደቱ መልኩን በመቀየር ይዛ የቆየችውን የግዛት አንድነት እና አስተዳደራዊ ነፃነት የእሚፈታተን በመሆን ፤ ከኤርትራ ችግር አንስቶ እስከ ዛሬ የኢትዮጵያን ህልውና የእሚፈታተኑ ፖለቲካዊ ፣ ኢከነሚያዊ እና ስነልቦናዊ ችግሮች መሠረት እንዲጥሉ ምክንያት ሆኖ ነው የአለፈው ። የእዚኽን ዝርዝር ፤ በምዕራፍ ሦሥት ላይ ፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ዝግመት በእሚለው ንዑስ ክፍል የእምናየው ይሆናል ።
እነ እዚኽ ኹለት የወቅቱ የአውሮፓ ኃያላን ፖርቹጋል እና ስፔን ፤ ተስፋፊው እስልምና ለመግታት እና የኢፍትኃዊውን የዖቶማንን ክልከላ ለማንሳት በአገኙት አቅጣጫ መንገድ ሲፈልጉ ከቆዩ በኋላ ፤ በለስ ቀንቷቸው በምሥራቅ እና በምዕራብ በባሕር ወደ ሌሎቹ የዓለማችን አህጉራት ሲደርሱ ግን ፤ የገጠማቸው ነባራዊ ኹኔታ ፤ ስሌታቸውን ብሎም የዓለምን ታሪክ በወሳኝነት የለወጠ ክስተትን ወለደ ።
ለምሳሌ ፦ በደቡባዊ ምሥራቅ አፍሪካ ፤ ሞዛምቢክ እና ሞምባሳ አከባቢ የነበሩት ‘የአስፈሪው’ የሙስሊም ኢምፓየር ሰፋሪዎች በጥቂት የፖርቹጋል ወታደሮች ተገፍተው ቦታው በፖርቹጋል ቁጥጥር ስር ዋለ ። ማለትም የኃይል ሚዛኑ አውሮፓዊያኑ አስቀድመው ያስቡት እንደ ነበረው ከአቅማቸው በላይ አልነበረም ፦
“በምሥራቅ አፍሪካ የነበሩ ዋነኛ የአረብ ሰፈራዎች ፤ ሞዛምቢክ ፣ ኪልዋ እና ሞምባሳ ፤ ፖርቱጋሎች ወስደው ሰፈሩበት …”
“ The Principal Arab settlements in East Africa, Mozambique, Kilwa, and Mombasa, were taken and settled by Portugese... [36]“
ፖርቹጋልቹ ይኽን ማድርግ የቻሉት ፤ እፍኝ በእማይሞሉት በንፋስ ኃይል በእሚገፉት የእንጨት መርከቦቻቸው ይዘው በመጡት ወታደር ነው ።
ከአፍሪካ ተሻግረው ወደ ኀንድም ሲደርሱ ፥ በጣም ሰፊ እና ለም መሬት ላይ ፤ በጎጥ እና በነገድ ተከፋፍለው ፤ እርስ በእርስ የእሚፎካከሩ ፤ ኋላ ቀር ሕዝብ እና አስተዳድር እንጂ ይኽ ነው የእሚባል ፤ ለንግድ ወይንም ለወታደራዊ ሥራ አጋር የእሚሆን ኹኔታ አልነበረም የገጠማቸው ፦
“በምዕራባዊ ደቡብ ኅንድ ጫፍ ፤ በባሕሩ እና ወደ ባሕሩ በእሚወስደው መሸጋገሪያ መሐል ፤ ለምለም የመሬት ሰርጥ አለ ። በእዚኽ መሬት ላይ በሙስሊሞች ጎርፍ መሰል ወረራ ያልተነኩ ትናንሽ የኂንዱ መንግሥታት ነበሩ ። ከእነዚኽ ዋነኛ የሆነችው ፥ ካሊከት የእምትባል ሲሆን ፤ የፖርቹጋል አሳሾች የኀንድን አፈር ለመጀምሪያ የረገጡባት ነበረች ። ነገር ግን ፤ በእዚያኽ እንደ ደረሱ ፤ የቦታው ራጃ (ልዑል) በክፉ ዓይን እንደ ዓያቸው ገባቸው … ለመነገድ ያደረጉት ሙከራ ኹሉ ተቃውሞ ገጠመው ፤ ስለ እዚኽ መሪዎቻቸው ፤ ከእነርሱ በላይ ጠንካራ በመሆኑ ይቀኑበት ከነበሩ ፤ ኮቺን እና ካኖር ከእሚባሉ የአጎራባች መንግሥታት ጋር ግንኙነት መሠረቱ ።”
“At the extreme south of Western India lies the country of Malabar, a fertile strip between the Ghats and the sea. Here were some small Hindu states as yet untouched by the flood of Musalman invasiin. The principal of these was Calicut, and it was here that the Portugese first touched Indian soil. They soon realised that the raja of that country looked on them with unfriendly eyes ... All attempts on part of tne Portugese to obtain trade were resisted, and their leaders therefore made friends with two minor states, Cochin and Cananor, which were jealous of their more powerful neighbor. [36]“
በተመሳሳይም ወደ ምዕራብ የተጓዙት ስፔኖች ፤ ያገኙት ሕዝብ የንግድ እድል እና የወታደራዊ ትብብር አቅም የአለው ሰአይሆን ፤ ከሦሥት መቶ በእማይበልጥ ወታደር ፤ ትልቁን የደቡብ አሜሪካ አህጉር አብዛኛውን ፖለቲካዊ ማሕበረሰብ ያለ ብዙ ችግር ፥ ያለተቀናቃኝ መቆጣጠር እስኪ ችሉ ድረስ ምንም ዓይነት የመከላከል አቅም የሌለው ነበር ።
ስለ እዚኽ ፦ የዘመናዊ ሉላዊነት ፋና ወጊ የነበሩት ስፔን እና ፖርቹጋሎች ፤ እ.አ.አ. ከ1532 ዓ.ም ጀምረው ፤ ከራሳቸው አንፃር እጅግ ኋላ ቀር የሆነውን ሕዝብ መኖሪያ ያለ ብዙ ችግር መቆጣጠር ጀመሩ ። ፒዛሮ የተባለው የእስፓኒያ ወታደሮች አዛዥ ጋር አብረው የተጓዙ ሰዎች ይኽን ኹኔታ እንዲኽ ዘግበውታል ፦
“የእማይታወቀውን እና የእማይታየውን ፤ ትልቅ ባሕር ተሻግሮ ፣ እንዲኽ ያለ ረዥም ርቀት በየብስ ተጉዞ ፤ በጥንታዊውም ይኹን በዘመናዊው ታሪክ ፤ በእንደ እዚኽ የእሚያኽል ጥቂት ሰዎች ይኽን ኹሉ ፥ የተለያየ የአየር ንብረት የእሚያካልል ምርኮ የሰበሰበ ማን አለ ? እስኪ ታሪካዊ ግብራቸው ከእስፔኖች ጋር የእሚነፃፀር ማን አለ ? የእኛ ስፓኒያዎች ፤ በቁጥር ጥቂት ሆነው ፤ በድምሩ ከ2 መቶ ወይንም ከ3 መቶ የእሚያንሱ ኾነው ፣ አንዳንዴም ከመቶ እያነሱ ፤ በዓለም ላይ ያሉት የክርስቲያን አማኞች እና ሌሎች ነገሥታት ከያዙት ግዛት በላይ መማረክ ችለዋል።”
“For when, either in ancient or modern times, have such great exploits been achieved by so few against so many, over so many climes, across so many seas, over such distances by land, to subdue the unseen and unknown ? Whose deeds can be compared with those of Spaniards, being few in number, never having more than 200 or 300 together, and sometimes only 100 and even fewer, have, in our times conquered more territory than has ever been known before, or than all the faithful and infidel princes possess. [37]“
ከእዚኽም በተጨማሪ ፤ እነ እዚኽ የፖርቹጋል እና የስፔን አሳሾች ፤ በእየደረሱበት ፤ እንደ አሰቡት ፦ በአረብ ሲራራ ነጋዴዎች ተጭኖ ፤ ጭል ጭል እያለ የእሚመጣላቸውን ምርት በገፍ ሰአይሆን የአገኙት ፦ በቀላሉ የእሚገኙ ማዕድናት እና ለሰብል እና ቅመማ ቅመም ምርት አመቺ የሆነ ለም መሬት ፤ በእዚኽም ሥራ ላይ ሊሰማራ የእሚችል ሰፊ የሰው ጉልበት ፥ ነገር ግን ለእዚኽ የእሚያበቃ ፖለቲካዊ አደረጃጀት እና ኢከነሚያዊ ንቃት የሌለው ሕዝብ ነው የገጠማቸው።
ስለ እዚኽ ፦ አውሮፓዊያኖች ፥ ‘ከወረሩት’ አከባቢ በተነፃፃሪነት የተሻለ የጦር መሳሪያ ይዘው እና ከተደራጀ የንግድ ስረዓት የእሚገኘውን ኢከነሚያዊ ጥቅም በአግባቡ የተረዱ ኾነው በመገኘታቸው ፤ የገጠማቸው ኹኔታ ስሌታቸውን እንዲቀይሩ ስለ አደረጋቸው ፤ እስከ ቀኝ ግዛት ማብቃት ድረስ የነበረውን የበላይነታቸውን እንዲይዙ አደረጋቸው ።
ቀኝ ግዛት ለቀኝ ግዛት ሲባል እንደ አልተጀመረ ፤ እነ እዚኽ የወቅቱ ወሳኝ ክስተቶች ዓይነተኛ ማሳያዎች ናቸው ። ምክንያቱም ፦ በየትኛውም የኃይል አሰላለፍ ምዘና ፤ 168 አንድ ጥይት እየተኮሰ የእሚያርፍ የድሮ ዘመን ጠመንጃ የያዙ ወታደሮች ፤ 80 ሺ ወታደር ያሉትን ንጉሥ ማርከው ፥ በ168 ወታደር በሚልየን የእሚቆጠር ሕዝብን ማስገበርን ታሳቢ አድርገው ይነሳሉ ተብሎ ሊታሰብ አይችልም ፤ ፒዛሮ የተባለው የስፔን ጦር መኮንን ግን ፤ በደቡብ አሜሪካ እ.አ.አ. በ1532 ዓ.ም. የአደረገው ይኽንን ነበር ፦
“ ፒዛሮ ፤ ቆሽማዳ 168 የስፔን ወታድሮች ያሉት ቡድን ይዞ ፤ በአግባቡ በእማያውቀው የመሬት አቀማመጥ ፣ ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር ምንም ግንኙነት ሳይኖረው ፤ ሊረዱት ከእሚችሉት ሌሎች የስፔን ሰዎች (በስተሰሜን በ 1ሺ ማይል ወይንም 1,609 ኪሎ ሜትር ርቅት ፓናማ ላይ) ፤ በጣም ሩቅ በመሆኑ አጋዥ ኃይል ሊደረስበት በእማይችልበት ርቀት ላይ ነበር ። አታኋልፓ በግዛቱ ውስጥ በእሚኖሩ በሚልዮን በእሚቆጠሩ ገባሮቹ መሐል እና በ 80, 000 ወታደሮቹ ተከቦ ፤ ከሌሎች ኢንዲያኖች ጋር በተደረገ ጦርነት አሸንፎ በቅርቡ ተመልሷል ። ቢሆንም እነዚኽ ኹለት መሪዎች ዐይን ለዐይን ሲገናኙ ፤ ፒዛሮ አታኋልፓን በጥቂት ደቂቃ ውስጥ ማርክታል ።”
“Pizzaro, leading a ragtag group of 168 Spanish soldiers, was in unfamiliar terrain, ignorant of the local inhabitants, completely out of touch with the nearest Spaniards (1, 000 miles to the north in Panama) and far beyond the reach of timely reinforcements. Atahualpa was in the middle of his own empire of millions of subjects and immediately surrounded by his army of 80,000 soldiers, recently victorious in a war with other Indians. Nevertheless, Pizzaro captured Atahualpa within a few minutes after the two leaders set eyes each other. [37]“
ይኽ እንግዲኽ ፤ የደቡብ አውሮፓዊያኖቹ ፤ ወታደራዊ እና የንግድ ሽርክና ፈልገው የተነሱት የፖርቹጋል እና የስፔን አካኼድ ነው ። እንግሊዞቹ ፖርቹጋሎቹ እና ስፔኖቹ ዓለምን ማካለል ከጀመሩ ከመቶ ዓመት በኋላ እ.አ.አ. በ1630 ዓ.ም. አከባቢ ፤ ሰሜን አሜሪካ ሲኼዱ ፤ በአውሮፓ የአለውን ድህነት እና የእሚደርስባቸውን የተለያየ ኃይማኖታዊ እንግልት ሽሽት ነበር ፦
“ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንግሊዝ የገነነ የሕዝብ ቁጥር መጨመር አጋጥሟት ነበር ፤ እናም በተፈጠረው መጨናነቅ እና አንኮታኳች ድህነት ለተጨነቁት ፤ ሰፈራዎቹ ተመራጭ ስፍራዎቹ ነበሩ … ሌላው ሰፈራዉን አቀጣጣዩ ጉዳይ ራሳቸውን ያልተቀየጡ የእሚሉት ኃይማነተኞች ፤ ልክ እንደ ቃሉ (መጽሐፍ ቅዱሱ) መኖር በመፈለጋቸው ፕሊመዝ ፣ ማሳቹሴትስ ቤይ ፣ ኒው ሐቨን ፣ ከነቲከት እና ሮድ አይላንድ የተባሉትን የኒው ኢንግላድ ሰፈራ በመጀመራቸው ነው ።”
“England had experienced a dramatic rise in population in the sixteenth century, and the colonies appeared a welcoming place for those who faced overcrowding and grinding poverty at home... Another stream, this one of pious Puritan families, sought to live as they believed scripture demanded and established the Plymouth, Massachusets Bay, New Haven, Connectict, and Rhode Island colonies of New England. [38]“
በእዚኽ መልኩ ፤ መቶ እና ኹለት መቶ ኾነው በጥገኝነት የኼዱት እንግሊዞች ፤ በመጀመሪያ አከባቢ እንኳን ወራሪ እና ጨፍጫፊ ለመሆን ይቅርና ፤ በህይወት መኖርም ትልቅ ፈተናቸው ነበር ።
ጀምስታወን የእምትባለውን የሰፈራ ከተማ በሰሜን አሜሪካ ለመጀመር ከኼዱት 144 ሰዎች በመጀመሪያው ክረምት 106ቱ ፤ በበሽታ ፣ በረሀብ እና ከሐገሬው ነዋሪዎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ሲሞቱ 38 ብቻ ነበር የተረፉት ። ይኽን 106ቱ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡበትን ፈታኝ ኹኔታ ፤ ጆርጅ ፔርሲ (George Percy) የተባለው አብሮ ተጓዥ እና በኋላም የአከባቢው ገዢ በመሆን ኹለት ግዜ ያገለገለው ሰው ፤ በመጀመሪያ ወር ላይ የነበረውን አሳዛኝ ኹኔታ እንደ እዚኽ ገልፆታል ፦
“በመስከረም ወር በአራተኛው ቀን ቶማስ ያዕቆብ ሻለቃው ሞተ ። በአምስተኛው ቀን ብንያም ቢስት ሞተ ። ሰዎቻችን በምህረት የለሾቹ በሽታዎች ፦ በእብጠት ፣ አተት ፣ በእሚፋጅ ትኩሳት እና በጦርነት አለቁ ። አንዳንዶችም በድንገት ይኽችን ዓለም ተለዩዋት ፥ አብዛኛዎቹ ግን በረኃብ ነበር የሞቱት ። በእዚኽ አዲስ በተገኘችው ቨርጂንያ የእኛ ሰዎች የደረሰባቸውን አበሳ ዓይነት አበሳ ፤ ማንም በሌላ ሐገር የእሚኖር የሐገረ እንግሊዝ ሰው አልደረሰበትም … ምግባችን በትንሽ ጣሳ ውስጥ በውኃ የረሰረሰች ገብስ ለአምስት ሰው በጋራ የቀን አንዴ ምግብ ነበረች ፣ የእምንጠጣው ውኃ ከቀዝቃዛ ወራጅ ወንዝ የእሚቀዳ ነበር ፥ የወራጁ ወንዝ እንደ ጅረት ከእሚፈስበት ሲቀዳ በጣም ጨዋማ ይሆናል ፥ ረጋ ከአለበት ሲቀዳ በቆሻሻ የደፈረሰና እና የጨቀየ ይሆናል ፤ ይኽ የመጠጥ ውኃ ነበር ለአብዛኛዎቹ ሰዎቻችን ማለቅ ምክንያት ። በእዚኽ ዓይነት አበሳ በሞላበት ኹኔታ ለአምስት ወራት ቆየን ፤ በእሚያስፈልግበት ወቅት በመጠበቂያ ማማችን ላይ አምስት ደህና ሰዎች ማስቀመጥ አንችልም ነበር ። የአምላክ ፈቃዱ ሆኖ ፤ በጨካኞቹ አረማዊያኑ ልብ ውስጥ ፍርሀት በአይለቅ ኖሮ ፥ እንደ እዚኽ በተዳከምነበት ያጠፉን ነበር ፤ ሰዎቻችን በሙሉ ቀን እና ማታ በምሽጋችን ውስጥ በኹሉም አቅጣጫ ፤ ለመስማት እጅግ በእሚያሳዝን ኹኔታ በሕመም ያቃስቱ ነበር ። ማንም የሰው ህሊና የአለው ሰው በእየቀኑ እና በእየማታው ለስድስት ሳምንታት ያኽል ፤ ምንም ማስታገሻ ሰአያገኙ የእኛ ህሙማን አሳዛኝ ማጉተምተም እና የስቃይ ለቅሶ ሲያለቅሱ ሲሰማ ልቡ ይደማል ፤ አንዳንዶቹ በእዚኽ ስቃያቸው ዓለምን ይሰናበታሉ ፤ ብዙ ግዜ ሦሥቱ ወይንም አራቱ በአንድ ምሽት ይሞታሉ ፤ ጠዋት ላይ አስክሬናቸው ከጎጆዋቸው እንደ ውሻ እየተጎተተ ለቀብር ይወሰዳል ። በእዚኽ መልኩ ነበር ሕዝባችን በተለያየ መልኩ ሲያልቅ የአየኹት ።”
“The fourth day of September died Thomas Jacob Sergeant. The fifth day, there died Benjamin Beast. Our men were dstroyed with cruel diseases, as Swellings, Fluxes, Burning Fevers, and by wars, and some departed suddenly, but for the most part they died of mere famine. There were no Englishmen left in a foreign Country in such misery as we were in this new discovered Virginia. ... Our food was but a small can of barley soaked in water, to five men a day, our drink cold water taken out of the River, which was at a flood very salty, at a lw tide full of slime and filth, which was ghe destruction of many of our men. Thus we lived for the space of five months in this miserable distress, not having five able men to man our Bulwarks upon any occassion. If it had not pleased God to put terror in the Savages’ heartsm we had all purished by those wild and cruel Pagans, being in the weak estate as we were; our men night and groaning in every corner of the Fort most pitiful to hear. If there were any conscious in men, it would make their hearts to bleed to hear the pitiful murmurings and outcries of our sick men without relief, every night and day, fir the space of six weeks, some departing out of the World, many times three or four in a night, their bodies trailed out of their cabins like Dogs to be buried. In this sort did I see the mortality of diverse of our people [38]“
