ይኽ ክፍል አምስት ያልኹት የታሪካችን ክፍል ፤ በንጉሥ ዳግማዊ ዳዊት[1] (ልብነ ድንግል) የንግሥና ዘመን ፤ እ.አ.አ. በ1529 ዓ.ም. ከጀመረው የግራኝ አህመድ ጥቃት አንስቶ ፥ የአጼ ሰሶንዮስ ንግሥና አብቅቶ የአጼ ፋሲለደስ ንግሥና እስከ እሚጀምርበት ግዜ እ.አ.አ. በ1632 ዓ.ም. የአለውን በጠቅላላው ወደ 103 ዓመታት የእሚጠጋውን ግዜ ነው።
የእዚኽ ክፍለ ታሪክ ዋነኛ ፖለቲካዊ መገለጫ ፤ በዘመነ አክሱም የተዘነጋው የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ፤ ከብዙ መቶ ዓመታት ልፋት በኋላ ፤ እንደገና ተጀምሮ መልካም ፍሬ ማፍራት ሲጀምር ፤ ከማንም ግምት ውጭ በሆነ መልኩ ፤ አዲስ የዓለም ዓቀፍ ፖለቲካዊ አቅጣጫ በመጀመሩ ፤ መልካም ፍሬ በማፍራት ላይ የነበረው ይኽ የውጭ ግንኙነት ፤ በድንገት ተገልብጦ በብዙ ዘመን ቆይታ ፤ በኢትዮጵያዊያን ላብ እና ደም የተገነባው ሐገር እና ኃብት ፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በእማይታወቁ መልኩ ለህልውና አደጋ የአጋለጠበት ዘመን በመሆኑ ነው ።
ክፍል አራት በአልነው የታሪካችን ዘመን የመጀመሪያው ግማሽ ላይ ወይንም እስከ 1400 ዓ.ም. ድረስ በአለው ወቅት ፤ ኢትዮጵያ እንደ አንድ ሉዓላዊት የፖለቲካ አስተዳደር ዛሬ ያአላ፟ትን መልከዓ ምድራዊ እና በአብዛኛው ከእዛኽ በኋላ በተደረጉ ስደቶች የተጨመሩትን ከአልሆነ በስተቀር የዛሬዎቹን ሕዝቦቿን አካታ ፤ እንደ አንድ ዘመናዊ ሐገር ተመስርታ እና ተደላድላ ጨርሳ ነበር ።
ይኽንንም ተከትሎ ፤ የእዚኽኛው የታሪክ ወቅት የኢትዮጵያ ቀዳሚው የፖለቲካ ፍላጎት የነበረው ፤ ከ6ኛው ምዕተ ዓመት መጨረሻ አከባቢ በአክሱም መዳከም ምክንያት እየተቀዛቀዘ እና እየደበዘዘ የነበረውን የዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ፤ ትርጉም በአለ፟ው መልኩ እንደ ገና በማስጀመር ፤ ከመልካም የውጭ ግንኙነት በእሚገኙት ትሩፋቶች ፤ የሐገር ግንባታውን ይበልጥ ማጠናከር ነበር ።
ለእዚኽም ደግሞ የሐገር ውስጡን ፖለቲካ የማደላደል ሥራ ፤ ከእላይ በአልነው አግባብ ስኬታማ በእሚባል መልኩ ከማጠናቀቅ በአሻገር ፤ ሌሎች በሐገር ውስጥ እና ከሐገር ውጭ ፤ በእዚኽን ወቅት የተከናወኑ ክስተቶች ፤ ይኽን የውጭ ጉዳይ ግንኙነትን እንደገና የማስጀመሩን ጉዳይ በማመቻቸት እና ግድ በማለት ፤ ለእዚኽ የዓለም ዓቀፍ ግንኙነት መታደስ የራሳቸውን በጎ ሚና ተጫውተዋል ።
በእዚኽ ረገድ ከ12ኛው ምዕተ ዓመት ጀምሮ በአውሮፓ ስሙ ገኖ የነበረው የንግርታዊው ቀሲስ ዮሐንስ ንግርት ወይንም ታሪክ ፤ በእዚኽ ዘመን ኢትዮጵያ ለእሚያስፈልጋት እና ለተዘጋጀችበት ውጤታማ የውጭ ግንኙነትን በድጋሚ ለማስጀመር ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ነበር ።
የቀሲስ ዮሐንስ (Prester John) ታሪክ ወይንም አፈ ታሪክ እንዴት እና በማን ወደ ሮማ ቤተክርስቲያን ሊደርስ እንደ ቻለ የተለያዩ መላምቶች የአሉ፟ ሲሆን ፤ ታሪኩ ግን በአንድ በሆነ ምክንያት ፤ ከሰፊው የእስልምና ግዛት በአሻገር እገኛለሁ በአለ ወይንም በተባለለት ታላቅ ንጉሥ አማካኝነት የተጀመረ እንደ ሆነ ነው የእሚታወቀው።
ይኽ ንግርትም በ12ኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ አከባቢ በአውሮፓ ከቤተ ክርስቲያን ወጥቶ ወደ ማሕበረሰቡ ውስጥ ከተዳረሰ በኋላ ፤ ይኽን ንጉሥ ማግኘት እና ከእዚኽ ታላቅ የክርስቲያን ንጉሥ ጋር ትብብር መፍጠር ፤ መላው አውሮፓ የእሚናፍቀው ጉዳይ ሆኗል ።
ይኽ የቀሲስ ዮሐንስ ታሪክ በአጭበርባሪዎች ይጀመር ወይንም ከተለያየ የዓለም አከባቢ ወደ ኢየሩሳሌም የእሚመጡ ክርስቲያኖች መካከል ውስጥ ውስጡን ሲወራ ቆይቶ በኋላ የሮማው ጳጳስ ጋር ይድረስ ፣ የወቅቱ የኢትዮጵያ ነገሥታት(ዛግዌ) ከአውሮፓ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ሕብረት ለመፍጠር ኾን ብለው ያስጀምሩት[2] ወይንም ሌላ ምክንያት ይኑረው በእርግጠኝነት አይታወቅም ።
አይ ዲ ራችዌልትዝ (I. De Rachewiltz) የእሚባለው ጸሐፊ ፤ የእዚኽ አፈ ታሪክ ምንጭ ፤ እ.አ.አ. በ1145 ዓ.ም. በሶርያ ይገኝ የነበረ አንድ ኢጵስ ቆጶስ ፤ ለሮማው ጳጳስ ፤ ልክ እኛ በአማርኛ ስሙን እንደ እምንለው ፥ ዮሐንስ የእሚባል የኤስያ ንጉሥ እንደ አለ በመንገሩ ነው ይላል ፦
“ኢጲስ ቆጶሱ (የሶሪያ) ለጳጳሱ ፤ ከትንሽ ዓመታት ቀደም ብሎ ዮሐንስ የእሚባል : በሩቅ ምሥራቅ የእሚኖር የኔስቶርያዊ ክርስቲያን ንጉሥ ፐርዥያኖችን እንደ አሸነፋቸው ነገረው ።“
“The bishop told the pope how some years previously a certain Iohannes, a Christian Nestorian King and priest living in the Far East, had defeated the Persians. [33]“
ማቲዮ ሳልቫዴር የእሚባለው ጸሐፊ ደግሞ ፤ እ.አ.አ በ1165 ዓ.ም. የቤዛንታይን ንጉሥ የነበረው ፤ ማኑኤል ቀዳማዊ ኮምኔነስ (Manuel I Komnenos) ከቀሲስ ዮሐንስ ደብዳቤ ስለ ደረሰው ነው ፤ የቀሲስ ዮሐንስ አፈ ታሪክ የጀመረው ይላል ፦
“የአፈታሪኩ ምንጭ መካከለኛው ዘመን ላይ ፤ በተለይ የቢዛንታይኑ ማኑኤል ቀዳማዊ ኮምኔነስ (እ.አ.አ. 1143 – 1180 ዓ.ም.) ፤ ራሱን ቀሲስ ዮሐንስ ነኝ ከእሚል ሰው ፤ ረዘም ያለ እና ከአውሮፓ አቻዎቹ ጋር ትብብር ማድረግ እፈልጋለሁ የእሚል ደብዳቤ ከደረሰው በኋላ ነው ። “
“The myth traces its origin to the Middle Ages, in particular to 1165 when Byzantine emperor Manuel I Komnenos (1143 – 1180) received a long letter through which a self-declared Prester John sought alliances with his European peers. [32]“
አኹን በአለው መረጃ ፤ ለአፈ ታሪኩ መነሻ የሆነው አጋጣሚ ትንሽ ድንግዝግዝ የአለበት ቢሆንም ፤ ከእዚኽ ዘመን አንስቶ ታሪኩ በሰፊው ሲወራ ቆይቶ የእዚኽን ታሪክ ባለቤት ሐገር ማግኘት የአውሮፓ ነገሥታት እና ሊህቃን ህልም ሆኗል ።
የቀሲስ ዮሐንስ ታሪክ ፤ በእዚኽ መልኩ ከጀመረ እና አውሮፓውያን ቀሲስ ዮሐንስ ጋር ለመድረስ እንቅስቃሴ ማድረግ በጀመሩበት እ.አ.አ. በ1177 ዓ.ም. አከባቢ ፤ ቀሲስ ዮሐንስ ኢስያ ውስጥ ነው የእሚገኘው የእሚለው ፤ ሰፊ ተቀባይነት የአለው መላምት ሆኖ ነበር ፦
“… በእዚኽ ወቅት ቀሲስ ዮሐንስ በኤስያ የእሚገኝ ክርስቲያን ገዢ እና... የምዕራባዊያን ወዳጅ ነው የእሚለው ዝናው በመላው አውሮፓ እና በሌቫንት (ሶሪያ ፣ ሌባኖስ እና እሥራኤል) በደንብ የታወቀ ነበር ።”
“…Prester John’s reputation as a Christian ruler of Asia and a friend ... of western nations was by now as well established in Europe as in the Levant. [33]”
የቀሲስ ዮሐንስ አፈ ታሪክ እንደ ጀመረ ፤ ማለትም በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ፤ የእዚኽ ኃያል ክርስቲያን ንጉሥ ሐገር መገኛ ኢስያ ውስጥ ነው የእሚለው ግምት ሰፊ ተቀባይነት ቢኖረውም ፤ አውሮፓዊያኖች ኢስያ ውስጥ ታላቅ የክርስቲያን ንጉሥ አለ መኖሩን ወደ እዚያኽ በመኼድ ከአረጋገጡ በኋላ ፤ ማለትም ከ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አከባቢ አንስቶ ፤ በተለያየ ምክንያት ኢትዮጵያ የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ነች ብለው ደምድመዋል ፦
“በእዚያኽ ምዕተ ዓመት (በ 13ኛው ምዕተ ዓመት) መጨረሻ ፤ አውሮፓዊያኖች ከሞንጎል ጋር ከተገናኙ በኋላ ፤ የእዚኽ ምናባዊ ንጉሥ ሐገር ኢትዮጵያ ነች ብለዋል ። … ይኽ ለውጥ ግን የአንድ ወገን ጉዳይ ብቻ አልነበረም ። ኢትዮጵያዊያኖች በአሥራ አራተኛው እና በአሥራ አምስተኛው ምዕተ ዓመታት የምሥራቁ የክርስቲያን ንጉሥ የእሚለውን ንግርት ወስደው ፤ ሐገራቸውን እንደ ሐይማኖተኛው ቄስ ሐገር አድርገው አቅርበው ነበር ።”
“By the end of that century, however, European encounters with the Mongols prompted the relocation of the imaginary sovereign to Ethiopia. … This shift was certainly not unidimensional. Between the fourteenth and fifteenth centuries Ethiopians successfully appropriated the myth of the Christian king of the East, transfiguring their own country into the land of the devout Prester. [32]“
ስለ እዚኽ ፤ እ.አ.አ. ከ1250 ዓ.ም. ገደማ አንስቶ ፤ አውሮፓዊያኖች ኢትዮጵያ የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ነች ብለው ደምድመው እና ኢትዮጵያም እኔ ነኝ የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ብላ ፤ ኢትዮጵያዊያኖች እና አውሮፓዊያን ፤ የእስልምናው ኢምፓየር በንግድ እና በፖለቲካ ጉዳይ የእሚያደርስባቸውን ተጽኖ ለመግፈፍ በጋራ ምስጢራዊ ግንኙነት ሲያደርጉ ቆይተዋል ።
የ’አፈታሪኩ’ ቀሲስ ዮሐንስ እና የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቁርኝት ይኽ ቢኾንም እና የዘመኑ አውሮፓዊያኖች በእዚኽ መልኩ የቂሲስ ዮሐንስ ሐገር ኢትዮጵያ ነች ብለው ደምድመው የአለ፟ፉት ፤ የአለ፟ፉትም ብቻ ሰአይሆን ፤ በእዚኽ እምነት ላይ ተመርኩዞ የዓለም ፖለቲካ ብዙ ርቀት ተጉዞ እና የዓለም ታሪክ ተለውጦ ከአበቃ በኋላ ፤ እንደ የ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የጀርመን ታሪክ ጸሐፊ ፥ እዮብ ሉዶልፍ የአሉ፟ ጸኃፍት ፤ የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ኢትዮጵያ ሰአትሆን ፤ ኀንድ ወይንም ቻይና ውስጥ የእሚገኝ አንድ አከባቢ ነው ብለው ሐተታ ይጽፋሉ ።
በእኔ መረጃ ፤ ለእዚኽ ተጠራጥሮ ታሪክ ቀዳሚው ፤ ከላይ የጠቀስነው በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1684 ዓ.ም. ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ የእሚል በብዙ መልኩ በጎ ሊባል የእሚችል መጽሐፍ የጻፈው ፤ ጀርመናዊው እዮብ ሉዶልፈስ ( Job Ludolphus or Hiob Ludolf ) ነው ።
ሉዶልፍ ከይመስልኛል የአለፈ ተጨባጭ ማስረጃ በአይኖረውም ፤ የመጽሐፉን ንዑስ ርዕስ ሳይቀር ፤ “በተለምዶ ፥ በስህተት የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ተብላ የእምትጠራው” ብሎ ሰይሟል ፦
“አዲስ የኢትዮጵያ ታሪክ ፥ በተለምዶ ነገር ግን በስህተት የቀሲስ ዮሐንስ ግዛት ስትባል የነበረችው ፤ ሙሉ እና ትክክለኛ ገለጻ”
“A NEW HISTORY OF ETHIOPIA , Being A full and accurate description of The kingdom of Abyssinia, Vulgarly, though Erroneously called, THE EMPIRE of PRESTER JOHN [104]“
ከእነርሱ ቀደም ብለው የነበሩት አውሮፓዊያን ፤ የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ኢስያ ውስጥ ነው ብለው ጀምረው ፤ ኢስያ ውስጥ መሰል ትልቅ የክርስቲያን ንጉሥ አለመኖሩን በመአረጋገጣቸው ፤ የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ኢትዮጵያ ነች ብለው ተቀብለው ፤ ኢትዮጵያም እንደ እዛው አድርጋ እና በእዚኽም መግባባት ፤ ኢትዮጵያን እና አውሮፓዊያን ብዙ ትብብር አድርገው እና በእዚኽም መሠረት የሰው ልጅ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ውስጥ ገብቶ ፤ በታሪክም በምድረ ኤስያ ታላቅ የክርስቲያን ንጉሥ የአልነበረ መሆኑ ተረጋግጦ ከአበቃ ፤ ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ የመጡት አንዳንድ የአውሮፓ ሙህራን ፤ የእኛ አባቶች ኢትዮጵያ ነች የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ነች የአሉት ተሳስተው ነው እንጂ ትክክለኛዋ የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ኢስያ ውስጥ ነው የአለ፟ችው ብለው አንደ ታሪክ ሊህቅ ሊጽፉ የእሚችሉት ፤ የቀሲስ ዮሐንስ ታሪክ በዘመናዊ ዓለም ውስጥ የአለ፟ውን ወሳኝ ታሪካዊ ስፍራ ፤ ስለ እዚኽም ኢትዮጲያ ከቀሲስ ዮሐንስ ጋር በታሪክ መቆራኘቷ በዘመናዊ ሉላዊነት መጀመር ውስጥ የአላ፟ትን ታሪካዊ ስፍራ ለማሳጣት ከአልሆነም ሳይንሳዊ ማጭበርበር በመፈጸም ራስን ታዋቂ ለማድረግ ከመፈለግ ውጭ ምንም ምክንያት ሊገኝለት የእሚችል አይደለም ።
ለእዚኽ ተነግሮ እና ተዘክሮ ለአለፈ ታሪክ አዲስ መላምት አለን ብለው የመጡ ሙህራን ፤ ቀሲስ ዮሐንስ ኤስያዊ ነው ለእሚለው ‘አዲስ’ መላምታቸው ማሳያ እንደ ማስረጃ አድርገው ከእሚያቀርቡዋቸው መከራከሪያዎች አንዱ ፤ ለምሳሌ ፦ ለአፈታሪኩ እንደ አንድ ምንጭነት የእሚጠቀሰው የሶሪያው ጳጳስ ፥ በቻይና ወይንም በኀንድ የሌለ ፤ ዮሐንስ (ልክ እንደ ኢትዮጵያዊኛው አጠራር ) የእሚባል ስያሜ ከየት አመጣ ለሚለው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ፦
“ታዲያ ዮሐንስ እንዴት ሊባል ቻለ ? … ምን አልባት ፦ የኔስቶሪያን ክርስትና ተከታይ የሆኑት የመካከለኛው ምሥራቅ አማኞች ፥ የህ-ሉል-ታሺሽ የእሚለውን ስም ዮሐንስ ብለው አንብበውት ወይንም ጠርተውት ይሆናል …”
“But why call him Iohannes ? ... The Nestorian Christians of Central Asia may have given him this name partly because a phonetic association with a name or title borne by Yeh-lu Tashish... [33]“
የእሚል እና መሰል ፤ ብዙም ርቀት የእማያስክኼዱ መላምቶች ነው የእሚሰነዝሩት ።
በእኔ እምነት ግን ፤ እነዚኽ የታሪክ ተመራማሪዎች ፤ አውሮፓዊያኖች ከ13ኛው ምዕተ ዓመት አንስቶ ፤ የቀሲሱ ሐገር ኤስያ ውስጥ እንድ አልሆነ ማረጋገጣቸውን የእሚያሳየው ታሪክ በአያውቁትም እንኳን ፤ እንደ ታሪክ ተመራማሪነታቸው ፤ በአውሮፓዊያን እና በኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች መካከል ረዥም ዘመን የቆየ ግንኙነት ቢመለከቱ ኖሮ ፤ የአውሮፓ ክርስቲያን መሪዎች ኢትዮጵያ የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ነች ብለው በስህተት እንደ እማይደመድሙ ሊረዱ ይችሉ ነበር ።
ኢትዮጵያ ከአውሮፓዊያን ጋር ፤ ከሮም ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ደረስ የአልተቋረጠ ታሪካዊ ግንኙነት የነበራት በመሆኑ እና በሶሪያ ፣ በኢየሩሳሌም ፣ ወዘተ ፤ በተመሳሳይ የቆየ ታዋቂነት የአላ፟ት በመሆኑ ፤ ከእዛም በአሻገር ፥ እነ ክርስታቮ ደጋማ የግራኝ ጦርነትን ለመቀልበስ በፖርቹጋል ነገሥታት ሲላኩ ፤ የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ኼዳችሁ አግዙ መባላቸው ፤ ምንም ማስተባበያ ሊቀርብበት የእማይችል ታሪካዊ ኃቅ በመሆኑ ፤ የታሪኩ ምንጭ ኢትዮጵያ ለምን እንደ ኾነች ማስረዳት አስቸገረ ቢባል እንኳን ፤ የታሪኩ ባለቤት ሆና እንደ ነበር ምንም የእማያጠያይቅ በመሆኑ ፤ በስህተት የቀሲስ ዮሐንስ የተባለችው ሐገር ወይንም ትክክለኛው የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ኤሲያ ውስጥ ነው አስብሎ ሐተታ የእሚያፅፍ ምንም ሳይንሳዊ ምክንያት እንደ ሌለ ሊያስረዳቸው ይገባ ነበር።
ለምሳሌ ፦ በሮማው ቄሳር ቆስጦንጢኖስ እና በኢትዮያው ኢዛና መካከል ፤ መተጋገዝን የአካተተ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደ ነበር በታሪክ የተመዘገበ ነው ፦
“እ.አ.አ. በ 356 ዓ.ም. ገደማ ፤ ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ ፤ ፍሬምናጦስ አሌክሳንድሪያ ላይ እርሱ በሾመው ጳጳስ የቀኖና ምርመራ ይደረግበት ዘንድ እንዲልከው ለማሳመን ለኢዛና ደብዳቤ ጽፎ ነበር … “
“In about 356 AD the emperor Constantinus II wrote to Ezana trying to persuade him to submit Frumentius to doctrinal examination by his own appointe to Alexanderia… [86]“
ይኽ እንግዲኽ የዛሬ 1,650 ዓመታት ቀደም ብሎ ነው ።
ከእዚያኽም በኋላ ፤ ከንጉሥ ኢዛና በኋላ ወደ 200 ዓመተታ ገደማ ዘግይቶ የመጣው ፤ ንጉሥ ካሌብ በእዛያን ዘመን በነበረው የክርስትና ዓለም በጣም ከመታወቁ የተነሳ ፤ እንደ ጊዮርጊስ ዓይነት የሰማዕትነት ማዕረግ የተሰጠው እና Saint Elesbaan እየተባለ (ካሌብ እለ አፅብኃ) ፤ ፈረንጆቹ እለ አፅበኃ ማለት ስለ እማይችሉ እለስባን እያሉት ፤ በራሺያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ኹሉ ፤ ቀኑ ታስቦ የእሚውል ቅዱስ ሰማዕት ነው ፦
“በብዙ ቤተክርስቲያን ቀን መቁጠሪያ ውስጥ በቅዱስነት ይከበራል (እለ አፅብሓ) ።”
“He is recognized as a saint in several church calendars. [86]“
ይኽ የቆየ ታሪክ ስለ ነበር ፤ የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር በአውሮፓ በገነነችበት ዘመን ተረስቶ ይሆናል እንደ አይባል ፤ ከ12ኛው ምዕተ ዓመት አንስቶ በኢትዮጲያ እና በተለያዩ የአውሮፓ ነገሥታት መካከል ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመኖሩ የተነሳ ፤ ከሉዶልፍ 200 መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ እ.አ.አ. በ1457 አከባቢ በሮም “Santo Stefano degli Abyssini” or in English “Saint Stephen of Abysinnia” ወይንም የአቢሲንያው ቅዱስ ዮሴፍ ፤ የተባለ ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የቅዳሴ ወግ ቅዳሴ የእሚደረግበት ፤ ኢትዮጵያዊ መነኩሳት የነበረቡት ገዳም እስከ መመሥረት ደርሶ ነበር። ስለ እዚኽ ገዳም ፤ ሰማንታ ኬሊ የተባለች ተመራማሪ እንደ እዚኽ ትላለች ፦
“ከኢትዮጵያ ውጭ ፤ በሜድትራኒያን ባሕር ዙሪያ በኢየሩሳሌም ፣ በካይሮ እና በግብፅ በጣም ቆየት ካለ ግዜ አንስቶ ከእሚገኙ የኢትዮጵያ ማሕበረሰባት በተጨማሪ ፤ በቅዱስ እስጢፋኖስ ይገኙ የነበሩ ኢትዮጵያዊ መነኮሳት ፤ በአሥራ ስድስተኛው እና አሥራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፤ በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ መካከል የባህል አምባሳደር በመሆን ዓይነተኛ ሚና ተጫውተዋል ። ምንም እንኳን ከየት እንደመጡ ግልፅ የሆነ ነገር በአይኖርም ፤ መጀመሪያ ላይ እ.አ.አ. በ1497 ዓ.ም. በቅዱስ እስጢፋኖስ እንደ ነበሩ ይታወቃል … “
“Part of the Ethiopian diaspora around the Mediterranean whose other centers, of much older foundation, were located in Jerusalem, Cairo, and Cyprus, the monks of Santo Stefano played a particularly important role as a cultural intermediary between Europe and Ethiopia in the sixteenth and seventeenth centuries. Despite the community’s murky origins – Ethiopians are first attested at Santo Stefano in 1497 ... [105]“
ይኽም ማለት ፤ ደቡብ ምዕራባዊ አውሮፓዊያኖች ስለ ኢትዮጵያ በስማ በለው ሰአይሆን ፤ ኢትዮጵያ ማን ነች ? የት ትገኛለች ? ታሪኳ ምንድነው ? የእሚለውን በእሚገባ ከማወቃቸው አልፎ ፤ አክራሪው የሮማ መንበር ፥ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፤ በግልፅም በአይሆን ፤ በወንዳማማች አክብሮት ፤ የራሷ ገዳም እንዲኖር ፈቅዷል ፤ ይኽም ደግሞ ኃይማኖታዊ ልዩነት ብዙ በእማይከበርበት በእዚያኽ ዘመን !
ስለ እዚኽ ፦ ጉዳዩ የእሚመለከታቸው ፤ የሮማው የካቶሊክ መንበር እና የተለያዩ የአውሮፓ ነገሥታት ፤ የቀሲስ ዮሐንስ ወይንም የፕሬስተር ጆን ሐገር ኢትዮጵያ ትሁን ወይንስ ሌላ የእሚል ብዥታ አይኖርባቸውም ፤ ምናልባት መደበኛ ሕዝቡ እንጂ ።
ከእዚኽም የተነሳ ፤ መላው የወቅቱ የአውሮፓ ነገሥታት ከ2 መቶ ዓመታት በላይ ለቆየ ግዜ ከኢትዮጲያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሲያደርጉ መልዕክታቸው በሙሉ ተደራሽ የእሚያደርገው ቀሲስ ዮሐንስን ነበር።
ለምሳሌ ፦ አውሮፓዊያኖች የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ኢትዮጵያ ነች ከአሉ ከ200 ዓመታት በኋላ ፤ በዲፕሎማሲያዊ መልዕክተኝነት ኢትዮጵያ የመጣው የካቶሊኩ ቄስ አልቫሬዝ ፤ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የፖርቹጋል ንጉሥ መልዕክተኛ ሆኖ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ፤ የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር እየመጣ እንደሆነ በደንብ አውቆ ነው የመጣው ። ወደ ኢትዮጵያም ከመጣ በኋላ እና ንጉሡንም ሲያገኝ (ንጉሠ ነገሥት ልብነ ድንግልን) ፤ ፕሬስተር ጆን ወይንም ቀሲስ ዮሐንስ እያለ ነው ይጠራው የነበረው ፤ ለዓመታት በኢትዮጵያ ቆይቶ ወደ ሐገሩ ሲመለስም በመጽሐፉ ስለ ቀሲስ ዮሐንስ ነው የጻፈው ።
በወቅቱ ፥ የዓለም ልዕለ ኃያል የነበረችው እና ከእርሷ በብዙ እጥፍ ትል፟ቅ የነበረውን የዖቶማን ተርክ እንዲያፈገፍግ የአደረገችው ፖርቹጋል ነገሥታት ራሳቸው ፤ ኢትዮጵያን የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ብለው እያወቁ እና ብዙ መልክት እየተለዋወጡ ፤ ከፖርቹጋልም በአሻገር ትንሽ ወረድ ብለን እንደ እምናየው ሌሎቹ የወቅቱ መላው አውሮፓ ነገሥታት እና ዓለም ዓቀፏ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ኢትዮጲያ የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር መሆኗን አውቆ ከኢትዮጵያ ጋር ዘርፈ ብዙ ግንኙነት እየአደረገ እና እየተባበረ ፤ በእዚኽም አግባብ የዓለም ታሪክ ወደ ሌላ ምዕራፍ ተሻግሮ ከበቃ በኋላ ፤ አንድ ታሪክ አጥኝ ፤ ምን በቂ ምክንያት ኖሮት ፤ ኢትዮጵያዊያኖች በታሪካቸው በእዚኽ የንግሥና ስም ፤ ማለትም ቀሲስ ዮሐንስ (ፕሬስተር ጆን) በእሚለው ስም ፤ የእሚጠራ ነጋሢ ስለ አልነበራቸው ፤ የእምትል ቀጭን ምክንያት ይዞ ፤ የቀሲስ ዮሐንስ አፈታሪክ ፖለቲካዊ እንደምታ ሳይረዳ ፤ የቀሲስ ዮሐንስ ወይንም የፕሬስተር ጆን ሐገር ኢትዮጵያ አይደለችም ለማለት እርግጠኛ እሚሆነው ?