ስለ እዚኽ ፦ የዘመናዊ ግሎባላይዜሽን መሥራች የሆነው ፤ የእነ ቫስኮ ደጋማ አፍሪካን ዞሮ ኅንድ መድረስ ፣ የእነ ከለምበስ ደቡብ አሜሪካ መድረስ እንዲሁም የእነ ጆርጅ ፔርሲ ሰሜን አሜሪካ መድረስ መነሻ ምክንያቶቹ ፦ ተስፋፊውን እስልምና ለመግታት ፣ ከእስልምናው ኢምፓየር የንግድ ማዕቀብ ለመውጣት ፣ የንግድ ሽርክና ፍለጋ ፣ ኃይማኖትን በስብከት የማስፋፋት ፍላጎት ፣ እጅግ የመረረ ድህነትን ሽሽት ፣ ኃይማኖታዊ መገለልን ሽሽት ፣ ወዘተ ፤ እንጂ የተትረፈረፈ ምርት ማራገፊያ ገበያ ፍለጋ ወይንም የእሚበዘበዝ እና የእሚገዛ ሕዝብ ፍለጋ እንደ አልተጀመረ እናያለን ።
በግዜ ኺደት ግን ፤ ቀኝ ግዛትን ታሳቢ አድረገው በአይነሱም ፤ እጅግ አናሳ ቁጥር ነገር ግን ከቀረው የዓለም ሕዝብ ኹሉ የተሻለ ዓቅም ይዘው በዓለም ላይ በአራቱም አቅጣጫ ፤ ከላይ በዘረዘርናቸው የተለያዩ ምክንያቶች የተበተኑት አውሮፓዊያኖች ፤ በእየደረሱበት የገጠማቸው ሕዝብ እጅግ ደካማ በመሆኑ ፤ ‘ድንገት’ ይኽንን ሕዝብ በግድ እየገዙ ፤ ይቻላል ብለው አስበውት የእማያውቁትን ኃብት እና ስልጣን ማግኘት እንደ እሚችሉ ታያቸው ።
በእዚኽ መልኩ ዘመናዊ ቀኝ ግዛት ሲጀመር እና በኋላም ፤ የአንዳንድ የአውሮፓ መንግሥታት ቋሚ ፖሊሲ ሲሆን ፤ ኢንደስትራላይዜሽን ገና ያልጀመረ እና ገበያ መር ካፒታሊዝም ያልታሰበ በመሆኑ ፤ የማርክሲዝም ተቀጣይ የሌኒንዝም ርዕዮት እንደ እሚለው ፤ የማሽን መብዛት የካፒታሊዝምን ምርት ያለልክ አትረፍርፎ ፤ ለእዚኽ የተትረፈረፈ ምርት የጥሬ ዕቃ ፍለጋ እና ምርት ማራገፊያ ገበያ ፍለጋ ቀኝ ግዛት ተጀመረ የእሚለው ብዙም አያስክኼድም ።
እንደ እሚታወቀው ኢንደስትራላይዜሽን የጀመረው በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ፤ ከቀኝ ግዛት መቶ አመታቶች በኋላ ነው ፤ በእዚኽ ኢንደስትራላይዜሽን በእሚጀምርበት ግዜ ደግሞ ቀኝ ግዛት ዳብሮ ጨርሶ ነበር ።
ከእዚኽ በኋላ አውሮፓዊያን የተሻለ የግንዛቤ ደረጃ ላይ ስለ ነበሩ ፤ በድርድርም ፣ በጉቦም ፣ በመድፍም በአጠቃላይ በሰራላቸው መንገድ እየተጠቀሙ ፤ ከምርት እስከ ስርጭት የአለውን ዓለም ዓቀፍ ንግድ ተቆጣጠሩት ። በእዚኽ ኹኔታ በተበታተነ መልኩ የጀመረው ቀኝ ግዛት ከ100 - 150 በአሉት ዓመታት ውስጥ ፤ የራሱ የሆነ ባሕሪ የተላበሰ ትልቅ ዓለም ዓቀፍ አዲስ ክስተተት ሆነ ።
ምንም እንኳን ቀኝ ግዛት ያለ መንግሥት ቀጥተኛ ተሳትፎ ቢጀምርም ፤ በግዜ ኺደት ግን ያመጣው ኢከነሚያዊ ጥቅም እና የፈጠረው ሰፊ ‘ሕዝባዊ’ ተሳትፎ መንግሥታትን ጎትቶ በማስገባት ፤ የአውሮፓ ነገሥታት የግዛት ማስፋፋት እሽቅድድም ውስጥ እንዲገቡ አደረጋቸው ።
ለምሳሌ ፦ ፒዛሮ የተባለው የስፓኒያ መኮንን ፤ አታኋልፓ የተባለውን ባለ 80 ሺ ወታደር የኢንካ ማሕበረሰብ ንጉሥ ከላይ በገለፅነው መልኩ ከማረከው በኋላ ፤ ንጉሣችሁን የእምፈታላችሁ ፤ 7 ሜትር በ 5 ሜትር ስፋት እና ወደ ላይ 2.5 ሜትር ከፍታ የአለውን ክፍል በወርቅ ከሞላችሁ ነው በማለት ፤ ያንን የእሚያኽል ወርቅ ሰብስቦ ነበር ፦
“ፒዛሮ ፤ የጠየቀው ወርቅ እስኪ ቀርብለት ለስምንት ወራት ያኽል በምርኮነት ከአቆየው በኋላ ፤ 22 በ 17 ጫማ ስፋት ኖሮት 8 ጫማ የእሚረዝም(7*8*2.5 ሚትር) ቤት የእሚሞላ ወርቅ ለመዋጃነት ከቀረበለት በኋላ ፤ ቃሉን በማጠፍ አታኋላፓን ገደለው ።”
“ Pizzaro proceeded to hold his prisoner for eight months, while extracting history’s largest ransom in return for a promise to free him. After the ransom – enough gold to fill a room 22 feet long by 17 feet wide to a height of over 8 feet – was delivered, Pizzaro reneged on his promise and executed Atahuallpa. [37]“
ይኽን መሰሉ የወርቅ ኃብት በጥቂት ወታደር የማጋበሱ ዜና ፤ መላው አውሮፓን ተመሳሳይ እድል እና አጋጣሚ ፈላጊ በማድረግ ፤ በአገኙት አጋጣሚ ኹሉ ፤ መርከብ እየጫኑ ወታደር እያስታጠቁ ዓለምን እንዲያስሱ አደረጋቸው ። ከእዚኽ የተነሳ ቀኝ ግዛት ማስፋፋት ፤ የመላው አውሮፓ ፖለቲካዊ ምህዳር አዲሱ ገዢ ኃሳብ ሆነ ።
ይኽ የቀኝ ግዛት አባዜ ፤ ኤልዶራዶ (Eldorado) የእሚባለው የእንግሊዘኛ ቃል ፤ በእዚኽ መልኩ የተነሳሳው ሕዝብ ብዙ ኃብት እና እድል አለበት ብሎ ይፈልገው የነበር ፤ ነገር ግን ያልነበረ ንጉሥ በመሆኑ ፤ የኢከነሚያዊ ቀቢፀ ተስፈኝነት የእሚገልፅ ቃል ለመሆን እንዲበቃ እስኪ ያደርግ ድረስ ፤ ቀኝ ግዛት እና ከእርሱም የእሚገኘው ‘ምርኮ’ የወቅቱን አውሮፓዊያን የተቆጣጠረ ኃሳብ አደረገው ፦
“ዘማቾቹም ፤ በባዕላት ቀን ሰውነቱን በወርቀ ዘቦ የእሚሸፍን ንግርታዊው ኤልደራዶ የእሚባል የኢንዲያኖች ንጉሥ አለ በእሚል ተነሳስተው ነበር ።”
“The conquistadors had been inspired by the legend of El-Dorado; an Indian king who believed to have covered his body with gold dust at festival times. [39]“
በግዜ ኺደት ግን ፤ ኹሉም አሳሽ እንደ ፒዛሮ አንድ ክፍል ሙሉ ወርቅ የእሚያፍስ ሰአይሆን ትላልቅ እርሻ ይዞ ትምባሆ ፣ ጥጥ ፣ ሸንኮራ ፣ ወዘተ ፤ ማልማት ብቸኛው የመበልፀጊያ መንገድ እየሆነ ሲመጣ እና ይኽም ብዙ መስዋትነት የእሚጠይቅ ጉዳይ መሆኑ ፤ ኹኔታው መልክ ቀይሮ ፥ ለእዚኽ ትላልቅ እርሻ የእሚያስፈልገውን እርሻ ለማግኘት የግዛት ማስፋት እሽቅድድም ፤ የስፔን ፣ የፖርቹጋል ፤ በኋላም የእንግሊዝ ፣ የፈረንሳይ ፣ የጀርመን እና የራሺያ ነገሥታትን በማፋጠጥ ፤ የቀኝ ግዛት ከእሚያመጣው ኢከነሚያዊ ጥቅም ይልቅ በሐገሬው ሕዝብ ዘንድ ለመንግሥታቱ የእሚያጎናፅፋቸው የታላቅነት ካባ ፤ ዋነኛ የፖለቲካ ሸቀጥ ሆነ ።
ፀሐይ በፖርቹጋል ግዛት ላይ አትጠልቅም የእሚለውን አባባል ፀሐይ በብሪታኒያ ግዛት ላይ አትጠልቅም በእሚለው መተካት ወይንም ይኽንን የ’ክብር’ ካባ መልበስ ከኢከነሚያዊ ጥቅሙ የበለጠ ተወደደ ።
አውሮፓዊያን ነገሥታት ኋላ ቀሩ ለአለመባል ወይንም ታላቅ ነገሥታት ለመባል ፤ ይኼ ነው የእሚባል ጥቅም የእማያገኙበትን ቦታ ኹሉ በኪሳራ መያዝ ጀመሩ ። በአጭሩ ለአውሮፓ ነገሥታት ፤ ቀኝ ግዛት ጉራው ከጥቅሙ በላይ ጠቃሚ ሆነ ።
ጀርመን ለጀርመኖች ብቻ በእሚል ፤ ፅንፈኛ ብሔርተኝነት ተንቀሳቅሶ ፤ ኹለተኛውን የዓለም ጦርነት ያስጀመረው አዶልፍ ሒትለር ፤ የራሳቸውን ሐገር ኖረውበት ሰአይጨርሱ ፤ በቀኝ ገዢነት አባዜ አፍሪካን ለመቀራመት እሽቅድድም ለገቡ ለሐገሩ ሕዝብ እንዲኽ ብሎዋቸው ነበር ፦
“ የጀርመን ሕዝብ ፤ ልጆቹን ኹሉ ሰብስቦ በአንድ መንግሥት ስር እስኪያሳድር ድረስ የቀኝ ግዛት ፖሊሲን ለማራመድ መብት የእሚባል አይኖረውም ። ያን ግዜ ፤ ግዛታቸው የጀርመንን ልጆች በሙሉ ከሰበሰበች በኋላ እና ግዛቱ ከመጥበቡ የተነሳ አላኖር ሲላቸው ፤ ያን ግዜ ነው ከሕዝቡ ፍላጎት በመነሳት የሌሎችን ድንበር ለመያዝ መንቀሳቀስ የእምንችለው ። ከእዚያኽም ማረሻውን ሰይፍ የሕዝቡም እንባ ለቀጣዩ ትውልድ እንጀራ መጋገሪያ ይሆናል ።”
“The German people will have no right to engage in a colonial policy until they shall have brought all their children together in the one State. When the territory of the Reich embraces all the Germans and finds itself unable to assure them a livelihood, only then can the moral right arise, from the need of the people to acquire foreign territory. The plough is then the sword; and the tears of war will produce the daily bread for the generations to come. [40]“
ምንም እንኳን ፤ አዶልፍ ሒትለር ፤ መነሻው የተሳሳተው ፅንፈኛ ነገዳዊነቱ ቢሆንም ፤ የሰው ሐገር ከመመኘታችን በፊት የራሳችንን እንኑርበት እያለ የእሚቀሰቅሰው ፤ ከእላይ እንደ አልነው ከዋናው የአውሮፓ አህጉር ውጭ ያለችው ደሴቷ ብሪታኒያ በተናጠል በአጋጠማት ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ማሻቀብ ምክንያት የቦታ እጥረት የነበረባት ቢሆንም ፤ በቀረው እና በዋናው የአውሮፓ አህጉር ሐገራት ዘንድ የሕዝቡ ቁጥር ከመሬቱ አንጻር ችግር የሆነበት ደረጃ ላይ ስለ አልደረሰ ፤ የወቅቱ የአውሮፓ ነገሥታት ፤ የግዛት ማስፋፋት አባዜ አስክሮዋቸው እንጂ ዋናው አውሮፓ ውስጥ ጀርመን ለጀርመናዊያን ወይንም ፈረንሳይ ለፈረንሳዊያን ጠባ፟ እንደ አይደለ ስለ ተገነዘበ እና ይኽም አካኼዳቸው የውስጥ ጉዳያቸውን ችላ እንዲሉ በማድረግ ለነውጠኛው ማርክሲዝም አመቺ ኹኔታ መፍጠሩን በማስተዋሉ ነው ።
በእዚኽ መልኩ ፤ ፍትኃዊ የሆነ ፥ ዓለም ዓቀፋዊ የባሕር እና የየብስ መንገዶችን ፤ ከአንድ ኢፍትኃዊ ኃይል ለማስለቀቅ ተብሎ የተጀመረው እንቅስቃሴ ፤ ጥቂት ሰዎች እየያዙ በመጡት ጀብደኝነት ሳቢያ እና ለንግድ ግንኙነት ምንም ዝግጅት ባል አደረጉ ከአውሮፓ ውጭ ባሉ ሕዝብ ደካማነት ምክንያት ፤ ወደ ዘረፋ ፣ ጉልበት ብዝበዛ እና የሰዎች መብት ረገጣ ተለወጠ ።
የአውሮፓ ደሴት የሆነችው ብሪታኒያ ፤ የዓለምን 1/4ኛ ሕዝብ የእምትገዛ ሆነች ፣ እንደ እነ ቤልጅየም ያሉ በጣም ትንሽ የአውሮፓ ሐገራት ፤ በስፋቷ ከሐገራቸው 80 እጥፍ የሆነችውን ዛየር/ኮንጎ ቀኝ ግዛት ማድረግ ጀመሩ ።
ይኽ ዓይነቱ ፥ የአውሮፓ ኃያላን የተጠመዱበት ጥቅም ተኮር ሰአይሆን ፤ ዝና እና ስግብግብነት ተኮር ዓለም ዓቀፋዊ ግዛት የማስፋፋት አባዜ ግን ኹለት መሠረታዊ ችግሮችን ይዞ መጣ ፦
አንደኛው ፦ በእዚኽ መልኩ ፤ ወደ ቀኝ ገዢነት የተቀየሩት አውሮፓዊያን ፤ ቀኝ በእሚገዙዋቸው ሐገሮች ዘንድ ሰፍረው እና ሕዝባዊ ውክልና ኖሮዋቸው ሰአይሆን ፤ በአላቸው የመሳሪያ ኃይል እና ፖለቲካዊ ልህቀት ፤ በጣም ጥቂት ሰዎች አስፍረው ፤ ትልቅ ቦታ እና ብዙ ሕዝብ በግድ የመግዛት ጉዳይ ስለ ሆነ ፤ ተገዢው ሕዝብ ንቃቱ እየጨመረ እና መብቱን እየጠየቀ ሲመጣ ፤ የተፈጠረውን ፖለቲካዊ ትኩሳት መቋቋም እየተሳናቸው መጣ ።
ኹለተኛው ፥ ብዙው ግዛት የእኔ ነው የእሚለው የእርስ በእርስ ፉክክር እና የራሳቸውን ሕዝብ ችላ ብለው ፤ ነገሥታቱ በመሳሪያ ጉልበት ቀኝ ከእሚገዙበት ሐገር በዝርፊያ የእሚያገኙት ኃብት ፤ ነገሥታቱን በተንደላቀቀ ኑሮ ሲያኖር ፤ የራሳቸው ሐገር ነዳያን ግን ቁራሽ ዳቦ የእሚቸግረው በመሆኑ ፤ በሐገራቸው ውስጥ የተፈጠረው አለመረጋጋት ፤ እንደ ፈረንሳይ አብዮት ዓይነቱን ችግር ፤ በሐገር ውስጥም ማስከተል ጀመረ ።
በአጠቃላይ ቀኝ ግዛት ፤ ጥቂት ነገሥታትን እና መኳንንቶችን ያከበረ ፤ በተረፈው ግን የቀኝ ገዢውንም ሆነ የቀኝ ተገዢውን ሐገር ሰፊ ሕዝብ በድህነት ረመጥ ውስጥ የረሳ ሆነ ። የፈረንሳይን ነገሥታት እጅግ በአማረ ቤተመንግሥት እየኖሩ ፤ በቤተመንግሥት ዙሪያ እንኳን የእሚኖረው የፈረንሳይ ሕዝብ ዳቦ አግኝቶ መብላት ተስኖት ነበር ።
ይኽ እንግዲኽ ፤ እነ እዚኽ ነገሥታት እና መኳንንቶቻቸው ፤ የትልቅ ግዛት ባለቤት ለመባል ፤ የሐገራቸውንም ሆነ የሌላውን ሕዝብ ችላ ብለው ፤ ደካማውን የዓለም አከባቢ ቀድመው ለመያዝ የእሚያደርጉት እሽቅድድም ፤ የራሳቸውን አህጉር አውሮፓን ጨምሮ በእየ አህጉሩ እርስ በእርስ ከእሚያደርጉት ደም አፋሳሽ ግጭት በአሻገር ማለት ነው ።
ይኽ የአውሮፓ ነገሥታት እና መኳንቶቻቸው የተዘፈቁበት ፤ የኪራይ ሰብሳቢነት አባዜ ፤ እንደ ፖለቲካዊ ባህል ዳብሮ እና ውስብስብነቱን በመጨመር ከእዚያኽም ጋር ተያይዞ የእሚፈለፍላቸው ማሕበራዊ ቀውሶች ከግዜ ወደ ግዜ እያየሉ ሲኼዱ ፤ በዓለማችን ታሪክ የመጀመሪያውን እና የመጨረሻውን ስኬታማ ዴሞክራሲያዊ አብዮት አስከተለ ።
የእዚኽ አብዮት መነሾም ፤ ከላይ በጠቅስነው መልኩ እጅግ የከፋ ድህነትን እና መገለልን ሽሽት ፤ ህይወታቸውን ለከፍተኛ አደጋ አጋልጠው ፤ በነፋስ በእሚገፉ የእንጨት መርከቦች አትላንቲክን አቋርጠው አሜሪካ የገቡት የሐገረ እንግሊዝ ሰፋሪዎች ፤ በዋናነት የብሪታኒያ ሰዎች ቢሆኑም ፥ ወደ እዚኽ ሰፈራ የመጡት ሰዎች በአብዛኛው ከዝቅተኛው የሕብረተሰብ ክፍል የነበሩ በመሆናቸው ፤ በወቅቱ ዴሞክራሲያዊ ፓርላማ በነበራት እንግሊዝ ፤ በፓርላማ የመወከል እድል ተነፍገው የነበሩ በመሆናቸው ነው ።
በፓርላማ በአይወከሉም ፤ ብሪታኒያ በእዚኽ ዓለም ዓቀፍ የግዛት ማስፋፋት ጦርነት ምክንያት የገባችበትን ብድር ለመክፈል ፤ በመላ ግዛቷ የተለያየ የግብር መጣል ስትጀምር ፤ እኛም የብሪታኒያ ዜጎች ስለ ሆንን ፤ በእንግሊዝ ፓርላማ ውክልና ሳይኖረን ግብር ለመክፈል ፈቃደኛ አንሆንም በማለታቸው አብዮት ተጀመረ ።
ይኽ ኹኔታ ፤ የወቅቱ መሪ ኃሳብ የነበረው የቀኝ ግዛት ፖሊሲ ችግሮች ወለል አድርጎ የእሚያሳይ ነው ። ከእነ እዚኽም ችግሮች ፤ የመጀመሪያው የቀኝ ግዛት የማስፋፋት ጦርነቱ ፤ ተሸናፊዎቹን ብቻ ሰአይሆን አሸናፊዎቹንም ያከሰረ የነበረ መሆኑን ነው ፦
“በአዲስ መልኩ የተስፋፋው የታላቋ ብሪታኒያ ግዛት ትልቅ የፋይናንስ ሸክም አስከተለ ፤ ይኽንም ተከትሎ እየፈላ የመጣው ጦርነቱ ያስከተለው ብድር አንድ ትልቅ የስጋት ምንጭ ነበር ። ጦርነቱ እ.አ.አ. በ1756 ዓ.ም. ፤ 33 ሚልዮን ፓውንድ የነበረውን የእንግሊዝ እዳ ወደ 133 ሚልዮን ፓውንድ በ1763 ዓ.ም. አሳደገው ። አመታዊው የእዳ ወለድ ክፍያ ብቻ የሐገሪቱን በጀት ግማሹን ጠየቀ ፤ በሺ የእሚቆጠር ወታደር በአሜሪካ ማስቀመጡም የግምጃ ቤቱን ያራቁተው ቀጠለ።”
“Great Britain’s neely enlarged empire meant a greater financial burden, and the mushrooming debt from the war was a major concern. The war bearly doubled the British national debt, from 75 million in 1756 to 133 million in 1763. Interest payments alone consumed over half the national budget, and the continuing military presence in America was a constant drain. [38]“
በጦርነቱ አሸናፊ የሆነችው ታላቋ ብሪታኒያ ራሷ ፤ የሰመጠችበት እዳ ትልቀት ፤ የእዳው ወለድ ብቻ የሐገሪቷን ዓመታዊ በጀት ግማሽ ከሆነ ፤ በእዚኽ አክሳሪ ግዛት የማስፋፋት ጦርነት የተሸነፉት ስፔን እና ፈረንሳይ መሰል ሐገራት የገቡበት ፤ የገንዘብ ፣ የሞራል እና ሰብዓዊ ኪሳራ ትልቅ እንደ ነበረ እና ሐገራቱንም በወሳኝነት እንደ ጎዳቸው መገመት ይቻላል ።
ኹለተኛው ፤ እነ እዚኽ ነገሥታት ፤ ለክብር እና ለዝና ሲሉ የእሚዋጉ እንጂ ለገዛ ሕዝባቸው እንኳን ደንታቢስ በመሆናቸው ፤ የሐገራቸውን ዜጎች እንኳን ፤ ዴሞክራሲያዊ በእምትባለው ብሪታኒያ ሳይቀር ፤ ቀኝ ግዛት በመሆናችሁ ፤ የፓርላማ ውክልና አታገኙም እስከ ማለት በእሚያደርስ ከንቱ ወገኝነት መተብተባቸው ነው ።