ስለ እዚኽ ፦ የቀሲስ ዮሐንስ እና የኢትዮጵያን ቁርኝት ፤ ከ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ የመጡ አንዳንድ ጸሐፍት ለማጣጣል የእሚሞክሩበት መንገድ ታሪካዊ መሠረት የሌለው እና ምክንያቱ ብዙም ግልፅ የአልሆነ አጉል ትንተና ነው ።
በተደጋጋሚ እንደ አልነው ፤ የቀሲስ ዮሐንስ ንግርት መነሻው በአይታወቅም ፤ ዋናው ጭብጥ[3] ፤ በኃብትም በጦርም ታላቅ የሆነ ከትልቁ ከእስልምና ኢምፓየር በአሻገር የእሚኖር ቀሲስ ዮሐንስ የእሚባል የክርስቲያን ንጉሥ አለ፟ የእሚል ሆኖ ፤ ይኽም ደግ እና ጀግና የክርስቲያን ንጉሥ ፤ ክርስቲያን አውሮፓዊያን ከትልቁ የእስልምና ኢምፓየር ጋር በእሚያደርጉት ጦርነት ሊያግዛቸው የእሚፈልግ እና የእሚችል ፥ የወቅቱ ክርስቲያኖች ኹሉ ጉጉት የሆነችውን ኢየሩሳሌምም ከሙስሊሞች አገዛዝ ነፃ ማውጣት የእሚችል የክርስቲያን ንጉሥ ነው የእሚል ነው ።
ይኽ የቀሲስ ዮሐንስ ንግርት ፤ አውሮፓዊያን ከሙስሊሞች ጋር በእሚያደርጉት ግብግብ ድል እየራቃቸው በኼደበት ዘመን አከባቢ ጀምሮ ፤ ግብግቡ ለአውሮፓዊያኖች ተስፋ አስቆራጭ ደረጃ ላይ በደረሰበት ግዜ ፤ ንግርቱ በጣም ገኖ በመላው አውሮፓ በመስፋፋቱ ፤ አውሮፓዊያን ይኽንን የክርስቲያን ንጉሥ ለማግኘት አሰሳ ውስጥ እንዲገቡ አነሳስቶዋቸዋል ።
አንድሪው ከርት (Andrew kurt) የተባለ ሰው ፤ አውሮፓዊያኖች በቀሲስ ዮሐንስ ንግርት ተነሳስተው ፤ ከ12ኛው ምዕተ ዓመት አጋማሽ ጀምሮ የቀሲስ ዮሐንስን ሐገር ወደ ማፈላለግ የገቡበትን ኹኔታ ፤ እንደ እዚኽ አስቀምጦታል ፦
“ዋና ገፀ ባሕሪያችን (ቀሲስ ዮሐንስ) የግዛት ባለቤት ነው … በእዚኽ የመስቀሉን ጦርነት የእሚያካኼዱት መንግሥታት ምጥ ውስጥ በነበሩበት ወቅት ፡ ይኽን መሰሉ ገለፃ ግዛቱን ለማግኘት ፍላጎት አጫረ ። እናም ፥ ፍለጋው ተጀመረ ።“
“our protagonist governed a kingdom … at a point when the Crusader states were in jeopardy, such a description naturally kindled the desire to find this realm. So, the search began. [106]“
እንደ ብዙዎች እምነት ፤ የቀሲስ ዮሐንስ ንግርት በአውሮፓ ከጀመረ በኋላ ፤ አውሮፓዊያኖች መጀመሪያ አከባቢ ፤ ቀሲስ ዮሐንስ በኤስያ የእሚገኝ ንጉሥ ነው ብለው በመገመት ፍለጋቸውን ከኤስያ ነው የጀመሩት ። በእዚኽ መሐል ግን ኢትዮጵያዊያን ነገሥታት ፤ የንግርቱ ሐገር ንጉሥ እኛ ነን ብለው ፤ አውሮፓዊያን የኤስያ ፍለጋቸው ውጤት አልባ ሲሆንባቸው ትኩረታቸውን ወደ ኢትዮጵያ እንዲያደርጉ አድርገዋል ፦
“የእዚኽ የትኩረት ለውጥ በእርግጥም የአንድ ወገን ጥረትም ብቻ አልነበረም ። በአሥራ አራተኛው እና በአሥራ አምስተኛው ምዕተ ዓመታት ፤ ኢትዮጵያዊያን ሐገራቸውን ወደ መንፈሳዊው ቀሲስ ዮሐንስ ሐገርነት በመቀየር ፤ ንግርቱ የእኛን ሐገር የእሚያመለክት ነው በማለት ራሳቸውን የታሪኩ ባለቤት ለማድረግ ተንቀሳቅሰዋል ።”
“This shift was certainly not unidimensional. between the fourteenth and fifteenth centuries Ethiopians successfully appropriated the myth of the Christian King of the East, transfiguring their own country into the land of the devout Prester. [32]“
በሐገር ውስጥ የነበረውን የሐገር ግንባታውን ማጠናቀቅ ፤ ለእዚኽ የታሪክ ክፍሉ የውጭ ጉዳይ እንደ ገና መጀመር አቀጣጣይ ሲሆኑ ፤ ከሐገር ውጭ በቀሲስ ዮሐንስ ንግርት በአውሮፓ እና በኢትዮጵያዊያን መካከል ለዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አዲስ ጅማሮ ወሳኝ እንዲሆን የአደረጉት ምክንያቶች ፦ በአውሮፓ ክርስቲያኖች እና በመካከለኛው ምሥራቅ ገዢ የሙስሊም መንግሥታት መካከል የነበረው ግብግብ እና የሮማዋ የካቶሊክ መንበር የዓለምን ክርስቲያኖች በሙሉ በመንበሯ ስር እንዲተዳደሩ የነበራት ፍላጎት በጋራ ተደማምረው ነው።
የዓለማችን ትልቁ ኢምፓየር የነበረው የሮማን ኢምፓየር ፤ ከአክሱም ጋር በተመሳሳይ ግዜ ፤ ማለትም በ5ኛው ምዕተ ዓመት ተዳክሞ ከውስጥ ከዘበጠ በኋላ ፤ በእሚቀጥሉት 6 እና 7 መቶ ዓመታት ፤ ከእዚኽ ሰፊው የሮማን ኢምፓየር ውስጥ እነ እንግሊዝ ፣ ስፔን ፣ ፖርቹጋል ፣ ፈረንሳይ ፣ ጣሊያን ያሉት ሐገራት እንደ ተናጠል ራሳቸውን የቻሉ ሐገራት ኾነው መነሳት የጀመሩበት እና በእየግዜው ድንበሩን በኃይል እየገፋ ‘ልዋጣችኹ’ እያለ የእሚያስፈራራቸውን የእስልምና ኢምፓየር እንደ ስጋት የእሚያዩበት ደረጃ ላይ የደረሱበት ግዜ ስለ ነበር ፤ ይኽን ስጋት ለማስወገድ ከፍተኛ ፍላጎት እያዳበሩ የመጡበት ወቅት ነበር ።
ለምሳሌ ፦ እስልምና በሰይፍ ኃይል ክርስቲያን በነበሩት በደቡባዊ አውሮፓ ወይንም የኢቤሪያን ወሽመጥ (Iberian peninsula) ሐገራት ፥ ፖርቹጋል እና ስፔን ሰርጎ ገብቶ በኃይል የመሠረተውን ግዛት ለማስመለስ የስፔን እና የፖርቹጋል ዜጎች ከሙሮቹ ጋር ከ600 ዓመታት በላይ የቆየ ተጋድሎ (Reconquista) አድርገው ነው ፤ ከወሽመጡ የእስልምናን መንግሥት በኃይል የማስወገዱን ሥራ በ15ኛው ምዕተ ዓመት አከባቢ ያጠናቀቁት።
እንደገናም በወቅቱ የኢየሩሳሌም አስተዳዳሪ ሙስሊሞች ፤ እ.አ.አ. በ1099 ዓ.ም. የክርስቶስ ኢየሱስ መቃብር ነበር ተብሎ በእሚታመንበት ቦታ ላይ የነበረው ቤተክርስቲያን እንዲ ፈረስ እና እንዲ ቃጠል መደረጉ ፤ እንዲኹም በኢየሩሳሌም የእሚኖሩ ክርስቲያኖች የእሚደርስባቸው የተለያየ ዓይነት በደል ፤ ከሌሎች ብዙ ምክንያቶች ጋር ተደራርቦ የመስቀሉን ጦርነት (Crusade) ያስነሳ እና በመጀመሪያ የመስቀሉ ጦርነት የተገኘው ድል ፤ ከመቶ ዓመት በኋላ ተቀልብሶ ፤ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኢየሩሳሌም ተመልሳ በሙስሊሞች እጅ መግባቷ ፣ ከእዚያኽም በተደጋጋሚ ሶሪያን ፣ ግብፅን ፣ ወዘተ ፤ ከሙስሊሞች ለማስለቀቅ የተደረጉ ሦሥተኛ ፣ አራተኛ ፣ ወዘተ ፤ የመስቀሉ ጦርነቶች በሙሉ በሽንፈት በመደምደማችው ፤ ክርስቲያን አውሮፓዊያን ከእስልምና ኢምፓየር ጋር የእሚያደርጉት ጦርነት ልባቸው እንዲወድቅ የአደረገበት ወቅት ነበር ።
በእዚኽ ላይ ደግሞ ፤ የእስልምናው ኢምፓየር ውስጥ ‘የመንግሥት ግልበጣ’ ተካኺዶ ፤ አመራሩ ከአረቦች ወደ ቱርኮች በመዛወሩ የመጣው አዲስ ለውጥ ፤ እስልምናን የበለጠ አምባገነን እና አስጊ በማድረግ ፤ ከባዛይንቲየም ጀምሮ እስከ ዛሬዎቹ የባልካን ሐገራት ከእሚባሉት ውስጥ እንደ ሐንጋሪ ያሉትን እየተቆጣጠረ ስለ ነበር ፤ የእስልምናው ኢምፓየር አካኼድ ለክርስቲያን አውሮፓ በእየግዜው አስጊነቱ እየጨመረ የእሚኼድ አድርጎታል ።
በአጠቃላይ ፤ ክርስቲያን አውሮፓዎች ከእስልምና ኢምፓየር ጋር በእሚያደርጉት ግብግብ ፤ ድላቸውን ማስጠበቅ እና የተነጠቁትን ነገር ማስመለስ በወቅቱ ገኖ በነበረው የእስልምና ኢምፓየር ቋሚ የስጋት ምንጭ ሆኖባቸው ነበር ፤ ስለ እዚኽ በእዚኽ ግብግብ የእሚያግዛቸውን አጋር መፈለግ ቀዳሚ የዲፕሎማሲያዊ ትኩረታቸውን የያዘ ጉዳያቸው ሆኖ ነበር።
ምንም እንኳን በእስልምናው ኢምፓየር እና በተለያዩ የአውሮፓ ነገሥታት መካከል የተካኼደው ግብግብ ከእዚኽ ዘመን በመቶ ዓመታት ቀደም ብሎ የጀመረ ቢሆንም ፤ ከ1200 እስከ 1400 በአሉት ዓመታት የኃይል ሚዛኑ ወደ እስልምናው ግዛት እያደላ እና ግብግቡ ለአውሮፓዊያን አስጊ የእሚባለው ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረ በመሆኑ ፤ በጣም ጥሩ ክርስቲያን ፣ ትልቅ ግዛት ፣ ኃብት እና ወታደር የአለው ከእስልምናው ኢምፓየር ማዶ የአለ፟ እና አውሮፓዊያን ለእሚያድርጉት ተጋድሎ እገዛ ሊሰጥ የእሚችል ፕሬስተር ጆን (ቀሲስ ዮሐንስ) የእሚባል የክርስቲያን ንጉሥ አለ፟ የእሚለው ንግርት ፤ ፕሬስተር ጆንን ለአውሮፓዊያን ተናፋቂ እና ተወዳጅ የሆነ የክርስቲያን ንጉሥ በማድረጉ ፤ ለሸዋው መንግሥት የውጭ ግንኙነቱን በአዲስ የመጀምር ጉዳይ እጅግ እንዲ ቀልለት የአደረገ ነበር ።
በተነፃፃሪነት ፤ አውሮፓዊያን የእስልምናው ኢምፓየር መንግሥት ፤ በእዚኽ መልኩ እረፍት በእሚነሳቸው በእዚኽ ወቅት ፤ በተለይ ቀሲስ ዮሐንስ ወይንም ፕሬስተር ጆን የኢትዮጵያ ነጋሢ ነው ተብሎ ከተደመደመ ወዲኽ ፤ የሸዋው መንግሥት ከሙስሊም ሱልጣኔቶች ጋር በተደጋጋሚ ለምዕተ ዓመታት በአደረገው ጦርነት ፤ ሱልጣኔቶቹን ኹሉ አሸንፎ ፤ በስተመጨረሻም እ.አ.አ. በ1400 ዓ.ም. አከባቢ የዘይላን ወደብ ተቆጣጥሮ እና የግዛቱ አካል አድርጎ ፤ የወቅቱ ሱልጣንም በእዚኽ በደረሰበት ሽንፈት ህይወቱን አጥቶ ልጆቹ ተሰደው የመን የገቡበት ኹኔታ ነበር ።
ይኽን ኹኔታ ፤ ታደሰ ታምራት የሐገር ውስጥ እና የውጭ የወቅቱ የታሪክ ድርሳናትን አጣቅሶ እንደ እዚኽ አስቀምጦቷል ፦
“ ንጉሥ ዳዊት[4] ራሱ ጦሩን እየመራ ከአንድ ግዜ በላይ ወደ አዳል ገብቷል ። በመጨረሻው ግጥሚያም ሰዓድ አዲን እ.አ.አ. በ1402/03 ዓ.ም ፤ በንጉሡ ወታደሮች እግር በእግር እስከ ዘይላ ተሳዶ እዝያው ተይዞ ተገድሏል. … ሰዓድ አዲን ከተገደለ በኋላ ፤ ልጆቹ ወደ ምድረ አረብ እንዲሰደዱ በመገደዳቸው እነ እርሱ ከተሰደዱ በኋላ ፤ ክርስቲያኖች አዳልን ተቆጣጠረው የበላይነታቸውን አስፍነው ነበር ። … ማክሪዚ ልጆቹ ምን ያኽል ግዜ በአረብ ምድር እንደ ሰነበቱ አይናገርም ። ነገር ግን የክርስቲያኖቹ የበላይነት ፤ … ለ20 ዓመት እንደ ቆየ ይናገራል ። “
“King Dawit himself led his army into Adal on more than one occasion. In the final encounter Sa'ad ad-Din was pursued by the king's troops as far as Zeila where he was captured and killed in 1402/3… When Sa'ad ad-Din was killed, his sons had been exiled in Arabia, and Christian superiority was assured in Adal which was occupied for a time… Maqrizi does not specifically state how long they had remained in Arabia. But he says that the Christian superiority lasted for twenty years …. [98]“
ይኽም ብቻ ሰአይሆን ፤ የኢትዮጵያ ነገሥታት ይኽንን ተደጋጋሚ ሽንፈት አከናንበው በስተመጨረሻም ፤ ከዘይላ ራሱ ያስወጡዋቸው ሱልጣኖች ፤ የራሳቸው የነብዩ መሐመድ ቤተ ዘመዶች ናቸው ተብሎ ስለ እሚታመን ፤ እያሸነፉ ያሉት ጭፍራውን ሰአይኾን ዋናውን ነው በእሚል ፤ አውሮፓዊያን የኢትዮጵያ ነገሥታት ከእስልምና ጋር ለእሚደረገው ትግል ይአግዛሉ የእሚለውን እምነታቸውን የበለጠ አጠናክሮታል ። ስለ እዚኽ ጉዳይ አንድሪው ከርት የተባለው ተመራማሪ እንደ እዚኽ ይላል ፦
“እ.አ.አ. በ1448 ዓ.ም. ለፈረንሳዩ ቻርልስ ሰባተኛ የሮድሱ ሹም ፤ ከህንድ (ኢትዮጵያ ለማለት ነው) ቀሳውስት የመጣ ዘገባ በማለት ' የህንዱ ቀሲስ ዮሐንስ ፤ ጎረቤቶቹ በሆኑት ሳርኪንሶች (ሙስሊሞች) ፤ ከኹሉም በላይ ደግሞ የመሐመድ የልጅ ልጆች ነን የእሚሉትን ፤ ከመካከላቸው ብዙዎቹን በመግደል ፤ የኃይሉን ታላቅነት አሳይቷል' - የመሐመድ የልጅ ልጆች የእሚለው ፤ የአዳሉ ሱልጣኔት መሪዎች የሆኑት ወላስማዎች ቁሬሽ ነን ከማለታቸው ጋር የእሚገናኝ ነው ። ሹሙም ፤ ቀሲስ ዮሐንስ ፤ በቅርቡ ግብፅን ብቻ ሰአይሆን አረብ ምድርን እና ሶሪያን ያርበደብዳል ብሎ እንደ እሚገምት ተናግሯል ።”
“In 1448 the grand master of Rhodes wrote to France’s Charles VII, passing on reports from Indian (i.e. Ethiopian) priests that ‘Prester John of the Indies has greatly demonstrated [his powers] over the Saracens, his neighbors, and has killed many among them, above all those who claim descent from Muhammad’ – this last phrase an apparent reference to the Quraishi descent claimed by the Walashma rulers of Adal. The grand master offered the prediction that Prester John would soon overwhelm not only Egypt but Arabia and Syria as well. [106]“
በእርግጥም ፤ በአንድም በሌላ ምክንያት ፤ በእዚኽ ዘመን የነበሩ የሙስሊም ገዢዎች ለኢትዮጵያዊያኖች የነበራቸው አክብሮት አውሮፓዊያንን ኃሳብ ሳይስብ አይቀርም። ለምሳሌ ፦ ሳላዲን የእሚባለው የሙስሊም ገዢ ፤ ኢየሩሳሌምን ከክሩሴደርሶቹ ከአስለቀቀ በኋላ ፤ የቅዱሱን መቃብር ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያዊያኖች ነው የሰጠው ይባላል ፣ እንዲኹም ከሌላው ክርስቲያን ኹሉ ኢትዮጵያዊያኖች በኢየሩሳሌም የበለጠ ‘ነፃነት’ ነበራቸው የእሚሉ የታሪክ ዘገባዎች አሉ።
እንደ ገናም ኢትዮጵያዊያኖች ቀጥታ በመዝመትም ሆነ ፤ የአባይን ፍሰት ማስቀየስ ይችላሉ በእሚል ፤ የግብፅ ካሊፎች ላይ የእሚያሳድሩት ተፅዕኖም የኢትዮጵያ ክርስቲያን ነገሥታትን በአውሮፓዊያን ዘንድ እንዲከበሩ አድርጓል ።
እንደ ታደሰ ታምራት በቀዳማዊ ንጉሥ ዳዊት የንግሥና ዘመን (እ.አ.አ. ከ1389 – 1412 ዓ.ም.) ለምሳሌ ፦ የግብፁ ካሊፍ በግብፅ የእሚገኙ ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ ፤ ንጉሥ ዳዊት ግብፅ ላይ ዘምቶ ካይሮ ለመግባት አስዋን ድረስ እንደ ተጠጋና ፤ የግብፁ ካሊፍ አማላጅ በላከው በጳጳስ ልመና እንደ ተመለሰ ፤ በሐገር ውስጥ በንጉሥ ዳዊት ገድል ፤ ከውጭ ሐገር በ15ኛው ክፍለ ዘመን የግብፅ ታሪክ ጸሐፊ ከነበረው ማርኪዚ እና የእዚኹ ዘመን ናፖሊ የእምትባለው የጣሊያን ከተማ ነዋሪ በሆነው ፒየትሮ መጽሐፍ እንደ ጠቀሰ ይናገራል ፦
“ብዙ ባህላዊ የዘገባ ሰንሰለቶች አሉ ንጉሥ ዳዊት የመምሉክ ግብፆች ላይ ሊዘምት እንደ ነበር የእሚናገሩ ። ይኽ ታሪክ ግን በባህላዊ ዘገባዎችም ብቻ የተነገረ ሰአይሆን ፤ በፒየትሮ እና ማርኪዚም በተቀራራቢ አኳኋን የተዘገበ ነው ። አንዳንዶቹ ባህላዊ ዘገባዎች ፤ ልክ እንደ ፒየትሮ የንጉሡ ግብ ኢየሩሳሌም መድረስ ነበር ይላሉ ። ማርኪዚም እንደ እሚለው የሐገር ውስጥ ባህላዊ ገድሎቹ ንጉሡ አስዋን ደርሶ ነበር ። … አንዱ ወግ ፤ ዳዊት ወደ ኋላ እዲመለስ የግብፁ ሱልጣን ጳጳስ በአማላጅ እንደላከና በአስዋን እንደ ተገናኙ ይዘግባል ...”
“A whole cycle of traditional accounts is available about Dawit's attempt to attack Mamluk Egypt, and, freed from their hagiographical trappings, these traditions essentially agree with both Pietro and Maqrizi. Like Pietro some of them indicate that the King's aim was to reach Jerusalem. Maqrizi's point that the Ethiopian army had reached the territory of Aswan is also reported by the Ethiopic traditions …. One version has it that the Egyptian Sultan sent the Patriarch to persuade Dawit to march back, and they met at Aswan... [98]“
ከእዚኽ በኹለተኝነት ፤ የሮማው ካቶሊክ ቤተክርስትያን ጳጳሶች ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ቁጥር 18 ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋሪያው ጴጥሮስ ፦
“እኔም እልኃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።”
ብሎ የአለው ፤ ሐዋሪያው ጴጥሮስ የመጀመሪያው የዓለም ዓቀፏ (Catholic) ቤተክርስቲያን መሥራች እና ጳጳስ ይሆናል ለማለት ነው ብለው ስለ እሚረዱት ፤ በዓለም ላይ ብቸኛዋ እና እውነተኛዋ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ፤ በሮም ያለቸው እና በሐዋሪያው ጴጥሮስ የተመሠረተችው ነች ብለው ስለ እሚያምኑ ፤ በዓለም ላይ የአሉ፟ እና በሮም መንበር ስር የእማይተዳደሩትን አብያተ ክርስቲያናት ፤ ወደ ብቸኛዋ “ትክክለኛዋ ወይንም እውነተኛዋ” የሮም ቤተ ክርስቲያን የመመለስ ፕሮግራም ስለ ነበራቸው ፤ የኢትዮጲያን ዖርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፤ ከነበረችበት የአሌክሳንደሪያ መንበር አላቀው በሮም ስር የእምትተዳደር ለማድረግ መፈለጋቸው ፤ አውሮፓውያን ከክርስቲያን ኢትዮጵያ ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዲያደርጉ የእሚገፋቸው ሌላ ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል ፦
“እ.አ.አ. በ1439 ዓ.ም. ጳጳሱ ፤ ፍራ አልቤርቶ ዳ ሳርቴኖን መለዕክተኛ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ፣ ህንድ ፣ ግብፅ እና ኢትዮጵያ ደብዳቤ በመላክ ፤ በእነ እዚኽ ሐገራት የአሉ፟ ቤተክርስቲያኖች ከሮማዋ ቤተክርስቲያን ጋር እንዲዋኃዱ ግብዣ አድርጓል ። ለኢትዮጵያ የተላከውም ደብዳቤ ተደራሽ ሌላ ማንም ሰአይሆን ለንግርታዊው ቀሲስ ዮሐንስ ነው የእሚል ነበር ።”
“In July 1439 the pope had sent Fra Alberto Da Sarteano on a grand voyage to Jerusalem, India, Egypt and Ethiopia with Letters inviting the Churches there to unite with Roman Church. The Letter intended for Ethiopia was addressed to none other than Prester John.” Kurt or Mathew?
እነ እዚኽ ፤ ከእላይ የጠቀስናቸው በሐገር ውስጥ እና ከሐገር ውጭ የነበሩ ኹኔታዎች የሸዋን ነገሥታት ፤ በአክሱማዊያን ዘምን በችልታ የተተወውን የውጭ ግንኙነትን እንደ ገና በአዲስ እንዲ ጀምሩ ኹኔታዎችን አመቻችተውላቸዋል ።
የሸዋው መንግሥት ይኽን አመቺ ኹኔታ ለመጠቀም ያነሳሳው ወይንም የሸዋው መንግሥት በእዚኽ አዲስ ዲፕሎማሲ ለማሳካት የተነሳበት ዋናው ምክንያት ደግሞ ፤ አክሱማውያን ጀርባቸውን የሰጡት የዓለም ዓቀፍ ፖለቲካ ውሎ አድሮ ፤ ኢትዮጵያን ከሌላው ዓለም በመነጠል የፈጠረውን የዕድገት ማነቆ የማንሳቱ ጉዳይ ይደር የማይባል በመሆኑ ነበር ።
ከእዚኽም የተነሳ ፤ የእዚኽ ወቅት የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ዋነኛ ፍላጎት የነበረው ፤ ከተለያዩ የዓለም ሕዝብ ጋር የንግድ ፣ የባሕል ፣ የእውቀት ፣ ወዘተ ፤ ልውውጥ በማድረግ ሐገርን ወደ እሚቀጥለው የእድገት ደረጃ መውሰድ ነበር ።
ምንም እንኳን ለእዚኽ ዘመን ተመልካች ይኽን ታሳቢ የአደረገ የውጭ ጉዳይ ግንኙነት በቀላሉ ሊከወን የእሚችል ቢመስልም ፤ በእዛኽን ወቅት በነበረው የዓለም ዓቀፉ ፖለቲካ ምክንያት ፤ በተለይ ለኢትዮጲያ በቀላሉ የእሚገኝ ነገር አልነበረም ።
ለእዚኽም ዋነኛ ምክንያቱ ፤ የእስልምና ኢምፓየር እንደ ውቂያኖስ በእዛን ዘመኑ ዓለም መሐል ላይ በመንሰራፍት ፤ በሰሜን ምዕራብ ፡ አውሮፓን ፣ በደቡብ ፡ ኢትዮጵያን እና በስተ ምሥራቅ እንደ ቻይና እና ህንድ የአሉ፟ የሩቅ ምሥራቅ ሐገራትን ፤ እርስ በርሳቸው በየብስም ሆነ በባሕር በቀጥታ መገናኘት እንደ አይችሉ ፤ የየብሱንም ሆነ የባህሩን የዓለም ዓቀፍ የግኙነት አውራ ጎዳናዎች በመቆጣጠሩ እና በእነዚኽም ዓለም ዓቀፍ ጎዳናዎች ላይ ነፃ እንቅስቃሴን በመከልከሉ ነው ።
እንደ እሚታወቀው ፤ እስከ 15ኛው ምዕተ ዓመት መጨረሻ አከባቢ ፤ የዛሬዎቹ ላቲን አሜሪካ ፣ ሰሜን አሜሪካ ፣ አውስትራሊያ ፤ በእዚያኽን ወቅት ራሳቸውን የዓለም ሕዝብ ነን በእሚሉት ፤ የአውሮፓ ፣ የአፍሪካ እና የኤስያ ነዋሪዎች ፤ መኖራቸውም የእማይታወቅ ነው ።
ከእዛኽም በተጨማሪ ፤ ቫስኮ ደጋማ እ.አ.አ. በ 1497 ዓ.ም. በባሕር ላይ በምዕራብ አፍሪካ ዞሮ ወደ ምሥራቅ አፍሪካ በኋላም ከደቡብ ምሥራቅ አፍሪካ ወደ ህንድ እስኪደርስ ድረስ ፤ የእዛኔው አፍሪካን ፣ አውሮፓን እና ኤስያን ብቻ የእሚያካትተው ዓለም ፤ ብቸኛው የባሕር ላይ መገናኛ መንገዱ ፦ ከሜድትራንያን በሱዌዙ ወሽመጥ በየብስ ማጓጓዣ ወደ ቀይ ባሕር ፤ ከእዛም ከቀይ ባሕር በየመን እና ኢራን ወደቦች ጥግ ጥግ ወደ ህንድ ብሎም ወደ ቻይና ነበር ።
ምስል 7 ፡ የጥንቱ የዓለም የባሕር ላይ ንግድ ብቸኛ ጎዳና ።
በየብስ ደግሞ በዋናነት ፦ ከቻይና እስከ አውሮፓ በተዘረጋው በተለምዶ የሲልኩ ጎዳና በእሚባለው የንግድ መስመር ነበር ፤ የወቅቱ የዓለም ወይንም የአፍሪካ ፣ አውሮፓ እና ኤስያ ሕዝብ ይገናኙ የነበረው ።
እስልምና ከመካ ተነስቶ መላው የአረቢያን ፔኒንሱላ ፣ ከእዛኽም ሰሜን አፍሪካን ፣ ቱርክ ፣ ሌቫንት ፣ የዛሬዎቹን ኢራን ፣ ኢራቅ ፣ ፓኪስታን ፣ አፍጋኒስታን ፣ ወዘተ ፤ ሲቆጣጠር ግን በእዛኽን ወቅት የነበረውን ዓለም ከመሐል ቦደሰው ማለት ይቻላል ። በእዚኽም ፤ የእዛኽን ወቅቱ ዓለም መሐል ላይ በመሆን ፤ የየብስና እና የባሕር ላይ ብቸኛ የንግድ መንገዶችን ተቆጣጥሮ ፤ ከእስልምና ውጭ የአሉ፟ትን ሐገራት እርስ በእርስ እንደ አይገናኙ ፤ የግንኙነት መረቡን በጥሶታል ።
ለእዚኽም የዓለም ዓቀፍ ግንኙነት መበጠስ ምክንያቱ ደግሞ ፤ እስልምና አከባቢውን መቆጣጠሩ ብቻ ሰአይሆን ፦ የወቅቱ እስልምና ዓለምን በሰይፍ ማስለም እንደ አጀንዳ ይዞት የእሚንቀሳቀሰው ጉዳይ በመሆኑ ፤ ይኽን በሰይፍ ኃይል የማስለም አካኼድ የመከላከል አቅም የአለው መንግሥት የነበራቸው ፤ የአውሮፓ ፣ የኢትዮጵያ ፣ የቻይና እና የተወሰኑ የህንድ ሕዝብ ፤ ከእዚኽ በሰይፍ አስላሚ ኃይል ጋር በአላንጣ ሆነው በመቆማቸው ወይንም ከእስልምናው መንግሥት ጋር ቀጥታ የፖለቲካ ጠላቶቹ በመሆናቸው ፤ በእስልምናው መንግሥት ቁጥጥር ስር የገባውን ይኽን የባሕር እና የየብስ ጎዳና መጠቀም እንደ አይችሉ ስለ አደረጋቸው ነው ።
በእዚኽም ፤ ኃይማኖትን በሰይፍ የማስፋፋት አቋሙ ከእነዚኽ መንግሥታት ጋር የፖለቲካ ጠላት የሆነው እና ዓለም ዓቀፉን ንግድ የእሚያስተሳስሩ የየብስ እና የባህሩን መንገዶች ተቆጣጥሮ ፤ በእነ እዚኽ መንገዶች ላይ ለእሚደረገው ንግድ የብቸኛ አስተላላፊነት መብትን ለእራሱ የሰጠው የእስልምና መንግሥት ፤ ለወቅቱ የዓለም ሕዝብ ትልቅ የግንኙነት እንቅፋት ሆኖ ነበር ።
ይኽ ኹኔታ ደግሞ ፤ በልማቱ ረገድ ፤ ከሌሎቹ የእዚኽ ወንጀል ተጠቂ የዓለም ሕዝብ በተለየ ኹኔታ ፤ ኢትዮጵያን ያጠቃ ነበር ። ምክንያቱም ፦ ይኽ የእዛኔውን ዓለም መሐል በሞቦደስ ፤ ሰሜን ምዕራቡን ከምሥራቁ ፣ ምሥራቁን ከደቡቡ የለየው የእስልምና ውቂያኖስ ፤ ኢትዮጵያን በእዚኽ በእስልምናው ውቂያኖስ በስተደቡብ የእምትገኝ ‘ትንሽ’ እና ከሌላው ዓለም የተነጠለች የክርስቲያን ደሴት ነበር ያደረጋት ።
አውሮፓዊያኖች ከሌላው ዓለም ቢነጠሉም ፤ እርስ በርሳቸው ለመገናኘት ፣ በሜድትራኒያን ባሕር ላይ የአለውን ንግድ ውስጥ ለመሳተፍ እንደገናም ትልቅ ገበያ በመሆናቸውም ነጋዴው የግድ የእሚፈልጋቸው በመሆኑ ፤ በራሳቸው ለመንቀሳቀስ ቢገደቡም ፤ በዋናነት በሙስሊም ነጋዴዎች አማካኝነት በልውውጥ እና በግንኙነት የእሚገኘውን ጥቅም በእሚጎዳቸው መልክ ያጡት አልነበሩም ።
ቻይና እና ህንድም እንደ እዛው ፤ በጣም ትልቅ ፣ ብዙ ሕዝብ የአላቸው እና ሰፊ የባሕር አዋሳኝ ድንበር የአላቸው በመሆኑ ፤ የእስልምናው ማነቆ ፤ የእንቅስቃሴ ገደብ ቢያደርግባቸውም ፤ ልክ እንደ አውሮፓዊያኖቹ እርስ በእርሳቸው እንደ አይገናኙ ፣ ከብዙው ህዝባቸው የእሚፈልቀውን እውቀት ፣ ልምድ እና ኃብት እንደ አይቀያየሩ የእሚያግዳቸው ነገር አልነበረም ።
የኢትዮጵያ ግን ለየት የአለ ነው ። ምክንያቱም ፦ በእዚኽ ዘመን ፤ በሰሜን ምዕራብ ከሰሜን ሱዳን እስከ ግብፅ እና መላው ሰሜን ምዕራብ አፍሪካ እንዲኹም በሰሜን ምሥራቅ በቀይባሕር እና መላው የአረብ ምድር ፥ ሌቫንት ፥ ኢራን ፥ ኢራቅ በመላው እስልምናን በሰይፍ ማስፋፋት አጀንደው የሆነው የእስልምና ውቂያኖስ ተንሰራፍቶ የነበረባቸው ቦታዎች ስለ ነበሩ እና የእስልምናው ኢምፓየር መንግሥት በእሚከተለው የኃይል ተስፋፊነት ፖሊሲ ምክንያት ኢትዮጵያን እንደ ሌላው ክርስቲያን መንግሥት ፖለቲካዊ ጠላቱ ስለ አደረጋት ፤ በሰሜኑ በኩል ፤ በምዕራቡም ሆነ በምሥራቁ ፤ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት የእማይታሰብ ነው ።
በደቡብ ምዕራብ ሆነ በደቡብ ምሥራቅ ደግሞ መጨረሻው የእማይታወቀው ሰፊው በደን የተሸፈነው የአፍሪካ ምድር እና ይህ ነው የእሚባል የእሚታወቅ ስልጣኔ የሌላቸው በጣም ተዘርዘርው እና ተበታትነው የእሚኖሩ ትናንሽ ኋላ ቀር ሕዝብ መኖሪያ ነው ።
ስለ እዚኽ ፦ አባቶቻችን በዘመነ አክሱም ቀይ ባሕርን ክፍቱን ትተው ወደ ሸዋ በመግባታቸው እና ቀይ ባሕርን ጨምሮ መላው የወቅቱ ዓለም ዓቀፍ የንግድ መስመሮች የተቆጣጠረው ጃውሳው የእስልምና መንግሥት ፤ ኢትዮጵያ በእስልምናው ውቂያኖስ በስተ ደቡብ ከሰለጠነው ዓለም በፍፁም ተነጥላ ፤ የእምትገኝ ‘አናሳ’ የክርስቲያን ደሴት በማድረግ ፤ ከዓለም ዓቀፉ የሰልጣነ ማሕበረሰብ ጋር በመገናኘት የእሚገኙ ብዙ የእውቀት ኃብት ድኃ እንድትሆን በማድረጉ ፤ ጃውሳው የእስልምና መንግሥት የነገሠበት የእስልምና ዊቂያኖስ ፤ ምንም እንኳን በዋናነት የእስልምና እምነት ተከታይ ያልሆነውን መላውን ዓለም ቢጎዳም ፤ የየትኞችም ሐገራት ጉዳት ፤ ይኽ ክስትት የክርስቲያን ደሴት የአደረጋትን ኢትዮጵያ ከጎዳበት ጋር የእሚነፃፀር አይደለም ።
በዘመነ አክሱም የስልጣኔ እኩዮቿ ከነበሩት ወይንም ከሰለጠነው ዓለም ፤ በእስልምና ውቂያኖስ ደቡባዊ ምዕራብ ጫፍ ላይ የክርስቲያን ደሴት እንድትሆን የተደረገችው ኢትዮጵያ ፤ ይኽ ወደ 1,000 ዓመት የቆየ መነጠል ፤ እንደ ማንኛውም የሰለጠነው የዓለም ፤ ‘የነቃ’ ወይንም ለስልጣኔ የተዘጋጀ ሕዝብ ኖሯት ሳለ ፤ በደረሰባት በእዚኽ ማነቆ ፤ በቴክኖሎጂው መስክ በእሚያሳዝን ኹኔታ ኋላ ቀር የሆነችበትን አግባብ ፤ እዮብ ሉዶልፍ ከእዚኽ በታች በተጠቀሰው ጽሁፉ ግሩም አድርጎ ገልፆታል ፦
“ሐበሾች ፤ ብዙም ያልሰለጠኑ እና ኋላ ቀር ሕዝብ ሲሆኑ ፤ የትምህርት እድል ቢያገኙ ግን ከመላው የአፍሪካ ሕዝብ ይልቅ ንቁዎች እና ማስተዋል የአላቸው ሕዝብ ናቸው … ። የመማር እና ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ጉግት አላቸው ። በእዚኽኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ አከባቢ ፤ የቀደሙት የጀስዊት ቄሶች ወደ አቢሲንያ ሲኼዱ ፤ በሐገሪቱ ነገሥታት እና ሉዕላን ዘንድ በታላቅ በጎነት የተቀበሉዋቸው በሌላ በምንም ሰአይሆን በሳይንስ እና በቴክኖሎጂ እውቀታቸው ነው ። ኹሉንም ዓይነት የውጭ ሐገር ክርስቲያን ሆኖ በሳይንስ እና በቴክኖሎጂ እውቀት ያሸበረቀውን ሰው ይወዱታል ያከብሩታል ። ጎርጎርዮስ[5] ራሱ ለእኔ እንደ ነገረኝ ፤ ከፖርቹጋል ፓትሪያሪክ አንዱ የተለያዩ መጽሐፍትን ተሸክሞ ወደ መኳንንቶች እና ሌሎች ዘንድ ሲታይ ፤ ከንጉሡ አማካሪዎች አንዱ ፤ ‘እነ እዚኽን ኹሉ መጽሐፍት መረዳት በመቻሉ እንዴት ታድሏል’ ብሎ በአድናቆት ሲተነፍስ እንደ ሰማው ነግሮኛል ። በእድሜያቸው የጎለበቱ ብዙ ሰዎች ፤ የላቲን ቋንቋ ልቀትን እና የአለውን ጥቅም ከተነገራቸው በኋላ ለመማር ትልቅ ጉግት አሳይተዋል ። እንዲያውም ለእኔ እንደ እሚመስለኝ ፤ ጎርጎርዮስ ምንም እንኳን እድሜ የገባው ቢሆንም ፤ ረዥም መንገድ ተጉዞ እኔ ጋር ጀርመን የመጣው ፤ እንዲኹም ወጣቱ አካለዋ ወዲያው የተከተለው እና ምንም እንኳን ኤርፈርት እላልኹ ብሎ ፈብረሀር በማለቱ ጀርመን ውስጥ የእሚረዳው አጥቶ ልፋቱ መና ቢቀርም ለሌላ አይመስለኝም ። ስለ እዚኽ ሐበሾቹ የአዕምሮ ንቃቱም ሆነ ትጋቱ አይጎድላቸውም ፤ እድሉ እና እገዛው ብቻ እንጂ ። እነርሱም ረዥም ርቀት መጓዝ አልቻሉም ፤ አውሮፓዊያኖችም በብዙ ችግር ወደ እነርሱ ሐገር እንደ አይገቡ ሆነዋል ፤ በባሕርም ሆነ በየብስ ከመንገዱ አድካሚነት የተነሳ ። በእዚኽ ኹሉ ላይ ቱርኮቹ ገደብ በሌለው ቅናታቸው ለእራሳቸው እና ለኹሉም መሐመዳዊያን (ሙስሊሞች) ሐፍረት በመሆን ወደ ሐበሾቹ የሰላም ሆነ የጦርነት ተክኖሎጂ እንዲገባ አይፈቅዱም ።”
“a Nation, otherwise rude and impolished; so that if they had but the advantages of Education, most certain it is, that the Abyssinians, would prove the most ingenious and understanding people of all Africa; … They are most Covetous after Learning, and desirous of the knowledge of Arts and Sciences. Nor was there any other greater reason of that kindness which was shewed to the Fathers of the Society towards the beginning of this Century, in Abyssinia, but that they were skilled in all sorts of Arts and Sciences, and therefore admired by the King and Princes of the Nation. For they love and reverence all sorts of Foreign Christians that are adorned with the Ornaments of Art and Learning. Gregory related to me, that when the Portuguese Patriarch carried thither a great number of very fair Books, sundry of the Nobility, and among the rest, Tine, one of the King’s Councilors, expressed himself with a Sigh in these words. Oh happy he that can understand all these Books! And many persons of full years, hearing of the Excellency and large use of the Latin Language, have most ardently desired to learn it. And that indeed seemed to me to be the most prevailing reason, why our Gregory though stricken in years, undertook long a journey after me into Germany; and why Acalexa young Abyssinian followed him soon after, though not being understood in Germany where he pronounced Fbrfaher instead of Erfurt he had the ill fortune to lose his labor. Therefore, they neither want ingenuity nor industry, but only Opportunity and Assistance, for they never travel long Journeys. our Europeans are hindered by the difficulties of getting into their Country, and the tediousness of the Journey, whether by Land or Sea: and besides all this the Envy of the Turks joined to their implacable Avarice will not permit them to suffer us to Import our Arts of Peace and War, to their own and the disadvantage of the rest of the Mouhamedeans. [104]“
ስለ እዚኽ ፤ የእዚኽ ዘመኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት ረኃብ የነበረው ፤ የእዚኽን ጃውሳ እጅ ፈልቅቆ ፤ ኢትዮጲያ በመነጠሏ ምክንያት ጎሎባት የነበረውን ይኽንን የእውቀት እና የቴክኖሎጂ ሥራዎች ወደ ሐገር ውስጥ ማስገባትን ታሳቢ የአደረገ ነበር ።
ምንም እንኳን አንዳንድ ቸልተኛ አውሮፓዊ ጸኃፍት ፤ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዋነኛ ማጠንጠኛ የነበረው የአውሮፓን መሳሪያ ማግኘት ነበር ሲሉ ቢታይም ፤ ስረዓት አልበኝነት በነገሠበት የዓለም ዓቀፍ ግንኙነት እና በወቅቱ የኃይል አሰላለፍ ምክንያት በከፍተኛ ኹኔታ በልዩ ጂኦፖለቲክሱ ምክንያት ለተጨባጭ አደጋ የተጋለጠች ኢትዮጵያ የወቅቱ መሪዎች ፤ ዋናው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ትኩረታቸው ፤ ቅቤው የእሚቆረጠው በቢላዋው ነው ብለው ፤ የአውሮፓን መሳሪያ ማግኘት ላይ ማድረጋቸው ብዙ ሊያስደንቅ በአይገባም ፤ የወቅቱ ኢትዮጵያዊያን ከመሳሪያም በአሻገር ሌሎች የስልጣኔ ትሩፋቶችን ለማግኘት ሲጥሩ ነበር።
ከእዚያኽም በአሻገር ፤ ኢትዮጵያዊያኖች እድሉን ነው የአጣነው እንጂ ፤ ትክክለኛውን ምህዳር ከአገኘን እኛም ሌላው ዓለም የደረሰበትን ስልጣኔ በራሳችን መጨበጥ እንችላለን የእሚል እምነት የአላቸው በመሆኑ ፤ ለችግራቸው ፖለቲካዊ መፍትኼ ፈላጊ እንጂ ኢከነሚያዊ ጥገኝነት የእሚፈልጉ አይደሉም ፤ ለእዚያኽም ነው ፤ በዋናነት ራሳችንን የመከላከል እና መብታችን ማስከበር አለብን በእሚል ፤ ቅድሚያ ራሳቸውን ከቦዘኔ መንግሥታት መከላከል ቅድሚያ የእሚሰጡት።
ይኽም በወቅቱ በነበሩት የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች ይዘት በእሚገባ ተንፀባርቋል ። በንጉሥ ዳዊት ቀዳማዊ የንግሥና ዘመን (እ.አ.አ. 1380 - 1412 ዓ.ም.) ፤ 12 ካራት እንቁ እና የተለያዩ ጌጣ ጌጦች ስጦታ ይዞ ወደ ጣሊያን ያቀናው የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ቡድን ፤ ይዟቸው ከተመለሰው ስጦታዎች መካከል ፤ ንጉሡ የጠየቀውን ሞያተኞችንም ያካተተ ነበር ፦
“የሆነው ይኹን ፤ የሉኳን ቡድኑ ጠቀም ያለ ቁጥር የአላ፟ቸው ሰዎች የአሉ፟በት እና በስጦታም 12 ካራት እንቁ ፣ አራት አነሮች ፣ የተለያዩ እንስሳት ቆዳ እና መልካም መዓዛ የአላ፟ቸው የተለያዩ ዕፅዋት ይዞ በመኼዱ በሰሜናዊ ጣሊያን የደስታ ስሜት ለመቀስቀስ በቂ ነበር ። በተጭማሪም ፤ የቬነሱ ሹም በምላሽ የሰጣቸው ስጦታዎች ፤ ሰዓት ፣ መስታወት ፣ ምንጣፍ ፣ የቅዳሴ ልብሶች ፣ የብር መጠጫ እና ግማደ መስቀሉን ያካተቱ ነበሩ ። ከባርቶሊ ጋር ፤ በኢትዮጵያው ንጉሥ ጥያቄ መሠረት ፤ አብረው የተላኩ ጥቂት ሰዓሊያን እና የእደ ጥበብ ሞያተኞች ነበሩ ፤ ከእነ እርሱም ውስጥ አንዱ የጦር መሳሪያ ሰሪ ነበር ። ለ 'ህንዱ' (ኢትዮጲያዊው) አምባሳደርም 1000 ዱካት በመባል የእሚታወቁት የቬነስ የወርቅ ሳንቲሞችም ተፈቅደው ነበር ።”
“Whatever the case, the delegation was sizable and the diplomatic gifts of a pearl of 12 carats, four leopards, animal skins and aromatic herbs were enough to cause a sensation in northern Italy. Furthermore, the doge’s gifts in return included a clock, a mirror, rugs, liturgical vestments, a silver chalice and apparently a fragment of the Holy Cross. Also sent back with Bartoli were a few artists and craftsmen requested by the Ethiopian monarch, one of whom was a maker of arms from Naples. A donation of 1000 ducats was approved as a gift to the ‘Indian’ ambassador. [106]”
እንደ እዚኹም ፤ ከንጉሥ ቀዳማዊ ዳዊት ንግሥና በኋላ በኹለተኝነት ተከትሎ የነገሠው ንጉሥ ይስኅቅ ፤ እ.አ.አ. ከ1414 - 1429 ዓ.ም. በቆየው ንግሥናው ፤ የእሚያደርጋቸው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ኹሉ ማጠንጠኛ ፤ የሳይንስ እና ቴክንሎጂ እውቀቶችን ወደ ሐገር ውስጥ ማስገባትን ታሳቢ የአደረገ ነበር ። በዘመኑ የዛሬዋ የስፔን አካል ከሆነችው እና አራጎን ትባል ከነበረው ግዛት ገዢ አልፎንዞ እንዲኹም ከቢዛንቲየም ጋር የነበረው ግንኙነት ኹሉ ማጠንጠኛው ፤ እንደ ኹሉም የሳይንስ እና የእደ ጥበብ እውቀትን ወደ ሐገር ማስገባትን መዓከል የአደረገ ነበር ። አጼ ይስኃቅ በሐር ኃይል የማቋቋም እቅድም ነበረው ፦
“ … ቤተ መንግሥቱን የእሚያስውቡለት የዕደ ጥበብ ሞያተኞችንም ጠይቋል ። አልፎንዞም ፤ 13 ዋና ሞያተኞችን የያዘ ቡድን ሲልክ ፥ ኢትዮጵያዊቷን ልዕልት እዲያገባ ሊልከው የነበረውን ልጁን በአጋጣሚ ከእነርሱ ጋር ሳይልከው በመቅረቱ እድለኛ ነበር ፤ ምክንያቱም እነ እዚኽ ኹሉ ተጓዦች በጉዞው አስቸጋሪነት ምክንያት ሕይወታቸውን በማጣታቸው ። ከእዚኽ ጋር በተቀራራቢ ግዜ ፤ ምናልባት በይስኃቅ ጥያቄ ፤ ዱክ ዲ ቤሪ ፦ ስፔናዊ ፣ ፍረንሳዊ እና ከናፖሊ ፒየትሮ የእሚባሉ ሰዎችን ያካተተ ልዑክ ልኮ ነበር ፤ ምንም እንኳን በህይወት የተረፈው ፒየትሮ ብቻ ቢሆንም ። ቢትራንደን ዲ ላ ብሮኪውየር የተባለው ጸሐፊ ፤ ከጥቂት ዓመት በኋላ ፒየትሮን ፤ ንጉሥ ይስኃቅ በሐር ኃይል ለመመሥረት እንዲያስችለው መርከብ የእሚሰሩ ሰዎች ከቢዛንቲየም ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ እየሰራ በአለበት በኮስታንቲንፖል አግኝቶት ፤ ኢትዮጵያዊት ሴት አግብቶ በኢትዮጵያ እየኖረ መሆኑን ጽፏል ።”
“... He also petitioned the king for craftsmen to decorate a royal palace. Alfonso did send a party of 13 masters on their way, and he was personally fortunate that he temporised about sending his son to marry an Ethiopian princess, since the return journey was to cost the lives of all the voyagers. Around the same time, perhaps in response to Yeshaq’s entreaties, the duc de Berry had reportedly sent an embassy to Ethiopia consisting of a Spaniard, a Frenchman and a Neapolitan named Pietro, the only one to survive. His story found narration in Bertrandon de la Broquière, who met him in Constantinople a few years later; it included his taking of an Ethiopian wife and his intentions to return with craftsmen from the Byzantine city who could enable Yeshaq to build a fleet. [106]”
እነ እዚኽ ለማሳያነት ቀረቡ እንጂ ፤ የወቅቱ ዲፕሎማሳያዊ ግንኙነት በሙሉ የእሚያሳየው ፤ ይኽኑን ዘመን የአልሻረው የኢትዮጵያዊያን ጥማት ነው ።
በጠቅላላው ፦ ኢትዮጵያ ከረዥም ግዜ መገለል በኋላ ፤ በጭል ጭልታም ቢሆን ፤ በእዚኽ ክፍል በዋናነት ከአውሮፓዊያን ጋር ዓለም ዓቀፍ ግንኙነትን እንደገና ስትጀምር ፤ መጀመሪያ በአክሱማዊያኑ ስህተት በኋላም በእስልምናው ውቂያኖስ እና በውቂያኖሱም ላይ በነገሠው ጃውሳ መንግሥት ምክንያት ከዓለም ዓቀፍ ግንኙነት በመለየቷ ጎድሎባት የነበረው እውቀት እና ሞያ ማግኘትን ታሳቢ የአደረገ ሲሆን ፤ በአውሮፓዊያኖቹ በኩል ደግሞ መጀመሪያ በቀሲስ ዮሐንስ ንግርት በኋላም ፤ ኢትዮጵያዊያኖች በዙሪያቸው ከነበሩ የተለያዩ የሙስሊም ኃይላት ጋር የነበራቸውን ግጭት በበላይነት በመወጣታቸው ፤ ከሙስሊም ኃይሎች ጋር በእሚደረገው ጦርነት ዓይነተኛ ሚና መጫወት ይችላሉ በእሚል ፤ የኢትዮጵያን ወታደራዊ ትብብር ማግኘትን ታሳቢ የአደረገ እና የሮማው መንበር እውነተኛው የዓለም ዓቀፍ ክርስቲያን ማዕከል እኔ ነኝ በእሚል የዓለምን ክርስቲያኖች በሮም መንበር ስር ማድረግ ከመፈለግ የእሚነሳ ነበር ።
ከላይ እንደ አልነው ፤ ከማንኛውም የእስልምና ዕምነት ተከታይ ከአልሆነ ሕዝብ በላይ ኢትዮጵያ የእስልምናው ውቂያኖስ ወይንም ሱናሚ ተጠቂ ብትሆንም ፤ የእዚኽን ውቂያኖስ ታሪካዊ እድገት ስንመለከት ፤ የአክሱም ነገሥታት ፤ ከማንኛውም የዓለም ሕዝብ በላይ ፤ ይኽ ውቂያኖስ ያለ ከልካይ እንዲስፋፋ በመፍቀድ ፤ ከማንኛውም የዓለም ሕዝብ በላይ ተጠያቂዎችም ይመስላሉ ፤ ምንም እንኳን ለእዚኽ ቸልተኝነታቸው መነሻ ምክንያቱ ፤ በመጃመሪያው ክፍል ላይ ለማለት እንደ ሞከርነው ፤ ታሪካዊ ይዘት የአለ፟ው የስረዓት ውድቀት ቢሆንም።
በእዚኽ የታሪክ ክፍልፋያችን የመጀመሪያው ክፍል ላይ እንደ አየነው ፤ በዘመነ አክሱም ፤ እስከ እነ አጼ ካሌብ ዘመን ድረስ ፤ በመላው ቀይ ባሕር እና በምድረ አረቡ ላይ ፤ አክሱማዊያን የበላይ ባለ ስልጣን የነበሩበት ግዜ እንደ ነበር አይተናል ።