የአውሮፓ ነገሥታት በእዚኽ መልኩ በወግ እና በኪራይ ሰብሳቢነት ተጠርቀው ፤ በሐገር ውስጥም ሆነ ከሐገር ውጭ ፤ ልማዳዊ አሰራራቸው እየፈጠረባቸው የአለውን ፖለቲካዊ እና ኢከነሚያዊ ችግር መገንዘብ የተሳናቸው ድንዙዝ እየሆኑ በመኼዳቸው ፤ የአሜሪካ ሰፋሪዎች ፤ በታላቋ ብሪታኒያ ላይ ለዴሞክራሲያዊ ስረዓት ምሥረታ አብዮት አካኺደው ፤ በዘመናዊው የዓለም ታሪክ የመጀመሪያውን ውጤታማ ሕዝባዊ መንግሥት መሠረቱ ።
በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ፤ በአይበገሬነቱ የእሚታወቀውን የሐገረ እንግሊዝ ቀይ ኮት ለባሽ ጦር ፤ በሌላ ጠንካራ ንጉሥ ሠራዊት ሰአይሆን በሕዝባዊ ወታድራዊ አመፅ አሜሪካኖች ማሸነፍ መቻላቸው ፤ በሐገሩ ቀኝ ገዢ መንግሥታት ችላ ተብሎ ፤ ሕዝባዊ መንግሥት ፍልስፍና እያነቃቃው ለመጣው የአውሮፓ ሕዝብ ፤ በሕዝባዊ ወታደራዊ አመፅ እነ እዚኽን አጉል ወግ አጥባቂ እና ኪራይ ሰብሳቢ የዘውድ መንግሥታት በሕዝባዊ መንግሥት ለመተካት ትልቅ የልብ መበረታታት የሰጠ ክስተትም ሆነ ።
የተጀመረበት የፍትሕ እና የትብብር ጉዳይ ሰአይሆን ፤ በኋላ ላይ የመጣው ኢከነሚያዊ ፋይዳው ራሱ ተረስቶ ግዛት ከማስፋፋት የእሚገኘው ዝና ዋነኛ አጀንዳ የሆነበት ቀኝ ግዛት ፤ ያተረፈው ነገር ቢኖር ጦርነት እና ጦርነት ያስከተለው ሰብዓዊ እና ኢከነሚያዊ ኪሳራ ሆነ ። ይኽም ብቻ ሰአይሆን ፤ የወቅቱ የአውሮፓ ነገሥታት ፤ በእዚኽ እነርሱን እና ነገሥታቶቻቸውን ብቻ በዘረፋ እና በብዝበዛ በእሚመጣ ኃብት እያናጠጠ ፤ በወቅቱ የሳይንስ አብዮት ፖለቲካዊ ንቃቱ እየዳበረ የመጣውን የራሳቸውን ሕዝብ እንኳን ችላ በማለቱ ፤ የአሜሪካን ዓይነት ሕዝባዊ ወታደራዊ አመፅ አድርጎ በመላ አውሮፓ የዘውድ ስረዓቶችን በሙሉ ሽሮ ሕዝባዊ መንግሥት ማቋቋም ይቻላል የእሚለው ኃሳብ ፤ በምድረ አውሮፓ ፖለቲካዊ ምህዳር ገኖ የነበረውን ቀኝ የመግዛት አጀንዳ ፤ ይዞት የነበረውን ገዢ መሬት አስለቀቀው ።
ይኽ አዲስ ፖለቲካዊ መነቃቃት ፤ በአውሮፓ እ.አ.አ. በ1889 ዓ.ም. የተጀምረውን የፈርንሳይ አብዮት አስጀመረ ። ምንም እንኳን ይኽ የፈረንሳዩ አብዮት ተሳክቶለት ፤ የዘውድ ስረዓቱን ቢገረስስም ፤ ከአሜሪካ አብዮት በኋላ በዓለም ዙሪያ እንደ ተካኼዱት ሌሎች አብዮቶች በሙሉ ፤ የቀኝ ግዛት ያናወዛቸውን አምባገነናዊ የዘውድ ስረዓቶችን በሕዝባዊ አመፅ ማስወገድ ይቻላል የእሚለውን ኃሳብ በተግባር ከማረጋገጥ የአለፈ የፈየደው መልካም ነገር አልነበረም ።
ይኽ የፈረንሳይ አብዮት ፤ በዓለም ዙሪያ በእሚታወቅበት ጊለቲን ፤ ምድረ ፈረንሳይን ለ10 ዓመት በደም አጨቅይቶ ፣ የአብዮቱን መሪ ሮብስፒርን ራሱ ለአስጀመረው ጊለቲን ዳርጎ ፤ በእ.አ.አ. በ1899 ዓ.ም. ናፖሊዮንን ወደ ስልጣን በማምጣት ወይንም ሌላ የዘውድ ስርወ መንግሥት ተክቶ ፤ በነበረበት ረግጦ ተጠናቀቀ ።
ምስል 2 ፡ ጊለቲን ፡ በፈረንሳይ አብዮት ወቅት የሞት ቅጣት ማስፈጸሚያ።
በእዚኽ መልኩ ‘እድል’ ፊቷን ያዞረችባቸው የአውሮፓ ነገሥታት ፤ ከገቡበት አጣብቂኝ ለመውጣት የእሚያበቃ ይኽ ነው የእሚባል አዲስ ፖለቲካዊ ስልት በአለማዳበራቸው ፤ በመላው ዓለም ተዘፍቀውበት አልአዋጣ የአላቸው እና የሐገራችውን ሕዝብ ራሱ ያስንሳባቸው ወግ አጥባቂነታቸው አልበቃ ያለ ይመስል ፤ በአውሮፓ ውስጥ የአደረጉት የግዛት ማስፋፋት ፉክክር ፤ አንድ የኦስትሪያ ልዑልን መገደልን ተከትሎ የአንደኛውን የዓለም ጦርነት አስከተለ ።
የአንደኛውን የዓለም ጦርነት ያስከተሉ ብዙ ተያያዥነት የአላቸው ምክንያቶች ቢኖሩም ፤ አቀጣጥይ ምክንያቱ ግን ፤ ስላቭ የእሚባሉት እና በወቅቱ በዖቶማን ተርክ ፣ በራሺያ እና በአስትሮ ሐንጋሪ ግዛቶች ውስጥ ነዋሪ የነበሩ አውሮፓዊያን ነገድ አባላት ፤ በተስፋፊዋ ራሻ አይዞዋቹሁ ባይነት ፤ አስትሮ-ሐንጋሪ ይባል በነበረው ኢምፓየር እና የቀድሞ ዖቶማን ተርክ ኢምፓየር ውስጥ የእሚገኙትን የስላቭ ሕዝባቸውን ያካተተ ፤ ታላቋ ሰርቢያ የእምትባል አዲስ ሐገር ለመመሥረት በአላቸው ህልም ፤ የአስትሮ-ሐንጋሪ በመባል ይታወቅ የነበረውን የኢምፓየሩ አልጋ ወራሽ ፍራንሲስ ፈርዲናንድ (Archduke Francis Ferdinand) ሳራይቮ በእሚባል ከተማ ላይ በጉብኝት ላይ ሳለ ፤ የስላቭ ሕዝብ ነፃ አውጭ ትግል መሪዎች በመግደላቸው ነው ፦
“ይኽ አውዳሚ እሳት የተለኮሰው ፤ የአስትሮ ሐንጋሪው አልጋወራሽ ፍራንሲስ ፈርዲናንድ ፤ በቦሲንያ ዋና ከተማ ሳራይቮ ፤ እ.አ.አ. በሰኔ 28, 1914 ዓ.ም. በሰርቢያ ነፃ አውጪዎች በመገደሉ ነው ።“
“The catastrphic conflagration was set off by a spark – the assassination of Austro-Hungarian Archduke Francis Ferdinand in Sarajevo, the capital of Bosnia, on June 28, 1914, by a serb nationalist. [41]“
ከግድያው በኋላ ፤ በስላቭ ነፃ አውጪዎች ፤ አልጋ ወራሻቸው የተገደለባቸው የአስትሮ-ሐንጋሪ ኢምፓየር መሪዎች ፤ ለሰርቢያኖች ፥ ያስጠለላችሁዋቸውን በአስትሮ-ሐንጋሪ ግዛት ውስጥ የአሉትን ስላቮች በመውስድ ሐገራችንን መቁረስ የእሚፈልጉትን ነፃ አውጭዎች በግልፅ ካለ አወገዛችኹ ፤ ማለትም በ48 ሰዓት ውስጥ ፤ የነፃ አውጪ ድርጅታቸውን በግልፅ ካል አገዳችሁ ፣ ጋዜጦቻችውን ከአልዘጋችኹ እና ከነፃ አውጪዎቹ ጋር ግንኙነት የአላቸውን እና እኛ የእምንጠቁማቸውን ሰዎች ከስልጣን ከአላወረዳችሁ ፤ እንዘምትባችኋለን የእሚል ማስጠንቀቂያ ሰጡዋቸው ።
ማስጠንቀቂያው በሰርቦች ቸል ሲባል ፤ በሰርቦች ላይ ስለ ዘመቱባቸው ፤ ሰርቦቹን ለማገዝ ደግሞ ኃይ ባያቸው ራሺያ ወደ ጦርነቱ በመግባቷ ፤ የራሺያ ወደ ጦርነቱ መግባት ጀርመኖችን ከአስትሮ ሓንጋሪ ኢምፓየር ጋር እንዲያብሩ ሲያደርግ ፤ በእየ ራሳቸው ምክንያት ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ከራሻ ጋር በማበራቸው ፤ በመላው አውሮፓ ብሎም በኋላ ላይ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ አዲስ የሆነ የኃይል አሰላለፍ ተፈጥሮ ፤ ራሺያ ፣ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ በአንድ ጎራ ፤ ጀርመን ፣ ጣሊያን እና አስትሮ-ሀንጋሪ በአንድ ጎራ ሆነው ለ4 ዓመት ቆይቶ ለ38 ሚልየን ሰዎች መሞት እና መቁሰል ምክንያት የሆነውን የአንደኛው የዓለም ጦርነት አስጀመሩት ።
ምንም እንኳን በእዚኽ አውድ ፤ ይኽን ደም አፋሳሽ ጦርነት የፈጠረውን ድባብ ለማብራራት ተገቢ በአይሆንም ፤ ራሺያ የሰርብ ነፃ አውጭዎችን ፤ አስትሮ-ሀንጋሪ እና ዖቶማን ተርክ ኢምፓየር ውስጥ የአሉትን ሕዝብ የጨመረ አዲስ ሐገር መስርቱ እያለች አይዙዋቸኹ የእምትልበት ዋና ዓላማ ፤ ታላቋ ሰርብ የስላቭ ሕዝብ መኖሪያ እንድትኾን ከአላት ጉጉት ሰአይሆን ፤ ታሪካዊቷን ወይንም ምሥራቃዊ ሮም የነበረችውን ፤የቤዛንታይን ኮንስታንቲኖፖል (ኢስታንቡል) ከቱርክ ፤ የዛሬውን ፖላንድ አከባቢ ደግሞ ከአስትሮ-ሐንጋሪ ኢምፓየሮች መንጠቅ ትፈግ ስለ ነበር ፤ ሰርቦች በነጻነት ስም አስትሮ ኃንጋሪን እና የዖቶማን ተርኮችን በሰርጎ ገብነት እንዲያስጨንቁላት ከመፈለግ ነው ።
እነ እዚኽን አዳዲስ ግዛቶች መጨመር የእምትፈልገው ራሺያ ፤ በምዕራቡ እና በምሥራቁ የሐገሯ ጫፍ የዘጠኝ ሰዓት ልዩነት ፤ ማለትም በአንዱ ከተማ ከጠዋቱ 1 ሰዓት ሲሆን በሌላው ጫፍ ከቀኑ 10 ሰዓት የእሚሆንባት ራሺያ በመሆኗ ፤ የወቅቱ የአውሮፓ ነገሥታት በቀኝ ግዛት ማስፋፋት ምክንያት የገቡበት ፖለቲካዊ መናወዝ በግልፅ የእሚታይ ነው ።
የቀኝ ግዛት አስተሳሰብ ፤ በእዚኽ መልኩ ወደ አፍራሽ ጡዘቱ ላይ ሲደርስ ፤ ከአሜሪካው ሕዝባዊ መንግሥት አስተሳሰብ ጋር ተመሳሳይነት የአለው እና በብዙ የፖሊሲ አቅጣጫው ከአሜሪካው የሕዝባዊ መንግሥት አስተሳሰብ እጅግ የተለየው የከምኒዝም/ሶሻሊዝም አስተሳሰብ ፤ በእንግሊዙ ባለ ኃብት ሮበርት ዖውን (Robert Owen) እና መሰል ሰዎች በ19ኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ አከባቢ ይቀነቀን ስለ ነበር ፤ የሮበርት ዖወን ደቀ መዝሙር የነበረው ፍሬድሪክ ኤንግልስ ፤ ከካርል ማርክስ ጋር በመሆን ራሳቸውን የዘመናዊ ከምኒዝም የእውቀት ነፍስ አባት ወደ ማድረግ አመጣቸው ።
በእነ ቫስኮ ደጋማ አሳሽነት እና በአውሮፓ የነበረውን አስከፊ ድህነት እና ማሕበራዊ ማግለል ሽሽት ፤ በእንጨት በተሰሩ እና በነፋስ ኃይል በእሚገፉ መርከቦች ፤ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ፤ በውል ወደ እማያውቁት ሐገር ከተሰድዱት የተወሰኑ የእንግሊዝ ማሕበረሰብ አካላት ጀምሮ ፤ ቢያንስ ለ300 ዓመታት ፤ ይኽ ትርጉም የለሽ የአንደኛው የዓለም ጦርነት እስኪ ጀምር የቆየው የቀኝ ግዛት ፤ ነገሥታቱ እና ተለጣፊዎቻቸው ፤ በተንደላቀቀ ኹኔታ ሲኖሩ ፤ ሰፊው ሕዝብ ግን ቁራሽ ዳቦ የተቸገረበት እና ይኽ ነው የእሚባል ፖለቲካዊ ውክልና እንደ አይኖረው የአደረገ በመሆኑ ፤ የወቅቱ ሙህራን ፤ ለእዚኽ ማሕበረሰባዊ ውድቀት ተጠያቂው ኋላ ቀሩ የፖለቲካ ስረዓታችን ነው ብለው ቀኝ ገዢውን ዘውዳዊ ስረዓት ተጠያቂ ያደረጉበት ዘመን በመሆኑ ፤ የሕብረተሰባዊነት ወይንም የሶሻሊዝም እንቅስቃሴ በአውሮፓ ቀስ በቀስ እያደገ ኼዶ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1848 ዓ.ም. አከባቢ አንድ ትልቅ ደረጃ ላይ እንዲ ደርስ አደረገው ።
ምንም እንኳን የከምኒዝም/ሶሻሊዝም አስተሳሰብ ፤ ከጥንታዊ ግሪኮቹ እነ ፓይታጎረስ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም ፤ በእነ ሮበርት ዖውን ፣ ፍሬድሪክ ኤንግልስ እና ማርክስ ራሱን እንደ ቻለ አንድ የፍልስፍና መስክ እንዲያድግ በዙ እሴት ስለ ተጨመረበት ፤ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ አከባቢ ፤ የከምኒስት ማንፌስቶ ፣ ዳስ ካፒታል እና ሌሎች ብዙ መሰል መጽሐፍት ተጽፈውበት ፤ ፍልስፍናው የማርክስን ስም ወደ ያዘበት ደረጃ ደርሶ እና ውስጥ ውስጡን ተራማጅ የእሚባለው የአውሮፓ የሕብረተሰብ ክፍል ኹሉ ፤ በስውር የእሚያጠናው ሆኖ ስለ ነበር ፤ የሶሻሊስት ወይንም የሕዝባዊ መንግሥት ማቋቋም መፈለግ በተለይ በአውሮፓ ዘመነኛው ኹሉ የእሚፈልገው ፖለቲካዊ ስረዓት አደረገው ።
ሶሻሊስቶች/ከምውኒስቶች ፤ በውስጣቸው ብዙ ፈርጅ ቢኖርም ፤ ከእነዚኽ መካከል የገነኑት ማርክሲስቶች ፤ የፈረንሳዩን ዓይነት ሕዝባዊ አብዮት በግብታዊነት ሰአይሆን በተደራጀ መልኩ ማድረግ በእሚፈልጉ የተለያዩ ቡድኖች በአውሮፓ በስውር ሲጠና ነበር ። ከእነዚኽ መካከል አንዱ ፤ አሌክሳንደር ኡልያኖቭ የእሚባለው የቭላድሚር ሌኔን ታላቅ ወንድም ነበር ። አሌክሳንደር ኡልያኖቭም በማርክሲዝም ጥናት ተነሳስቶ የገባበት የሳሻሊስት አብዮት እንቅስቃሴ ከወቅቱ ዘውዳዊ የራሺያ መንግሥት ጋር አጋጭቶት ፤ በመንግሥት ላይ በማሴር ተከሶ ፤ በስቅላት በሞት እንዲቀጣ አድርጎታል ።
በቀለም እውቀቱ የተመሰከረለት የአሌክሳንደር ታናሽ ወንድም ሌኒን ፤ በአብዮተኝነቱ በራሻው ዛር ህይወቱን የተነጠቀውን የወንድሙን ዱካ ተከትሎ ፤ በአሥራዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ከነበረበት ጀምሮ በማርክሲዝም ጥናት የእሚመራ አብዮት ለመአካኼድ ሲፈልግ የነበረ በመሆኑ ፤ እ.አ.አ. በ1917 ዓ.ም. የራሻው ዛር ፤ በአክሳሪው የአንደኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ ለ3 ተከታታይ ዓመታት በመቆየት ፤ ሐገሪቱ ላይ በአደረሰው ከፍተኛ ኢከነሚያዊ እና ሰብዓዊ ኪሳራ ፤ በእዚኽም በተነሳበት ሕዝባዊ ተቃውሞ ተዳክሞ ፥ ራሱን ከስልጣን ገሸሽ የአደረገበት እና የተረጋጋ መንግሥት አለመኖሩን ተጥቅሞ ፤ የሶሻሊስት አብዮት በእሚል ፤ ግዜያዊ አስተዳደሩን ገልብጦ ፤ ራሻን በዓለም ላይ ፤ በማርክሲዝም ፍልስፍና የእምትመራ የመጀመሪያዋ ከምኒስት ሐገር አደረጋት ።
ይኽም ማለት ፤ አሜሪካኖች ከእንግሊዝ ነፃ ከወጡ ከ150 ዓመት ገደማ በኋላ በመሆኑ ፤ እ.አ.አ. በ1918 ዓ.ም. የራሺያን ከምኒስት መሆንን ተከትሎ ኹለት የዓለም ትላልቅ ሐገራት ፤ በተፃራሪ የሕዝባዊ መንግሥት ፍልስፍና የእሚመሩ ኹለት ሕዝባዊ ሐገራት ሆኑ ።
ይኽም ታሪካዊ ክስተት ፤ ክርስቶፈር ከለምበስ አዲስ ዓለም ከአገኘበት አንስቶ እስከ እዚኽ ግዜ ድረስ (እ.አ.አ. 1495 – 1917/8 ዓ.ም.) ፤ የዓለም ዓቀፍ ፖለቲካ ድባብ ገዢ መገለጫ የነበረውን ዘውዳዊ መንግሥት አስተሳሰብ እና ቀኝ ግዛት (The globally dominant political ideology) ፤ በማስረጀት የሕዝባዊ መንግሥት አስተሳሰብ በዓለም ዓቀፍ የፖለቲካው ምህዳር ፤ ገዢ የፖለቲካ አስተሳሰብ እንዲሆን በማድረግ ፤ የዓለምን ታሪክ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያስገባ ነበር ።
በእዚኽም ምክንያት ፤ ይኽ የራሺያ አብዮት ፦ የዘውዳዊ መንግሥት አስተሳሰብ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለሕዝባዊ መንግሥት አስተሳሰብ የመሪነቱን ስፍራ የለቀቀበት መሆኑን ያረጋገጠ ክስተት በመሆን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ያስጀመረ ነበር ።
የእዚኽ የአዲሱ የዓለም ዓቀፍ ፖለቲካዊ ገፅታ ወይንም የሕዝባዊ መንግሥት አስተሳሰብ ፤ አክሳሪውን እና ፀረ ሕዝብ የሆነውን ቀኝ ግዛት ማስወገጃ መንገድ አድርጎ ይዞ የመጣው አንድ መሠረታዊ እና አዲስ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ደግሞ የሕዝብ የራስን እድል በራስ የመወሰንን መርህ ነበር ።
ይኽ የራስን እድል በራስ የመወሰን አዲስ ፖለቲካዊ አካኼድ ግን ፤ በዴሞክራሲያዊ መንግሥታት እና በአንዳንድ የከምኒስት ፍልስፍና አራማጆች ፍፁም ተፃራሪ በሆኑ አግባቦች መቅረብ ጀመረ ።
የዴመክራሲያዊ መንግሥት አስተሳሰብ አራማጅ በሆነችው አሜሪካ ወይንም በኋላ የምዕራቡ ዓለም በመባል የእሚታወቁት ሐገራት መገለጫ የሆነው የምዕራባዊያን ዴሞክራሲ ፤ ይኽን የራስን እድል በራስ የመወሰን ኃሳብ ፤ በኪራይ ሰብሳቢነት እና ምክንያት የለሽ ወግ አጥባቂነቱ ሳቢያ ፤ የመቀመጫ ሐገሩንም ሆነ በቀኝ ግዛት የያዛቸውን ሕዝብ ሰላም ፣ ደህንነት እና ጥቅም ችላ በማለት ፤ ለዝና በእሚደረግ እሽቅድድም ከገባበበት የግዛት ማስፋፋት አባዜ እና እርሱንም ተከትሎ ከመጡት ተደጋጋሚ እና ትላልቅ ፤ ኢከነሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ ፣ ሰብዓዊ እዳ ከአስከተሉ ጦርነቶች ዓለምን እና የዓለምን ሕዝብ ለማዳን ወይንም ቀኝ-ግዢን/ከለናይዜሽንን ለማስቀረት ፤ ሰዎች በእየሚኖሩባቸው አከባቢዎች ከእዚኽ እኩይ ቀኝ ግዛት ተላቀው የራሳቸውን እድል በራሳቸው ይወስኑ ወይንም ራሳቸውን በራሳቸው የአስተዳድሩ የእሚል ሆነ ።
በካርል ማርክስ አስተምህሮ መሠረት የከምኒስት ርዕዮት ማዕከል ሆና የመጣችው ራሺያ ወይንም በአብዛኛው የምሥራቁ ዓለም መገለጫ የሆነው የከምኒዝም ፍልስፍና ውስጥ በተለይ ወደ መጀመሪያ አከባቢ የነበሩ እንደ ሌኒን የአሉ አንዳንድ ከምንስቶች ፤ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ወይንም መርህ ፤ በዋናነት የታሪክ ቁሳዊነት (Historical Materialism) አጋዥ ሆኖ ፤ ወግ አጥባቂ የሆኑ እና በታሪክ ቁሳዊነት የእድገት ደረጃ ፤ ከፊውዳሊዝም ወደ ካፒታሊዝም ወይንም ከካፒታሊዝም ወደ ሶሻሊዝም ለመሸጋገር የእሚደረገውን አብዮት የእሚቃወሙ እምቢተኞችን ወይንም ወግ አጥባቂያንን (reactionaries) ለመጣል እስከ አገለገለ ድረስ ፤ እንደ ስልት ፤ በእየ ሐገሩ ያሉ ብሔርተኞችን ወይንም ተገንጣዮችን በእዚኽ መልክ በማደራጀት ወግ አጥባቂ መንግሥቶቻቸውን እንዲ ገለብጡ ለማድረግ ልንጠቀምበት ይገባል የእሚል ሆነ ።
የእነ እዚኽ አንዳንድ የከምኒስት ተከታዮች አካኼድ ፤ በእዚኽ መልኩ እነ እዚኽ ወግ አጥባቂ መንግሥታት ከተወገዱ በኋላ ፤ በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ሰብስበን ፤ የዓለም ዓቀፍ ወዛደሮች ተባበሩ በእሚል በአንድ ዓለም ዓቀፍ አስተዳደር ስር እናመጣቸዋለን የእሚል ነው ።
በአጭሩ ፤ ለአሜሪካ እና ለዴሞክራሲ ኃይላት ፤ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ፤ ከቀኝ ግዛት አከባቢዎችን ነፃ ማውጫ ተድርጎ ሲቀርብ ፤ በአንዳንድ የከሚውኒስት ፖለቲከኞች ደግሞ በማንኛውም ሶሻሊስት በአልሆነ መንግሥት ላይ በብሔርተኝነት ወይንም በገንጣይነት ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን በእሚል ቢኽል የመገንጠል ጥያቄን ሕዝባዊ አመፅ ማቀጣጠያ ስልት ሆኖ ቀረበ ።
በእዚኽ በዴሞክራሲያኖቹ የራስን እድል በራስ መወሰን የእሚለውን መብት በእሚገነዘቡበት አግባብ ነው ፤ የዛሬው የተባበሩት መንግሥታት የተመሠረተው እና የዛሬው የሐገራት ሉዓላዊነት የተከበረበት ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት የተቃኘው።
በዴሞክራሲያኑ እሳቤ መሠረት ፤ ማለትም ፦ ከቀኝ ግዛት ነጻ ለመውጣት እና ሉዓላዊ ሐገር ለመሆን ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን የእሚለው መብት ፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እውቅና የአለው መብት እንዲሆን ፤ ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱት ፤ 28ኛው የአሜሪካን ፕሬዝደንት የነበሩት እና ሊግ ኦፍ ኔሽንስ ፥ የአኹኑ የተባበሩት መንግሥታት ቀዳሚ የነበረውን ተቋም የማቋቋም ኺደት የመሩት ፤ ውድሮው ዊልሰን (Woodrow Wilson እ.አ.አ. 1856 – 1924 ዓ.ም.) ናቸው ፦
“ ... ፕሬዝደነት ውድሮው ዊልሰን … ከመርሁ (የራስን እድል በራስ መወሰን) ጋር ተነጣጥሎ ሊታይ በእማይችል መልኩ የመርሁ አራማጅ ርዕሰብሔር ነበሩ ።”
“ ... President Woodrow Wilson ... the statesman most closely identified with the principle. [42]“
በውድሮው ዊልሰን የተጀመረው ይኽ ቀኝ ግዛትን እና አሉታዊ ውጤቱን ለማስቀረት ታስቦ ፤ ሰላም ወዳዱ የዓለም ሕዝብ ፤ ቀኝ ግዛትን የእሚያግድበት ዓለም ዓቀፋዊ እውቅና የአለው መብት ሆኖ በተባበሩት መንግሥታት ለመታወጅ የበቃው እ.አ.አ. በ1960 ዓ.ም. ነበር ።
ይኽ በተባበሩት መንግሥታት እ.አ.አ. በ1960 ዓ.ም. የታወጀው ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን የእሚለው ፅንሰ ኃሳብ ፤ የተቀመጠበት አግባብ ጠባቦች ፣ ጎጥኞች ወይንም እንደ ማርክሲስት ያሉ ነውጠኞች ፤ የተከበረውን የመብት ጥያቄን የመፈንቅለ መንግሥት መሸፈኛ እንደ አያደርጉት ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን የእሚለው መርህ በቀኝ ግዛት ስር ላሉ ሐገራት ሕዝብ ከቀኝ ግዛት ነፃ ለመውጣት የእሚያስችላቸውን ኹኔታ ለማስቻል በማሰብ የተቀመጠ መሆኑን እንዲያሳይ ተደርጎ የተቀመጠ ነው ።
የተባበሩት መንግሥታት አዋጅ ፤ ሐገራት እና ሕዝብ የእሚል ቢኖረውም ፤ ሕዝብ የእሚለው ቃል ፅንፈኛ ብሔርተኞች እንደ እሚሉት ለማንኛውም የብሔራዊ ወይንም የመገንጠል ጥያቄ ለእሚያነሱ የሕዝብ ንዑሳንን የእሚወክል ሰአይሆን በቀኝ ግዛት ስር የአለን የአንድ አከባቢ ነዋሪን ሕዝብ የእሚያመለክት መሆኑ ከአዋጁ ዝርዝር ግልፅ ነው። እንደ እሚታወቀው ፤ ከቀኝ ግዛት በፊት ሐገር የአልነበረ ግን በቀኝ ግዛት ስር የወደቀ ብዙ የዓለም ሕዝብ ነበር ፦
“ቀኝ ለተገዙ ሐገሮች እና ሕዝብ ከቀኝ ግዛት ነፃ እንዲወጡ የእሚያዝ አዋጅ
የጠቅላላው ጉባኤ ውሳኔ 1514 (፲፭) እ.አ.አ. ታሕሳስ 14, 1960 ዓ.ም.”
“Declaration on the Granting of Independence to Colonial Countries and Peoples General Assembly resolution 1514 (XV) of 14 December 1960”
በአሜሪካ የሰላም ማዕከል በተደረገ ኮንፍረንስም ላይ ፤ ይኽ የተበባበሩት መንግሥታት አዋጅ ፤ ከጽንፈኛ ብሔርተኞች በተቃራኒ ፤ በቀኝ ግዛት የአለን አከባቢ ከቀኝ ግዛት ነጻ ለማውጣት ታሳቢ የሆነ አዋጅ መሆኑን በእዚኽ መልኩ ያስቀምጡታል ፦
“በእዚኽ ዘመን የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ኃሳብን በማስፋፋት እና ትርጉሙን በእማያሻማ መልኩ በማስቀመጥ ኺደት ውስጥ ወሳኝ ሰነድ የነበረው ፤ እ.አ.አ. በ1960 ዓ.ም. ቀኝ ለተገዙ ሕዝብ ነፃነትን የሰጠው የተባበሩት መንግሥታት አዋጅ ነው ። … የመብቱ ባለቤት ለመሆን የእሚያስፈልጉትን ቅድመ ኹኔታዎች ዝርዝር ውስጥ የተለየ ነገድ መሆን ፣ የተለየ ቋንቋ ተናጋሪ መሆን ወይንም አንድ የሆነ ባሕል ይዞ መገኘት የተካተቱ አይደሉም ፤ ይልቁንም የራስን እድል በራስ መወሰንም በዋናነት ከቀኝ ግዛት ነጻ መውጣት ጋር የተያያዘ ነው የሆነው።”
“The most important document in the promotion of the right to self-determination, and one that provides a clear indication of its meaning during this era, was the 1960 UN decleration on the granting of Independence to Colonial Peoples. …, the criteria underlying the right did not include possession of a distinct ethnicity, language, or culture; rather, self-determination was simply a more appealing term for decolonization. [42]“
እስከ ዛሬም ድረስ ፤ ከተወሰኑ ጥራዝ ነጠቅ (Exceptional) ገጠመኞች በስተቀር ፤ ዓለም ዓቀፋዊ እውቅና የአለው እና የእምንኖርበትን የአኹኑ ዓለም ፤ በተሻለ ኹኔታ የተረጋጋ እና ለሕዝብ ሰላም ፣ ደህንነት እና ተጠቃሚነት አዎንታዊ ሚና የአለው ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን የእሚለው መብት አረዳድ ፤ የሐገራትን (የነገድ ወይንም ጎሳ ወይንም ሰፋሪዎች ፣ ወዘተ ፤ ነፃ ማውጣት ታሳቢ የአደረገ ሰአይሆን ) ሉዓላዊነት እያከበረ ፤ በአንድ ጂኦግራፊያዊ አከባቢ የእሚኖር ሕዝብ (ከነገድ ፣ ከጎጥ ፣ ከቋንቋ ፣ ወዘተ ፤ እሳቤ ውጭ) ከውጭ መንግሥት አሉታዊ ጣልቃ ገብነት በፀዳ መልኩ የራሳቸውን ጉዳይ በራሳቸው እንዲወስኑ የእሚፈቅድበት አግባብ ነው ።
ይኽ ግን የአኹኑ እና ነባራዊው ዓለም አብይ ተቋማት ፦ ሐገራት ፣ መንግሥታት ፣ ዓለም ዓቀፍ ንግድ ፣ ኃይማኖት ፣ ወዘተ ፤ ማሕበረ ኢከነሚ ስሪቶች በመሆናቸው መጥፋት አለባቸው እና የዓለም ሕዝብ በዓለም ዓቀፍ የሠራተኛው አብዮት አስተሳሰብ በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት እና በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ በመመራት ፤ ወደ ሶሻሊዝም ከሶሻሊዝምም ወደ ከምኒዝም መመራት አለበት ለእሚሉት ማርክሲስቶች ፤ ዓለም ዓቀፋዊ ይዘት የአለውን የአብዮታቸውን አስተሳሰብ እማያፈናፍን በመሆኑ ፤ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብትን ከዓለም ዓቀፋዊ ጠርናፊው ርዕዮታቸው ጋር እንዴት ሊያዋድዱት እንደ እሚችሉ የተቸገሩበት ጉዳይ ነው የሆነው።
ለማርክሲስቶች ፦ ሐገራት ወይንም ሕዝብ የራሳቸውን እድል በራሳቸው የመወሰን መብት አላቸው የእሚለውን መብት አለመቀበል ቀጥታ ከአብዛኛው ከሰፊው ሕዝብ ጋር መጋጨት ነው ፤ ይኽንን መርኽ ደግፎ ሐገራት ወይንም ሕዝብ ከቀኝ ግዛት ነጻ ከወጡ ፤ የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው እንዲወስኑ ሉዓላዊነታቸው ሊከበርላቸው ይገባል ማለት ደግሞ ፤ በዋናነት በመደብ ትግል አስተሳሰብ ከተቃኘው ዓለም ዓቀፋዊ ወይንም ድንበር ተሻጋሪው የሠራተኛው አብዮት ጋር የእሚጋጭ ነው።
እንደ አብዛኛው ማርክስሲቶች ፦ በእዚኽ መልኩ ሕዝብ የራሳቸውን እድል በራሳቸው ይወስኑ በእሚል ማለት ፤ የካፒታሊዝም ወይንም የፊውዳሊዝም ስረዓት በላብ አደሩ እና በገበሬው ላይ የእሚያደርሰውን ብዝበዛ ማስቀጠል ነው ።
ይኽን ከምኒስቶች የፈተነው የራስን እድል በራስ የመወሰን መብትን ለመረዳት ፤ ከምኒዝም ስለ ሐገር እና መንግሥት የአለውን ትንታኔ መረዳት የግድ ነው ።
ስለ ፖለቲካዊ ፅንፈኝነት በእምንነጋገርበት ወቅት ፤ ከምኒዝም ሐገር የቡርዣ ስሪት እንደሆነች እና መጥፋት አለባት እንደ እሚል አስቀምጠናል ። በተመሳሳይ ፥ ለከምኒዝም መንግሥት ፤ በመደብ ትግል ውስጥ የበላይነቱን የያዘው መደብ ሌላውን መደብ የእሚጨቁንበት መሳሪያ ነው ብሎ ነው የእሚያምነው ።
ከምኒዝም ስለ መንግሥት የአለውን አስተሳሰብ ሌኒን ፤ መንግሥት እና አብዮት በእሚለው መጽሐፉ ላይ እንዲ እዚኽ አስቀምጦታል ፦
“መንግሥት ፤ የመደብ ተቃርኖ ሊታረቅ የእማይችል መሆኑ ማሳያ እና የእርሱም ውጤት ነው ። መንግሥት የእሚቆመው ፤ የመደብ ተቃርኖው በመርህ ደረጃ ሊታረቅ በእማይችልበት ቦታ እና ግዜ ነው ። በተገላቢጦሽ ፤ መንግሥት አለ ማለት የመደብ ተቃርኖው ሊታረቅ አይችልም ማለት ነው ።”
“The state is a product and a manifestation of the irreconcilability of class antagonisms. The state arises where, when and insofar as class antagonism objectively cannot be reconciled. And, conversely, the existence of the state proves that the class antagonisms are irreconcilable. [29]“
ይኽ የሌኒን ኃሳብ ብቻ ሰአይሆን ፤ የማርክስም አስተሳሰብ መሆኑን ለማሳየት ሌኒን ፥ ማርክስን በመጥቀስ ፤ ማርክስ ስለ መንግሥት የአለውን አስተሳሰብ እንደ እዚኽ ያስቀምጠዋል ፦
“እንደ ማርክስ አባባል ፤ መንግሥት የመደብ መግዣ እጅ (መዋቅር) ነው ፤ አንዱ መደብ ሌላኛውን መደብ የእሚጨቁንበት እጅ ነው ፤ ይኽንን ጭቆና ሕጋዊነት ለመስጠት እና ለማስቀጠል የመደብ ግጭቶችን እያለሰለሰ የእሚኼድ ፤ አንድ ዓይነት ስረዓት መፍጠሪያ መሳሪያ ነው ።”
“According to Marx, the state is an organ of class rule, an organ for the oppression of one class by another; it is the creation of ‘order’, which legalizes and perpetuates this oppression by moderating the conflict between classes. [29]“
ስለ እዚኽ ፦ ከምኒዝም ፤ መንግሥትን የጭቆና እጅ ነው ካለ ፤ የከምኒዝምን የመንግሥት ፍልስፍና የእሚመለከተው ኹለተኛ ጥያቄ ፤ ከምኒዝም መንግሥት የሌለበትን ማሕበረሰብ ለመፍጠር የእሚኼድበት አግባብ ምንድነው ነው የእሚለው ይሆናል ።
ለእዚኽ ጥያቄ ሌኒን የእሚሰጠው መልስ ፤ የመጀመሪያው ሥራ ከምኒስት ያልሆኑ መንግሥታትን ኹሉ በዓለም ዙሪያ ከምኒስት በሆኑ መንግሥታት መተካት ነው ።
ይኽ እንዲሆን ደግሞ ነባራዊውን (በከምኒዝም ቋንቋ የፊውዳል ወይንም የቡርዣ) መንግሥት በኃይል ማፍረስ የግድ ነው ። ስለ እዚኽ ፦ የከምኒስት አብዮተኛ ፤ ከምኒስት ያልሆነ ማንኛውንም መንግሥት ማፍረስ አብዮታዊ ግቡ ነው ። ይኽንንም ሌኒን እንደ እዚኽ ያስቀምጠዋል ፦
“… ኹኔታዎች አብዮቱን ‘የማውደሚያ ኃይሎቹን ኹሉ’ በመንግሥት ኃይል ላይ እንዲያስተባብር እና ራሱን መንግሥትን በማፍረስ እና በማጥፋት ዓላማ እንዲያስታጥቅ እንጂ መንግሥትን ለማሻሻል እንዲሰራ አይገፉትም ።”
“... events compels the revolution ‘to concentrate all its forces of destruction’ against the state power, and to set itself the aim, not of improving the state machine, but of smashing and destroying it. [29]“
አብዮተኛው በተለምዶ የእምናውቀውን ፤ የግለሰብ ነፃነት ፣ የህይወት ክቡርነት እና የዜጎችን ንብረት ጥበቃ የእሚያደርገውን ወይንም ከምኒስቶች የቡርዣውን መንግሥት ብለው የእሚጠሩትን መንግሥት ፤ በአብዮት ከአፈረሰ በኋላ ፤ የሶሻሊስት መንግሥት ያቋቁማል ።
ይኽ የሶሻሊስት መንግሥት ዋነኛ ግብም ፤ ጨቋኝ የነበረውን እና በአብዮት ከስልጣን የወረደውን መደብ እየጨቆነ መቆየት ነው ፦
“ወዛደሩ ወይንም ሠራተኛው ቡርዣውን እንዲ ረግጠው (የሠራተኛው ወይንም የወዛደሩ አምባገነንነት) ፤ መንግሥት … ‘ለየት ባለ የማስገደጃ ኃይል’ መተካት አለበት ። ‘መንግሥትን እንደ መንግሥት መደምሰስ’ ማለት ትክክለኛው ይኼ ነው ። የማምረቻ መንገዶችን/ተቋሞችን በማሕበረሰብ ስም የመውረስ ‘ተግባር’ ማለት በትክክል ይኽ ነው ። ይኽ ዓይነቱ አንድን (የቡርዥዋውን) ‘ልዩ ኃይል’ በሌላ (የላብ አደሩ ወይንም የሠራተኛው) ልዩ ኃይል መተካት ደግሞ ‘በራሱ ግዜ መክሰም’ በእሚለው አግባብ እንደ እማይሆን ከኹኔታው በግልፅ መረዳት ይቻላል ።”
“The state ... must be replaced by a ‘special coercive force’ for the supprssion of the bourgeoisie by the proletrait (the dictatorship of the proletrait). This is precisely what is meant by ‘abolution of yhe ztste as state’. This is prcisely the ‘act’ of taking possession of the means of production in the name of society. And it is self-evident that such a replacement of one (bourgeois) ‘special force’ by another (proletarian) ‘special force’ can not take place in the form of ‘weathering away’. [29]“
ሶሻሊስቱ መንግሥት በካሚኒስቶቹ የስነ መንግሥት ትንታኔ መሠረት ፤ ጨቋኙን እየጨቆነ በተጓዳኝ ፤ የቡርዥዋ ወይንም የፊውዳል መንግሥት መሠረት የሆነ የመደብ ልዩነትን ከአጠፋ በኋላ ፤ ይኽ የሶሻሊስት መንግሥት ራሱ አስፈላጊነቱ ስለ እሚያበቃ በራሱ ግዜ ይከስማል ፤ በማርክሲዝም መሠረት ፦
“ የቡርዣው መንግሥት ‘አይከስምም’ ነገር ግን በላብ አደሩ አብዮት ወቅት ‘ይደመሰሳል’ ። ከእዚኽ አብዮት በኋላ የእሚከስመው የላብ አደሩ መንግሥት ወይንም መንግሥት መሰል መንግሥት ነው ።”
“The bourgeois state does not ‘wither away’, but is ‘abolished’ by the proletariat in the course of the revolution. What weathers away after this revolution is the proletarian state or semi-state. [29]“
ሌኒን በእዚኽ ክፍል ላይ እየ አለ የአለው ፤ በማርክሲዝም ወይንም ከምኒዝም መሠረት መንግሥት የጭቆና መሳሪያ በመሆኑ መጥፋት የአለበት ተቋም ነው ። የጭቆና መሳሪያ የሆነው መንግሥት የእሚጠፋው ግን በኹለት ደረጃ ነው። በመጀመሪያው ደረጃ ፤ የሶሻሊስት ወይንም የሠራተኛ አብዮት ተካኺዶ ፤ የቡርዥዋው ወይንም የፊውዳሉ መንግሥት በኃይል ይደመሰሳል።