አንድ ግዜ ክርስትና ስር ከሰደደ እና መላውን የሰለጠነውን ዓለም ከያዘ በኋላ ግን ይዞት የመጣው የሰብዓዊነት መልዕክት የቀደሙትን መንግሥታት ራሳቸውን በአዲስ መልክ እንዲያዋቅሩ ግድ ስለ አለ ፤ እውቀት ዳብሮ ይኽ አዲስ የውቅር ቀመር እስኪገኝ ድረስ ፤ የአክሱም መንግሥት እንደ ሌሎቹ የክርስቲያን መንግሥታት ከእለት ወደ እለት እየተዳከመ ፤ ለውድቀት ተዳረገ ።
እንደ እምናስታውሰው አክሱማዊያን በቅድመ ክርስትና ፤ በሰፊው ምሥራቅ አፍሪካ እና በደቡባዊ አረብያ ከነበሩት ፤ ቲብስ ፣ ሜሮ ፣ የኃ ፣ ወዘተ ፤ ከተሞች በተለየ በኃይል ልቀው ፤ ራሳቸውን የአከባቢው የፖለቲካ ፣ የኢከነሚ እና የባህል መዓከል የአደረጉት ፤ የእዚኽን ሰፊ አከባቢ የንግድ መስመሮች በመቆጣጠር ፤ በእዚኽ ሰፊ አከባቢ ላይ የእሚደረገውን የባሕር እና የየብስ ንግድ ያለምንም መስተጓጎል እንዲኼድ በማድረግ ነው ።
ነገሥታቱ ክርስትና ይዞ በመጣው መንፈሳዊነት እና ሰብዓዊነት እየተሳቡ የምድራዊውን መንግሥት ጉዳይ ችላ ሲሉት ፤ መንግሥታቸው ከእለት ወደ እለት እየጠበበ እየጠበበ መጥቶ ፤ በስተመጨረሻ በአክሱምም ሆነው መኖር የእማይችሉበት ኹኔታ ተፈጠረ ። ዓለምን ክደን ገዳም እንገባለን ሲሉ እንኳን ፤ በመንግሥት መዳከም ምክንያት የተፈጠረው ስረዓት አልበኝነት ፤ በእየመሸጉበት ‘ገዳምም’ እየገባ አላስመነኩስ አላቸው ።
ሐገር ከሌለ ፣ ነገሥታት የነገሥታትነት ቦታቸውን ጠብቀው ሐገርን ከአልመሩ ፣ መንግሥት በመንግሥትነቱ ከአልቀጠለ ፦ ገዳምም ፣ ቤተክርስቲያንም ፣ ንግድም ፣ ትዳርም ፣ ሳይንስም ፣ እውቀትም ፤ በአጠቃላይ ሰው በሰላም ግዜ የእሚያደርገውን ነገር ማድረግ አይችልም ።
የክርስትናው መልዕክት በፈጠረባቸው መደናገር ኃላፊነታቸውን ሲዘነጉ ፤ ከእላይ እንደ አልነው መንግሥታቸው እየጠበበ መጥቶ ፤ በስተመጨረሻም ከአክሱም ሲፈናቀሉ ፤ እነርሱ በፍትኽ እያስተዳደሩት የነበረውን የወቅቱን ብቸኛውን የዓለም ዓቀፍ ንግድ የባሕር ላይ መንገድ ፤ ክፍቱን አገኘው እና ጃውሳው የእስልምና መንግሥት ተቆጣጥሮት ፤ ለቀጣዩ አንድ ሺ ዓመት የዓለምን ሕዝብ አቆራርጦ ፤ የክርስትና ሰብዓዊነት በፖለቲካው ዓለም ከፈጠረው መደናበር ጋር ተዳምሮ ፤ ከእስልምና እምነት ውጭ የነበረውን ዓለም ፤ የጨለማ ዘመን በመባል ለእሚታወቀው እና አንድ ሺ ዓመት ገደማ ለቆየው ዘመን ዳረገው ።
ይኽ ኹኔታ የአክሱም ነገሥታትን ከሌላው የዓለም ሕዝብ በተለየ ኹኔታ ተጠያቂ የእሚያደርጋቸውም ፤ ምንም እንኳን የአንድ ዘመን ሰዎች ሊጋፉት በእማይችሉት የስረዓት ውድቀት ቢሆንም ለመንግሥታዊ ቸልተኝነት የዳረጋቸው ፤ ቀይ ባሕር ታሪካዊ ደጃቸው በመሆኑ እና ይኽ ደጃቸውም ዓለም ዓቀፋዊ ትልቅ ፋይዳ የአለው በመሆኑ ፤ የባሕር በሩን በተሻለ ኹኔታ ለማስተዳደር ከእነርሱ በላይ ተመራጭ ወይንም ተገቢነት የአለው መንግሥት በአለመኖሩ ነው።
ክርስትናው ይዞት የመጣው መልዕክት መደናገር ውስጥ አስገብቷቸው ፤ አይደለም የዓለም ዓቀፍ ግንኙነታቸውን ፤ በራሳቸው ሐገር በገዳም ውስጥ በሰላም የመኖራቸውን መብት ከከለከላቸው በኋላ ፤ ከአክሱም ወደ ሸዋ ዞረው ፤ ከገቡበት መደናበር በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ወጥተው ፤ እንደ ገና ወደ መንበረ ስልጣን ሲመጡ ፤ በተመቻቸላቸው አዲስ ኹኔታ ፤ የሸዋ ነገሥታት ፤ ከእላይ እንደ አልነው ፤ የቀደመው ስህተታቸውን በማረም ፤ መገናኘት ከእሚችሉት የዓለም ሕዝብ ኹሉ ጋር ለመገናኘት በንቃት ወደ መንቀሳቀስ ገቡ ።
ከእንግሊዝ ፣ ከስፔን ፣ ከፖርቹጋል ፣ ከፈረንሳይ ፣ ከጣሊያን ፣ ከቢዛንትየም ፣ ከህንድ ፣ ከቻይና ጋር ግንኙነት ለማድረግ በተገኘው አጋጣሚ ተጠቀሙ። የእዚኽ ግንኙነት ጅማሮ በተመለከተ አንድሪው ከርት እንደ እዚኽ ይላል ፦
“ለአራጎኑ (በስፔን ውስጥ የእምትገኝ ታሪካዊ ግዛት) ቀዳማዊ ጁዋን ፤ ስፔናዊው ቄስ በአደረገው ጉዞ እ.አ.አ. በ1391 ዓ.ም. ስለ ኢትዮጵያ ካስታወቀው ጀምሮ ፤ የአህጉር አቋራጩ ግንኙነት ተፋጠነ ። እ.አ.አ. በ1400 ዓ.ም. የእንግሊዙ ሔንሪ አራተኛ ፤ 'ለአብሲኒያው ንጉሥ ቀሲስ ዮሐንስ' ፤ ቅዱስ መቃብሩን[6] ለመያዝ በሙስሊሞች ላይ ለመዝመት ትብብር መመሥረትን የእሚፈልግ መሆኑን የእሚገልፅ መንፈስ የአለው ደብዳቤ ጽፎ ነበር ፤ መድረስ አለመድረሱ በአይታወቅም ። ይኽ ከሆነ ከኹለት ዓመት በኋላ ፤ የፍሎረንስ ሰው የሆነው አንቶንዮ ባርቶሊ ፤ ከንጉሠ ነገሥት ዳዊት ቀዳማዊ (እ.አ.አ. 1380-1412 ዓ.ም.) የተላኩ አምባሳደሮችን ይዞ የቬንሱ ገዢ ጋር መጣ ፤ ሰዎቹንም በወቅቱ የነበሩት ጣሊያናዊዮች ' የህንድ ጥቁር ኢትዮጵያዊያኖች ፤ መልካም ክርስቲያኖች' ብለው ገልፀዋቸዋል ።”
“From the time of the journey of the Spanish priest who reported on Ethiopia to Juan I of Aragon in 1391, the pace of the transcontinental intercourse accelerated. Henry IV of England sent a letter to ‘the king of Abyssinia, Prester John’ in 1400, with the intention of forming a crusade alliance against the Muslims and recapturing the Holy Sepulchre, but whether it arrived is not known. Two years later the Florentine Antonio Bartoli returned from Ethiopia with ambassadors sent by nəgusä nägäst (negus, or king of kings) Dawit I (1380–1412) to the doge of Venice, men whom an Italian at that time described as ‘black Ethiopians, of India, good Christians’. [106]“
በእዚኹ ዘመን አከባቢ ኢትዮጲያዊያኖች ከአውሮፓዊያኖች ጋር ብቻ ሰአይሆን ከሩቅ ምሥራቆቹ ከእነ ቻይናም ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለመመሥረት እየጣሩ ነበር ፤ ለምሳሌ ፦ ዘራ ያዕቆብ ወደ ህንድ እና ቻይና የልዑክ ቡድን ይልክ ነበር ፦
“ተጓዡ ፒየትሮ ሮምቡሎ በግዛቱ ወስጥ ፤ እ.አ.አ. ከ1407 እስከ 1444 ዓ.ም. ቆይቷል ። … ከእዛኽም ለስድስት ዓመታት በህንድ እና ቻይና የዘራ ያዕቆብ ተወካይ ነበር ፤ የሜድትራንያኑን ግንኙነት ለማስተባበር ሳይሾም በፊት ።”
“The adventurer Pietro Rombulo had been in the kingdom from 1407 to 1444. …Then for six years he was Zara Yakob’s delegate to India and China before being given charge of the deputation to the Mediterranean. [106]“
ከእነ እዚኽ ኹሉ ፤ የመላው አውሮፓ እና የሩቅ ምሥራቅ የትብብር ማዕቀፎች መካከል ፤ ፖርቹጋሎች ከመላው አውሮፓ ቀድመው በባሕር አሰሳ ትልቅ ውጤት እያስመዘገቡ በመምጣታቸው ፤ ከኢትዮጵያ ጋር በሙስሊሞች ላይ ለማበር የበለጠ ተግባራዊ ትብብር እንዲያደርጉ የእሚያስችላቸው ኹኔታ እየተፈጠረ መጣ ።
በፖርቹጋላዊ አሳሽ ልዑል ሔነሪ ይመራ የነበረው ባህሩን የማሰስ ጥረት ፤ እ.አ.አ. በ 1487 ዓ.ም. የዛሬይቱ ደቡብ አፍሪካ ፤ ኬፕ ኦፍ ጉድ ሆፕ (Cape of Good Hope) ከደረሰ በኋላ ፤ የወቅቱ የፖርቹጋል ንጉሥ ፤ ዳግማዊ ዮሐንስ ፤ በምሥራቅ ደግሞ የየብስ አሰሳ ተደርጎ ቀሲስ ዮሐንስ ጋር እንዲደረስ በእሚል ኹለት ‘ነጭ ለባሽ’ አሳሾች ወደ ቀሲስ ዮሐንስ ላከ ።
አንደኛው አሳሽ ፤ በግብፅ ካይሮ ሲሞት ፤ ኮቭልኃም የእሚባለው ግን እ.አ.አ. በ1490 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሥ ወደ ነበረው ንጉሥ እስክንድር (አሌክሳንደር) ቤተመንግሥት ፤ የፖርቹጋል ንጉሥ ዳግማዊ ዮሐንስን ደብዳቤ ይዞ ደረሰ ፦
“ኮቭልኃም … እንደ ታዘዘው እና በመንገዱ አስቸጋሪነት ሳይበገር ፤ ወደ አብሲንያ በመዝለቅ ፤ በእዚያን ወቅት እ.አ.አ. በ1490 ዓ.ም. በደቡባዊ ሸዋ በነበረው የንጉሡ ቤተመንግሥት ደረሰ ። የፖርቹጋሉንም ንጉሥ ደብዳቤ ለቀሲስ ዮሐንስ ንጉሥ እስክንድር (አሌክሳንደር) አቀረበ …”
“Covilham...So, in pursuance of his instructions, and undeterred by the dangers of the journey, he penetrated into Abyssinia, and presented himself at the court of the Negus, which was then in the Southern Province of Shoa, in the year 1490. He Delivered the king of Portugal's letter to Prester John to King Alexander... [107]“
ኮቭልኃም ፤ ከእዚኽ በኋላ ወደ ፖርቹጋል ያልተመለሰ ሲሆን ፤ እዚኹ ኢትዮጵያዊት ሴት አግብቶ እና ርስት ተሰጥቶት ፤ የተከበረ የቤተ መንግሥት ሰው ሆኖ በመቆየት ፤ ከሰላሳ ዓመት በኋላ እ.አ.አ. በ1520 ዓ.ም. እነ ቄስ አልቫሬዝ ሌላኛው የእዚኽ ዲፕሎማሲዊ ጥረት መልዕክተኞች ሆነው ሲመጡ አግኝተውታል ።
ከእዚኽ በኋላ ፤ በተለይ በፖርቹጋል ነገሥታት እና በኢትዮጵያ ነገሥታት መካከል የእሚደረገው ግንኙነት ሚስጥራዊ በመሆኑ ይኹን ወይንስ በሌላ ብዙም ዝርዝር መረጃ ያልተገኘበት ቢሆንም ፤ ከኮቭሊኃም መድረስ 19 ዓመታት በኋላ ፤ እነ ቫስኮ ደጋማ ህንድ ደርሰው እና ግዛት አቋቁመው ከአበቁ በኋላ ፤ ስማቸው ያልተጠቀሰ የፖርቹጋል መልዕክተኞች ፤ ኢትዮጵያ የስንቅ እና የወታደር እገዛ እንድ እታደርግላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎ ፤ የወቅቱ ንጉሥ ልብነ ድንግል ‘አያት’ ወይንም የአጼ ዘራ ያዕቆብ ባለቤት የነበረችው ንግሥት እሌኒ ፤ በነበራት ስልጣን ፤ ይኽን ጥያቄ ለመመለስ ኢትዮጵያ ዝግጁ እንደ ሆነች እና ይኽንንም እንዲያስረዳ ፤ ታማኝ አገልጋያችን ነው የአለችውን አርመናዊውን ማቴዎስ ከመጡት ሰዎች ጋር ወደ ፖርቹጋል አምባሳደር አድርጋ ላከች ።
ይኽ በንግሥት እሌኒ እ.አ.አ. በ1509 ዓ.መ. የተጻፈ ደብዳቤ ፤ መጀመሪያ በግዕዝ የተጻፈ ሲሆን ፤ በኋላ ላይ በታሪክ አጥኝዎች ወደ ላቲን እና ጀርመንኛን ጨምሮ የተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ሲቀርብ ቀይቶ እንደ https://www.hadiyajourney.com ስቴፈን ሪተር (Stefan Ritter) በእሚባል የጀርመን ሚስዮናዊ ከጀርመንኛ ወደ እንግሊዝኛ የተመለሰውን ትርጉም ፤ እኔ የእንግሊዝኛውን ትርጉም ወደ አምህርኛ መልሼ ኹለቱንም ከታች አስቀምጨአቸዋለሁ ፦
“ከንግሥት እሌኒ ፥ የኢትዮጵያ ንግሥት ነገሥት ተወዳጁ ዮሐንስ (ፕሬስተር ጆን ለማለት ይመስላል ፕሬሸስ ጆን የአሉት ንግሥቲቱ) ዳዊት (ዳግማዊ ዳዊት) አያት ፥ ለ ኢማኑኤል (ቀዳማዊ ማንዌል) ፥ የፖርቹጋል ንጉሥ ፥ ወዘተ ። ተጻፈ በ1509 ዓ.ም. (እ.አ.አ.) ።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ ፤ በአንድነት ሦሥትነት አንድ አምላክ ፡ ከድንግል ማሪያም በቤትሔልሔም ከተወለደው ከጌታችን እና ከመድኃኒታችን (አዳኛችን) ከኢየሱስ ክርስቶስ ፦ ሰላም ፣ ምህረት እና በረከት ፤ ለባህሩ ገዢ ፣ የዱሩ እና የከኃዲዎቹ ሙር [ሙስሊሞች] ባለ ድል ለሆነው ለተወደደው ወንድማችን እና ለተከበረው የክርስቲያን ንጉሥ ኢማኑኤል ይድረስ ።
የአዳኛችን ክርስቶስ አራቱ ወንጌላዊያን ፤ ማለትም ፦ ቅዱስ ዮሐንስ ፣ ሉቃስ ፣ ማርቆስ እና ማቴዎስ ፤ በቅድስናቸው እና በፀሎታቸው ያድኑህ ፤ በጻድቃን ፀሎታቸው እግዚአብሔር አምላክ ይባርክህ ፥ በጠላቶችህም ላይ ድል ይስጥህ ፥ መንግሥትህን እና ግዛትህን በወርዱም በስፋቱም ያብዛልህ ።
የተወደድኽ ወንድም ሆይ ፤ ከታላቁ እና ከከበረው ቤተ መንግሥትህ ዘንድ ፦ ቄስ ነኝ የእሚለው ዮሐንስ እና ዮሐንስ ጎሜዝ (ጆዓ ጎሜዝ) ተብሎ የእሚጠሩ ሰዎች ወደ እኛ ወጥተው የወታደር እና የስንቅ እገዛ ከእኛ ጠይቀዋል ።
በእዚኽም ምክንያት ነው ፤ እኛን በማገልገል ወዳጃችን የሆነውን ማቴዎስን ስለ እኛ ሆኖ እንዲደራደር የላክነው ። ስንልከውም ፤ ወደ ኢየሩሳሌም ቀሳውስትን ስንልክ በእሚባርክልን በአቡነ ማርቆስ ፈቃድ ነው የላክነው ። እርሱም የእኛ እና በግዛታችን ኹሉ ውስጥ ለአሉ፟ ኹሉ የጋራ አባታችን እና በክርስቶስ እና በቅድስት ሥላሴ ለሆነው እምነት አምድ ነው ። እርሱም ፤ በእኛ ትዕዛዝ ፤ በህንድ ሐገር በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአለ፟ው እምነት እየተጋደለ ለእሚገኘው ታላቁ መሪ (ያም ማለት ፦ የፖርቹጋሎቹ መሪ) ፤ የእሚያስፈልግ ከሆነ ፤ ስንቅ እና ወታደር ለመላክ ዝግጁ መሆናችንን አመልክቶታል ።
ከአንዳንድ ሰዎች ላይ እንደ ሰማነው በካይሮ የአለ፟ው ሉዕል ፤ (እኛም እርግጡን እንደ እምናውቀው) ከሠራዊትህ መሪዎች (በህንድ ሐገር ውስጥ ካሉህ) የደረሰበትን በደል እና ጉዳት ለመበቀል ፤ በአንተ ላይ ብዙ መርከቦች ያአሉ፟ት ጦር እንደ ሰበሰበብህ ሰምተናል ።
ስለ እዚኽ ፤ እግዚአብሔር በቅዱስ ቸርነቱ ፤ አረማውያኑን ኹሉ በቀንበሩ ስር እስክታመጣ በእየ እለቱ ይባርክህ ። እነ እዚኽ አረማዊያን የእሚሉክብህን ጦር የእሚቃወሙ ወታደሮች እንልክልኃለን ።
ወደ ቅዱስ መቃብር[7] የእሚኼዱትን ስጦታዎች እና መስዕዋቶች በእነ እዚኽ ውሾች ከእዚኽ በኋላ እንደ አይመዘበር ፤ እንዲኽ የአሉ፟ትን ሙሮች እና አረማውያን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት እንዲያግዙህ ፤ እነ እዚኽ የእምንልክልኽ ወታደሮች ፤ ባብ አል ማደብ በእሚባለው በሞካ ጥበት ወይንም አንተ ከፈልግኽ በጁዳኽ (ጅዳ?) ወደብ ወይንም በቶር (ቱር?) ሆነው ሊጠብቁ ይችላሉ ።
ሰዎች እንደ እሚሉት ፤ ክርስቶስ እና እናቱ ማሪያም በመጭረሻው ዘመን ከፍራንኮቹ ምድር (አውሮፓ) ፤ አረማዊያኖቹን እና ሙሮቹን ፈፅሞ የእሚያጠፋ ንጉሥ ይነሳል ብለው በአሉት መሠረት የሰጡት ተስፋ የእሚፈፀምበት ዘመን ደርሷል ። ክርስቶስ ለብፅዕት እናቱ ያመለከታት ቀን ደርሷል ።
ከእዚኽ በተጨማሪ ፤ ተደራዳሪያችን የእሚነግራችሁን ማንኛውንም ነገር ከእኛ ከእራሳችን እንደ መጣ አድርጋችሁ ውሰዱት ። ማቴዎስ በቤተ መንግሥታችን አንደኛ ደረጃ ከእሚባሉት ሰዎች በመሆኑ ነው ወደ እናንተ ልእንልከው የወደድነው ። ይኽን መልዕክት እናንተ እኛ ጋር በላካችኋቸው ሰዎች እጅ ልእንልከው ነበር ፤ ነገር ግን መልዕክቱን እኛ እንደ እምንፈልገው አድርገው አያቀርቡት ይሆናል ብለን ፈራን ።
በተደራዳሪያችን በማቴዎስ እጅ መስቀል ልከንላችኋል ። መስቀሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም ተሰቅሎ ከነበረበት ግማድ ተወስዶ የተሰራ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም ። ይኽ የመስቀሉ ግማድ ለእኛ ከኢየሩሳሌም የመጣልን ነው ።
ከግማዱ ላይ ተወስዶ መስቀል እንዲሰራ አዘን ፤ አንደኛው እዚኽ ከእኛ ጋር ሲቀር ፣ ሌላኛውን ተደራዳሪያችን ለእናንተ እንዲያደርሰው ሰጥተነዋል ።
ሴት ልጆቻችሁ የእኛን ወንድ ልጆች እንዲያገቡ ከፈለጋችሁ ወይንም ወንድ ልጆቻችሁ የእኛን ሴት ልጆች እንዲያገቡ ከፈለጋችሁ ፤ ይኽ በእኛ ዘንድ በደስታ ይኹን የእሚባል እና ለኹለታችንም ጠቃሚ ይሆናል ። ከረዥም ግዜ ጀምሮ በእኛ በኩል ከእናንተ ጋር የትዳር ትስስር ዛሬም ቢሆን ወደፊትም የእምንፈልግ በመሆኑ ፤ ይኽ ከሆነ በመካከላችን የወንድማማችነት ህብረት መጀመሪያ ይሆናል ።
በመጨረሻም ፤ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እና የቅድስት እመቤታችን ፥ የድንግል ማሪያም ፤ ድህነት እና ፀጋ ለወንዶች እና ሴት ልጆቻችሁ እንዲኹም ለመላው ቤተሰባችሁ ይብዛ ። አሜን!
በተጨማሪም ፤ በጋራ ሆነን ዘመቻ እንድ እናደርግ እና ወታደራዊ ትብብር እንድ እናደርግ ከፈለጋችሁ ፤ የቅዱስ እምነታችንን ጠላቶች በሙሉ ሊያጠፉ የእሚችሉ (በእግዚአብሔር እርዳታ) ጦር እንደ አለን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን ። ሆኖም ግን ፤ ግዛታችን እና ምድራችን የባሕር ደጅ የሌላት ዝግ ነች ።
እኛ በባህሩ ላይ ኃያል አይደለንም ፤ እናንተ ግን (ክብሩ ለእግዚአብሔር ይኹንና) በባህሩ ላይ ወደር የሌለው ኃይለኞች ናችሁ ። በህንድ የፈፀማችሁት ገድል የተለመደ ሰአይሆን አስገራሚ ተግባር ነው ። አንድ ሺ መርከብ ማዝመት ከፈለጋችሁ ፤ ለእዚኽ የመርከብ ቅፍለት የእሚያስፈልገውን ስንቅ እና ሌላውን ማንኛውንም ነገር አትረፍርፈን ማቅረብ እንችላለን ።”
“Letter from Helena (Elleni), the grandmother of David [Daawit II], the Precious John,
the Emperor of Ethiopia, to Emanuel [Manuel I], king of Portugal, etc. written in AD 1509
In the name of God the Father and the Son and the Holy Spirit, one God in three persons: hail [well-being], mercy and blessings of our Lord and Savior Jesus Christ, the Son of the Virgin Mary, born in Bethlehem, upon our beloved brother, the Most Christian King Emanuel, the ruler of the sea, the victor of the wild and infidel Moors [Muslims]. The Lord God bless you, grant you victory over your enemies, expand your realm and dominions far and wide and stretch them out by the pious prayers of the messengers of Christ the Redeemer, namely the four Evangelists, St. John, Luke, Mark and Matthew, whose sanctity and prayer may save you.
Dear brother, we inform you that two messengers from your great and important court have come to us – namely, John, who called himself a priest, and John Gomez [João Gomes] – and that they requested provisions and soldiers from us.
This is why we send our negotiator Mateus, a friend in our services. We send him with the permission of the Patriarch [Metropolitan] Marcus, who blesses us when he sends clergymen to Jerusalem. He is a father to us and all our dominions, a pillar of faith in Christ and the Holy Trinity. On our order, he sent a letter to your great leader of those who contend for the faith in our Savior Jesus Christ in India, to signify to him [i.e., the leader of the Portuguese] that we are ready to send supplies and soldiers if required.
We heard some people mentioning that the prince in Cairo assembles a large fleet against your forces – surely, to take revenge for the injustice and damage which he (as we truly know) often suffered from the leaders of your army (which you have in India).
Therefore, may God in his sacred kindness grant you day by day his blessing to finally bring all unbelievers entirely under the yoke. We will send troops against the incursions of those unbelievers.
The troops shall wait at the Straits of Mecha [Mokka], which is Bab El Mandeb [Baab al-Mandab], or – if you prefer – at the port of Judah [Jidda?] or Thor [Toor?], so that you will finally destroy and eliminate this type of Moors and the infidels from the face of the earth, so that the gifts and offerings that are brought to the holy grave [in Jerusalem] no longer be devoured by these “dogs”.
The promised time has arrived which – as people say – has been foreseen by Christ and his mother Mary when they predicted that during the last days a certain king will rise from the Frankish areas [Europe] who will destroy the entire race of the barbarians and Moors. The time which Christ has predicted to his Blessed Mother has arrived now.
Furthermore, whatever our negotiator Mateus will tell you, do receive it as if it would come from ourselves, and do believe him.
Mateus belongs to the first-rate people at our court, and for this reason we wanted to send him to you. We would have liked to entrust this [message] to your messengers whom you have sent here, but we feared that our affairs would not made known according to our wishes.
Through our negotiator Mateus we send you a cross. There is no doubt that it has been made from a fragment of the wood to which our Savior Jesus Christ had been crucified in Jerusalem. This fragment of the sacred wood was brought to us from Jerusalem.
We order to make from it two crosses, one of which remains with us, and the other one we have given to our negotiator to deliver it to you. The wood is black in color and hangs on a tiny silver ring.