የቡርዥዋው ወይንም የፊውዳሉ መንግሥት በሠራተኛው አብዮት ከተደመሰሰ በኋላ ፤ በመጀመሪያ ደረጃ መንግሥት እንዲፈጠር ምክንያት የሆነው የመደብ ልዩነት የአልጠፋ በመሆኑ እና ከስልጣን የተወገደው የቡርዣው ወይንም የፊውዳሉ መንግሥቱ ተመልሶ ወደ ስልጣን እንደ አይመጣ ፤ የቡርዣውን ወይንም የፊውዳሉን መንግሥት በኃይል የአስወገደው የሶሻሊስቱ አብዮተኛ ፤ ይኽንን ከስልጣን የተወገደውን ኃይል እየጨቆነ እና በመጀመሪያ ደረጃም ለመንግሥት መምጣት ምክንያት የሆነውን ቁሳዊ ኹኔታ ፤ ማለትም ፦ የመደብ ልዩነትን ለማጥፋት እየሰራ ይቆይ እና የቡርዣው ወይንም የፊውዳሉ ኃይል ወደ ስልጣን ሊመጣ በእማይችልበት መልኩ ከተዳከመ እና የመደብ ልዩነት ከጠፋ በኋላ ፤ ይኸው ሶሻሊስታዊ መንግሥትም በራሱ ግዜ ይከስማል ነው።
ይኼ የቡርዥዋውን መንግሥትን ደምስሶ ፤ ማሕበራዊ የመደብ ልዩነቶች ከአጠፋ በኋላ በራሱ ግዜ የእሚከስመው ፤ የሶሻሊስት መንግሥት ወይንም የላብ አደሩ አምባገነንነት የእሚያነግሰው መንግሥት ፤ ሕግ አውጭ እና አስፈፃሚ በእሚል መከፋፈል ፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ፣ ወዘተ ፤ በእሚሉ ‘የቡርዣ’ ሰበካዎች ሳይታለል ፤ እርሱ ሕግ አውጪ ራሱ ሕግ አስፈፃሚ ሆኖ የተማከለ ወይንም በእማያፈናፍነው ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መመራት አለበት ፦
“ማሕበሩ (ግንባሩ ፣ የጭቁኑ ሕዝብ ሞግዚቱ ፣ ደርጉ ፣ ወዘተ) የሥራ እንጂ የፓርላማ ንትርክ አካል በአለ መሆኑ ፤ ሕግ አውጭም አስፈፃሚም ራሱ መሆን አለበት ።”
“The Commune was not to be a working, not a parliamentary, body, executive and legislative at the sametime. [29]“
የከምኒስት መንግሥት ፤ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ፣ ኃላፊነት ላይ የተመሠረቱ የስልጣን ክፍፍሎችን ብቻ ሰአይሆን የእማይቀበለው ፤ ከዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ውጭ ያሉ ፤ የፖለቲካ ስልጣንን በአከባቢ የእሚያከፋፍሉ ፤ ፌደራላዊ አደረጃጀቶችንም አይቀበልም ።
ሌኒን ፥ ስለ አብዮት እና መንግሥታት በእሚተነትንበት መጽሐፍ ውስጥ እንደ አስቀመጠው ፤ፌደራላዊ የመንግሥት አወቃቀር ፤ ቅዥት እና አብዮቱን መካድ ነው ብሎ የእሚያጣጥለው አካኼድ ነው ፦
“… ትናንሽ መንግሥታት እንዲኖሩ እና የጀርመን ክልሎች የራሳቸው ክልላዊ መንግሥት ኖሮዋቸው በፌደራላዊ ስርዓት ስር በማድረግ ፤‘የፍፁማዊነት ለምድ’ በመሆን ‘ለምርት የእሚያስፈልጉ ቁሶችን በሙሉ የጋራ ንብረት’ እናደርጋለን የእሚለው ምኞት ‘ግልፅ ቅዥት’ ነው ።”
“..., ‘the fig leaf of absolutism’ and that to wish ‘to transform all the instruments of labor into common property’ on the basis of a constitution which legalizes the existence of petty states and the federation of German states is an ‘obvious absurdity’ [29]“
ይኽንም የእሚልበት ምክንያት ፤ የሶሻሊዝም መንግሥት በፍፁም ማዕከላዊነት መመራት የአለበት መሆኑ በእነ ኤንግልስም የተቀመጠ ኃሳብ ስለ ሆነ ነው ይላል ፦
“ጉዳዩን ሠራተኛው እና ከሠራተኛው አብዮት አንፃር ፤ ኤንግልስም እንደ ማርክስ ፤ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን በመደገፍ ፤ ሕዝባዊቷ አንድ እና የእማትከፋፈል መሆን እንደ አለባት ነው የእሚያምነው ። ሕዛባዊ ፌደራሊዝም የእሚባለው ኃሳብ ወጣ ያለ ከአልሆነም ለእድገት ሰንካራ እንደሆነ ያስባል ።”
“Approaching the matter from the standpoint of the proletariat and the proletarian revolution, Engles, like Marx, upheld democratic centralism, the republic one and indivisible. He regarded the federal republic an exception or a hinderance to development. [29]“
ከእዚኽም የከምኒስት የመንግሥት ውጥን የተነሳ ፤ የራስን እድል በራስ የመወሰንን መብት የብሔራዊ ሉዓላዊነታቸው ማስከበሪያ መሳሪያ አድርገው የእሚያዩ የፖለቲካ ኃይላት ፤ የቡርዣ አስተሳሰብ የአላቸው ፥ በአገኙት አጋጣሚ ርካሽ ጥቅምን አሳዳጆች ናቸው ለከምኒስቶች ፦
“ቡርዣው ኹል ግዜ የሐገሩን/የብሔሩን ጥያቄ ኹል ግዜ በእሚባል ኹኔታ ግንባር ቀደም አድርጎ ያስቀምጣል ። ለላብ አደሩ ግን ይኽ ጥያቄ ለመደብ ትግሉ ጥቅም የእሚገዛ ነው ።”
“The bourgeoisie always places its national demands in the forefront, and does so in categorical fashion. With the proletariat, howeverm these demands are subordinated to the interests of the class struggle. [29]“
ሲጠቃለል ፦ ከምንስታዊ የመንግሥት አስተሳሰብ ፤ መንግሥት የመደብ ቅራኔ የእሚወልደው የጭቆና መሳሪያ ነው ፤ ስለ እዚኽ በፅንሰ ኃሳብ ደረጃ መንግሥት አያስፈልግም ። ሆኖም ፤ የመንግሥት መሠረት የሆኑት ፤ ማሕበራዊ የመደብ ቅራኔዎች ወይንም የመደብ ልዩነት ሳይጠፋ በፊት መንግሥት የእማይጠፉ በመሆኑ ፤ በግዚያዊነት መንግሥታት በሙሉ ፤ በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት በእሚገዛው ፤ ራሱ ሕግ አውጭ እና አስፈፃሚ በሆነው ፤ በምርጫ ሰአይሆን በአብዮት ስልጣን የእሚይዘው ፤ የሶሻሊስት መንግሥት መተካት አለበት ።
ይኽ ሶሻሊስታዊ መንግሥት ደግሞ የመደብ ቅራኔን በሙሉ ከአጠፋ በኋላ በራሱ ይከስም እና ዓለም ፤ መንግሥት የሌለባት ትሆናለች ፤ ምክንያቱም ፦ መንግሥትን አስፈላጊ የእሚያደርገው የመደብ ቅራኔ በሶሻሊስት መንግሥቱ ስለ ጠፋ ።
ስለ እዚኽ ፦ ይኽን ተከትሎ ፤ ዋናው ጥያቄ የእሚሆነው ፦ ይኽን መሰል የመንግሥት ፍልስፍና የአለው ከምኒዝም/ሶሻሊዝም ፤ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብትን እንዴት ነው የእሚያየው የእሚለው ይሆናል ።
ለእዚኽ ጥያቄ አንድ መልስ የለም ፤ ምክንያቱም ፦ ይኽ የራስን እድል በእራስን የመወሰን መብት ፤ ከእላይ እንደ አልነው ከመሠረታዊ የከምንስታዊ ግዜያዊ አምባገነናዊ መንግሥት አስፈላጊነት ግዴታ የተነሳ አንድ ወጥ አቋም በከምኒስቶች ዘንድ የሌለ በመሆኑ።
ከምኒስቶች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብትን ያለ ምንም ቅድመ ኹኔታ ከፈቀዱ ፤ ይኽ መብት የእሚሰጣቸው ምን ዓይነት ቅርጽ የአላቸው ማሕበረሰባት ናቸው ከእሚለው ጥያቄ አንስቶ ፤ የራስን እድል በራስ የመወሰን አካኼድ ከከምንስታዊው ግዜያዊው እና በዴሞክራሲያዊ መዓከላዊነት ከእሚመራው ፤ ጸረ ፌደራሊዝም ፣ ጸረ ፓርላማ እና ጸረ ምርጫ ከሆነው የመንግሥት አስተሳሰብ ጋር እንዴት ነው መታየት የአለበት የእሚለው ጥያቄ ፤ የከምንስቱን ጎራ በከፍተኛ ኹኔታ ድንብርብር ውስጥ የከተተ ነው የሆነው።
ይኽም በመሆኑ ፤ በተለይ ሌኒን ፤ መጀመሪያ ላይ ፤ መብቱን የወግ አጥባቂ መንግሥታት ላይ ፤ የመገንጥል ጥያቄ ማንሻ እና መንግሥትን ማፍረሻ ታክቲክ ሊሆን ይችላል በእሚል እንደ አብዮት ማስነሻ ስልት ሲያቀርበው ይታያል።
ሌኒን ፤ ‘የሶሻሊስት አብዮት እና የብሔራት የራስን እድል በራስ መወሰን’ (The Socialist Revolution and the Right of Nations to Self Determination” በእሚለው ጽሑፍ ላይ በእዚኽ መልኩ አስቀምጦታል ፦
“የሶሻሊስት አብዮት በትልቅ አድማ ፣ በጎዳና ላይ ሰልፍ ፣ በርኃብ አድማ ፣ በወታደር መክዳት ወይንም ከቀኝ ግዛት ለመውጣት በእሚደረግ አመፅ ብቻ ሰአይሆን በማንኛውም ዓይነት ፖለቲካዊ ቀውስ … አንድ የተጨቆነ ሕዝብ ለመገንጠል ሪፈረንደም አደርጋለኹ ብሎ በእሚያነሳውም ጥያቄ ሊፈነዳ ይችላል ።”
“The socialist revolution may breakout not only in consequence of a great strike, a street demonstration, a hunger riot, a mutiny in the forces, or a colonial rebellion, but also in consequence of any political crisis, ... like or in connection with a referendum on the secession of an oppressed nation, etc. [43]“
ለእዚኽም ነው ሌኒን ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን መብት ፤ እስከ መገንጠል የእሚለውን ሐረግ ካል አካተተ ፋይዳ የለውም የእሚለው ፤ ምክንያቱም ፦ እገነጠላለኹ የእሚለው ከሌለበት ወደ አብዮት ሊያመራ ስለ እማይችል ፦
“የብሔራት የራስን እድል በራስ መወሰን የእሚለው ፤ ፖለቲካዊ ፋይዳ የአለው ብቸኛ ትርጉም ነፃ (የመገንጠል) መብት ሲሆን ነው ፤ ከጨቋኙ ብሔር (ሐገር) ለመገንጠል ። በተጨባጭ ፤ ይኽ ዴሞክራሲያዊ እና ፖለቲካዊ ጥያቄ ፤ በሪፈረንደም ለመገንጠል የእሚፈልገው ብሔር(ሐገር) ለመገንጠል ፖለቲካዊ ቅስቀሳ እንዲያደርግ ነው ።”
“The right of nations to self-determination means only the right to independence in a political sense, the right to free, political secession from the oppressing nation. Concretely, this political, democratic demand implies complete freedom to carry on agitation in favor of secession, and freedom to settle the question of secession by means of a referendum of the nation that desires to secede. [43]“
የእኛ ሐገሩ ዋለልኝም ይኽኑን የሌኒን ኃሳብ ተከትሎ ነው ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአማራው እና ከትግሬው ውጭ የአለው የሕብረተሰብ ክፍል ጭቆና ስለ አለበት ፤ በእየ ነገዱ ስም የእሚነሱ የብሔር ጥያቄ[3] ወይንም የመገንጠልን ጥያቄዎችን ፤ ተማሪው ወይንም ተራማጁ ኃይል ፤ ሐገር ያፈርሳል ብሎ መፍራት የለበትም ፤ እንዲያውም የብሔር ወይንም የመገንጠል ጥያቄ የእሚያነሱት ሶሻሊስት እስከ ሆኑ ድረስ ፤ በትጥቅ ትግልም ኹሉ መታገዝ አለባቸው የአለው ።
ዋለልኝ ይኽንን ኃሳቡን “የብሔሮች ጥያቄ ላይ በኢትዮጵያ (On the Question of Nationalities in Ethiopia)” በእሚለው በእንግሊዘኛ በጻፈው ጽኹፉ ላይ እንደ እዚኽ አስቀምጦታል ፦
“የመገንጠል ጥያቄ ፤ በሠራተኛው እና በገበሬው እስከ ተመራ እና ዓለም ዓቀፋዊ ግዴታውን እስከ አመነበት ድረስ ፤ መደገፍ ብቻ ሰአይሆን ወታደራዊ እገዛም ሊደረግለት ይገባል ። … አብዮት የቱም ጋር ሊጀምር ይችላል ፤ እንዲያውም መጀመሪያ ላይ የመገንጠል ጥያቄም ሊሆን ይችላል … “
“As long as secession is led by the peasants and workers and believes in its international obligation, it is not only to be supported but also militarily assisted. ... The revolution can start anywhere. It can even be secessionist to begin with... [44]“
ይኽ በሌኒን የቀረበው እና ሌኒን ዋቢ በማድረግ በእኛም ሐገር የገባው ፤ የራስን እድል በራስ የመወሰን ገለጻ ፤ የቡርዣውን ወይንም የፊውዳሉን መንግሥት በሪፈረንደም እና በመገንጠል ጥያቄ አስጨንቆ ለማፍረስ እና የእዚያን ሕዝብ ፖለቲካዊ ተቋማት በአንድ ሶሻሊስታዊ ጥላ ስር ለማምጣት እንጂ ፤ ነገዶቹ ወይንም ተጨቆነ የእሚባለው የሕዝብ ንዑሳን ሐገር እና መንግሥት እንዲሆኑ ከመፈለግ አለመሆኑ ፤ ሐገርን የእሚጠላ ከምኒዝም ወይንም የእርሱ ተከታይ የሆነው ፥ ይኽን ሊል እንደ እማይችል የእምንረዳው ነው። ምክንያቱም ፦ የሶሻሊስት ግብ ከሐገር አንፃር በሌኒን በራሱ በእዚኹ ጽኹፉ ላይ ከታች በተቀመጠው መልኩ በግልፅ የተቀመጠ ስለ ኾነ ፦
“ የሶሻሊዝም ግቡ ፤ አሁን ሐገራት በትንንሽ መንግሥታት የተከፋፈሉበትን እና በሐገር ድንበር የተለያዩበትን ማጥፋት ብቻ ሰአይሆን ፣ በእዚኽ ሐገራትን ማቀራረብ ብቻ ሰአይሆን ፣ በአንድ ለማዋሀድም ነው ።”
“ The aim of socialism is not only to abolish the present division of mankind into small states and all national isolation; not only to bring the nations closer to each other, but also to merge them. [45]“
ይኽም በመሆኑ ፤ እንደ ሌኒን የአሉ አንዳንድ ከምኒስቶች የራስን እድል በራስ የመወሰን መርህን የእሚደግፉት ፤ በእርሱ ሰበብ የእሚነሳው የመገንጠል ጥያቄ የቡርዣውን እና የፊውዳሉን መንግሥትን የእሚጥለውን አብዮት ማስነሻ አጋጣሚ መሆን ስለ እሚችል ነው እንጂ ተጨቆኑ የእሚሉት ሕዝብ የራሱን እድል በራስ መወሰን በእሚል ሉዓላዊ ሐገር እንዲመሠርት አይደለም።
አንዳንድ ሰዎች ፤ የሌኒንን ኃሳብ የያዘው ዋለልኝ በሐገራችን የብሔር ጽንፈኞች የእሚወደስበትን የብሔሮች ጥያቄ በኢትዮጵያ የእሚለው ጽሑፍ የጻፈው ፤ ዋለለኝ ለጭቁን የሕዝብ ንዑሳን ከአለው ወገንተኝነት ነው የእሚለው ግንዛቤያቸው ስህተት የእሚሆነውም ፤ የዋለልኝ ጽሑፍ ዋነኛ ጭብጥ ፤ የሌኒን ኃሳብ ተከትሎ ፤ ይኽን ማሕበራዊ ቅራኔን መጠቀም እና በእዚኽም የብሔር ጥያቄ መሠረት በእሚነሳ የመገንጠል ጥያቄ ፤ የቡርዣ/ፊውዳል መንግሥቱን የእሚጥለውን አብዮት ማስነሻ መንገድ ሊሆን ይችላል ከእሚል እምነት የተጻፈ በመሆኑ ነው።
ይኽ እንግዲኽ ፤ ከምኒዝም ወይንም ሌኒን መሰል አንዳንድ ከምኒስት ኃይላት ፤ የምሥራቁ ዓለም ፖለቲካ አውራ ሆነው ፤ በምዕራቡ ዓለም የራስን እድል በራስ መወሰን ፤ ሕዝብ ወይንም ሐገራት ከቀኝ ግዛት ነጻ ወጥተው በራሳቸው ሉዓላዊ ሐገር ውስጥ በእሚመስላቸው መንገድ መንግሥት ሊመሠርቱ ይገባል የእሚለውን ፅንሰ ኃሳብ ፤ ለእራሳቸው አይዲዮሎጂ ወይንም ርዕዮት እንዲጠቅም በእሚችልበት መልኩ አስተካክሎ ያራመደበት አግባብ ነው ።
የከምኒዝም እንቅስቃሴም ፤ እንደ ማንኛውም እንቅስቃሴ በውስጡ የራሱ አንጃዎች የነበሩት በመሆኑ ፤ ከላይ ያስቀመጥነው በሌኒን ፊታውራሪነት የእሚመራው እና በውስጥ ትግሉ አሸንፎ የከምኒዝም መንግሥት ጅማሮ ላይ ስልጣን የያዘው አንጃ የእሚያራምደው ኃሳብ ነው ።
በእዚኽም አንጃ እምነት መሠረት ፤ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ፤ በመብትነቱ ሰአይሆን በስልትነት ፤ ሶሻሊስት መንግሥት በሌላቸው ሐገሮች ለእሚገኙ የሕዝብ ንዑሳን በሙሉ ተሰጥቶ እንደ አንድ ፤ አብዮት ማስነሻ አጀነዳ መሆን አለበት የእሚል ነው ።
በእዚኽ አንጃ እምነትም ፤ ይኽ መብት ፤ ሶሻሊስታዊ መንግሥት በሌላቸው ሐገራት ውስጥ ላሉ ለኹሉም አንጀኞች ወይንም ገንጣዮች ይሰጡና ፤ የመገንጠል ጥያቄ አብዮት ማቀጣጠያ ይሁን አካኼድ ግን ፤ እንደ ሮዛ ሉክሰምበርግ ላሉ ከምኒስቶች ስልታዊ ስህተት በመሆኑ ፤ የነገዶችን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል ማረጋገጥ የእሚለው ሐረግ ፤ በፓርቲ ፕሮግራም ላይ መስፈር የለበትም ብለው ተቃውመዋል ።
እንደ ሮዛ ኃሳብ እና የተለያዩ የማርክስን እና የኤንግልስን ጽህፎች እያጠቀሰች እንደ አሳየችውም ፤ ይኽንን መርኽ ለኹሉም የብሔር ወይንም የመገንጠል ጥያቄ ለእሚያነሳ ሕዝብ መስጠት አንዳንዶችን በነፃነት ስም ከስልጣኔ እንዲያፈገፍጉ በማድረግ ፤ ከፊውዳሊዝም ወደ ካፒታሊዝም ፤ ከካፖታሊዝም ወደ ሶሻሊዝም የእሚደረገውን የታሪክ ቁሳዊነት ኺደት ስለ እሚያስተጓጉል ፤ አንዳንዴ መደገፍ ሰአይሆን መቃወም አለብን ብላለች ።
በሌላ አገላለጽ ፤ ማንኛውም የጋራ ጠባይ ወይንም አንዳች ታሪካዊ ምክንያት አለኝ የእሚል የሕዝብ ንዑስ ፤ የመገንጠል ወይንም የብሔር ጥያቄ ፤ የፊውዳል እና የቡርዣ መንግሥት ለመጣል ይጠቅማል በእሚል በመደዳ እና ያለ ቅድመ ኹኔታ በመብትነት ሊሰጠው አይገባም ፤ ምክንያቱም፦ አንዳንድ ግዜ ኋላ ቀር የሆነ ሕዝብ ከእነርሱ በስልጣኔ በእሚሻል ፤ በቡርዣ ወይንም በፊውዳል መንግሥት ስር ቆይቶ ፤ ከኋላ ቀርነቱ መጀመሪያ መላቀቁ ፤ ለሶሻሊስታዊ አብዮት ቅድመ ኹኔታ የእሚሆንበት ግዜ ይኖራል ማለት ነው።
ሮዛ ፤ በመደዳ ልክ በኢሕአዴግ ሕገመንግሥት ላይ እንደተጠቀሰው ፤ ለኹሉም ነገዶች ወይንም የራስን እድል በራስ መወሰን መብትን ለብሔርነት ወይንም የመገንጠል ጥያቄ ማንሳት ለእሚፈልግ ለማንኛውም የሕዝብ ጎጥ ያለ ምንም ገደብ ማጎናፀፍ በመንቀፍ ከአቀረበችው ሰፊ ማብራሪያ ፤ የመጀመሪያው ፦ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት በመደዳ እና ያለ ገደብ ለኹሉም ማጎናፀፍ ፤ የመብቱ ዝርግነት እና ገደብ አልባነት ፤ በማማከል ከእሚታወቀው ማርክሲስታዊ ፍልስፍና በፍፁም ተቃራኒ ፤ ነገዳት ወይንም የትኛውም ዓይነቱ የሕዝብ ንዑሳን በሙሉ በመሰላችሁ መንገድ የውስጥም ሆነ የውጭ ችግራችሁን በራሳችኹ መንገድ መፍታት ትችላላቹ ማለት በእሚሆንበት ግዜ ፤ ይኽ መብት የተፈለገበትን የሶሻሊስታዊ አብዮት ግብ ችላ በማለት ወይንም በሶሻሊስታዊ እውቀት ያልተቃኙ የመገንጠል ጥያቄዎችንም ስለ እሚፈቅድ ፤ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ብላለች ፦
“ዝም ብሎ ወሰን የሌለው ስልጣን ለሕዝብ በመስጠት ፤ ፍላጎቱ የአላቸው ‘ሕዝብ’ ኹሉ ችግራቸውን በእሚመስላቸው መንገድ ፍቱ የእሚል ነው ።”
“ It offers instead only an unlimited authorization to all interested ‘nations’ to settle their national problems in anyway they like. [46]“
ይኽ አካኼድ ደግሞ ፤ ከሳሻሊስታዊ አብዮት አንፃር ጉዳትን የእሚያስከትል በመሆኑ ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን ለኹሉም ነገዶች ሰአይሆን ፤ እንደ አስፈላጊነቱ እየታየ መሰጠት የአለበት ነው በማለት ፤ ይኽ ኃሳቧ በማርክስም የእሚድገፍ መሆኑን ለማሳየት ፤ ካርል ማርክስ ዴይሊ ትሪቢውን (Daily Tribune) የእሚባለው የአሜሪካ ጋዜጣ ላይ ፤ ፖላንድ ነፃ ሐገር መሆን አለባት ወይንስ የለባትም በእሚለው ጉዳይ ፤ ከጀርመን እና ከራሻ አንፃር የገለፀበትን ሐተታ ታስቀምጣለች ።
በእዚኽ በጠቀሰችው ጽሑፍ ላይ ፤ ማርክስ ቀድሞ የፖላንድ መሬት የነበረ ፤ አኹን ገሚሱ በጀርመኖች እጅ እና ገሚሱ በራሻ እጅ የእሚገኝ መሬት አለ ፤ ስለ እዚኽ ፦ ፖላንድ ነፃ ሐገር ትሁን ከተባለ ፤ እነ እዚኽ ኹሉቱም መሬቶች መመለስ ሊኖርባቸው ነው ፤ ይኽ ግን አግባብ አይደለም ይላል ።
በሌላ አገላለፅ ፤ ማርክስ ፤ እያለ የአለው ፤ በጀርመን ከፖላንድ አንጻር ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን መደገፍ የአለበት ፤ በጀርመን ውስጥ የተካተተውን የፖላንድ ግዛት ነፃ ለማውጣት ሰአይሆን ፤ በራሺያ ውስጥ የተካተተውን የፖላንድ ግዛት ነፃ ለማውጣት ነው ።
ማርክስ ፤ ጀርመን ውስጥ የአለው ፖላንድ ነፃ አይውጣ ፤ ራሺያው ውስጥ የአለው ግን ነፃ ይውጣ የአለበትን ምክንያት ሲያስረዳ ደግሞ ፦ በጀርመን የተወሰደው የፖላንድ ግዛት ብዙ ጀርመኖች ሰፍረውበት እና አከባቢውም ለምቶ ተለውጧል ፤ ስለ እዚኽ ይኽንን አከባቢ በአግባቡ እንኳን ፊውዳል ስረዓት ለአላዳበረው የፖላንድ ማሕበረሰብ መመለስ አይገባም ። በራሺያ የተወሰደው ግን እንዲ መለስ ፤ የጀርመኖች አብዮተኞች የፖላንድ ነፃ አውጪን ማገዝ አለባቸው ፤ ምክንያቱም ፦ ተስፋፊዋ እና ኋላ ቀሯ ራሺያ ወደ አውሮፓ ዋናው መሬት እንደ አትገባ ለመከልከል ስለ እሚያግዝ ብሏል ።
ስለ እዚኽ ፦ ማርክስ ራሱ ፤ መርሁን እንደ መርህ ለኹሉም አከባቢ በአብዮት ስም በወጥነት ያለ ምንም ቅድም ኹኔታ የእሚተገበር ሰአይሆን ፤ እንደ ስልት የእሚመለከተው እና እንደ አስፈላጊነቱ የእሚተገበር መኾኑን አመላክቷል። ማርክስ ይኽን በእሚልበት ወቅት በጀርመን የሶሻሊስት መንግሥት አልነበረም። ሮዛ የጠቀሰችው የማርክስ ጽሑፍ ከእዚኽ በታች ተቀንጭቦ የተቀመጠው ነው ፦
“የተጨቆኑ ሕዝብ ኹሉ ነጻ ይኹኑ ፤ የራሳቸውን ጉዳይ በራሳቸው መንገድ ይወስኑ በእሚል ፤ ጥንታዊቷ ፖላንድ እ.አ.አ. ከ1772 ዓ.ም. በፊት ወደ ነበረችበት ኹኔታ ትመለስ ማለት ተገቢ ይሆን ነበር ። … ጀርመኖች ይኽንን የፖላንዶችን የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ከደገፍን ፤ ለእውነተኛነታችን ማሳያ ፥ እኛም ከፖላንድ የወሰድነውን መሬት እንድ እንመልስ እንገደዳለን ብለው ይሰጋሉ ። በሌላ በኩል ደግሞ ፤ በጀርመኖች የተያዘ ሰፊ መሬት እና ትልልቅ ከተሞች ፤ መሉ በሙሉ የጀርመን ነዋሪዎች ያሉበት ፤ ራሱን በጉልት ስረዓት ላይ ከተመሠረተ ፊውዳሊዝም ማላቀቅ ለአልቻለ ሕዝብ ተመልሰው ይሰጡ ? ጥያቄው ትንሽ ውስብስብ ነው ። … አብዮታዊ በሆኑ ሕዝብ መካከል የአለው የድንበር ጥያቄ ፤ የጋራ ድንበርን በጋራ ጠላት ላይ መፍጠርን ቀዳሚ በማድረግ ኹለተኛ ጉዳይ ነው መሆን የአለበት ። ... ተራማጁ ፓርቲ በጀርመን ፤ ተስፋፊዋ ሪሺያ ወደ አውሮፓ የእምታደርገውን ግስጋሴ ለመግታት ፤ ጦርነት አስፈላጊ ነው ብሎ በመቁጠር እናም ፖላንድ እንደ ሕዝብ እንደገና መዋቀሯ ይኽንን ጦርነት ለማቀጣጠል ይበጃል በእሚል ፖላንዶችን ያግዛል …“
“ calling forth at once the claim of all oppressed nations to an independent existence, and to the right to settle their own affairs for themselves, it was quite natural that the poles should demand the restoration of their country within the old Polish republic before 1972 ... but then, the Germans had proclaimed such an enthusiasm for the restoration of Poland, that they must expect to be asked, at the first proof of the reality of their sympathies, to give up their share of the plunder. On the other hand, should whole tracts of land, inhabited chiefly by Germans, should large towns, entirely German, be given up to a people that as yet had never given any proofs of its capability of progressing beyond a state of feudalism based upon agricultural serfdom? The question was intricate enough... The advanced party in Germany, deeming a war with Russia necessary to keep up the Continental movement, and considering the national reestablishment even part of Poland would inevitably lead to such a war, supported the Poles; [46]“
ስለ እዚኽ ፦ ሮዛም ልክ እንደ ሌኒን ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን የእሚለው መርህ ፤ የሶሻሊስት አብዮቱን ለማገዝ እንደ ስልት መጠቀሙ ተገቢ መሆኑን ብትስማማም ፤ እንደ እማይሻር መርህ ለኹሉም የብሔር ወይንም የመገንጠል ጥያቄ ለእሚያነሳ የሕዝብ ንዑስ (ነገድ ፣ ጎጥ ፣ ጎሳ ወይንም የአከባቢ ነዋሪ ) የእሚሰጥ መብት ሆኖ በፓርቲ ፕሮግራም ላይ መቀመጥ የለበትም ፤ ምክንያቱም ፦ በአጉል ቀቢፀ ተስፈኞች እየተያዘ የታሪክ ቁሳዊነት ኺደትን ከማስተጓገሉ በአሻገር ፥ የሕዝብን ችግር ለመፍታት የእሚኖረው ፋይዳ በጣም ጥቂት ነው በእሚል ተቃውማለች ፦
“ በእርግጥ ፤ እንደ ሶሻሊስቶች የኹሉንም ሕዝብ ነፃ የመሆን መብት እውቅና ብንሰጣቸው ፤ የሕዝብ እጣ ፈንታ አንድ ነጥብ እንኳን አይሻሻልም … ፋይዳው ልክ ፥ ኹሉም ሰው በወርቅ ሰሀን ላይ የመብላት መብት አለው ያኽል ነው ፤ …”
“Actually, even if as socialists we recognized the immediate right of all nations to independence, the fates of nations would not change an iota because of this…only worth as much as the right of each man to eat off gold plates, [46]“
መብቱን ያለ ቅድመ ኹኔታ ለኹሉም ሕዝብ ማጎናፀፍ ፤ አብዮቱን አይረዳም ብቻ ሰአይሆን ፤ እንደ ሮዛ ፤ ኹሉንም ሰዎች በወርቅ ሳህን ላይ የመብላት መብት አላችሁ ብሎ መደንገግ ከስላቅነት ያለፈ ኹሉም ሰው በወርቅ ሰሀን እንዲበላ ምንም የእሚያግዘው ወይንም የእሚፈይደው ነገር የአለመኖሩን ያኽል ፤ ኹሉንም ዓይነት ሕዝብ ያለ ምንም ቅድመ ኹኔታ የራሳችሁን እድል በራሳችሁ መወሰን ትችላላቹ ማለትም ፤ ለአብዛኛው የዓለም ሕዝብ ነጻ እና የበለጸጉ ሐገራት ባለቤት እንዲሆኑ ምንም የእሚፈይደው ነገር አይኖርም ፤ እንደ እዚኽ ዓይነቱ የቀቢጸ ተስፈኞች ፖሊሲም በሙግት ቁሳዊነት (Dialectical Materialism) ለእምናምነው ሶሻሊስቶች አይመጥንም ብላለች ።
ከማርክስ ኃሳብ ጋር መጋጨቱ በአደባባይ በሮዛ የተጋለጠበት ሌኒን ፤ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ፤ ከሶሻሊዝም አንፃር የመገንጠል ጥያቄ ለማንሳት ስለ እሚጠቅም ሶሻሊስታዊ መንግሥት ስር ለሌሉ ለኹሉም የብሔር ጥያቄ ማንሳት ለእሚፈልግ ሕዝብ ያለ ገደብ መሰጠት አለበት ሲል የነበረ እና የራስን እድል በራስ መወሰን መብት የመገንጠል መብትን ከአላጎናጸፈ ፋይዳቢስ ነው ሲል የነበረ ሌኒን ፤ በአደባባይ በመሳሳቱ የደረሰበትን ፖለቲካዊ ኪሳራ ለማረም ፤ እንዲያውም እኮ የመገንጠልን መብት ስናረጋግጥ ፤ ኹሉም እየተነሳ ልገንጠል ከማለት ይልቅ ፤ አብሮ ለመኖር ይነሳሳል የእሚል ትርጉም አልባ መከራከሪያ አቀረበ ፦
“በጠቅላላው ከዴሞክራሲያዊ አስተሳስብ አንፃር ፤ የእሚሆነው ተቃራኒው ነው ፤ ለመገንጠል መብት እውቅና መስጠት ፤ ‘የመንግሥትን ወይንም የሐገርን መፈራረስ’ ‘አደጋ’ ይቀንሳል ።“
“From the viewpoint of democracy in general, the very opposite is the case : recognition of the right to secession reduces the danger of the ‘disintegration of the state’. [45]“
እዚኽ ኃሳብ ላይ ሌኒን ፤ ይቀንሳል የእሚለውን ቃል ማንጋድዱ (Italicized) እና የመንግሥትን መፍረስ የእሚለውን ሐረግ በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ማድረጉ ፤ በአጋጣሚ ሰአይሆን ፤ እኔ እንደ ከምኒስት ፤ የመንግሥት መፍረስ እንዲቀንስ አልፈልግም ፤ ነገር ግን መብቱ ይኽን ይቀንሳል ፤ ስለ እዚኽ ፦ ሮዛ ትርጉም የለሹን የመገንጠል መብት ያለ ምንም ቅድመ ኹኔታ ለኹሉም ዓይነት ሕዝብ ሰጥተህ ሶሻሊስታዊ አብዮትን እንዲጋረድ በማድረግ ፤ ከማርክስ ጋር ተጋጭተኃል የእምትለኝ ፤ መሠረት የለሽ ትችት ነው ብሎ ለማጣጣል እየሞከረ ነው ።
ከላይ እንደ አስቀመጥነው ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን ፤ የመገንጠል መብትን ካል አካተተ እና በእገነጠላለው ስም አብዮት ካል አስነሳ ፋይዳ የለውም የእሚለው ሌኒን ፤ እዚኽ ጋር መብቱ የመገንጠል አደጋን ይቀንሳል ማለቱ ፤ መርኽን መሠረት የአደረገ ሰአይሆን ፤ የደረሰበትን ትችት ማስተባበያ መሆኑ ፤ እርስ በእርሱ የእሚጋጭ ኃሳብ በማንፀባረቁ ይታወቃል ።
ስለ እዚኽ ፦ ሌኒን በክርክር በአደባባይ ለአለመሸነፍ ሲል ይኽን እንዳለ ግልፅ ነው ።
የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት የመገንጠልን መብት ከአላካተተ እና ተጨቁኛለው የእሚለው ሕዝብ ይኽንን መብት ተጠቅሞ የመገንጠልን ወይንም የብሔርን ጥያቄ አንስቶ በሪፈረንደም ሰበብ አብዮት ከአላስነሳ ምንም ጥቅም የለውም የአለ ሊኒን ፤ ለማንኛውም የብሔር ወይንም የመገንጠል ጥያቄ ለእሚያነሳ ሕዝብ ያለ ቅድመ ኹኔታ ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል መብት አለኽ ብለን መብት ስንሰጠው ይኽ ሕዝብ የመገንጠል ፍላጎቱ ይቀንሳል አለ።
ይኽን መርህ መብት አድርጎ ያለ ገደብ መስጠት ፤ የብሔርን ወይንም የመገንጠልን ጥያቄ የአለ ቦታው ቦታ በመስጠት በመገንጠል ጥያቄ ምክንያት አንድ ማሕበረሰብን ያውካል ወይንም መብቱን መጎናጸፍ ሕዝብን ያረጋጋል ፤ ኹለቱንም ግን በአንድ ግዜ ሊሆን አይችልም ።
ይኽ ሮዛ ፤ ብኋላም እንደ እምናየው ጆሴፍ ስታሊን ያወገዘው የሌኒን አቋም ፥ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ለኹሉም ብሔራዊ ጥያቄ ለእሚያነሳ ሕዝብ ያለ ቅድመ ኹኔታ እስከ መገንጠል የእሚለው ሐረግ ተካቶበት ይሰጥ የእሚለው ብኺል ፤ በመላምትም ደረጃ ብቻ ሰአይሆን ፤ በዓለም ላይ እስከ ዛሬም የቀቢጸ ተስፈኞች ህልም በመሆን ለዓለም ስጋት እንደ ሆነ እየታየ ነው።
በአሜሪካ የሰላም ጥናት ተቋም ፤ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እና ከእርሱ ጋር ተያይዘው በመጡ የዓለም ሰላም መደፍረስ ጉዳዮች ላይ ፤ በተደረገ የፖሊሲ አጋዥ ጥናት ሪፖርት መሠረት ፤ ይኽ መብት ከቀኝ ግዛት ለመውጣት ሰአይሆን ለማንኛውም የብሔር ወይንም የመገንጠል ጥያቄ አራማጅ የእሚሰጥ መብት ነው ብለው የፖለቲካ ኃይላት ይዘውት ሲንቀሳቀሱ ፤ የዓለምን ሰላም እየረበሸ እንደሆነ በግልፅ አስቀምጠውታል ፦
“እስከ አኹንም ቢሆን ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን ለአከባቢ (ክልል ወይንም ስፍራ) የተሰጠ መብት እንጂ ለሕዝብ የተሰጠ መብት አይደለም ።
እ.አ.አ. ከ1970 ዓ.ም. ወዲህ ግን የአናሳዎች መብትን ከቀኝ ግዛት ነፃ መውጣት ከእሚለው ኃሳብ ጋር በማምታት ፤ ውጤቱ በአንዳንድ ተማጓቾች ዘንድ የራስን እድል በራስ መወሰን እያንዳንዱ ልዩ ነገድ ነፃ ሐገር መሆን ይችላል የእሚል አዝማሚያ ተስተውሏል ።
ብዙ የእዚኽ አዝማሚያ ታዛቢዎች ፤ የእሚጋሩት ጭንቀት የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት መርህ እና ይኽ መርህ በግልፅ የእሚሰጣቸው መብቶች መካከል የአለው ብዥታ ፤ በዓለም ላይ በነፃ አውጪዎች እየተቀጣጠለ የአለውን አመፅ እየረዳ መሆኑ ግልፅ ሆኖ እየወጣ መሆኑን ነው ። “
“ Still, self-determination applied to territories not to peoples.
Since the 1970s, there has been a move to combine the ideas of minority rights and decolonization, and the result has been a tendency on the part of some advocates to define self-determination as conferring the right to independent state on every distinctive ethnic group.