If it pleases you to either have your daughters marry our sons or to have your sons marry our daughters, then that will be very appreciated by us and be helpful for both of us. It will be the beginning of a fraternal bond among us, since we (at least) long [desire] to form a marital alliance with you both in the present state of things as well as in the future.
Finally, we express our wish that the salvation and grace of our Savior Jesus Christ and our Holy Lady, the Virgin Mary, extends to you as well as to (your) sons and daughters and your whole house. Amen.
In addition, we inform you that if we wish to wage wars and lead armies together, we will have enough armed forces to destroy (with God’s help) all the enemies of our holy faith. However, our empires and dominions are landlocked so that we have no access to the sea.
We are not a naval power, whereas you of all have (praise be to God) the strongest power at sea. Jesus Christ may help you. The deeds you accomplished in India are truly admirable rather than customary. If you want to arm 1000 ships, we will provide in abundance the provisions and everything else that is needed for this fleet.”
ይኽ የንግሥት እሌኒ ደብዳቤ በእሚጻፍበት ፤ በ16ኛው መዕተ ዓመት መጀመሪያ ላይ ፤ ክርስቶፈር ከለምበስ እ.አ.አ. በ1492 ዓ.ም. ዓለም ክብ ነች እና ወደ መዕራብ በመጓዝ ተመልሶ ምሥራቅ (ህንድ እና ቻይና) መድረስ ይቻላል በእሚል አዲስ የመልከዓ ምድር ግንዛቤ በመመራት ፤ በስፔን ነገሥታት ድርጎ ወደ ምዕራብ በባሕር በአደረገው ጉዞ የዛሬዎቹን ሰሜን እና ደብቡ አሜሪካ ‘ለመጀመሪያ ግዜ’ በማግኘቱ ፤ እንዲኹ ቫስኮ ደጋማ ደግሞ ከስድስት ዓመት በኋላ እ.አ.አ. በ1498 ዓ.ም. በምዕራብ አፍሪካ ዞሮ ፤ ከምሥራቅ አፍሪካ ወደቦች ተነስቶ ህንድ በመድረሱ ፤ እነ እዚኽ ክስተቶች ፤ ይኽ አዲስ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ፖለቲካ ተመስርቶበት የነበረውን የወቅቱን የዓለም ዓቅፍ ግንኙነት ይዘት በመሠረታዊነት ቀየሩት ።
ከእላይ እንደ አልነው ፤ ከሙስሊሙ ዓለም ውጭ ፤ ቢያንስ ከ11ኛው ምዕተ ዓመት አንስቶ እስከ 15ኛው ምዕተ ዓመት ድረስ የነበረው ዋነኛው የጋራ ፖለቲካዊ ግብ ፤ የእስልምናው ውቂያኖስ ኢየሩሳሌምን ጨምሮ የእዛን ዘመኑን ዓለም መሐል ተቆጣጥሮ ወይንም የወቅቱን ዓለም ኃይማኖታዊ እና ኢከነሚያዊ መዓከል ተቆጣጥሮ ፤ ሙስሊም የአልሆነውን የዓለም ማሕበረሰብ ኃይማኖታዊ እና ኢከነሚያዊ ነፃነቱን ከማፈኑ በተጨማሪ ፤ ይኽን የዓለምን መካከለኛ አከባቢ በመቆጣጠር የአካበተውን ኃብት እና አቅም በማስተባበር ፤ የቀረውን ዓለም በኃይል ሱናሚ ለማጥለቅለቅ የጋረጠውን አደጋ ማስወገድ ነበር ።
አንድ ግዜ ግን ፤ አውሮፓዊያን በተለይም ፤ ስፔን እና ፖርቹጋል ፤ በእነዚኽ አዲስ የባሕር ላይ መንገዶች ተጠቅመው ፤ ተዝቆ ‘የእማያልቅ’ የኃብት ምድር የሆኑት አሜሪካ እና ህንድ ሲደርሱ ፤ የወቅቱ አውሮፓዊያን የውጭ ግንኙነት የትኩረት አቅጣጫ ብቻም ሰአይሆን የዓለም ታሪክ በመሠረታዊነት ተቀየረ ።
ይኽም በፍፁም ያልተጠበቀ የፖርቹጋሎች እና የስፔኖች ትልቅ ስኬት ፤ የወቅቱን የትኩረት አቅጣጫ እና የፖለቲካ ኃይል ስሌት በመሠረታዊነት በመቀየሩ ፤ ኢትዮጵያ እየተፈለገችበት የነበረውን ምክንያት እርባናቢስ በማድረግ የድርድሩን መልከዓ መድር ለኢትዮጵያ በማይበጅ መልኩ ቀየረው ።
ምን አልባት ፤ በእዛኽ ወቅት የፖርቹጋል እና የስፔን ፤ በእዚኽ መልኩ ወደ ምሥራቅ እና ምዕራብ መዘርጋት ፤ የመጨውን ብቻ ሰአይሆን የነባራዊውን ዓለም የኃይል ሚዛን እንዴት እንደ አዛባው ሊያሳየን የእሚችለው ፤ ከአንድ ሺ ለአላነሱ ዓመታት የአውሮፓዊያን የስልጣኔ መዓከል ሆና የቆየችውን ሮም ፣ የአውሮፓ ህዳሴ መፍለቂያ የሆነችውን ፍሎረንስ ፣ የመካከለኛው ዘመን ሎንዶን ወይንም ኒው ዮርክ የነበረችውን ቬነስ ፤ ታሪክ ሆነው መቅረት የጀመሩት እና የአውሮፓ ማዕከልነት ምዕራፋቸው የተዘጋው በእነ እዚኽ ኹለት ክስተቶች ምክንያት መሆኑ ነው ።
ፖርቹጋሎች እና ስፓኞች ፤ አዲስ የኃብት ምንጭ እና ወደ ኃብቱ የእሚያደርሰውን መንገድ በጦር ኃይል ማስጠበቅ የእሚችሉበት ኹኔታ ሲፈጠር ፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ተፈላጊነት በማሽቆልቆል እና በእዚኽ አዲስ እየመጣ በአለው ዓለም ዓቀፋዊ የኃይል አሰላለፍ ሕልውናው ስጋት ውስጥ የገባው የእስልምናው ኢምፓየር ኢትዮጲያን ነጥሎ ለማጥቃት ኹኔታውን በማመቻቸቱ ፤ ዲፕሎማሲው የታሰበለትን ቴክኖሎጂ እና ሳይንስን ወደ ሐገር ውስጥ ሳያስገባ እስከ እነ ጭራሹም በእዚኽ የታሪክ ክፍል በዝርዝር የእምናያቸው ፤ የኢትዮጵያን ህልውና የእሚፈታተኑ አራት ትልልቅ ክስተቶች የጋበዘ ሆነ ።
እነ እዚኽን በኢትዮጵያ ህልውና ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ሚና የነበራቸውን አራት ትላልቅ ክስተቶች በዝርዝር ከመመልከታችን በፊት ፤ በወቅቱ የኢትዮጲያ ኢከነሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጥንካሬ በውሸት አጉል ተጋኖ የቀረበ እና የወቅቱን የኢትዮጲያን ነባራዊ ኹኔታ የእማይመጥን የግነት ታሪክ ብቻ ነው እና ኢትዮጲያ ለመስልጠን እንቢ ስላለች ነው ፤ ብዙ መከራ የደረሰባት በእሚል በአንዳንድ የታሪክ ተንታኞች የእሚቀርቡት ትችቶች ፤ ብዙም አሳማኝ እንደ አልሆኑ ፤ መግቢያ አስቀምጠን እንጀምር።
የመጀመሪያው መታወቅ የአለበት ፤ የቀሲስ ዮሐንስ ታሪክ ፤ ኢትዮጵያን የአለ ልክ አጋኗት ስለ ነበር ነው እንጂ ፤ ኢትዮጵያ በጣም ኋላ ቀር እና ከአውሮፓዊያን ጋር በእኩልነት እንድታብር የእሚያደርጋት ኢከነሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ መዋቅር የነበራት ሐገር አልነበረችም የእሚለው የአንዳንዶች አስተያየት ፤ የእዛኽን ዘመኑን ኢትዮጵያ የእሚወክል አይመስልም ።
በእርግጥ የቀሲስ ዮሐንስ ንግርት እንደ ማንኛውም ንግርት ፤ በውስጡ ግነት የነበረው እና በአውሮፓውያን ማሕበረሰባት ውስጥ ሰርጎ ገብቶ እንደ አዳኝ ወይንም እንደ ተወዳጅ ትላልቅ ተውኔቶች መሪ ገጸ ባሕሪ በብዙ ሰዎች በግነት አድናቆት የእሚነሳ ነበር ። ለምሳሌ ፦ ብዙ ከንቱ ጭንቀት (Much Ado About Nothing) በእሚለው ቀልድ አዘል የሼክስፒር ድርሰት ላይ እንዲኽ ዓይነት ትዕይንት አለ ፦
“ክብርነቶ ወደ ምድር ጫፍ የእሚያስኼደኝ ሥራ የሎትም? ቢልኩኝ ለማንኛውም ቀላል መልዕክት እንኳን ቢሆን እስከ ምድር አናት ድረስ እኼዳለኹ ፤ ከሩቅ ምሥራቁ የኤሽያ ጫፍ ጥርስ መጎርጎሪያ ስንጥር አመጣለሁ ፣ የቁሲስ ዮሐንስን እግር ለክቼ እመጣለሁ ፣ ከታላቁ ካምፖዴያዊ ጺም ላይ ፀጉር አመጣለሁ -- ወደ አፍሪካ ድንኮች ምንም ዓይነት መልዕክት ይዤ እኼዳለው -- ከእዚኽች ጨቅጫቃ ሴትዮ ጋር ሦሥት ቃላት ከመነጋገር ። ለእኔ የእሚሆን ሥራ የሎትም?”
“ Will your Grace command me any service to the world's end? I will go on the slightest errand now to the Antipodes that you can devise to send me on; I will fetch you a toothpicker now from the furthest inch of Asia; bring you the length of Prester John's foot; fetch you a hair off the great Cham's beard; do you any embassage to the Pygmies--rather than hold three words' conference with this harpy. You have no employment for me. [108]“
በእዚኽ ፤ የሼክስፒር ተውኔት ላይ ፤ ልክ በግሪክ ድርሰቶች ውስጥ እንደ ነበሩት እነ ኼርኩለስ ፤ ቀሲስ ዮሐንስ የሰው ፍጥረት ሰአይኾን አንዳች ዓይነት ምናባዊ ንፍሊም መስሎ ፤ የእግሩን ትልቀት ለማወቅ ልኬት የእሚያስፈልገው መስሎ በተውኔታዊ ግነት ቀርቧል ።
ስለ እዚኽ ፦ እንደ እዚኽ ዓይነት ምናባዊ ንጉሥ ከነበረ የወቅቱ አውሮፓዊያኖቹ ሲፈልጉ የነበሩት ፤ በእውነትም ኢትዮጵያ መጥተው የአገኙዋቸው የኢትዮጵያ ነገሥታት ሰዎች በመሆናቸው ፤ ቀሲስ ዮሐንስ ከአሰቡት በታች ነበር ማለት ይቻላል ። ወይንም ደግሞ በቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ፣ የእማያስረጅ ወንዝ አለ ፣ ሐገሩም ከኤደን ገነት ጎን ነው ፤ ይሉ እንደ ነበሩት የንግርቱ ትርክቶች እርጅና የእሚያጠፋ ወንዝ የአለባት እና ከኤደን ገነት ጎን የአለ፟ች ሐገር ፍለጋ ከሆነ የተነሱት ፤ በእውነትም ኢትዮጵያ እንደ እዛኽ ዓይነት ሐገር ስለ አልሆነች ፤ ኢትዮጵያ ከአሰቡት በታች ሆና አግኝተዋታል ።
የወቅቱ አውሮፓዊያን እና የተቀረው የዓለም ሕዝብ ግን ፤ ስለ ቀሲስ ዮሐንስ በአውሮፓ ይነገሩ የነበሩ ፤ ከላይ ያነሳናቸውን ዓይነት የተጋነኑ መግለጫዎች ፤ እውነት ናቸው ብሎ ውስዶ የእሚቀበልበት የንቃት ኋላ ቀርነት ደረጃ ላይ የነበረ አይደለም ።
ያም ብቻ ሰአይሆን ፤ ከላይ በጠቀስናቸው ብዙ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ምክንያት ፤ አውሮፓዊያን ቀሲስ ዮሐንስ ማን ነው? ምን ዓይነት ቁመና እና መልክ አለው? የሐገሩ ሕዝብ ምን ዓይነት ነው? ወዘተ ፤ የእሚሉትን ጥያቄዎች በአግባቡ መልሰዋል ። የወቅቱን አውሮፓዊያን ፤ የቀሲስ ዮሐንስን ሐገር ሕዝብ እና ቀሲስ ዮሐንስን በተመለከት የአላቸውን ግንዛቤ ያጠኑ ሰዎች ፤ የአገኙትን ግኝት እንደ እዚኽ አስቀምጠውታል ፦
“ተክለ ሰውነታቸው እና ባሕሪያቸው ፤ ጥልቅ ስር ከአለው የክርስትና እምነታቸው ጋር ፤ ከተለመደው (ጥቁር ሕዝብ) ለየት ያደርጋቸዋል ። እ.አ.አ. በ1350 ዓ.ም. የታተመው የወቅቱን የዓለም መንግሥታትን የእሚዘረዝረው መጽሐፍ ፤ 'ጥቁር ቢሆኑም እንኳን' ኢትዮጵያዊያኖች 'ጥሩ ማስተዋል ፣ ጥሩ ንቃት እና እውቀት እና ትምህርት' የአላቸው ናቸው ይላል ። ዣን ለተባለው የፈረንሳይ ሹም ፤ ከኔፕልስ የሆነው እና እ.አ.አ. በ1430 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ኼጄ ነበር የአለው ፒየትሮ ኢትዮጵያዊያኖችን ሲገልፃቸው 'ታላቅ ሕዝብ ፤ ጥቁርም ነጭም ያልሆኑ ነገር ግን የቀይ ዳማዎች … መልካም እና ጠቢብ ሕዝብ ናቸው' በእሚል ነበር ። ከመቶ ዓመት ገደማ በኋላ - ኩንስትማን አራት - ተብሎ የእሚታወቅ ካርታ ያዘጋጀ ጆርጅ ሬይል የእሚባል ሰው 'የአብሲኒያው ንጉሥ እጅግ ኃያል እና ክርስቲያን ነው' ፤ ምንም እንኳን በስህተት የህንዱ ቀሲስ ዮሐንስ ቢባልም ፤ ከጠበቀው ውጭ የሆነበትን መልኩን ልብ ብሎ እንደ እዚኽ ብሏል ፡ ጥቁር አፍሪካዊ እና ጥቅልል ፀጉር የአለው ሲሆን ፤ ትንሽ ወደ ነጭነትም ያደላል ። በኢትዮጵያ ስድስት ዓመት ቆይቶ ፤ እ.አ.አ. በ1540 ዓ.ም. ወደ አቢሲኒያ የተደረገ ጉዞ በእሚል መጽሐፍ ያሳተመው ቄስ ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ 'ንጕሱ ወጣት ሲሆን ቆዳውም በጣም ጥቁር አይደለም ፤ ይልቁንም ሳንቃ ይመስላል ወይንም በጣም ቡናማ የአልሆነ ቱፋ ፤ እናም የተከበረ ጭምት ነው በሰውነቱ ።”
“Their physical features and comportment, together with their deeply rooted Christianity, set them apart from the norm. The Libro del conosçimiento of c.1350 averred that ‘though black’, Ethiopians were ‘men of good understanding and good sense and have knowledge and learning’. The description from a man of Naples called Pietro, who claimed to have travelled to Ethiopia around 1430 for Jean, duc de Berry, is of a ‘big people, neither white nor black, but of reddish-brown color and … they were virtuous and wise people’. Almost a century later a map attributed to Jorge Reinel – referred to as the KunstmannIV map – affirming that ‘the king of Abyssinia is extremely powerful and a Christian’, though wrongly referred to as Prester John of India, notes an unexpected aspect of his appearance: he is black African and has frizzy hair, tending a bit toward whiteness.Similarly Ho Preste Joam das Indias of 1540, written by the priest Francisco Alvares who spent six years in Ethiopia, observes that the king ‘was young and not very black, he was more of a chestnut colour or a not very brown Bayonnese apple, and in his colour quite a gentleman’. [106]“
ያውቃሉም ብቻ ሰአይሆን ፤ በአውሮፓ በእዚያኽን ዘመን የዳበሩ ፤ ለምሳሌ ፦ የመርከብ አገነባብ ፣ የህንፃ ሥራ ጥበብ ፣ የግምጃ ምርት ፣ ወዘተ ፤ በኢትዮጵያ በአይኖሩም እና የኢትዮጵያም ዲፕሎማሲያዊ ግብ እነ እዚኽን ሞያዎች እና እውቀቶች ወደ ሐገር ውስጥ ለማስገባትን ታሳቢ የአደረገ ቢሆንም ፤ የወቅቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ፤ አውሮፓዊያኖች የእሚንቁት እና ብዙ አድንቀን ስንፈልገው የነበረው ቀሲስ ዮሐንስ ተራ ሰው ነው የእሚያስብላቸው ሰአይሆን ፤ በንግርቱ ተነሳስተው ከኢትዮጵያ ጋር ስፋ የአለ፟ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማድረግ ከጀመሩ አንስቶ ፤ አክብሮታዊ ቦታ እንዲኖራቸው የአደረገ ነው ። ማቲዎ ሶልቫዶር የእሚባል አጥኝ በወቅቱ የነበሩ አውሮፓዊያን ስለ ኢትዮጵያን የነበረቻውን ግንዛቤ እንደ እዚኽ አስቀምጦታል ፦
“ የዘራ ያዕቆብን መንግሥት የስልጣን አወቃቀር የእሚያብራራው የራንዛኖ-ሮምቡሎ ዘገባ ውስጥ የቆዳን ቀለም (ዘርን) ወይንም ንቀትን የእሚያንፀባርቅ ምንም ዓይነት ነገር የለውም ። እንዲያውም ጠቅለል የአለ አድናቆት የተሞላበት ገላፃው ፤ ስለ ኢትዮጵያ የተማሩ ሊህቃን በተመለከተ በቀረበው ገለፃ በድጋሚ ይጠናከራል ፡ 'በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሳይንቲስቶች ፣ የስነ ከዋክብት ተመራማሪዎች አሉ ፣ ሀኪሞች በጣም የተከበሩ ናቸው ።' ይኽን መሰሉ ገለፃ ደግሞ በተለየ ኹኔታ ሳቢ የእሚያደርገው - ኢትዮጵያዊያኖች ጥሩ ክርስቲያን ናቸው በእሚል በክርስትና የአላቸውን መንፈሳዊነት ከመግለፅ የአለፈ በመሆኑ ነው ። በጠቅላላውም ፤ ኢትዮጵያዊያኖች በሳይንሱ መስክ በእኩልነት ወይንም በበላይነት የእሚገልፅ ነው ፤ ይኽም በአውሮፓ ህዳሴ መመዘኛ የተቀመጠ መግለጫ በመሆኑ እጅግ ትልቅ እንደምታ የአለው ነው ።”
“The Ranzano-Rombulo account, which offers a faithful description of Zar'a Ya'eqob's power structure, is devoid of any sort of racial or derogatory reference. The overall appreciative attitude is confirmed by further claims, such as one relating to Ethiopian educated elites: “there are in Ethiopia many scientists and astrologists, physicians are in high regard.” This kind of description is particularly interesting because it goes beyond a discourse engrained in Christian piety - that of the Ethiopian as the good Christian - and it conveys altogether an image of either equality or Ethiopian superiority in the field of science, a stance that seems all the more impressive when read against the standards of the Italian Renaissance. [109]“
እ.አ.አ. በ1441 ዓ.ም. በፍሎረንስ ጳጳስ ዩጂን አራተኛ (Pope Eugene IV) ጋባዥነት በተካኼደው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የኼዱትን አርባ መነኮሳት ሉዕክ ቡድን በመምራት የኼደው ዲያቆን ጴጥሮስ ፤ ከጳጳሱ ጸሐፍት አንዱ ፍላቪዮ ኦሎንዶ ፤ ቃለ መጠይቅ አድርጎለት ያገኘው እውቀት ፤ ከታላቁ አሌክሳንደር ጀነራሎች አንዱ የሆነው ጠለሚዎስ ፤ ከአሌክሳንደር መሞት በኋላ ፤ ሰፊውን የአሌክሳንደር ግዛት ከተካፈሉት አራት ጀነራሎች አንዱ ሆኖ ግብፅን በመውሰድ ፤ የጠለሚዎስ ስርወ መንግሥትን በግብፅ የመሠረተው እና አብዛኛው የአውሮፓዊያኖች የሉላዊ የመልክዓ ምድር እውቀት (Global Geographic Understanding) ምንጭ የሆነው ሰው ፤ ያስተላለፈላቸው እውቀት ስህተት መሆኑን ያሳየ ነበር ። ይኽም ከኢትዮጵያኑ የተገኘው አዲሱ እውቀት ፤ ለእነ ክርስቶፈር ከለምበስ ስኬት አጋዥ የነበረ ነው ፦
“ጴጥሮስ ኢትዮጵያ የእምትገኝበትን ቦታ በእሚያስረዳበት ወቅት ምንም ተጨባጭ ማስረጃ በአያቀርብም ፤ ዲያቆኑ የሰጠው ገላፃ ፤ ብዮንዶን 'ጠለሚዮስ በብዙ ጉዳዮች ላይ መሀይም ነበር' ብሎ ከመደምደም አላገደውም ። የኢትዮጵያዊያኖቹ ተጓዦች አስተያየት ፤ ምዕተ ዓመታት ያስቆጠሩ የአውሮፓዊያን የመልክዓ ምድር አቀማመጥ ግንዛቤ ውስጥ በቀላሉ ዘርዝሮ ገብቶ አዋድቆታል ፤ የወቅቱ ሳይንሳዊ ትርክት ከጥንታዊ ታዋቂ ጸኃፍት የተወሰደ እና በቤተክርስቲያን ታውሎጊያ አስተምህርቶች ላይ የተመሠረተ ቢሆንም ፤ ብዮንዶ ግን ብዙም ሳይጨነቅ ኢትዮጵያዊው ጴጥሮስ የእሚለውን በመቀበል ልማዱን ለመተው ፈቃደኛ አድርጎታል ።“
“While Pietro could adduce any tangible evidence to substantiate his point about Ethiopia's location, Biondo did not refrain from believing the deacon and argued that ”Ptolemy was ignorant of many things.” The opinion of an Ethiopian traveler seems to have penetrated and disqualified with ease centuries of European geographical tradition; the scientific discourse of the time was derived from classical authorities and strongly intertwined with the theological tenets of the Church, yet it took Biondo little to throw in his lot with Pietro the Ethiopian. [109]”
አውሮፓዊያን ከሐገራቸው ሳይወጡ በፊት ፤ ኢትዮጵያዊያን አውሮፓ በመኼድ የአውሮፓ ከተሞችን ያጠኑ ነበር ፦
“በተጨማሪም ፤ አውሮፓዊያኖች ከሰሐራ በታች የአለውን የትኛውንም የአፍሪካ ክፍል ከመጎብኝታቸው በፊት ፤ ኢትዮጵያዊያን የአውሮፓን ከተማ ጎዳናዎች እየበረበሩ ነበር ።”
“furthermore, Ethiopians were exploring the city streets of Europe long before Europeans visited Ethiopia or any other part of sub-Saharan Africa. [106]“
ስለ እዚኽ ፤ አለ ዝበት (Objectively) የወቅቱን ታሪክ የቃኘ ሰው የእሚኖረው መረዳት ፤ ምንም እንኳን የቀሲስ ዮሐንስ ንግርት ሲጀምር እና በአውሮፓ ሲስፋፋ ፤ ምትኃታዊ ኃይል የአለው ነጋሢ የእሚል እንደ አንድ ተውኔት ወይንም ልብ ወለድ ታሪክ መሪ ገፀባሕሪ የእሚታይ ዓይነት ሰው ቢሆንም ፤ የወቅቱ የአውሮፓ ነገሥታት የቀሲስ ዮሐንስን ሐገር ሲፈልጉ ፤ በእዚኽ ዓይነቱ የምናባዊ ቅዠት ሰአይሆን ፤ ከአውሮፓዊያን ጋር ፀረ እስልምና መንግሥት ትግል የእሚያደርግ ሰው የሆነ ንጉሥ ፍለጋ መሆኑ ግልፅ ነው ።