Many observers of this trend share the concern that confusion about what the principle of self-determination means and what putative rights ut confers is helping to fuel the violence characterizing contemporary independence movements. [42]“
የእዚኽ ጥናት ሪፖርት እንደ እሚለው ፤ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ፤ ማንኛውም የጋራ መለያ ጠባይ አለኝ የእሚል ሕዝብ እየተነሳ የብሔር ወይንም የመገንጠል ጥያቄ ሊያነሳበት ይችላል በእሚል ሲታይ ፤ በውስጡ የተለያዩ ንዑስ የጋራ መለያ ጠባይ የአላቸው ሕዝብ የሌሉበት ብሔራዊ ሐገር የሌለ በመሆኑ ፤ የተለያዩ አናሳ የሕዝብ ንዑሳን እንገንጠል እና የራሳችን ሐገር እንሁን በእሚል እንዲ ይንቀሳቀሱ በማድረግ ፤ መብቱ በእዚኽ አግባብ ሲተረጎም የሰላም ወይንም የአንድነት ምንጭ ከመሆን ይልቅ ለዓለም ሰላም መደፍረስ ምክንያት እየሆነ ነው ።
እንደ እዚኽ ጥናትም ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን የእሚለውን መብት በጠባብ ብሔርተኞች ወይንም ገንጣዮች ሲያዝ ፤ ራሺያ እና ቻይናን መሰል ትላልቅ የዓለማችንን ሐገራትም ብሔራዊ አንድነት የእሚፈታተን እንደ ኾነም ይላል ፦
“ለአመጽ እና ዓለም ዓቀፋዊ አለመረጋጋት ለማስከተል የአለው አቅምም (የራስን እድል በራስ መወሰን መርኽ) ፤ እስካኹንም በጣም ትልቅ ግዛት ለአላቸው እንደ ራሺያ እና ቻይና ለአሉ ሐገራት በእዚኽ ችግር ተጋላጭ መሆናቸው ሲታሰብ ግልጽ ይሆናል።”
“The potential for violence and international instability becomes even more obvious when one considers that some still very large empires, such as Russia and China, are likely to be affected by these movements. [42]“
ይኽም በመሆኑ የዘመነ ኢሕአዴግ ማርክሲስቶች ነን ባዮች ፤ ሌኒን ተከትለው ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል ለማንኛውም ብሔርተኛ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ውስጥ መስጠት ወይንም በኢትዮጵያ ሕገመንግሥት ውስጥ አንቀጽ 39ን ማኖር ፤ ተጨቆኑ የእሚባሉ የሕዝብ ንዑሳንን ጭቆና በማስቀረት ፤ የኢትዮጵያን ብሔራዊ አንድነት የአጠናክራል ብለው የእሚሉት ፤ ሌኒን ለክርክር ማሸነፊያ የአቀረበውን እና የማርክሲዝም ስረዓት አብዛኛው ፖለቲከኞች ማርክስ ፣ ሮዛ እና ስታሊንንም ጨምሮ የአወገዙትን ኃሳብ ተንተርሶ መሆኑ መታወቅ አለበት ።
ይኽ የኢሕአዴግ ጨለምተኞች የያዙት ከሌኒን የተቀዳ ኃሳብ ግን ፤ በራሱ በሌኒን የትግል አባቶች እና አጋሮች ፦ በማርክስ ፣ በሮዛ እና በስታሊን የተወገዘ ብቻም ሰአይሆን ፤ ይኽን መሰሉ አረዳድ ፤ ለዓለም ሕዝቦች መረጋጋት የችግር ምንጭ እንደ ሆነ ፤ ከእላይ በቀረበው ሪፖርት መሠረት ፤ የስጋት ምንጫ እንደ ሆነ የታየ ነው።
ለእዛኽም ይመስላል ፤ ይኽንን መብት ሌኒን አድራጊ ፈጣሪ በኾነበት ሦሥተኛው ከምኒስት ኢንተራናሽናል ፕሮግራም ላይ ፤ እስከ መገንጠል የእሚለው ሐረግ ሳይኖርበት የእምናገኘው ። ያም ብቻ ሰአይኾን ፤ የብሔሮች እስር ቤት ነች በተባለችው እና በውስጧ ብዙ ነገዳዊ እና ኃይማኖታዊ ልዩነት የአላቸው ሕዝብ በአቀፈችው በሶሻሊስት ራሺያ ሕገመንግሥት ላይ ደግሞ ፤ እስከ እነ ጭራሹ የራስን እድል በራስ መወሰን የእሚለው መብት የለም።
ይኽ ደግሞ ራሱ ሌኒን እያ፟ለ፟ በፀደቁት ሕገመንግሥታት ውስጥም ጭምር በመሆኑ እና ሕገመንግሥቱም በዲሞክራሲያዊ መዓከላዊነት በእሚመራው የራሺያ ከምኒስት ፓርቲ ውስጥ ሌኒን በድምፅ ብልጫ በእማይሸነፍበት ወቅት የፀደቀ በመኾኑ ፤ ሌኒን የራስን እድል በራስ መወሰን የእሚለው መርህ እርሱ በእሚለው መልኩ መተግበሩ የስልጣን መዓከሉ ለሆነችው ራሺያ የአለውን አደገኝነት እንደ ተረዳው ግልፅ ነው ።
የጸረ ቀኝ ግዛት እንቅስንቃሴ የወለወደ የሕዛባዊ ፖለቲካ አስተሳሰብ ፤ በዋናነት የዴሞክራሲያውኑን የራስ እድል በራስ የመወሰን መብትን ከቀኝ ግዛት የተላቀቁ ሉዓላዊ ሐገራትን ለመመሥረት በር ሲከፍት ፤ በከምኒዝሙ ጎራ ደግሞ ዓለም ዓቀፋዊውን የሠራተኛ አብዮት ትግል እና የራስን እድል በራስ የመወሰን አስተሳሰብ ከእላይ በገለጽነው መልክ የብሔር ጽንፈኝነትን አስከተለ።
የከምኒዝም የጸረ ሉዓላዊ ሐገራት ፍልስፍና በተራው ደግሞ ፤ በተለይ በጀርመን በአዶልፍ ሒትለር መሪነት ፤ በይዘቱ የከምኒዝሙ ጸረ ቡርዣ እና ጸረ ፊውዳል መንግሥት ከአስከተለው ጽንፈኛ ብሔርተኝነት በይዘቱ ለየት የአለ የብሔር ጽንፈኝነት አስከተለ።
ሒትለር በአንደኛው የዓለም ጦርነት ላይ በወታደርነት ጀርመንን ሲያገለግል ቆይቶ ፤ በደረሰበት የመርዝ ጋዝ ጥቃት ፤ ግዜያዊ የመታወር አደጋ አጋጥሞት በቁስለኝነት ተመልሶ እያለ ነው ፤ ጀርመን በጦርነቱ ተሸንፋ የአንደኛው የዓለም ጦርነት የአበቃው ።
ከደረሰበት ጉዳት እንደ አገገመ ፤ ሥራ አጥ ሆኖ በነበረበት ወቅት ፤ በጀርመን የነበረው የማርክሲዝም ክንፍ ሊመለምለው ጥረት እየአደረገ ስለ ነበር ከማርክሲዝም እንቅስቃሴ ጋር ትውውቅ የጀመረው አዶልፍ ሒትለር ፤ ከእዚያኽም በኋላ ፖለቲካዊ ተሳትፎ በራሱ መንገድ ሲጀምር ፤ ማርክሲዝምን አጥንቷል ።
በእነ እዚኽ አጋጣሚዎች ሐገር መጥፋት አለባት ከእሚለው ማርክሲዝም ጋር የተዋወቀው የጀርመን ጽንፈኛ ብሔርተኛ የሆነው ሒትለር ለማርክሲዝም ከፍተኛ ጥላቻ ነው የአለው ።
የትግል ህይወቴ ፤ በእሚለው መጽሐፉ ላይ ፤ ከከምኒዝም ጋር የነበረውን ገጠመኝ እንደ እዚኽ አስቀምጦታል ፦
“ከበቂ በላይ ሰምቻለኹ ። ብዙ ግዜ ፥ መወሰን እንድ እችል ፤ የእሚሉትን ነገር ሆን ብለው እኔ እንድ ሰማው አስበው ነው ብዬ ገምቻለሁ ። ነገር ግን የእምሰማው ነገር በሙሉ በውስጤ ከፍተኛ ጥላቻ የእሚያነሳሳ ነበር ። ኹሉ ነገር ይሰደባል - ሐገር ፥ ምክንያቱም ፦ ‘የካፒታሊስቱ’ መደብ ፈጠራ ነው በእሚል (ያንን ሐረግ ምን ያህል ግዜ መስማት እንደ ነበረብኝ !) ፣ እናት ሐገር ፥ ምክንያቱም ፦ ሰፊውን ሠራተኛ ሕዝብ ለመበዝበዝ በቡርዥዋ እጅ ስላለች ፣ የሕግ የበላይነት ፥ ምክንያቱም ላበአደሩን ጠፍንጎ መያዣ ስለሆነ ፣ ኃይማኖት ፥ ሕዝብን በማናወዝ ለብዝበዛ የእሚያዘጋጅ ስለሆነ ፣ ስነምግባር ፥ የድድብና ማህተም እና እንደ በግ መንጃ ስለሆነ ። ጭቃ ውስጥ የእማይጥሉት ነገር አልነበረም ።“
“ Yet I heard more than enough. And i often thought that some of what they said was meant for my ears, in the hope of bringing me to a decision.. but all that i heard had the effect of arousing the stringiest antagonism in me. Everything was disparaged – the nation, because it was held to be an invention of the ‘capitalist’ class (how often I had to listen to that phrase !) ; the Fatherland, because it was held to be an instrument in the hands of the bourgeoisie for the exploitation of the working masses; the authority of the law, because that was a means of holding down the proletariat; religion, as a means of doping the people, so as to exploit them afterwards; morality, as a badge of stupidty and sheepish docility. There was nothing that they did not drag in the mud. [40]“
ሒትለር ፤ ማርክሲዝምን በቅስቀሳ ደረጃም ብቻ ሰአይሆን በኋላ ላይ ፤ የማርክሲዝምን ጽሁፎችን ወስዶ በማጥናት ፤ በወቅቱ እየፈጠረ ከነበረው ፖለቲካዊ ድባብ ጋር በማዛመድ ፤ ግንዛቤዬን በማርክሲዝም ላይ በጥናት አሳድጌያለኹ ይላል ፦
“በኺደት በማርክሲዝም ቀኖና የተካንኹ ሆንሁ ፤ ይኽንንም እውቀቴን በፅኑ የእማምንበትን ነገር ለማስኼድ ተጠቀምኹበት ። በኹሉ ጉዳይ ማለት በእሚቻል መልኩ ስኬታማ ነበርኹ ። … ለኹለተኛ ግዜ ራሴን በእዚኽ አውዳሚ አስተምህሮ ውስጥ ጥልቅ አድርጌ ነከርኹ ። በእዚኽ ግዜ ግን እንደ በፊቱ የተገፋፋሁት ፤ የቀን ውሎዬ እና የግል አከባቢዬ በእሚያሳድርቡኝ ጥያቄዎች ሰአይሆን ፤ በጀርመን ፖለቲካዊ ህይወት ላይ በእማስተውላቸው ነገሮች ነው ። በእዚኽ አዲስ ዓለም መላምት ጽሁፎች ውስጥ እንደ ገና ራሴን በማጥለቅ ፤ የእዚኽ መላምት አስተምህሮ ሊያስከትል የእሚችለውን እንደምታ በጥራት ለመረዳት ፤ የማርክሲዝም መላምት መርህዎች ፤ በፖለቲካው ፣ በባህሉ እና በኢከነሚው መስክ እያመጣ የአላቸውን ክስተቶች እና ኹናቴዎች ለማጤን ሞከርኹ ።”
“Gradually I became an expert in the doctrine of the Marxists and used this knowledge as an instrument to drive home my own firm convictions. I was successful in nearly every case…. For the second time in my life, I plunged deep into the study of that destructive teaching. This time, however, I was not urged by the study of the question by the impressions and influences on my daily environment but directed rather by the observation of general phenomena in the political life of Germany. In delving again into the theoretical literature of this new world and endeavoring to get a clear view of the possible consequences of its teaching, I compared the theoretical principles of Marxism with the phenomena and happenings brought about by its activities in the political, cultural, and economic spheres. [40]“
በእዚኽም መሠረት ፤ ሒትለር በፓርቲው አሰራር እና የማርክሲዝም ጽሁፎችን በማጥናት የደረሰበት ድምዳሜ ፤ ኹሉንም ሐገር ማውድም ወይንም ማክሰም የማርክሲዝም ግብ እንደሆነ ነው ፦
“ … ማርክሲዝም፥ የመጨረሻ ግቡ የነበረው ፣ የሆነው እና ኹልግዜ የእሚሆነው ፤ … ኹሉንም ብሔራዊ ሐገራትን እና መንግሥታቸውን … ፈፅሞ ማጥፋት ነው ።”
“… Marxism, whose final objective was and is and will continue to be the destruction of all … national States. [40]“
በእዚኽ መልኩ ከማርክሲዝም ተዋውቆ ማርክሲዝምን በራሱ ልዩ መንገድ የገመገመው ሒትለር ፤ የማርክሲስቶችን ተግባራዊም ሆነ ቲየረቲካል መርህ በእነርሱ በራሳቸው ላይ መልሶ በመጠቀም ከጀርመን የፖለቲካ መድረክ ፈጽሞ አስወገዳቸው ።
ትንሽ ቀደም ብለን እንደ አልነው ፤ የማርክሲዝም ፍልስፍና ዋና ምርት ፤ ኢከነሚያዊ መሠረት የአለው የሰዎች የመደብ አስተሳሰብ እና ትግል ተፈጥሮዋዊ ሕግ በመሆኑ ፤ መደቦች እርስ በእርሳቸው ተጋጭተው ትልቁ እና ጉልበተኛው መደብ ትንሹን እና ደካማውን መደብ እያሸነፈ ፤ ታሪክ በግዜ ኺደት መደብ አልባ ማሕበረሰብ ይፈጥራል የእሚል ነው ። ስለ እዚኽ ፤ መደብ አልባው የመጨረሻው ጋርዮሽ ወይንም ከምኒዝም እስኪፈጠር ተቃራኒ መደቦች መኖራቸው እና አንዱ አንዱን መጨቆኑ የእማይቀር ነው የእሚል ነው ።
ሒትለር ይኽንን በማሻሻል ፤ ቡርዣ እና ላብአደር የእሚለውን ተፃራሪ መደባት የማርክሲዝም ክፍፍል ፤ ምርጥ እና ዝቅተኛ ዘር በእሚል ተክቶ ፤ በሰው ልጅ ዝርያዎች ውስጥ ያሉት ምርጥ ዘር እና ዝቅተኛ ዘር ናቸው ፤ ምርጡ ዘር ዝቅተኛውን ዘር እየጨቆነ መኖሩ የእማይቀር ተፈጥሮዋዊ ሕግ ነው የእሚል ኃሳብ ለማምጣት ሞከረ ፦
“ስለ እዚኽ ፦ በእኛ ርዕዮት መርህ መሠረት ኹሉም ዘሮች እኩል ናቸው የእሚባለውን አንቀበለም ። ይልቁንም ርዕዮታችን ፤ ዘሮች ልዩ መሆናቸውን በመረዳት ፤ የሰው ልጆችን የበላይ እና የበታች ዘሮች ብሎ ይከፋፍላቸዋል ።”
“Therefore on the volkisch principle we cannot admit that one race is equal to another. By recognizing that they are different, the volkisch concept separates mankind into races of superior and inferior quality. [40]“
ስለ እዚኽ ፦ ስልጣኔ የበላይ ዘሮቹ ስለ ሆነ ፤ ስልጣኔ እንዲ ቀጥል ፤ የበላይ ዘሮቹ ዝቅተኞቹን እየገዙ መቆየት እና ራሳቸውን ከዝቅተኛው ዘር ጋር ማቀላቀል የለባቸውም ። ሒትለርም ይኽን ኃሳቡን በመጽሐፉ አንድ ክፍል ላይ እንደ እዚኽ ያብራራዋል ፦
“አርያን ነገዶች ፥ ብዙ ግዜ በእሚያስገርም ኹኔታ ትንሽ ሆነው ፤ ሌሎች ሕዝብን በማስገበር እና አዲሱ ሐገራቸው በእሚሰጣቸው አመቺ ኹኔታ (የመሬቱ ለምነት ፣ የአየር ጠባዩ ፣ ወዘተ) እንዲሁም ዝቅተኛው ዘር በእሚያቀርብላቸው ጉልበት ፤ በውስጣቸው ተሰውሮ የነበረውን የማደራጀት እና የእውቀት አቅም አሳድገዋል ። በጥቂት ሺ ዓመታት ውስጥም ፣ አንዳንዴም በመቶ ዓመታት ፤ መሠረታዊ ባሕሪው ከእነርሱ ባሕሪ ጋር የእሚመሳሰል ባህል አዳብረዋል ፤ ምንም እንኳን አዳንድ ግዜ ከእሚኖሩበት መሬት እና ከአስገበሩት ሕዝብ ጋር የማጣጣም ነገር ቢኖርም ። በስተመጨረሻ ግን ፤ አሸናፊው ዘር ፥ የመጀመሪያ መርኃቸውን መጣል ጀመሩ ፤ ይኽም ዘራቸው ከሌላ ዘር ጋር እንዳይቀላቀል ይጠብቁ የነበሩትን ተውት እና ከአስገበሩት ሕዝብ ጋር መዋሀድ ጀመሩ ። ከእዛኽ በኋላ ህልውናቸው እየከሰመ መጣ ። በኤደን ገነት የተፈፀመው የመጀመሪያው ሀጢያት ደግሞ ኹል ግዜ መባረርን ያስከትላል ።”
“ Aryan tribes, often almost ridiculously small in number, subjguated foreign peoples and, stimulated by the conditions of life which their new country offered them (fertility, the nature of the climate, etc.), And profiting also by the abundance of manual labor furnished them by the inferior race, they developed intellectual and organizing faculties which had hitherto been dormant in these conquering tribes. With the course of a few thousand years, or even centuries they give life to cultures whose primitive traits completely correspond to the character of the founders, though modified by adaptation to peculiarities of the soil and the characteristics of the subjugated people. But finally, the conquering race offended the principles which they first had observed, namely, the maintenance of their racial stock unmixed, and they began to intermingle with subjugated people. They put an end to their own separate existence; for the original sin committed in Paradise has always been followed by the expulsion of the guilty party. [40]“
ማርክሲስቶች የመደብ ትግል የእማይሻር የተፈጥሮ ሕግ ነው እንደ እሚሉት ፤ ሒትለር ብረት የሆነው የተፈጥሮ ወይንም በሰዎች ላይ በተፈጥሮ አስገዳጅነት የተቀመጠ ሕግ የእሚለው ፤ የበላዩን ዘር ከዝቅተኛው ዘር ጋር ያለ መቀላቀልን ሕግ ነው ፦
“ … አንድ ሰው ይኽን ብረት የሆነው የተፈጥሮ ሕግ ሊለው ይችላል - በራሳቸው ቅርፅ ተወስነው ብቻ እንዲራቡ የተለያዩ ዝርያዎችን የእሚያስገድደውን ይኽን ሕግ …”
“ ... one may call it an iron law of Nature – which compels the various species to keep within the definite limits of their own life-forms... [40]“
ይኽ የዘርን ንፅህና መጠበቅ ደግሞ ተፈጥሮ ራሷ ያስቀመጠችው ሕግ በመሆኑ ፤ በሰብዓዊነት ወይንም በሌላ ምክንያት ችላ የእሚለው ፤ የእማይሻረውን የተፈጥሮ ሕግ ችላ ስለ አለ ፤ የስልጣኔን መርህ እምቢ ስለ አለ ፤ ኋላ ቀር እና ደካማ ይሆናል በሒትለር ርዕዮት መሠረት ፦
“ የዘርን ሕግ የእሚንቅ ወይንም ችላ የእሚል ማንኛውም ሰው ፤ ሊያገኘው የእሚመኘውን ደስታ ከማግኘት ራሱን ይከለክላል ። ምክንያቱም በየበላይ ዘር የድል መንገድ ላይ ደንቃራ በማስቀመጥ ፤ ለሰው ልጅ ኹለንተናዊ እድገት ቅድመ ኹኔታ ውስጥ ያልተገባ ጣልቃገብ በመሆን ፤በሰብዓዊ ስሜት ራሱን ጭኖ ፤ ራሳቸውን መሆን ወደ እሚገባቸው ደረጃ ገፍተው ማምጣት እንደ እማይችሉ እና እንደ እሚወድቁት ሰዎች በመሆን ።“
“Whoever ignores or despises the laws of race really deprives himself if the happiness to which he believes he can attain. For he places an obstacle in the victorious path of the superior race, and, by so doing, he interferes with a prerequisite condition of all human progress. Loaded with the burden of humaniterian sentiment, he falls back to the level of those who are unable to raise themselves in the scale of being. [40]“
ምክንያቱም ፦ በሒትለር ‘ትንታኔ’ ፤ የዘር መደባለቅ ነው የስልጣኔን ውድቀት የእሚያመጣው ፦