በኋላም ፤ የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ኢትዮጵያ ነች ብለው ደምድመው ፤ ከኢትዮጵያ ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት ሲጀምሩ ፤ ኢትዮጵያዊያኖች ፤ በቴክኖሎጂ ረገድ ከአውሮፓዊያን ቢያንሱም ፤ በመንግሥታቸው ጥንካሬ ፣ በክርስትና እምነታቸው ፣ በአሳዩት ስልጡንነት እና እውቀት ፤ ጥሩ ማሕበራዊ አቅም (Social Capital) ፣ ወዘተ ፤ እንደ አላቸው ተገንዝበው ከእላይ እንደ አየነው መላው አውሮፓ ፤ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በደስታ እና በአክብሮት የተቀበሉት እንጂ ፤ ቀሲስ ዮሐንስ እና ሐገሩ ፤ የተናቁ ናቸው የእሚል አልነበረም ።
የወቅቱ አውሮፓዊያን ፤ ለቀሲስ ዮሐንስ ሐገር ኢትዮጲያ ፤ አንዳንድ የኋለኛ ዘመን የታሪክ አጥኚ ነን የእሚሉ ሰዎች የእሚሉት ዓይነት ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ንቀት ቢያድርባቸው ኖሮ ፤ ኃሳባቸውን አዲሱ የባሕር ላይ መንገድ እና አዲሱ ዓለም (አሜሪካ) እስኪወስደው ድረስ ፤ ከ200 ለአላነሱ ዓመታት ፤ ብዙ የሕይወት እና የንብረት ዋጋ እያስከፈላቸው ፤ ከእላይ የገለጽነውን ዓይነት ጥረት በማድረግ ከኢትዮጲያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመመሥረት ሢሠሩ አይኖሩም ነበር።
ታላቁ የእስልምና መንግሥትም ኢትዮጵያን ማዳከም እና ማክሰም ግቡ አድርጎ ለብዙ ዓመታት ይኽን ኹሉ ጥቃት ሲዘነዝርም አይኖርም ነበር።
እነ ከለምበስ እና ደጋማ አዲሱን የባሕር መንገድ እና አዲሱን ዓለም ከማግኘታቸው በፊት ፤ ታሪክ የእሚያሳየው ፤ አውሮፓዊያን ኢትዮጵያዊያንን እንደ እኩያ እንጂ ፤ ብዙ ጠብቀን ፤ ማሀይም እና ኋላ ቀር ሕዝብ ገጠመን በእሚል ንቀት መሞላታቸውን የእሚያሳይ ነገር የለም ። የወቅቱ የአውሮፓ ሕዝብ እና መንግሥት ከእደ ጥበብ ሞያ እና እውቀት በስተቀር ከኢትዮጵያ የእሚያንስ እንጂ የእሚሻል አልነበረም ።
ነገር ግን ፤ ከለምበስ እና ደጋማ ያመጡት አዲስ ጥርመሳ ፤ ውሎ አድሮ የቅኝ ግዛት እና የዘመናዊ ካፒታሊዝምን ስረዓት ሲወልድ ፤ በኢትዮጵያ እና በአውሮፓዊያን መካከል የአለው የስልጣኔ ልዩነት ፤ ‘በብርኃን ፍጥነት’ ሊባል በእሚችል ኹኔታ ልዩነት እያሳየ መጣ ።
ይኽም ኹኔታ ፤ ኢትዮጵያ በ16ኛውም ምዕተ ዓመት መጀመሪያ ላይ ከነበራት አቅም እና ጥንካሬ በብዙ መልኩ ወደ ኋላ ስታፈገፍግ ፤ በተቃራኒው አውሮፓዊያኖች በኹሉም መስክ ወደ ፊት ተራምደው ፤ ዛሬ ላይ በአውሮፓዊያን እና በኢትዮጵያዊያን የእምናየው ሰፊ ልዩነት ተፈጠረ ።
ከኹኔታው እንደ እሚታየው ፤ ኢትዮጵያ ልክ እንደ እዛን ወቅቱ ጣሊያን (ሮም ፣ ፍሎረንስ ፣ ቬነስ ፣ ወዘተ) ለእዚኽ ታሪካዊ መጥፎ አጋጣሚ ለመዳረጓ ፤ ከአጋጣሚ በስተቀር ማንንም ተወቃሽ ማድረግ የእሚቻል አይመስልም ።
የትኛውም ዓይነት የፖለቲካ ተቋም ፤ እነ አሜሪካን የመሰሉ ትልልቅ ፣ ብዙ ሰው ያልሰፈረባቸው ፣ በተፈጥሮ ኃብት የተሽቆጠቆጡ አህጉራት ሊገኙ ይችላሉ ፥ መገኘትም ብቻ ሰአይሆን ፤ እነ እዚኽን አከባቢዎችን ኹለት መቶ በእማይሞሉ ወታደሮች መዝረፍ እና ትልልቅ ሐገራት መፍጠር ይቻላል ፣ በእሚገኙት አዲስ የባሕር ላይ መንገዶች ዓለም ዓቀፍ ንግዱን በአዲስ መንገድ ማስተሳሰር ይቻላል ፣ ይኽም የዓለምን ማሕበረ ኢከነሚ በመሠረታዊነት ይለውጣል ብሎ መተንበይ ሊችል አይችልም ። ቢችልም እንኳን ይኽ ፍፁም ያልተጠበቀ ክስተት የእሚያስተዋውቀውን ፍፁም አዲስ የማሕበረ ኢከነሚ አስተሳሰብ የእሚፈጥረውን አሉታዊ ተፅኖ ለመመከት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አይችልም ።
በእዚኽም ምክንያት ፤ በእዚኽ ወቅት ኢትዮጵያ የገጠማት መጥፎ ኹኔታ ፤ በዋናነት ከመደበኛ መጥፎ ገጠመኝነት በአለፈ ሌላ ፓለቲካዊ እና ኢከነሚያዊ ትንታኔ የእሚገኝለት አይመስልም።
ይኽ ያልተጠበቀ ገጠመኝ ግን ፤ ከግዜያዊ ትልቅ አደጋነት ወደ ትውልድ ተሻጋሪ ሐገራዊ ቀውስ እንዲሻገር ፤ በዋናነት የፖርቹጋል እና የስፔን አከባቢ የካቶሊክ ጀስዊት ቄሶች ፤ ስግብብነት እና ከኃዲነት ፤ ዓለም በሕዝባዊ አብዮት ከቀኝ ግዛት አስተሳሰብ እስክ ትወጣ ፤ በአብዛኛው የካቶሊክ አውሮፓዊያኖች ዘንድ ኢትዮጵያ ላይ ለደረሰው ከፍተኛ የማጥላላት ዘመቻ እንደ አጋለጣት ግን በታሪክ መመዝገብ አለበት ።
የመጀመሪያው ፤ ስለ ወቅቱ ፖርቹጋሎች እና ስፓኞች የማሕበረ ኢከነሚ አስተሳሰብ ሰው ሊረዳው የእሚገባው ፤ እነ እዚኽን ኹለት ትናንሽ ሐገራት የዘመናዊው ቀኝ ግዛት ፈር ቀዳጅ የአደረጋቸው ፤ ዘረፋ እና በመሳሪያ የታጀበ የሞኖፖሊ ንግድ መሆኑን ነው ። በሌላ አገላለፅ ፤ እንታገለዋለን ብለው ከተነሱት የወቅቱ የእስልምና ጃውሳ መንግሥት የእሚለዩት በኃይማኖት እንጂ በማሕበረ ኢከነሚ አስተሳሰባቸው አይደለም ።
ስፔኖች እና ፖርቹጋሎች ፤ በእየደረሱበት የዓለም ክፍል ኹሉ ፤ እንደ እነርሱው ካቶሊክ ሆኖ ለአላገኙት ሰው ሰብዓዊ ክብር ቅንጣት እንኳን ሳይጨነቁ ፤ እየጨፈጨፉ ፣ እየዘረፉ እና ባሪያ አድርገው እያሰሩ ፤ ኃብትን ማካበት ከክርስትና እምነታችን ጋር ይጋጫል ብለው አልጨነቃቸውም ፤ እንዲያውም ቀሳውስቱ በእዚኽ ተግባር ውስጥ ግንባር ቀደም ሚና ተጫዋቾች ነበሩ ።
በእዚኽም መልኩ ፤ በዘረፋ የአካበቱት ኃብት ፤ በዋናነት የወርቅ እና የጠገራ ብር ክምር ፤ በሐገራቸው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አስከትሎ ኢከነሚያቸውን ያዛባበትን ኹኔታ እስከ መፍጠር ደርሷል ። እንዲያውም የእነዚኽ ኹለት የአውሮፓ ሐገራት የፖለቲካል ኢከነሚ አስተሳሰብ ፤ በእዚኽ ዓይነቱ የወርቅ እና የጠገራ ብር ፍቅር ላይ መመሥረቱ ፤ አብዛኛው የእነርሱ ስሪት የሆነው የዛሬው የላቲን አሜሪካ ሕዝብ ማሕበረ ኢከነሚ ቀውስ ምንጭ እንደ ሆነ ፤ የኢከነሚክስ ሞያተኞች እምነት ነው ።
ኒየል ፈርጉሰን (Niall Ferguson) የተባለው ኢከነሚስት ፤ የወቅቱ የእነዚኽ ሰዎች በኃሪ በግሪክ አፈታሪክ ከእሚነገረው ፤ የሚዳስ ዳሰሳ ከእሚለው ታሪክ ጋር አመሳስሎ ያስቀምጠዋል ።
በእዚኽ የግሪክ አፈታሪክ ፤ መሠረት ሚዳስ የእሚባል ብዙ ስኬት እና መልካም እድል የአለው ፤ ነገር ግን ለየት ያለ የወርቅ ፍቅር የነበረው ንጉሥ ነበር ። ይኽ ንጉሥ በአንድ አጋጣሚ ዳይናሰስ የእሚባለውን አንዱን የግሪክ ዓምላክ ደስ በማሰኘቱ ፤ ዳይናሰስ ምን እንዲያደርግለት እንደ እሚፈልግ ይጠይቀዋል ። ንጉሥ ሚዳስም ለትንሽ ግዜ ከአሰበ በኋላ ፤ የእምነካው ነገር ኹሉ ወርቅ ይኹን ይላል ፤ ዳይናሰስም በጉዳዪ ላይ በደንብ እንዲያስብበት ከአሳሰበው በኋላ ፤ ንጉሥ ሚዳስ በደንብ አስቤበታለኹ ፤ በፍላጎቴ እርግጠኛ ነኝ ሲለው ፤ ከበንጋታው ጀምሮ የእሚነካው ኹሉ ወርቅ እንደ እሚኾን ነግሮት ይኼዳል ።
እንደ ተባለውም ፤ ንጉሥ ሚዳስ በንጋታው ከእንቅልፉ ሲነቃ የእሚነካው ነገር ኹሉ ወርቅ ይኾናል። በምኞቱ መሳካት የተደሰተው ንጉሥ ሚዳስ ቤተመንግሥቱን ኹሉ እየዞረ የአገኘውን ነገር ኹሉ እስኪ ደክመው ወደ ወርቅ ከለወጠ በኋላ ፤ ፅጌረዳ አንስቶ ሊያሸት ሲል ፅጌሬዳው ወርቅ ሆነበት ፤ ችግር የለውም ሳልነካ አሸተዋለኹ ብሎ ፤ የነካውን ኹሉ ወርቅ ከማድረግ ድካሙ አረፍ እያለ ቁርስ ሊበላ ኼደ ።
ለቁርስ የቀረበለትን ዳቦ እና ወይን ሲያነሳ ኹለቱም ወርቅ ኾኑ ፤ በእዚኽ ተደናግጦ ሳያበቃ የእሚወዳት ሴት ልጁ መጥታ ስታቅፈው እርሷም የወርቅ ኃውልት ሆነች ። ከእዚኽ በኋላ ፤ ሚዳስ ምርር ብሎ አልቅሶ ፤ ይኽንን እርግማን ዳይናሰስ እንዲያነሳለት በመለመን ፤ በዳይናሰስ ትዕዛዝ አንዱ ወንዝ ላይ ኼዶ በመታጠብ ፤ የእሚነካውን ነገር ኹሉ ወርቅ ከእሚያደርገው ርግማን ተላቀቀ ።
ይኽን የንዋየ ፍቅርን ለመገሰፅ በቀረበ የግሪኮች አፈታሪክ ጋር በማመሳሰል ፤ ኒየል ፈርጉሰን ፤ የእዛን ወቅት ስፓኞች የወርቅ አፍቅሮት ያስከተለውን የኢከነሚ ቀውስ እንደ እዚኽ ያብራራዋል ፦
“የአዲሱ ዓለም የጠገራ ብር የእምታምፅባቸውን የደቾች (ሆላንድ) ሕዝባዊ መንግሥት እንዲያፈገፍግ ማድረግ አልቻለም ፤ ኢንግሊዝም የስፔን ዘውዱ ግዛት እንድትሆን ማድረግ አልቻለም ፣ የስፔንንም ዘውዳዊ መንግሥት ከኢከነሚያዊ እና ፖለቲካዊ ውድቀት ሊታደግ አልቻለም ። ልክ እንደ አፈታሪኩ ንጉሥ ሚዳስ ፤ የ16ኛው ምዕተ ዓመት የስፔን የዘውድ ነገሥታት ፤ ቻርልስ 5ኛ እና ዳግማዊ ፊልፕ ፤ የከበሩ መዓድናት ክምር በረከት የመሆናቸውን ያኽል ርግማንም ሊሆኑ እንደ እሚችሉ አዩ ። ምክንያቱም? ለወረራ የእሚያድርጉትን ጦርነት በጀት ለመሸፈን እጅግ ብዙ ማዕድን ቆፍረው በማውጣታቸው ፤ ማዕድናቱ ራሳቸው በገበያ የአላቸው ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ወደቀ ፤ ይኽም ማለት የእነዚኽ ማዕድናት በገበያው ከእሚገኙት ሌሎች ሸቀጦች አንፃር የአላቸው የመግዛት አቅም ማለት ነው ። ‘የዋጋ አብዮት’ ተብሎ ፤ መላው አውሮፓን እ.አ.አ. ከ1540 ዓ.ም. እስከ 1640 ዓ.ም. የአመሰቃቀለው - ለአለፉት 300 ዓመታት ምንም ዓይነት የጎላ ዋጋ ጭማሪ ሳያሳይ የቆየው ገበያ - በእዚኽ ወቅት በእጅጉ ተመነጠቀ ። በሐገረ እንግሊዝ (ከሌላው የአውሮፓ ይልቅ የወቅቱ የዋጋ ዝርዝር የእሚገኝባት) በእዚኽ ወቅት የኑሮ ውድነት በሳባት እጥፍ ጨመረ (በእርግጥ ይኽ አሁን እኛ በእምንኖርበት እና ዋጋ በየዓመቱ በ2% በእሚጨምርበት ብዙ አይደለም) ይኽ ግን ለመካከለኛው ዘመን ስፔን የዳቦ ዋጋን በእጅጉ ያናረ ነበር ። በስፔን የጠገራ ብር መብዛት ፤ በእኛ ዘመን ነዳጅ በአረቢያ ፣ ናይጄርያ ፣ ፐርዥያ ፣ ራሺያ እና ቬንዙዌላ ፤ ‘የኃብት ርግማን’ እንደ ሆነው ፤ ሆኖባቸው ነበር ፤ ሰዎች በሌሎች አምራች የንግድ መስኮች ላይ እንዳይሳተፉ መነሳሳታቸውን ሲገደል ፤ በተጓዳኝ ደግሞ ኪራይ ሰብሳቢ አምባገነኖችን በሕዝብ ከእሚወከሉ ማህበራት ይልቅ እያጠናከረ (ስፔንን በተመለከተ እነ ኮርቴዝ) ።”
“And yet all the silver of the New World could not bring the rebellious Dutch Republic to heel; could not secure England for the Spanish crown; could not save Spain from an inexorable economic and imperial decline. Like King Midas, the Spanish monarchs of the sixteenth century, Charles V and Philip II, found that an abundance of precious metal could be as much a curse as a blessing. The reason? They dug up so much silver to pay for their wars of conquest that the metal itself dramatically declined in value - that is to say, in its purchasing power with respect to other goods. During the so-called 'price revolution', which affected all of Europe from the 1540s until the 1640s, the cost of food which had shown no sustained upward trend for three hundred years - rose markedly. In England (the country for which we have the best price data) the cost of living increased by a factor of seven in the same period; not a high rate of inflation these days (on average around 2 per cent per year), but a revolutionary increase in the price of bread by medieval standards. Within Spain, the abundance of silver also acted as a 'resource curse', like the abundant oil of Arabia, Nigeria, Persia, Russia and Venezuela in our own time, removing the incentives for more productive economic activity, while at the same time strengthening rent-seeking autocrats at the expense of representative assemblies (in Spain's case the Cortes). [39]“
ይኽም ብቻ ሰአይኾን የአገኙት አዲስ የንግድ መስመር እና አከባቢ ሌላ አውሮፓዊ እንኳን ነጋዴ መጥቶ እንደ አይጋራቸው ፤ ዘመናቸውን ኹሉ ሲዋጉ የነበሩ እና በእንግሊዝ በመሸነፋቸው ይኽንን ሞኖፖሊ እንደ አስጣቸው ይታወቃል ።
ይኽም የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ ፤ እስከ ዛሬም ድረስ መነሻቸው ፖርቹጋል እና ስፔን አከባቢ የሆኑት ሕዝብ ፤ የላቲና አሜሪካን ሐገራት እስከ ዛሬ ድረስ ለእሚሰቃዩበት የወንጀል ፣ የመልካም አስተዳደር እጦት ፣ ወዘተ ፤ መነሻ መሆኑ የኢከነሚክስ ሞያተኞች እምነት ነው ።
በውበቱ ፣ በተፈጥሮ እና የሰው ኃብቱ የታወቀው የላቲን አሜሪካ ፤ ምንም እንኳን ከአፊሪካ ጋር በአይነፃፀርም ፤ በወንጀል ፣ በአድንዛዥ እፅ ንግድ ፣ በመልካም አስተዳደር እጦት ፤ ዜጎቻቸው ወደ ሰሜን አሜሪካ ለዝቅተኛ የእርሻ ላይ የጉልበት ሥራ ለመሥራት በእየመኸሩ የእሚሰደዱት እና ትንሽ ነቃ ያአሉት ደግሞ የአሜሪካ መንግሥት የእሚሰጠው የማሕበራዊ ዋስትና ጡረታ ተመፅዋች ለመሆን ፤ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ወንዝ እና ተራራ አቋርጠው በእግራቸው የእሚኼዱት ፤ ለዘመናት የተከተሉት በዘረፋ የመበልፀግ ማሕበረ ኢከነሚ ፤ በመንጠፉ ነው ።
እንደ እዚኽ ዓይነት በዘረፋ የመበልፀግ ማሕበረ ኢከነሚ የእሚከተሉ በመሆኑ እንጂ ፤ ስፓኞች እና ፖርቹጋሎች ፤ የዛሬዎቹን አሜሪካ አህጉራት በማግኘትም ሆነ ቀድሞ በመድረስ እና ሰፈራ በመመሥረት ፣ ሰፈራ በመመሥረት ብቻ ሰአይሆን ፤ በመላው አሜሪካ የአለውን የወርቅ እና የጠገራ ብር በመሰብሰብ እንዲሁም በነበራቸው ቴክኒካዊ እውቀት ዛሬ እንደ ማንኛውም የሦሥተኛው ዓለም ሰው ፤ ሊስደዱባት የእሚፈልጓትን አሜሪካ ከመስረቱት እንግሊዞች ያነሰም እውቀት ስለ ነበራቸው አይደለም ። እንዲያው እንግሊዝ ከእነርሱ የዘረፋ ኃብት አሉታዊ ተፅኖ ለመላቀቅ እና የስፓኝ ቀኝ ግዛት ለአለመሆን ዓመታት የቆየ የሞት ሽረት ትግል ስታደርግ ነበር ።
ሐገራት ለምን ይቆረቁዛሉ (WHY NATIONS FAIL) በእሚል ርዕስ ፤ የተለያዩ ሐገራትን የፖለቲካ አወቃቀር ታሪክ አጥንተው ፤ ግኝታቸውን የጻፉ ኢከነሚስቶች በእዚኽ መጽሐፋቸው መግቢያ ላይ ፤ የግኝታቸውን ዋና ነጥብ ይአንፀባርቃል በእሚል ፤ ኖጋሊስ የእምትባል ከተማ ፤ በታሪክ አጋጣሚ ፤ በአሜሪካ እና በሜክሲኮ መንግሥታት ስር ፤ ኖጋሌስ አሪዞና እና ኖጋሊስ ሶኖራ ተብላ ከተከፋፈለች በኋላ ፤ በእነዚኽ በአጥር ብቻ በእሚለያዩ ኹለት መንግሥታት ስር የእሚኖሩ የአንድ ከተማ/አውራጃ ሕዝብ ፤ ለእዚኽ እጅግ የተራራቀ ማሕበራዊ ደረጃ ለመገኘታቸው ፤ ከማሕበረ ኢከነሚ አወቃቀር ልዩነታቸው ውጭ ፣ የመልከዓ ምድር ፣ የአየር ንብረት ፣ የሕዝብ ስብጥር ፣ ወዘተ ፤ ልዩነታቸው በምክንያትነት ሊቀርቡ እንደ እማይችሉ በእሚከተለው መልኩ አስቀምጠውታል ፦
“የኖጋሌስ ከተማ በአጥር ለኹለት ተከፍላለች ። በአጥሩ ላይ ቆመው ወደ ላይ ቢመለከቱ ፤ በአሪዞና (ዪናይትድ ስቴትስ ፡ አሜሪካ) ሳንታ ክሩዝ በእሚባለው አውራጃ ውስጥ የአለችውን ኖጋሌስን ያያሉ ። በእዚኽ አማካይ የቤተሰብ አመታዊ ገቢ 30,000 የአሜሪካን ዳላር ነው ። በአሥራዎቹ ውስጥ የሆኑ አብዛኛዎቹ ልጆች ትምህርት ቤት ናቸው ፣ አብዛኛዎቹ ጎልማሶች ደግሞ የከፍተኛ ኹለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጨርሰዋል ። ስለ አሜሪካ የጤና ጥበቃ ችግር ሰዎች የእሚያነሱት ቅሬታ እንደ አለ ሆኖ ፤ ነዋሪዎቹ በተነፃፃሪነት ጤናማዎች እና በዓለም ዓቀፍ የእድሜ ጣራ መመዘኛ መሠረት ከፍተኛውን የእድሜ ጣራ የእሚኖሩ ናቸው ። አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች እድሜያቸው ከስልሳ አምስት አመት በላይ የሆኑ እና ከአስፈለጋቸው በመንግሥት የእሚደጎም የጤና ጥበቃ አገልግሎት ማግኘት የእሚችሉ ናቸው ። ይኽም የጤና አገልግልት ፤ መንግሥት እንደ ኤሌክትሪክ መብራት ፣ ስልክ ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ፣ የአከባቢ ጤና ፣ ከአከባቢው ከተማ እና ከተቀረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ከተሞች ጋር የእሚያገናኝ የመንገድ መረብ ፣ በስተመጨረሻም እና የእማይናቀው ፤ ሕግ እና ስረዓት ፤ መንግሥት ለሕዝብ ከእሚያቀርባቸው እና ሰውም እነ እዚኽን ግልጋሎት መንግሥት ማቅረቡን ከመጤፍም የእማይቆጥሩዋቸው መንግሥታዊ ግልጋሎቶች ናቸው ። የአሪዞና ኖጋሌስ ነዋሪዎች ፤ ወደ እየ እለት እንቅስቃሴያቸው ህይወቴ ወይንም ደህንነቴ አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል ሳይሉ እና ከአሁን ከአሁን ተሰረቁሁ ፣ ተዘርፍሁ ወይንም በቤታቸው እና በንግዳቸው ላይ ያዋሉት ኃብት አንዳች ዓይነት አደጋ ይደርስበት ይሆን ሆይ ብለው ሳይሰጉ ይኖራሉ ። ከእዚኽም መሰሉ የህይወት እና የንብረት ደህንነት በተጓዳኝ እና በተመሳሳይ ፤ የአሪዞናዋ ኖጋሌዝ ነዋሪዎች ፤ መንግሥታቸው በእየ ግዜው ከእሚያሳየው ውሽልሽልነት እና ሙስናው ጋር ፤ መንግሥት የእነርሱ ወኪል መሆኑ ከመጤፍም የእሚቆጥሩት አይደለም ። የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎቻቸውን ፣ በኹሉም የመንግሥት ሕግ አውጪ ምክር ቤት ያሉ እንደ ራሴዎቻቸውን እና የሐገራቸውን ርዕሰ ብሔር መሆን አለበት የእሚሉትን ሰው በምርጫ ካርዳቸው ማስገባት እና ማስወጣት ይችላሉ ። ዴሞክራሲ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የባህላቸው አካል ነው ።
ህይወት ከአጥሩ በስተደቡብ ፤ በጥቂት ጫማዎች ርቀት ላይ ፤ ሌላ ታሪክ ነው ። በሶኖሮዋ ኖጋሌዝ (የላቲን አሜሪካዋ ሜክሲኮ) የእሚገኙት ነዋሪዎች ፤ በተነፃፅሪነት ከሌላው የሜክሲኮ አከባቢ የተሻለ የበለፀገው ቢሆንም ፤ አማካይ የቤተሰብ ዓመታዊ ገቢ ፤ ከአሪዞናዋ ኖጋሌዝ አንድ ሦሥተኛውን ብቻ ነው ። አብዛኛዎቹ ፤ በሶኖራ ኖጋሌዝ የእሚገኙ ጎልማሶች ፤ የከፍተኛ ኹለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አልጭረሱም ። እናቶች በስፋት በአለ፟ው ከፍተኛ የህጻናት ሞት ምክንያት ይጨነቃሉ ። በሶኖሮዋ ኖጋሌዝ ከአለ፟ው ደካማ የጤና አገልግሎት የተነሳ ነዋሪዎቿ እንደ ዘመናዊዎቹ ጎረቤቶቻቸው ረዥም እድሜ አይኖሩም ። እንደ እዚኹም ብዙ የሕዝብ አገግሎትም አያገኙም ። ከአጥሩ በስተደቡብ መንገዶች በደካማ ኹኔታ ላይ ናቸው ። የሕግ እና የስረዓት ኹኔታ በእጅግ አስከፊ ደረጃ ላይ ነው ። ወንጀል ተንሰራፍቷል ፣ ንግድ መጀመር በጣም አስጊ ጉዳይ ነው ። ንግድ ለመጀመር ዘረፋው ብቻ ሰአይሆን ፈተና የእሚሆነው ፤ የንግድ ፈቃድ ለማግኘት የአለው ውጣ ውረድ እና በእጅ የመኼዱ ግዴታ ፤ ጉዳዩን የበለጠ ከባድ ይአደርገዋል ። የሶሮኖዋ ኖጋሌዝ ነዋሪዎች ፤ ከፖለቲከኞቻቸው መውሸልሸል እና ሙስና ጋር መኖር የህይወታቸው አካል ነው ።”
“THE CITY OF NOGALES is cut in half by a fence. If you stand by it and look north, you’ll see Nogales, Arizona, located in Santa Cruz County. The income of the average household there is about $30,000 a year. Most teenagers are in school, and the majority of the adults are high school graduates. Despite all the arguments people make about how deficient the U.S. health care system is, the population is relatively healthy, with high life expectancy by global standards. Many of the residents are above age sixty-five and have access to Medicare. It’s just one of the many services the government provides that most take for granted, such as electricity, telephones, a sewage system, public health, a road network linking them to other cities in the area and to the rest of the United States, and, last but not least, law and order. The people of Nogales, Arizona, can go about their daily activities without fear for life or safety and not constantly afraid of theft, expropriation, or other things that might jeopardize their investments in their businesses and houses. Equally important, the residents of Nogales, Arizona, take it for granted that, with all its inefficiency and occasional corruption, the government is their agent. They can vote to replace their mayor, congressmen, and senators; they vote in the presidential elections that determine who will lead their country. Democracy is second nature to them.