“ ከእዚኽ ቀደም የነበሩ ታላላቅ ስልጣኔዎች ኹሉ ጃጅተው የፈረሱት ፤ የስልጣኔዎች መሠረት የነበረው የመጀመሪያው ሕዝብ ፤ ከሌሎች ጋር ደሙ እየተቀላቀለ እየጠፋ ስለ ኼደ ነው ።”
“All great civilizationns of the past became decadent because the originally creative race died out, as a result if contaminatiin of blood. [40]“
ከእዚኽ መሰል ትንታኔው በመነሳት ፤ ሒትለር ፥ ሐገር ማለት እና የሐገር ግብ ፤ የአንድ ዘር መኖሪያን እና የዘር ንፅህናን ማስጠበቅ ነው ። ስለ እዚኽ በአንድ ሐገር መኖር የአለበት አንድ ዘር ነው ፤ የእሚል ዓይነት ድምዳሜ ላይ ይደርሳል ፦
“አኹን ዓለም የሐገርን/መንግሥትን ውጥን የእሚረዳበት አግባብ ፤ ምንም እንኳን ስልጣኔን ለመገንባት የእሚያስፈልጉት የፈጠራ ክህሎቶችን ታሳቢ ቢያደርግም ፤ ዘር የሐገር መሠረት ነው ከእሚለው አስተሳሰብ ጋር ምንም የጋራ ነገር የለውም ። ሐገርን የእሚያያት የሕዝብ ኢከነሚያዊ ፍላጎት እንደ እሚያስከትላት ወይንም ቢበዛ የፖለቲካ ኃይሎች እና ፍላጎቶች ፍትጊያ ውጤት እንደ ሆነች ነው ። … እነ እዚኽ ኹሉ አስተያየቶች ይኽ የጋራ ገፅታ እና ድካም አለባቸው ፡ እርሱም ፦ ባሕላዊ እሴቶችን የመፍጠር አቅም በዋናነት በዘር ላይ ነው የእሚመሠረተው ፥ በእዚኽም መሠረት ፥ ለሰው ልጅ ስልጣኔ መተኪያ የሌለው ቅድመ ኹኔታ በመሆኑ ፤ የመንግሥት ወይንም የሐገር ሚና ዘርን ጥራት መጠበቅ እና ማሻሻል ነው የእሚለውን ጉልህ እውነት ያለ መቀበል ነው ።”
“The current political conception of the world is that the State, though it possesses a creative force which can build up civilizations, has nothing incommon with the concept of race as the foundation of the State. … that they are not grounded in a recognition of the profound truth that the capacity for creating cultural values is essentially based on the racial element and that, in accordance with this fact, the paramount purpose of the State is to preserve and improve the race; for this is an indispensable condition of all progress in human civilization. [40]“
ሒትለር ፥ ሐገር የዘር ጥራት ማስጠበቂያ እና ማሻሻያ መሳሪያ ነች ከአለ በኋላ ፤ ከእላይ ማርክሲዝምን አጥንቼ ፤ የማርክሲዝምን ስልት የራሴን ዓላማ ለማራመድ ተጠቀምኩበት እንዳለው ፦
“በኺደት በማርክሲዝም ቀኖና የተካንኹ ሆንኩ ፤ ይኽንንም እውቀቴን በፅኑ የእማምንበትን ነገር ለማስኬድ ተጠቀምኩበት ። በኹሉ ጉዳይ ማለት በእሚቻል መልኩ ስኬታማ ነበርኹ ።“
“Gradually I became an expert in the doctrine of the Marxists and used this knowledge as an instrument to drive home my own firm convictions. I was successful in nearly every case. [40]“
ማርክሲዝም የግል ንብረቴ ወይንም የእኔ የእሚባለው አስተሳሰብ ፤ የቡርዥዋ አዕምሮ ውጤት በመኾኑ ሶሻሊስቱ የእኔ የእሚለው የለውም የእሚለውን ኃሳብ ፤ ሒትለር ምርጡ ዘር ፤ ለግሉ ብሎ የእሚሰራው ነገር የለም ፤ የእሚያድርገውን ኹሉ ለዘሩ ጥራት ጥበቃ እና ማሻሻል በማሰብ ነው በእሚለው ተካው ። ለግል ጥቅም መሥራት እንዲያውም ዘረፋ ነው አለ ፦
“ የግል ሥራን ፤ ነፍስንም ቢሆን ለሌሎች ለመሰዋት ያለ ዝግጁነት በአርያን ዘር ውስጥ በከፍተኛው የእድገት ደረጃ ላይ ይገኛል ። የአርያን ዘር ታላቅነት በአዕምሮ ልቀት ላይ የተመሠረተ አይደለም ፤ ይልቁንም የግሉን አገልግሎት ለማሕበረሰቡ ለመሰዋት በአለው ፈቃደኝነት ላይ ነው ። በአርያን ዘር ዘሩን የማስቀጠል ዝንባሌ ትልቅ ልህቀት ላይ ደርሷል ፤ ምክንያቱም ፦ አርያኑ የግል ምኞቱን ለጋራ ምኞት ለማስገዛት ኹኔታው ሲጠይቅም ለማሕበረሰቡ ነፍስንም ለመሰዋት ዝግጁ ነው ። የአርያኑ ገንቢ አቅሙ እና ባህልን ለመገንባት የአለው ልዩ ኃይል በአዕምሮ ልህቀቱ ላይ ብቻ የተመሠረተ አይደለም ። … ለምሳሌ ፦ ለራሱ አይሰራም ፤ ነገር ግን ሥራውን የእሚገኝበት ቡድን እንቅስቃሴ አካል ያደርገዋል ፤ ለራሱ ጥቅም ብቻ ሰአይሆን ነገር ግን ለኹሉም ጥቅምም ። የእዚኽ አመለካከቱ መንፈስ በአንድ ቃል ይገለፃል ፡ ሥራ ፦ ሥራ ለእርሱ የእለት ጉርሱን ማግኛ መንገድ ሰአይሆን ነገር ግን የማምረት እንቅስቃሴው አካል የሆነ እና ከማሕበረሰቡ ፍላጎት ጋር ሊጋጭ የእማይችል ነው ። … የሰው ልጅ እንቅስቃሴ ራስን ለማቆየት በእሚል ሲደረግ ስርቆት ፣ አራጣ ማበደር ፣ ቅሚያ ፣ ዘረፋ ፣ ወዘተ ፤ ይባላል ።»
“The readiness to sacrifice one;s personal work and, if necessary, even one’s life for others shows its most highly developed form in the Aryan race. The greatness of the Aryan is not based on his intellectual powers, but rather on his willingness to devote all his faculties to the service of the community. Here the instinct for self-preservation has reached its noblest form; for the Aryan willingly subordinates his own ego to the common weal and when necessity calls he will even sacrifice his own life to the community. The constructive powers of the Aryan and that peculiar ability he has for the building up of a culture are not grounded in his intellectual gifts alone. …. For example, he dies not work directly for himself but makes his productive work a part of the activity of the group to which he belongs, not only for his own benefit but for the general. The spirit underlying this attitude is expressed by the word: WORK, which to him does not at all signify a means of earning one’s daily livelihood buy rather a productive activity which cannot clash with the interests of the community… whenever human activity is directed exclusively to the service of the instinct of self-preservation it is called theft or usury, robbery or burglary, etc. [40]“
ማርክሲዝም የቡርዣውን የንብረት እና የሥራ አስተሳሰብ ከላብ አደሩ ወይንም ሠራተኛው የግል ንበረት እና የሥራ አስተሳሰብ በእሚያነፃፅርበት አግባብ ፤ ሒትለር የአርያን ታላቁ ዘር ስለ ሥራ እና የግል ንብረት የአለው አመለካከት ከሌላው ዘር ጋር በማነፃፀር ፤ አርያኖች የእኔ የእሚሉት ነገር የላቸውም ፣ ራሳቸውን ለዘራቸው ለመሰዋት ዝግጁ ናቸው ፣ ሥራቸውን ለመኖር ሰአይሆን ለዘሩ ጥንካሬ ነው የእሚሰሩት ፣ ወዘተ ፤ በማለት ፤ ከእዚኽም የተነሳ ፤ ከሌላው ዘር የበለጠ የላቁ ናቸው የእሚል አፈታሪክ ይዞ መጣ።
ይኽንን ሒትለር ከማርክሲዝም የቀዳውን እና በአርያኖች ሕዝብ የሥራ ባሕል አንጻር በአስቀመጠው የሰራተኝነት ኃስብ ታኮ ነው የሒትለሩ ፓርቲ ፤ በጀርመንኛ ብሔራዊ (National) እና ሶሻሊዝም በልማድ ሶዚ (Sozi) ፤ ከእሚሉት ቃላቶች ተወጣቶ ናዚ (Nazi) በእሚል እየተጠራ ፤ ብሔራዊ ሶሻሊዝም የደቾች (የጀርመኖች) የሰራተኞች ፓርቲ ተብሎ የተሰየመው።
ከእዛያኽም ፦ ልክ ከምኒስት ወይንም የጋርዮሽ ስረዓት አቀንቃኝ ነኝ የአለው ሌኒን ፤ በስልጣን ጉዳይ ጋርዮሽ የለም እንደ አለው ፦
“ማህበሩ (ግንባሩ ፣ ደርጉ ፣ የጭቁኑ ሕዝብ ሞግዚቱ ፣ ወዘተ) የሥራ እንጂ የፓርላማ ንትርክ አካል በአለመሆኑ ፤ ሕግ አውጭም አስፈፃሚም ራሱ መሆን አለበት ።”
“The Commune was not to be a working, not a parliamentary, body, executive and legislative at the sametime. [29]“
የአርያን ዘር ትልቅነቱ ፤ ከአዕምሮው ልቀት ሰአይሆን ፤ ከትብብር መንፈሱ ራሱን ለሌሎች ሲል ለመሰዋት ከአለው ዝግጁነት ነው ሲለን የነበረው ሒትለር ፦
“የሰው ልጅ እድገት እና የሰው ልጅ ባህል በብዙዎች ላይ የተመሠረተ አይደለም ። በእማያሻማ መልኩ የግለሰብ የዓዕምሮ ምጥቀት እና የግለሰብ ብቃት የሥራ ውጤቶች ናቸው ። በእዚኽ መርህ ምክንያት ፦ የእኛ እንቅስቃሴ የግድ ፀረ-ፓርላማ መሆን አለበት ፤ ፓርላማ ውስጥም በአጋጣሚ ከተሳተፈ ይኽንን ተቋም ከውስጥ ለማፍረስ መሆን አለበት ፤ በሌላ አገላለፅ ፤ የሰው ልጅ የመዝቀጥ ምልክት የሆነውን ማንኛውም ተቋም ወዲያ ማለት አለብን ።”
“Human progress and human cultures are not founded by the multitude. They are exclusively the work of personal genius and personal eficiency. Because of this principle, our movement must necessarily be anti-parlamentarian, and if it takes part in the parliamentary institutions it is only for the purpose of destroying this institution from within; in otjer words, we wish to do away with an institutiin which we must look upon as one of the gravest symptoms of human decline. [40]“
በማለት ፤ የብሔር ጽንፈኝነት ሒትለር ጋር ሲደርስ ፤ ሐገር ማለት የአንድ ዘር መኖሪያ እና የእዚኽ ዘር ጥራት እና እድገት ማስጠበቂያ መሳሪያ የሆነች እና እንደ እርሱ በአለ ድንቅ መሪ ብቻ መመራት የአለባት ነች ብሎ ባየነው መልክ ካስቀመጠ በኋላ ፦
“በጀርመን ሐገር የ ጀርመን መንግሥት!”
“A GERMAN STATE IN A GERMAN NATION! [40]“
ብሎ ፤ ይኽ እንደ ብረት የፀና የተፈጥሮ ሕግ የገባኝ እኔ ብቻ ስለ ሆንሁ ፤ እንደ ፓርላማ ያሉ የወሬ ተቋሞችን ወዲያ ብለን ፤ እኔ ብቻ ሕግ አውጭም ሆነ አስፈፃሚ የሆንኹበት ኹኔታ መፈጠር አለበት ብሎ ደምድሟል ።
የጸረ ቀኝ ግዛት ትግል በዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የራስን እድል በራስ መወሰን በእሚል መርኽ ሐገር ወይንም ሕዝብ ከቀኝ ግዛት ነጻ ወጥቶ የራሱን ነጻ እና ሉዓላዊ መንግሥት እንዲያቋቁም በእሚል ተጀምሮ ፤ በኋላ ላይ ቀኝ ግዛት ራሱ የቡርዣው የማሕበረ ኢከነሚ ውላጅ ነው በአለው ማርክሲዝም ፤ ነጻ እና ሉዓላዊ መንግሥት (ሐገር) ራሱ የቡርዣው ማሕበረ ኢከነሚ ስሪት ነው በእሚል ጸረ ሐገር የሆነው ማርክሲዝም በጸረ ቡርዣ ስም ጽነፈኛ ብሔርተኝነትን ወደ እሚያስፋፋበት ኹኔታ መጣ።
የማርክሲዝም ጸረ ሐገርነት ደግሞ በዓይነቱ ለየት የአለውን እና በዋናነት በሒትለር የተቀነቀነውን ዘረኝነት በማስከተል ፤ ጽንፈኛ ብሔርተኝነቱን አንድ ደረጃ በመውሰድ ፤ ኹሉም የሰው ዘር እኩል በአለመሆናቸው ፤ በምርጥ ዘሮቹ ሐገር ፤ ሌላ ዘር የአለው ሰው በእኩልነት መኖር የለበትም የእሚል ሆኖ አዲስ መልክ ያዘ። ይኽም በግዜ ኺደት ብሔራዊ ስሜትን ወደ ጽንፈኛ ብሔርተኝነት በመቀየር ሐገራት ከማንነት ወይንም ከዘር ጋር በማያያዝ ፤ ሐገርነት ወይንም ብሔርነት በዋናነት ከዘር ወይንም ከማንንነት ጋር ወደ እሚያያዝበት ጽንፈኝነት ዘቀጠ።
ዴሞክራሲያውኑ ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን የእሚለውን መርህ ፤ በዋናነት የቀኝ ግዛትን ለማስቀረት እና ሐገራት (የአንድ ዓይነት የሕዝብ ንዑሳን (ነገድ ፣ ጎጥ ፣ ወዘተ ) መኖሪያ የሆኑትን ሰአይሆን የተለያዩ ዓይነት የሕዝብ ንዑሳንን በውስጧቸው ይዘው ወይንም ሊይዙ ችለው ነገር ግን በአንድ ሕዝባዊ መንግሥት ስር መኾን የእሚችሉትን) ሉዓላዊነታቸው ከሌላ መሰል ሐገር ጣልቃ ገብነት ሕጋዊ ጥበቃ እንዲኖረው ታሳቢ በእሚያደርግ አግባብ የእሚረዱት እና ለማስከበር የእሚወዱት ነው ።
ለማርክሲስቶች ፤ ሐገር በግል ንብረት ፣ በግለሰብ ነፃነት እና ደህንነት ዋስትና ላይ የተመሠረተው የካፒታሊስት የፖለቲካል ኢከነሚ ስረዓት ውጤት በመኾና ወይንም የቡርዣ ስሪት በመኾኗ ፤ ሐገር እና መንግሥት መጥፋት የአለባቸው በመኾናቸው ፤ የዓለም ሐገራት እና መንግሥታት በሶሻሊስት አብዮት ከስመው ፤ ዓለም በላብ አደሮች ወይንም በሰራተኞች ወንድማማችነት ያለ ሐገር ድንበር እና ያለ ተለያዩ መንግሥታት አደረጃጀት ፤ በአንድ ከምንስታዊ ዓለም ዓቀፍ አስተዳደር ፤ በሶሻሊዝም ስር ከቆዩ በኋላ ወደ መጨረሻው ፤ መንግሥት አልባ ፣ ሐገር አልባ ፣ መደብ አልባ ኃይማኖት አልባ ፍፁም እኩልነት እና ጓዳዊ ትስስር ወይንም ጋርዮሽ ትሻገራለች ብለው ስለ እሚያምኑ እና ይኽም የእሚሳካው በአብዮት ነው ስለ እሚሉ ፤ የራስን እድል በራስ መወሰን ፤ በመርኽ ደረጃ ከማርክሲዝም የመንግሥት እና የሐገር አስተሳሰብ ጋር ቀጥታ የእሚጋጭ ስለሆነ ሊቀበሉት የእሚፈልጉት ነገር አይደለም።
ሆኖም ይኽን አለመቀበል ከፍተኛ ፖለቲካዊ ኪሳራ ስለ እሚያደርስባቸው ፤ ማርክስን ጨምሮ እነ ሮዛ ሉክሰምበርግ እና ስታሊን ራሱ ፤ መብቱን ዴሞክራሲያዊያኑ በእሚቀበሉበት አግባብ ነው የእሚቀበሉት ፤ ከማርክሲስታዊ የመንገሥት እና የሐገር ፍልስፍና አፈንግጠው።
ሌኒን ግን በጉዳዩ ላይ በአለው የግንዛቤ እጥረት ምክንያት የተምታታ አቋም ከመያዙ በላይ ፤ ከእላይ በአጣቀስነው መልኩ ፤ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት የመገንጠልን መብት ከአላካተተ ፋይዳ የለውም በማለቱ ፤ እንደ እኛ ሐገሮቹ አንዳንድ አብዮተኞች ፥ ግማሽ ብስል ማርክሲስቶች ፤ በተቀሩት ማርክሲስቶች ተተችቶ የተተውን የሌኒን ኃሳብ ፤ ሌኒን ስላለው ብቻ እንደ ማርክሲስታዊ አቋም በመውሰድ ፤ የብሔር ጥያቄ ለእሚያነሳ ለማንኛውም ንዑሳን ሕዝብ (ነገድ ፣ ጎሳ ፣ ወዘተ) የራስን እድል በእራስ መወሰን እስከ መገንጠል ያለ ምንም ቅድመ ኹኔታ ለኹሉም የብሔር ጥያቄ አንሺ ሕዝብ መሰጠት አለበት የእሚል አቋም በመያዛቸው ፤ ይኽ የመብቱ አረዳድ ፤ የተወሰኑ ማርክሲስታዊያን ነን የእሚሉ ግራ ዘመሞችን ፤ በማርክሲዝም ስም ፤ ከማርክስ ከእራሱ በተጻራሪ ፤ የብሔር ወይንም የመገንጠል ጥያቄ አራማጅ ጽንፈኛ አደረጋቸው።
ሒትለር ደግሞ ይኽ የማርክሲዝም ጸረ ሐገር አካኼድ ከዓለም ሕዝብ ኹሉ በላይ ምርጡ ዘር በሆነው በአርያን ሕዝብ ላይ የተቃጣ የጥፋት እቅድ ነው በእሚል ፤ ሕዝብ የበላይ ሕዝብ/ዘር እና የበታች ሕዝብ/ዘር ተብለው ለኹለት ይከፈላሉ እንጂ ሕዝብ ኹሉ እኩል አይደሉም በእሚል የራሱ ዝበታዊ አስተሳሰብ ላይ ተመርኩዞ ፤ እኛ ጀርመኖች የኹሉም ሕዝብ የበላይ ስለ ሆንን ፤ ሐገራችን የእዚኽ የበላይ ሕዝብ መኖሪያ ነች ፤ መኖሪያም ብቻ ሳትሆን ፤ የጀርመን መንግሥት ይኽ የበላይ ዘር ከበታቹ ዘር ጋር እየተዳቀለ የበላይነቱን እንደ አያጣ ፤ የዘሩን ጥራት ማስጠበቅ ዋነኛ ግቡ ነው በእሚል ፤ የዘር ጥበቃ እና እድገት የሐገር መሠረት በመሆኑ መንግሥት ይኽን ማስካት ግዴታው ነው በእሚል ፤ ከማርክሲስቱ ውላጅ ከሆነው የብሔር ጽንፈኝነት የተለየ እና በዋናነት በአርያን ሕዝብ ዘረኝነት ላይ የተመሠረተ የብሔር ጽንፈኝነት አስተዋውቋል።
ይኽም በዝግመት ከእላይ እንደ አልነው ብሔርተኝነትን ከዘር ወይንም ከማንነት ጋር በማያያዝ ወደ ብሔር ጽንፈኝነት የዘቀጠበትን ኹኔታ ፈጥሯል።
ይኽንን ንዑስ ክፍል ስናጠናቅቅ ፤ የብሔር ጽንፈኝነት በኹለት መልኩ የእሚገኝ ሆኖ እኛገኘዋለን።
አንደኛው የሌኒንን ክርክር ማሳመሪያ አባባል መሠረት በማድረግ ፤ የራስን እድል በእራስ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል ድረስ ማንኛውም የብሔር ጥያቄ ለእሚያነሳ የሕዝብ ንዑሳን ያለ ቅድመ ኹኔታ መሰጠት የአለበት የእሚል ነው።
ኹለተኛው ደግሞ በተለይ በአዶልፍ ሒትለር አስተሳሰብ መሠረት ፤ የስልጣኔ መሠረቱ የዘር ጥራት በመሆኑ ፤ ብሔራዊ ሐገራት የአንድ ዘር መኖሪያ ብቻ መሆን አለባቸው በእሚል ተጀምሮ በግዜ ፤ ሐገር የሆኑ ዘርያ ወይንም ማንነት ባለቤት ሰዎች መኖሪያ ነች ወደ እሚል የዘቀጠበት ኹኔታ ተፈጥሯል።
ይኽም በመሆኑ ለብሔር ጽንፈኛው ፦ ሐገርን ከታሪካዊ ፣ ኢከነሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ኹኔታዎች በተነጠለ መልኩ ፤ በቀቢጸ ተስፈኛ ወይንም እንደ ሒትለር ላሉት ደግሞ በምርጡ እና የበላይ ዘር አስተሳሰብ ፤ አንድ የሆነ የጋራ ጠባይ አላቸው የእሚሉዋቸው ንዑሳን መኖሪያ ነች ።
[1] ምንም እንኳን ፤ በእዚኽ በማሕበራዊ ፍጥረትነታችን ምክንያት ስለ እምንፈጥረው ማሕበረሰብ ፤ አርስቶትልን መሰል ጥንታዊ የፖለቲካ ሊህቃንን ጨምሮ የተለያዩ ሙህራን ፤ ይኽ በሰዎች ፖለቲካዊ ተፈጥሮ አማካኝነት የእሚፈጠረው ፖለቲካዊ ማሕበረሰብ ከተወሰነ መጠን ሲያልፍ ውጤታማነቱ ይቀንሳል የእሚል ኃሳብ የነበራቸው ቢሆንም ፤ አኹን በደረስንበት የማሕበራዊ ሳይንስ መርህ አንድ መሐበረሰብ ከተዋቀረ ፤ የማሕበረሰቡ መጠን በተለቀ ቁጥር ፤ ራሱን በራሱ የመቻሉ እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በማሕበረሰባዊ ትስስር ውስጥ ያለው ሚና እየጎላ የእሚኼድ በመሆኑ እና በእዚኽም በሌሎች ላይ ያለው ተደጋፊነት እየቀነሰ ፤ መጠኑ በአነሰ ቁጥር ደግሞ በተቃራኒው ስለ እሚሆን ፤ ሰፋ ያለ ማሕበረሰብ ፥ በተገቢው መልኩ ከተመራ ለአባላቱ የእሚሰጠው ጥቅም በእዛው መጠን የእሚጨምር እንጂ የጉዳት ምንጭ እንደ አልሆነ የታወቀ ነው።
[3] የብሔር ጥያቄ ማለት ፦ በአንድ ሕዝብ (ነገድ ፣ ጎጥ ፣ ጎሳ ፣ ወይንም እነ እዚኽን ኹሉ በአካተተ የሆነ የሕዝብ ንዑሳን) ስም ፤ ነጻ እና ሉዓላዊት ሐገር የመመሥረት ጥያቄ ማለት ነው።