Life south of the fence, just a few feet away, is rather different. While the residents of Nogales, Sonora, live in a relatively prosperous part of Mexico, the income of the average household there is about one-third that in Nogales, Arizona. Most adults in Nogales, Sonora, do not have a high school degree, and many teenagers are not in school. Mothers have to worry about high rates of infant mortality. Poor public health conditions mean it’s no surprise that the residents of Nogales, Sonora, do not live as long as their northern neighbors. They also don’t have access to many public amenities. Roads are in bad condition south of the fence. Law and order is in worse condition. Crime is high, and opening a business is a risky activity. Not only do you risk robbery, but getting all the permissions and greasing all the palms just to open is no easy endeavor. Residents of Nogales, Sonora, live with politicians’ corruption and ineptitude every day. [110]“
በዋናነት ፤ የፖርቹጋል እና የስፔን የጀስዊት ቄሶች የፈለቁበት የማሕበረ ኢከነሚ አስተሳሰብ ይኽን ሲመስል ፤ ጀስዊቶቹ በተናጠል ደግሞ ምንም እንኳን ኃይማኖታዊ ቀንዓናዊነት እንዳላቸው ግልፅ ቢሆንም ፤ ከኃይማኖታዊ ቀንዓናዊነታቸው በአልተናነሰ ምን አልባትም በበለጠ እና በተጓዳኝ ፤ የአላቸው የወርቅ እና ኃይማኖታዊ ኢምፓየር የመመሥረት ፍላጎት ፤ በደንብ የእሚታወቅ ነው ።
የአባይን ምንጭ ፍለጋ መጥቶ ፤ ለብዙ ዓመት በኢትዮጵያ በመቆየት ባለ አምስት ጥራዝ ትልልቅ መጽሀፍት የጻፈው ጄምስ ብሩስ ፤ ጀስዊቶች እናሪያ ወደ እሚባለው የኢትዮጵያ ግዛት ለምን እንደ አልገቡ ይገርመኛል ምክንያቱም ፦
“ሊያማልላቸው የእሚችል በቂ መኃይምነት እና ወርቅ ነበር ።”
“There was enough gold and ignorance to have allured them. [111]“
እንደ አለው ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ወርቁን ቢያገኙም መኃይምነቱን ኢምፓየራቸውን ለመመሥረት በእሚያስችላቸው መጠን በአለማግኘታቸው ፤ ከእዚኽም የተነሳ ፤ የኃይማኖት ኢምፓየራቸውን በኢትዮጵያ ለመመሥረት እየጓጉ ስለ አልተሳካላቸው ፤ መሠረት የለሽ ትችት ሲሰነዝሩ የነበሩ መሆኑ መታወቅም አለበት ። ልብነ ድንግል ፤ ፖርቹጋል በጣም ትንሽ ሐገር እና ከስፔን የእምታንስ ሆና ሳለ ከአቅሟ በላይ በውሸት አጋንናችኹ አቅርባችኹልኛል በማለቱ ፤ በእነ አልቫሬዝ ዘንድ የፈጠረው ድንጋጤ እና ቁጣ ፤ ይኽም የአስጀመራቸው የፕሮፖጋንዳ ጥቃት ፤ በታሪክ የተመዘገበ ነው።
ስለ እዚኽ የጀስዊት ቀሳውስቶቹ ፤ የኃይማኖት ቀንዓዊነት የአላቸው መሆን በአይካድም ፤ የራሳቸውንም ‘መንግሥት’ የማቋቋም ስውር ፍላጎት የአላቸው በመሆኑ አስተያየታቸው እንደ ነፃ እና ገለልተኛ አካል አስተያየት መታየት የለበትም ።
ስለ እዚኽም ፦ ኃይማኖትን አሳባው ሊመሰርቱ ለፈለጉት ኢምፓየር ኢትዮጵያን አመቺ ሆና በአለማግኘታቸው የተፈጠረባቸው ቁጭት ፤ ድሮም ስጋሽ አይጣፍጥም (The grape is sour) በእሚል ዓይነት ፤ የሆነ ያልሆነውን ኹሉ እየቀጣጠሉ ፤ የውስጥ ቁጭታቸውን እንደ እሚገልፁ መረዳት ተገቢ ነው ።
ይኽም ቅጣ ይአጣ የስግብግብነት እና የቀማኝነት መንፈሳቸው ነው ፤ ከኢትዮጵያ ነገሥታት እና አርበኛ የኃይማኖት አባቶች ጋር ለረዥም ግዜ አጋጭቶዋቸው ፤ የጀስዊቶቹ ዕቡይነት የኢትዮጵያን ሕዳሴ ከማገዝ ይልቅ ፤ በመቀጠል ከእምናያቸው አራት ፈተናዎች አንዱ እና ዋነኛው ሆኖ ኢትዮጵያን ያመሰው ።
በእርግጥ ፤ ይኽ ማለት የፖርቹጋል መንግሥት እና የጀስዊቶች እገዛ ለኢትዮጵያ ምንም አልፈየደም ፤ ሙሉ በሙሉ አፍራሽ ነበር ለማለት አይደለም ። ሌላውን ብንተው እንኳን ፤ የፖርቹጋል ወታደሮች ግራኝ አህመድ በተገደለበት ጦርነት ላይ ትልቅ እገዛ አድርገዋል ።
ሆኖም ግን ፤ ግራኝን እሚያኽል አደጋ ለማስወገድ የአገዙትን ያኽል ፤ ከግራኝ ጥቃት የባሰ ጉዳት ያስከተለ የእርስ በእርስ ጦርነትም አስነስተዋል ለማለት ነው ።
ይኽም ብቻ ሰአይሆን ፤ በግልፅ ከአደረጉት ከእዚኽ ይአልተሳካ የቀኝ አዙር አገዛዝ ሙከራ በተጨማሪ ፤ ምኞታቸው እየከሸፈ ሲኼድ ፤ በኢትዮጵያ መንግሥት እና ቤተ ክርስቲያን ላይ ሲያቀርቡት የነበረው ትችት ፤ ለመጪው ዘመን የኢትዮጵያን እና የአውሮፓዊያንን ፤ በተለይ ከካቶሊክ አውሮፓዊያን ጋር ኢትዮጵያ የአላ፟ትን ግኑኝነት ለረዥም ግዜ ይአሻከረ ነበር ።
ለምሳሌ ፦ ከእላይ በአጭሩ የተቀመጠውን የኢትዮጵያዊያን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለተመለከተ ሰው ፤ ኢትዮጵያዊያን ነገሥታት ለአውሮፓዊያን ልባቸውን እና ጓዳቸውን ከፍተው ነበር ። በኋላ ላይ ግን ፤ ፖርቹጋል እና ስፔን የዓለም ኃያል መሆን ሲጀምሩ ፤ ክርስትናቸው ለዘራፊ እና ስግብግብ ማንነታቸው ቦታ እየለቀቀ ሲመጣ ፣ ከአጋርነት ትብብራቸው ይልቅ ሴረኛ ቀማኝነታቸው እያየለ ሲመጣ ፤ የኢትዮጲያ ነገሥታት እጅግ ድብቅ እና ሚስጥረኛ ሲሆኑባቸው ይታያል ።
የቄስ ፍራንሲስኮ አልቫሬዝን መጽኃፍ ያነበበ ማንም ሰው ሊረዳ እንደ እሚችለው ፤ ከእዚኽ በፊት አድርገው በእማያውቁት መልኩ ነገሥታቱ ጓዳቸውን እንደ ቆለፉባቸውን ይታያል ።
ጀስዊቶቹ በእዚኽ መልኩ ወደ ኢትዮጵያ ጓዳ ለመዝለቅ የአላቸው ተስፋ ሲመክን ፤ ራሳቸውን እንደ እውነተኛ ወዳጅ እና ኢትዮጲያ ደግሞ የእነርሱን እውነተኛ ወዳጅነት በእማይረባ ባሕል ተተብትቧ እንቢ እንደ አለች በማስመስል (ምንም እንኳን ኢትዮጲያ እንቢ የአለቸው እብሪታቸውን እና ስግብግብነታቸውን ቢሆንም) ወደ ተራ ኃሜት ሲገቡ ይታያል ፤ ለምሳሌ ፦ ቄስ አልቫሬዝ ምንም እንኳን ቆንጆ የወቅቱን ታሪክ የእሚዘግብ መጽሐፍ ቢያስቀርልንም ፤ አንዳንድ አፍራሽ ትችቶች ሲሰነዝር ነበር ።
አልቫሬዝ ፤ በሪፖርቱ ላይ እነ ኮቪልኃም እና ኢትዮጵያዊያኖች መርቆርየስ እያሉ የእሚጠሩት እና ትክክለኛ ስሙ ብራንካ ሊዮን (Branca Leone) የተባለው ከቬነስ እ.አ.አ. በ1485 ዓ.ም. የመጣውን ሰዓሊ እና መሰሎቹ ፤ በንጉሡ ቤተመንግሥት 30 እና 40 ዓመታት የቆዩት ፤ እንዲኼዱ ከፈቅድንላቸው ስለ ሐገራችን መጥፎ ነገር እየተናገሩ ስም ያጠፋሉ በእሚል ፤ በነገሥታቱ ከሐገር እንዳይወጡ እየተከለከሉ በመሆኑ ያለፈቃዳቸው ነው በኢትዮጵያ የቆዩት ፤ እነርሱም በኢትዮጵያ ከፈቃዳቸው ውጭ እንደ እሚኖሩ ነግረውኛል ይላል ።
ይኽንም በማለት ፤ የኢትዮጵያ ነገሥታት ኋላ ቀር እና ጨካኝ ናቸው የእሚል ዓይነት ውስጠ ወይራ መልዕክት ሊያስተላልፍ ፈልጓል ።
ከእላይ በብዙ አጣቅሰን እንደ አየነው ግን ፤ የኢትዮጵያ ነገሥታት ፤ በመልካም ዲፕሎማሲ እና ለሞያተኞችም በእሚደረግ ዳጎስ ያለ ክፍያ ፤ ሞያተኞችን ከአውሮፓ ያስመጡ ነበር እንጂ ፤ አላፊ አግዳሚውን ተጓዥ አውሮፓዊ እያገቱ ከሐገር አትውጡ የእሚሉ አልነበሩም ።
በተጨማሪም በእራሱ የአልቫሬዝ ዘገባ ፤ በእዚያን ወቅት በቤተ መንግሥት እያገለገሉ የነበሩ እነ እዚኽ ፤ ከጣሊያን ፣ አርሜንያ ፣ ፖርቹጋል ፣ ወዘተ ፤ የመጡ ፍራንኮች ፤ ባለ ርስት ፣ ባለ ብዙ አገልጋይ እና በቤተ መንግሥት የተከበሩ እንደ ነበሩ ይነግረናል ። ወደ ትውልድ ሐገሩ ቢመለስ የሐገር ስም ያጠፋል ተብሎ በእዚኽ የቁም እስረኛ ሆኗል የእሚባል ዓይነት ሰው ፤ በእዚኽ ኹኔታ የእሚያዝ አይመስልም ።
በተጨማሪም ፤ ነገሥታቱ አልቫሬዝ እንደ እሚለው ወደ እነርሱ የመጣውን ፈረንጅ ኹሉ የእሚያስሩ ቢሆን ኖሮ ፤ ከአልቫሬዝ በፊት የመጡ ብዙ መልዕክተኞች እና አልቫሬዝ ራሱም ከእነ አጋሮቹ ተመልሶ እንዲኼድ አይፈቀድለትም ነበር ። አውሮፓዊያኑም ከመቶ ዓመት ላላነሰ ግዜ በተከታታይ መልዕክተኛ ሲልኩም አይኖሩም ነበር ።
እዚኽ ላይ ደግሞ ፤ የግራኝ ጦር ከ15,000 በእማይበልጡት ወታደሮቹ ከ200,000 በላይ የነበረውን የንጉሥ ገላውዴዎስን ጦር ድል በመንሳት እና ለቀጣዪ አስር ዓመት ኢትዮጵያን በማወኩ ፤ አንዳንድ አርፋጅ ታሪከኞች ፤ ድሮውንም የኢትዮጵያ ነገሥታት ጥንካሬ ጉም ነበር በማለት ፤ ብዙ ይናገራሉ ።
አውሮፓዊያኖች በሙሉ ተባብረው ከሙስሊሞች ጋር ከአደረጉት ከስድስት ዙር ያላነሰ የመስቀሉ ጦርነት በአንዱ ብቻ ሲያሸንፉ በቀረው በሙሉ ተሸናፊ ነበርሩ ፣ ፖርቹጋል እና ስፔን በሙሮች ግዛታቸውን ለ600 ዓመታት እና ከእዚያኽ በላይ ተነጥቀው ነበር ፣ እስከ አንደኛው የዓለም ጦርነት ከፊል ባልካን ማለትም የምዕራብ አውሮፓ በኦቶማን ሙስሊም ቁጥጥር ውስጥ ነበር ።
እናም ፤ ከ5 መቶ ዓመት ባል አነሰ የጦርነት ዘመን ውስጥ ፤ ለ10 ዓመት የቆየ ክፉኛ ሽንፈት በኢትዮጵያ ነገሥታት ላይ መድረሱ ፤ እንዴት የኢትዮጵያዊያን ጥንካሬ ግነት እንጂ እውነታ የለውም ያስብላል? ከእዚያኽ በፊትም ሆነ በኋላ ፤ ኢትዮጵያዊያን ነገሥታት በከሐዲ ብዛት ተከበው እንኳን ፤ ከቁሪሽ እስከ ዖቶማን ተርክ ወታደሮችን ከ14ኛው እስከ 18ኛው ምዕተ ዓመት በብዙ ጦርነቶች እና ግንባሮች በተደጋጋሚ እንደ አሸነፉ በታሪክ የተመዘገበ ነው።
ስለ እዚኽ ፤ ምንም እንኳን ፤ በዋናነት በጀስዊቶች ከዳ፟ተኝነት እና በካቶሊክ ቄሶች ግብዝነት ኢትዮጵያ ለብዙ ጉዳት ብትጋለጥም ፤ ይኽም በአለፉት 3 እና 4 መቶ ዓመታት ኢትዮጵያ ከአውሮፓዊያን ጋር እኩል እንደ አትራመድ ቢይአደርጋትም ፤ አውሮፓዊያኖች የዓለም ፖለቲካ ወደ ቀኝ ግዛት ትኩረቱን ሳያዞር በፊት ፤ ኢትዮጵያን እንደ እኩል አጋር አይቶ የትብብር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሲያደርግ ነበር የእሚለው አስተያየት ነው ተዓማኒነት የአለው ።
ከእዛ ውጭ የአለው ፤ በዋናነት በካቶሊክ እና በፕሮቴስታንት ሚስዮናዊዎች ፤ በኢትዮጲያዊያን ላይ የእሚወርደው የትችት ናዳ ፤ ከእውነተኛ ግንዛቤ የመነጨ ሰአይሆን ፤ የራሱ ብዙ ሰነፍ ምክንያት የአለው ተራ አሉባልታ ነው ።
በአጭሩ ፤ በ15ኛው እና በ16ኛው ምዕተ ዓመት ፤ ኢትዮጵያ እና መንግሥቷ ፤ ከአውሮፓዊያን ነገሥታት እና ሕዝብ ፤ ከጥቂት የግንባታ እና መሰል እውቀቶች በስተቀር ፤ የእሚሻል እንጂ የእሚያንስ አልነብረም።
ለእዚኽ ክፍል መግቢያ ይኽን ከአልን ዘንዳ ፤ በዘጠኝ ክፍል ከፋፍለን በእምናየው ፤ በእዚኽ የኢትዮጲያ ታሪክ ዳሰሳችን ውስጥ ፤ እንደ እዚኽኛው ክፍል ፤ የኢትዮጲያን ህልውና የተፈታተኑ ወሳኝ የሆኑ ኹነቶች በጣም በአጭር ግዜ ውስጥ ፥ ከ104 ዓመት ባነሰ ግዜ ውስጥ ፤ የተከናውነበት የለም ።
በእዚኽ መቶ አመት ውስጥ ፤ ከውስጥም ከውጭም በተነሱ የተለያዩ የፖለቲካ መዓበሎች ምክንያት በኢትዮጵያ ታሪክ ከእዚያኽም በፊት ሆነ ከእዚያኽ በኋላ ታይቶ በእማይታወቅ መልኩ ፤ ኢትዮጲያን እንደ ሐገር የመቀጠሏ ጉዳይ የህልውና ጥያቄ ውስጥ የአስገቡ አራት ፖለቲካዊ ማዕበሎች ተነስተዋል ፤ እነርሱም ፦
ከእነ እዚኽ የወቅቱ አራት ወሳኝ ፖለቲካዊ ክስተቶች በግዜ ቅደም ተከተል ቀዳሚ የሆነው ፤ የግራኝ አህመድ ኢትዮጵያን መውረር ፤ ከይኩኖ አምላክ ጀምሮ እስከ አጼ ልብነ ድንግል ፤ ለ 257 ዓመታት ያኽል ረግቶ የቆየውን የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ርጋታ እና የእርሱንም ትሩፋቶች በመሠረታዊነት ያናወጠ ትልቅ ፖለቲካዊ ፣ ኢከነሚያዊ እና ማሕበራዊ ዳፋ የነበረው ክስተት ነበር ።
በሙሉ ስሙ ፤ አህመድ ኢብን ኢብራኺም አልጋዚ (አህመድ የኢብራኺም አልጋዚ ልጅ ወይንም አህመድ ወልደ ኢብራኺም አልጋዚ እንደ ማለት ነው) ወይንም በተለምዶ ስሙ ግራኝ አህመድ ፤ በመባል የእሚታወቀው እና በአንዳንዶች ዘንድ ሱማሌ እንደ ሆነ የእሚታሰበው ነገር ግን ብዙ ታሪካዊ ማስረጃዎች አረብ እንደ ሆነ የእሚያሳዩት ሰው ፤ እ.አ.አ. በ1530 ዓ.ም. አከባቢ ኢትዮጵያን ለማጥቃት መነሳቱ ለእሚቀጥሉት ሰባ ዓመታት ፥ በወቅቱ ኢትዮጵያን ሊያፈርስ ከመጡት አራት ትልልቅ ፖለቲካዊ መዓበላት ፊት ቀዳሚው ነበር ።
በተለምዶ ግራኝ አህመድ ሱማሌ ነው ቢባልም ፤ አረብ እንደ ሆነ ሊያመላክቱ ከእሚችሉ ታሪካዊ ኹኔታዎች አንዱ ፤ በክፍል አራቱ ላይ እንደ አልነው በኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩት ኹሉም የሙስሊም ሱልጣኔቶች ፤ ለንግድና እና ከኃይማኖታዊ ጉዳይ ጋር ተያያዥነት በአላችው ምክንያቶች ወደ ኢትዮጵያ በመጡ አረቦች የተጀመሩ እና የእሚመሩ ስለ ነበሩ እና ግራኝ አህመድም ከእነዚኽ የሙስሊም ሱልጣኔቶች የመጨረሻው እና የትልቁ የአዳል ሱልጣኔት ሱልጣን ስለ ነበረ ፤ ግራኝም አረብ እንጂ ሱማሌ ሊሆን አይችልም እንድ እንል ማድረጉ ነው።
እነ እዚኽ በኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ እና ክፍል አራት ላይ በአልነው አግባብ የእሚመሠረቱ እና የተፅዕኖ ክልላቸው በሰፈር እና በግቢ የተወሰነ ሱልጣኔቶች ፥ ይኽ ውስን ስልጣናቸው ከሸዋ መንግሥት ከአልሆነ ሱልጣን በሆኑባቸው አከባቢዎች በሙሉ ፤ በእዚያኽ አከባቢ ከእሚኖረው ከአከባቢው ነዋሪ የስልጣን ሽሚያ የለባቸውም ።
ምክንያቱም ፦ የስልጣናቸው እና የቀጣይነቱ ምንጭ ፦ ለሸዋው መንግሥት ማቅረብ የእሚችሉት የንግድ አገልግሎት በመሆኑ እና ይኽም ለሸዋው መንግሥት የንግድ አጋርነት የአስመረጣቸው እሴታቸው ፦ የእስልምና እምነት ተከታይ መሆናቸው ፣ አረብኛ ቋንቋ እውቀታቸው እንዲኹም በአረብነታቸው ምክንያት የአላቸው የወቅቱ ንግድ እውቀት እና ትስስር ፤ በሐገሬው ሰው በቀላሉ ሊተካ ስለ እማይችል ፤ ሱልጣኔቶቹን በእሚመሰርቱባቸው አከባቢ የአለው ሐገሬው ፤ በወቅቱ ከአረብነት ጋር ብቻ የተያያዙት እነ እዚኽን እሴቶች በቀላሉ ሊተካቸው ስለ እማይችል ፤ ይኽ ነው የእሚባል ስልጣናቸውን ለመንጠቅ የእሚደረግ ግፊት ከሐገሬው ሊገጥማቸው አይችልም ፥ ይኽም በመሆኑ ሱልጣኔቱን ከአረብ ቁጥጥር ውጭ የእሚያደርጉበት ፖለቲካዊ ምክንያት አልነበረም ። ይኽም ኹኔታ ፤ የአዳሉ ሱልጣን የነበረው ግራኝ አህመድ ፤ ሱማል ሊሆን እንደ አይችል ያደርገዋል ።
ፖል ሔንዝ የተባለው ፤ የኢትዮጲያ ታሪክ ጸሐፊም ፤ ግራኝ አህመድ ሱማሌ ነበር የእሚለው ጉዳይ ብዙም አሳማኝ እንደ አልሆነ በእዚኽ መልኩ ያስረዳል ፦
“ምንም እንኳን አንዳንድ የሱማሌ ብሔርተኞች ብሔራዊ ጀግናቸው ሊያደርጉት ቢሞክሩም ጉዳዩ አሳማኝ አይደለም ። በእዚኽ ወቅት የሱማሌ ሕዝብ የጋራ ማንነት አላዳበረም ነበር ። ዛሬ ወደ ያዙት አከባቢ ገና በመስፋፋት ላይ ነበሩ ። የግራኝ የጦር ኃይል ፦ ከማሮች ፣ ሐረሪዎች ፣ ሶማሊዎች ፣ አረቦች ፤ ተውጣጥቶ እንዲኹም ጥቂት ቱርኮች ያጠናከሩት ነው የነበረው ። የጋራ መግባቢያ ቁንቋዋቸው አረብኛ ነው የነበረው ፤ አንድ አድርጎ የአስተሳሰራቸው ዓላማም ለእስልምና የአላቸው ተዓማኝነት ነው ።“
“Though some modern Somali nationalists have attempted to make him a national hero, the case is Unconvincing. Somali tribes had not developed a sense of common identity in his time. They were still in the process of expanding into the territories they eventually occupied. Gragn's forces were composed of Mars, Hararis, Somalis and Arabs and were augmented by a few Turks. Their common language was Arabic and their sense of purpose lay in their loyalty to Islam. [35]“
ስለ እዚኽ ፦ ተቀባይነት ባላቸው ታሪካዊ ማስረጃዎች ላይ የተመረኮዘው ግምት ፤ ግራኝ አህመድ በኢትዮጵያ ከነበሩት የሙስሊም ሱልጣኔቶች የመጨረሻው እና የትልቁ አዳል ሱልጣኔት ሱልጣን የሆነ ፤ የአረብ ሙስሊም እንጂ ሱማል አይደለም ፤ የእሚልው ነው የበለጠ ተዓማኒነት የአለው ።
አረቡ ግራኝ አህመድ በእዚኽ ዘመን ቢኖር እና በነበረበት ወቅት የነበረውን በኻሪ ቢላበስ ፥ በፖለቲካ አስተሳሰቡ እና ዘዬው ከአፍጋኒስታን ታሊባን ሙጂኻዲኖች ጋር ሳይዛነፍ የእሚገጥም ነው ። በእርግጥ ፥ ሐበሻን መቀራመት (The Conquest of Abyssinia) የእሚለውን መጽሐፍ የጻፈው ፥ ሲሐብ አላዲን የተባለው ፤ አረብ የግራኝ ታሪክ ጸሐፊ ወይንም የግራኝ ዜና መዋዕለኛ ፥ ግራኝን ሲያሞግሰው ፦
“...ሱልጣኑ ፥ ኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሒም አልጋዚ ፥ ሙጅሐዲው…።”
“...the sultan, the imam Ahmad bin Ibrahim al-Gazi, the mujahid... [34]“
እያለ ነው ።
በሚርያም ዌብስተር ፥ መዝገበ ቃላት ትርጓሜ ፥ ሙጃኺድ ወይንም የብዙ ቁጥር የሆነው ሙጃኺድን ማለት ፦ በዘመናዊ ትርጉሙ ፥ ለእስልምና ኃይማኖት ሲል የሽምቅ ውጊያ የእሚያካኺድ ግለሰብ ማለት ነው ፦
“ሙጅኺዲን [ ብዙ ቁጥር] ፡ በተለይ በሩቅ ምሥራቅ የእሚገኝ እስላማዊ የሽምቅ ተዋጊ ።”
“Mujahideen [plural] : Islamic guerrilla fighters especially in the middle east.”
በቀደምት አረቦች ትርጉም ደግሞ ጅሀድ የእሚያደርግ ጦረኛ ማለት ነው ።
ግራኝ አህመድም ልክ እንደ ታሊባኖቹ ፤ የእስልምና እምነት ተከታይ ብቻ ሰአይሆን ፥ የእስልምና ሕግ ውልፍ ሳይባል በሰይፍ ጉልበትም ከአልተተገበረ ፤ በሙስሊም መሪም ላይ ቢሆን ጦር ለማንሳት እና ለማመፅ ዝግጁ የሆነ ሰው ነበር ። የወታደራዊ እንቅስቃሴውን የጀመረውም ፤ እንደ እርሱው አረብ እና ሙስሊም የሆነው እና የአዳል ወይንም የዘይላ ሱልጣን የነበረው ጋራድ አቡን ፤ የቁራንን መንገድ በትክክል አልተከተለም ብሎ በማመፅ ነው ፦
“ኢማም አህመድ ፤ ሱልጣኑ እና ወታደሮቹ ፤ በድፍረታቸው ከቁራን እና ከሱና መንገድ ወጥተው የተከለከለውን ነገር ማድረግ በመጀመራቸው ፤ የአቡ ጋራድ ወታደር ከነበሩት የተወሰኑትን የሐገሩን ነዋሪዎች አስከትሎ ፥ ሸሸ…።”
“When the imam Ahmad realized that the sultan and his army had left the path of the Qur'an and the Sunna by their daring to do what was forbidden, and their ignoring of the prohibition against illicit acts, he took to flight, accompanied by people of the country who had formed part of the army of Garad Abun. [34]“
ይኽ የግራኝን መንፈሳዊ ቅናትን የእሚዘግበው ታሪክ ፤ የግራኝን ሙጅኺዲነት ከማሳየቱ በአሻገር ፤ ግራኝ ሱማል ወይንም የሐገሬው ሰው እንደ አልሆነ የእሚጠቁምም ነገር አለው ። ምክንያቱም ፦ ‘የጋራድ አቡን ወታደሮች ከነበሩት ውስጥ የሐገሩን ነዋሪዎች አስከትሎ …’ የእሚለው ሐረግ ፤ በግራኝ እና የሐገሩ ነዋሪዎች መካከል እርሱ እና እነርሱ የእሚል ዓይነት ልዩነት የእሚያስቀምጥ ስለሆነ ፤ ግራኝ የሐገሬው ተወላጅ አይደለም ብለን እንድናስብ ያደርገናል ። በሌላም ቦታ እንደ እዚኹ ፥ አልኮል የእሚጠጡ ሱማሎችን አሳደዳቸው ይላል ፦
“ክፉ በእሚያደርጉት በሱማሎች ላይ ፥ በረታባቸው ። ሱማሎቹም ተበታተኑ ፥ ኢማም አህመድም የአንድ ቀን መንገድ ያኽል የእሚሆን አሳደዳቸው ፤ ወደ ባህሩ ዳር እስኪ ደርሱ ድረስ ሸሹ ። ሐገራቸውን ካወደመ እና ከዘረፈ በኋላ ተመለሰ።”
“But then he doubled back towards the country of the Somali evildoers. The Somalis were routed, and the imam Ahmad followed them almost to the sea, a day’s march. He plundered their territory thoroughly and devastated it. Then he turned round and went back. [34]“
በእዚኽኛውም ዘገባ ጸኃፊው ፦ በግራኝ እና በሶማሎቹ መካከል ልዩነት አድርጎ ፤ ኢማሙ ሱማሎቹ ላይ በረታባቸው ፣ እስከ ባህሩ ድረስ አሳደዳቸው ፣ ሐገራቸውን አወደመ ፣ ዘረፈ ፣ የእሚልበት አግባብ ፤ በግራኝ እና በሶማሎቹ መካከል ከኃይማኖት የአለፈ ነገዳዊ ልዩነት እንደ አለ በደንብ የእሚያሳይ ነው ።
በተጨማሪም ይኽ ታሪክ እንደ እሚያሳየን ፤ ግራኝ አህመድ ፥ የሐይማኖቱ ቀናዒ የሆነ እና ፤ ኃይማኖቱ እርሱ በእሚረዳው መልኩ ቃል በቃል ፤ ከአልተተገበረ ከማንም ጋር ጦር ለመማዘዝ ፤ ፍላጎቱ እና አቅሙ የአለው ሰው የነበረ መሆኑን ነው ። በእዚኽ ቅናቱም ፥ የእስልምናን ሕግ ፤ በሰይፍ ጉልበት በሶማሎች ኹሉ ላይ መጫን ችሏል ። ሲሐብ አላዲንም ይኽን ግራኝ አህመድ ሶማልችን በሰይፍ ጉልበት ያሰለመበትን አግባብ እንዲኽ ያስቀምጠዋል ፦
“ቢፀየፉትም እንኳን ፥ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ተጫነችባቸው ።”
“The command of God prevailed, even though they detested it. [34]“
ይኽም የሲኃብ አድ አዲን ገለፃ ፤ በድጋሚ በግራኝ እና በአከባቢው ነዋሪዎች መካከል ፤ ልክ ከላይ እንደ አሉት ኹለት ገለፃዎች ፤ ‘እርሱ እና እነርሱ’ የእሚል ዓይነት ክፍፍል ስለ እሚያደርግ ፤ ግራኝ አረብ ወይንም ከአከባቢው ነዋሪ እንደ አልተወለደ የእሚያመለክት ነገር አለው ።
ከእዚያኽ በተጨማሪም ፤ ከታሪኩ በግልፅ እንደ እምናየው ሱማሌዎች በክፍያ ለእነ እዚኽ ሱልጣኔቶች የውትድርና አገግሎት የእሚሰጡ እንጂ በሐይማኖታቸው ምክንያት የሱልጣኔቶች ወታደሮች የእሚሆኑ በአለመሆናቸው ፤ ከእነርሱ መካከል ይኽን ዓይነት የፖለቲካ ስልጣን ፣ ኃብት እና የውጭ ሙስሊም መንግሥታትን እርዳታ ገና በ18 ዓመቱ ማግኘት የእሚችል ሱማሌ የመፈጠሩ እድልም በጣም ጠባብ ነው ።
ስለ እዚኽ ፥ የራሱን ታሪክ ጸሐፊ ዋቢ አድርገን ስናየው ግራኝ የአረብ ተወላጅ እና ፖለቲካዊ መሠረቱም ፤ ጀብደኝነት እና እስልምናን በመንግሥታዊ ኃይል ለማስቀጠል ከአለው ፍላጎት ፣ ቁርጠኝነት እና አቅም የመነጨ መሆኑን እናያለን ። ግራኝ እስልምናን በመንግሥታዊ ኃይል የማስፋፋት ፍላጎቱ እና ቁርጠኝነቱ ብቻ አልነበረም የነበረው ፤ ምንም እንኳን አንዳንድ ግዜ ወደር የሌለው ጭካኔ ቢያሳይም ፤ ቀላል የእማይባል እንዲያውም ለየት ያለ ጀግንነት እና ጦርነት የመምራት ክህሎት የአለው ፤ ውጤታማ የጦር ጀነራልም ነበር ።
ይኽን ዓይነት የአጉል ጀብደኝነት ስብዕና እና የተወናበደ ኃይማኖታዊ ቀንዓዊነት የተላበሰው ግራኝ ፤ ኢትዮጵያን ማጥቃት እንዲፈልግ እና እንዲችል ያደረጉት ብዙ ውስብስብ ታሪካዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢከነሚያዊ እና ስነ ልቦናዊ ምክንያቶች እናገኛለን ።
በእዚኽ ረገድ የመጀመሪያው ምክንያት ፤ በክፍል አራት ላይ የዓየነው ብዙ መቶ ዓመታት የአስቆጠረው በሸዋ እና በተለያዩት የሙስሊም ሱልጣኔቶች መካከል የነበረው ግጭት ነው ።
በክፍል አራቱ ታሪክ ላይ እንደ አልነው ፤ በሸዋ እና በሙስሊም ሱልጣኔቶቹ መካከል ለረዥም ግዜ የቆየው ግጭት ፤ በዋናነት ኢከነሚያዊ የኾነ እና ብዙ ግዜ ግን ኃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ሽፋን የእሚሰጠው የነበረ እና መነሻውም ፦ የሙስሊም ሱልጣኔቶቹ ፤ በወቅቱ የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ላይ የአላቸውን ብቸኛ አስመጪ እና ላኪነት ፤ ለሌላ ሙስሊም እንኳን ለማጋራት በአለ መፈለግ እና በእዚኽ የንግድ ሥራ ላይ የአላቸውን ሞኖፖሊ ተቀናቃኝ ሲመጣባቸው ፤ ተፎካካሪ ሲራራ ነጋዴውን ከማገት ጀመሮ የተለያዩ ሌሎች የማደናቀፍ ተግባራትን የእሚፈፅሙ በመሆናቸው ነው ።
ይኽ የአደናቃፊነት ተግባራቸው ፤ ከሸዋው መንግሥት ጋር የእሚፈጥረው አለመግባባት በንግግር አልፈታ ብሎ ወደ ግጭት ሲያመራ ደግሞ ሲያመች ሌሎቹን የሸዋ ገባር አናሳ መንግሥታት ፤ የሸዋው መንግሥት እያስገበረ እየበዘበዛችኹ ነው በሎ በመቀስቀስ ማሳመፅ ፤ እርሱም ሳይሳካ ወይንም ከእርሱ በተጓዳኝ ደግሞ ቀጥታ በኢትዮጵያ ላይ ጅኃድ በማወጅ በገንዘባቸው መግዛት የእሚችሉትን የሐገርም ሆነ የውጭ ወታደር ይዘው ፤ በጅኃድ ኢትዮጵያን ማስለም አለብን በእሚል ፤ የጦርነት ነጋሪት ሲጎስሙ ነው በአብዛኛው ዘመናቸውን የፈጁት ።
ይኽ እድሜ ጠገብ በእየግዜው የእሚያገረሽ የነበረ በክርስቲያን ኢትዮጵያ እና በሙስሊም ሱልጣኔቶች መካከል የነበረ ጦርነት ደግሞ አንድ ግዜ ከተጀመረ በኋላ ፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በድል አሸብርቀው የነበሩት ሙስሊሞች ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የደረሰባቸው ተከታታይ ሽንፈት እና ይኽን ተከትሎ የግድ የእሚፈጠሩት ደም መቀባባቶች እና መቃቃሮች ፤ በመቶ ለሚቆጠሩ ዓመታት የተዳፈነ ረመጥ በመሆን ፤ ለግራኝ ጦርነት መጀምር ከነበሩት ብዙ አቀጣጣይ ምክንያቶች አንደኛው ሆኗል ።
ይኽ ከእላይ የአልነው በሐገር ውስጥ የነበረውን የጦርነቱን አቀጣጣይ ምክንያቶች ሲያሳይ ፤ ከውጭ ደግሞ በወቅቱ የእስልምናው ዓለም መሪነት ከአረቦች የተረኩበት ቱርኮች ከአውሮፓዊያኖች እና ሙስሊም ከአልሆነው ከቀረው ዓለም ጋር ከገቡበት ግጭት ጋር ይያዛል ።
እንደ እሚታወቀው እስልምና በወታደራዊ ኃይል እምነቱን ማስፋፋት የቀኖናው አካል በመሆኑ ፤ ከመካ ጀምሮ በመላው ዓለም ራሱን የአስፋፋው በወታድራዊ ኃይል ነው ። ይኽም በመሆኑ ፤ ጠንካራ የክርስቲያን ማሕበረሰባት የሌለባቸው አከባቢዎች እና ሕዝብ በሰይፍ ጉልበት ከአሰለመ በኋላ ፤ በእዚኽ ኺደት ያካበተውን ኃብት እና ልምድ ቀምሮ ፤ ድንበሩን ወደ ክርስቲያን ሐገራትም መግፋት ጀምሮ ነበር ። በተነፃፃሪ ደግሞ ፤ ከሮም ወውደቅ በኋላ ፤ በእንግሊዝ ፣ በስፔን ፣ በፖርቹጋል ፣ በፈረንሳይ ፣ በጣሊያን ፣ ወዘተ ፤ ጠንካራ የክርስቲያን ባለ አባቶች እየተፈጠሩ እና እነ እዚኽም የክርስቲያን በአላባቶች ለሮማው ጳጳስ በአላቸው ታዛዥነት ምክንያት ፤ ለምሳሌ ፦ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች ላይ የእሚደርሰውን በደል ለማስቆም በእሚል በሮማው ጳጳስ የመስቀሉ ጦርነት ጥሪ ሲደረግላቸው ለመዝመት ፈቃደኛ ነበሩ ። ይኽም ታሪካዊ ክስተት ነው ፤ ባለ ብዙውን ዙር የመስቀሉን ጦርነት የአስከተለው ።
እንደገናም ፤ የሙስሊሙ መንግሥት ፤ በደቡብ ምዕራብ አውሮፓ ፤ በኢቤሪያን ወሽመጥ (Iberian Peninsula) ላይ የእሚገኙትን ፖርቹጋል እና ስፔን የክርስቲያን ግዛቶች በኃይል ይዞ ለረዥም ዘመን ከቆየ በኋላ ፤ የአከባቢው ክርስቲያኖች ራሳቸውን እንደገና በማደራጀት ፤ በፖርቹጋል እና ስፔን ሪኮንኪስታ (Reconquista: በእስልምና ወታደራዊ ኃይል የተወሰዱ ቦታዎችን እንደገና ማስመለስ) የእሚል እንቅስቃሴ በማድረግ ፤ በኃይል የተወሰደባቸውን መሬት እንደ ገና በኃይል አስመልሰዋል ።
ክርስቲያኖች በደቡብ ምዕራብ አውሮፓ ይኽን ድል ሲያገኙ ፤ የእስልምናውን ኢምፓየር መሪነት ከአረቦች የተረከበው የዖቶማን ተርኮች መንግሥት ፤ በምሥራቅ ለረዥም ዘመን ታሪካዊ የክርስቲያኖች ግዛት ሆና የቆየችውን ፤ የምሥራቃዊው የሮም መንግሥት አካል ቤዛንታየም በኃይል ሰብሮ ገብቶ ኮንስታንቲኖፖልን መናገሻው አድርጓት ነበር ።
በአጠቃላይ ፤ እየተለወጠ በመጣው ዓለም ዓቀፋዊ ፖለቲካ ምክንያት ፤ ክርስቲያኖች ሪኮንኪስታውን ለማስቀጠል እና የወቅቱ የእስላምና መንግሥታት ፤ ከህንድ እና ቻይና ገበያ ጋር አውሮፓን እና የተቀረውን ዓለም የእሚያገናኘውን ፤ የባሕር እና የየበስ የንግድ መንገድ እንዲኹም ኢየሩሳሌምን ተቆጣጥረው ፤ ክርስቲያኑን ዓለም ፤ ከመንፈሳዊ ‘መዓከሉ’ እና ከዓለም ዓቀፍ የንግድ ጎዳናዎች በማገድ ፤ እነ እዚኽን መንፈሳዊ መዓከላት እና መንገዶች በመጠቀም የእሚገኙ ኃማኖታዊ ፣ ኢከነሚያዊ እና ባህላዊ ጥቅሞች እንደ አያገኝ ከልክለውት ስለ ነበር ፤ አምባገነኑን የሙስሊም ኃይል ከእዚኽ የትምክህት ማማው ላይ ማውረድ ፤ የኹሉም ክርስቲያን እና ሰላም ወዳድ የዓለም ሕዝብ የጋራ ፍላጎት በመሆን ሪኮንኪስታውን ዓለም ዓቀፋዊ ማድረግ ፤ በተለይ የመላው የክርስቲያን ሐገራት የጋራ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከሆነ ውሎ አድሮ ነበር ።
ይኽም ደግሞ የዖቶማን ተርኩ መንግሥት በተራው ፤ ከእዚኽ ልማዳዊ የኢፍትኃዊ የስልጣን ማማው ላይ ለአለመውረድ የህልውና ትግል እንዲ ያደረግ የእሚጋብዘው በመሆኑ ፤ ወቅቱ ዓለም በእዚኽ መልኩ የተፋጠጠበት ነበር ።
በእዚኽ ወቅት ፤ የእዚኽ የትልቁ እና የአምባገነኑ የእስልምና ዓለም የበላይ የነበረው የዖቶማን ተርክ ፤ በእዚኽ መልኩ የዓለም ሕዝብ እንደ ተነሳበት ማወቁ እና ኢትዮጵያ የቀሲስ ዮሐንስ ሐገር በእሚል ከአውሮፓዊያን ጋር የእምታደርገው ትብብር ፤ ከፍተኛ የሕልውና ስጋት ስለፈጠረበት ፤ በእዚኽ ፀረ-ሞኖፖሊ እንቅስቃሴ ውስጥ ስልታዊ ሚና መጫወት የእምትችለውን ክርስቲያን ኢትዮጵያ ለማጥቃት እድሜ ጠገቡን የሙስሊም ሱልጣኔቶች ትንኮሳ በኃይል ረገድ ማገዝ አዋጭ ሆኖ በማግኘቱ ፤ ኢማሙን ግራኝ አህመድን ፤ በወታደር ፣ በትጥቅ እና በስልት በማገዝ ፤ የግራኝን ጦርነት ፤ ከነበረው እላይ ከጠቀስነው ሐገራዊ ምክንያት በአሻገር ዓለም ዓቀፋዊ ምክንያት እንዲኖረው አድርጎታል ።
የወቅቱ የዓለም ልዕለ ኃያል ዖቶማን ተርኮች ፤ ከአውሮፓ ክርስቲያን እየመጣባቸው የአለውን ግፊያ ላይ ኢትዮጵያ ተባባሪ መሆኗን ስለ ተረዱ ፤ ኢትዮጵያን ለማጥቃት በመወሰናቸው ፤ ለግራኝ የጦር መሳሪያ እና የወታደር እገዛ በማድረግ ፤ ለእዚኽ ጦርነት ከሐገራዊው ምክንያት በአሻገር ዓለም ዓቀፋዊ ምክንያት መሆናቸውን በተመለከተ ሪቻርድ ፓንክረስት እንዲኽ ብለዋል ፦
“ከኢማሙ ጋር የተያያዘው ሰልፍ ፤ እጅግ ወሳኝ ዓለም ዓቀፍ ደርዝ የአለው በመኾኑ ፥ በቀጣይነት በክርስቲያኖቹ ፖርቹጋሎች እና በሙስሊሞቹ ዖቶማን ተርኮች መካከል ከእሚካኼደው ዓለም ዓቀፍ ጦርነት ጋር እየተጠላለፈ ነበር ።”
“The warfare associated with the imam, which had an important international dimension, became increasingly enmeshed in the global conflict between the Christian Portuguese and the Muslim Ottoman Turks. [34]“
ለግራኝ ጦርነት ፤ ነባራዊው በኢትዮጵያ ክርስቲያን ነገሥታት እና በሙስሊም ሱልጣኔቶቹ መካከል ለዘመናት የነበረው ግጭት ከውስጥ ፤ ከውጭ ደግሞ በዋናነት በክርስቲያኖች በዋናነት ደግሞ በፖርቹጋል እና በቱርኮች መካከል ይካኼድ የነበረው ግብግብ የጦርነቱ አቀጣጣዮች ሲሆኑ ፤ በእዚኽ ላይ ፤ የግራኝ ስብዕና ፦ የጦር ስልት አዋቂነቱ ፣ ጀግንነቱ ፣ ሽፍታነቱ እና ኢትዮጵያን የማጥቃት ከምክንያት የአለፈው አንገብጋቢ ምኞቱ ፤ ከእነዚኽ ኹለት ምክንያቶች የአልተናነሰ ጦርነቱን የማፋፋም ሚና የነበረው ነው ።
ግራኝ እንደ እዚኽ ወረራ መሪ ይኽን ወረራ በማስቀጠል እና ውጤታማ በማድረግ ረገድ ፤ ከፍተኛ ሚና የአለው በመሆኑ ፤ በእዚኽ ወረራ ላይ የነበረውን አስተሳሰብ እና ግራኝ እንደ ግለሰብ የአለውን በኃሪ ማየቱ ተገቢ ይሆናል ።
የመጀመሪያው ጉዳይ ፤ ግራኝ በአንድ በአልታወቀ ምክንያት ፤ ኢትዮጵያ ላይ የእሚችለውን ዓይነት ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ የእሚፈልግ እና በእዚኽም መልክ ኢትዮጵያን ለመጉዳት መፈለግ ብቻ ሰአይሆን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ይኽንን ፍላጎቱን ያለምንም ፍርኃት ለማሳካት እስከ ህይወት መስዕዋትነት ድረስ ዋጋ ለመክፈል ሙሉ ዝግጁነት የነበረው ሰው መሆኑ ነው ።
ግራኝ ምንም እንኳን ፤ ይኽን የመሰለ የእሚነዳው ውሳጣዊ ፍላጎት ፥ በደንብ ከዓየነው ደግሞ ‘ዕብደት’ ቢኖረውም ፤ ይኽ ፍላጎቱ ወይንም ‘ዕብደቱ’ በአግባቡ በተዘጋጀ እና የመሳካት እድል በአለው የጦርነት እቅድ እና ግብ የእሚመራ አልነበረም ። በዋናነት በድል ስካር መንፈስ የእሚመራ እና ተለዋዋጭ ወይንም ወጥነት የሌለው አካኼድ የእሚከተል ነበር ።
ለምሳሌ ፦ ምንም እንኳን ፤ ከእርሱ በፊት እንደ ነበሩት እና ከሸዋ ጋር ረዥም ዘመን የቆየ ግጭት ውስጥ እንደ ነበሩት ሱልጣኔቶች ፤ አንዳንድ ግዜ ኢትዮጵያን ማስለም አለብኝ የእሚል አካኼድ ሲከተል የእሚታይ ቢሆንም ፤ በኢትዮጵያ ጦርነቱን ሲጀምር ፤ እንደ ማንኛውም ወታደራዊ ሽፍታ ፤ ድንገተኛ ጥቃት ሰንዝሮ የአገኘውን ዘርፎ የመመለስ አካኼድ ነበር ይከተል የነበረው ።
ይኽንንም ፤ በጦርነቱ ውስጥ ለዓመታት ከቆየ በኋላ ፤ ምርኮ እንቀያየር በማለት ለንጉሥ ልብነ ድንግል በጻፈው ደብዳቤ ላይ በግልፅ ተናግሮታል ፦
“ከእዚኽ ቀደም እንደ እምናደርገው ፤ ጥቃት አድርሰን ወደ ሰፈራችን የእምንመለስ አይምሰለህ ። ከእዚኽ በኋላ ፥ እግዚአብሔር ሐገሪቱን በሙሉ እንድ እንገዛ ሰአያደርገን አንመለሰም ይኽም በአይሳካ እና የእግዚአብሔር ፈቃድ ቢሆን ለመሞት ዝግጁ ነን ፤ ‘በዳኝነቱ ወደር የሌለው እግዚአብሔር ፤ በመካከላችን ይፈርዳል’።”
“You should not think of us as we were before, making an incursion and then going home. This time we shall not return until God has conquered the country for us - if it be God’s will - or we have died: “Thus he will judge between us, and he is the best of Judges [34]“
ከእዚኽ ከራሱ ኑዛዜ እንደ እምንረዳው ፤ መጀመሪያ ላይ ወይንም ይኽን ደብዳቤ ከጻፈበት ግዜ በፊት ግራኝ ይታወቅበት የነበረው ባሕሪው እና እርሱም ራሱን ይረዳበት የነበረበት አግባብ ፤ አደጋ ጣይ ዘሪፊ ጦር መሪ እንደ ነበር ነው ።
በእዚኽ ኑዛዜው እና ከእዚኽ በታች እንደ አለው አዋጁ የአለውን መላውን ኢትዮጵያን የመቆጣጠሩን እቅዱን ወይንም ምኞቱን ያመጣው ፤ ጦርነቱ ለዓመታት ከተካኼደና ሐበሾቹ አይችሉኝም ብሎ ከአሰበ በኋላ ነው ፦
“አኹን እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ድልን ሰጥቶናል ፥ ሐፍረትን አከናንቦዋቸዋል ፤ አኹን ንጉሡ ወደ እሚኖርበት ቦታ … ኼደን እናውድመው ። አብሲንያን እንውረራት ፥ ድል ነስተን እናዳክማት።”
“Now that God has given us the victory over them, and has humiliated them, now let us march on to … the place where the king’s residences are, to take him, and to demolish it. Let us occupy Abyssinia, conquering the country, and weakening them. [34]“
እንደ ገናም ፤ ትንሽ ወረድ ብለን እንደ እምናየውም ፤ ብዙ የተባለለትን የመጀመሪያውን እና ትልቁን የሽምብራ ኩሬው ጦርነት ፤ በአስገራሚ ኹኔታ ከአሽነፈ በኋላ ፤ ከሽምብራ ኩሬ ብዙ ኪሎ ሜትር ወደ ኋላ ወደ ሐረር ተመልሶ ፤ ለአንድ ወር ምንም ዘመቻ ሳያደርግ ተቀምጧል ።
ይኽም ወደ ጦርነቱ መሐል ላይ እየ አንፀባረቀ የመጣው መላው ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ፍላጎት፤ እኔ ከጦርነት ውጭ ህይወት የለኝም ፤ ስለ እዚኽ እስከ እለተ ሞቴ ስዋጋ እናራለሁ ከእሚል የጦርነት ናዋዥነት ወይንም በጅኃድ ጦርነት ለመሰዋት ካለ ፍላጎት ወይንም ከሙጅኃዲነት ከእሚመነጭ የአጥፍቶ ጠፊነት ስነ ልቦናው ፤ የእማይጨበጥ ትልቅ ህልምን የማታገያ አጀንዳ አድርጎ ለማቅረብ ከመፈልግ የመነጨ እንጂ ፤ የኢትዮጵያን ስፋት ፣ የሕዝቦቿን የቆየ የክርስትና እምነት ተከታየነት እና ነባራዊ ፖለቲካዊ ፍላጎት ፣ እርሱ ይዞ የእሚንቀሳቀሰውን ጦር ፣ ወዘተ ፤ ከግምት የአስገባ ወይንም በአጭሩ ፥ ሊሳካ እና ሊተገበር የእሚችል እቅድን መሠረት የአደረገ አልነበረም ።
አብዛኛው ሕዝብ እድሜ ጠገብ የክርስቲያን እምነት ተከታይ በአለባት ፣ ሰፊዋ እና የመሠረተ ልማት በበቂ ኹኔታ በአልነበረባት የ16ኛዋ ምዕተ ዓመት ኢትዮጵያ ፣ ግራኝ ይዞ ከእሚንቀሳቀሰው ቢበዛ ከ10 እስከ 15 ሺ የእማይበልጥ ወታደር የአለው ሠራዊት ይዞ ፣ በእየግዜው እርሱ ይዞ ከእሚንቀሳቀሰው ሠራዊት አራት እና አምስት እጥፍ የበዛ ሠራዊት በእምታዘምትበት ፣ ይኽም የያዘው በተነፃፃሪነት አናሳ ጦር ለአስር ዓመት ፥ ይኽ ነው የእሚባል የእሚጨበጥ ግብ ሰአይኖረው በሰፊዋ ኢትዮጲያ ለዓመታት በጦርነት ሲዳክር ከመቆየቱ የተነሳ በመሰላቸት ፣ በማጉተምተም እና በክዳት ተሞልቶ ፤ ኢትዮጵያን የእምታኽል ትልቅ ሐገር መቆጣጠር እና ማስለም አይቻልም ።
በእርግጥ በሰይፍ ጉልበት ያሰለማቸው ኢትዮጵያዊያኖች የነበሩ መሆኑ በታሪክ የተመዘገበ ቢሆንም ፤ ይኽ ግን ቋሚ አካኼዱ አልነበረም ፦
“ከእዚያኽም ወናግ ጃን የባሊን ሕዝብ እንዲህ አላቸው ፤ ‘ወደ እስልምና ግቡ እና በሙስሊም የታረደውን ብሉ ፤ አለበለዚያ በመሪዎቻችኹ ላይ ያደረኹትን አደርግባችኋለሁ’ ይኽንም ተከትሎ ትንሽ ትልቁ ሙስሊም ሆነ ።”
“Then Wanag Jan said to the people of Bali. ‘Convert to Islam, and eat the meat slaughtered by the Muslims; otherwise I will do to you what I did to your leaders,’ So all of them converted to Islam, great and small alike. [34]“
እንደ እዚኽ በሰይፍ ኃይል ያሰለማቸው ሰዎች እንደ አሉ ኹሉ ፤ በራሱ ታሪክ ጸሐፊ ዘገባ ፤ የግራኝ ጦር በደረሰበት ስፍራ ኹሉ ፤ የአገኘውን ሐብት ሲዘርፍ ፤ ሐገሩን በሙሉ ሲያቃጥል ፤ የቻለውን አግዞ በባርነት ወደ ህንድ ሲሸጥ ነበር ፦
“ሙስሊሞቹ ያለፉበት ፤ ዱካው እስኪጠፋ ድረስ የአላቃጠሉት የአረማዊያኑ[8] መንደር የለም ።”
“The Muslims never passed by an infidel village without destroying every trace of it. [34]“
ግራኝ በእዚኽ መልኩ መንደራቸውን ሲያወድም አግኝቶ የማረካቸውን የየመንደሩ ነዋሪዎች እያፈነ በባርነት ይሸጣቸው ነበር ። እንደ ሪቻርድ ፓንክረስት በእዚኽ መልኩ በአብዛኛው የሸጣቸው ኢትዮጵያዊያን የኼዱት ጉጅራት ወደ እሚባለው የህንድ ክፍል ነው ፦
“ጉጀራት ፥ የእምትባለው የህንድ ግዛት … በዘመቻው ወቅት በኢማሙ የተያዙት አብዛኛዎቹ ምርኮኞች ባሪያ ሆነው መዳረሻቸው ነበር ።”
«…Gujarat, the region of India …, and the destination of numerous slaves captured by the imam in the course of his campaigns. [34]“
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ፤ መንግሥቱ ሐይለማሪያም ፥ የታሪክ እውቀታቸው ምን ያህል ተጠቃሽ ሊያደርጋቸው እንደ እሚችል በአላውቅም ፤ ታሪክን ፥ በታሪክ ሙህራን እውቀት ላይ እንጂ በፖለቲካ ትርክት ላይ ለአለማንተራስ ከአላቸው ፍላጎት እና እንደ ርዕሰ ብሔርነታቸው ፥ የቅርብ ግዜ ታሪክ ውጤት የሆኑ ሐገራዊ ኹነቶች ላይ ከመደበኛው ሕዝብ የተሻለ መረጃ ይኖራቸዋል ብዬ ስለ አሰብኩ ፤ ትግላችን [112] በእሚል በአሳተሙት መጽሐፍ ላይ ከእነ እዚኹ ሌሎች የታሪክ ዘጋቢዎች ጋር የእሚስማማ ነገር ፤ ስለ ግራኝ ወረራ የአውዳሚነት የእሚገልጽ ዘገባ በራሳቸው መንገድ እንደ እዚኽ በእሚል አስቀምጠዋል ።
ግራኝ አህመድ አደረጋቸው ከአሉት ተግባራት መካከል ፦
ብለው ሲገልጹ ፤ በእዚኽም ፥ የግራኝ አህመድ ግብር ላይ አስተያየት ሲሰጡም ፦
“የጠላውን ወይንም ተፋላሚውን ገዢ መደብ ወይም መንግሥት በመበቀል ታግሎ መጣልና ብሎም የፖለቲካ ስልጣን በመቆናጠጥ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሐገር ብቻ ማድረግ አንድ ነገር ነው ።…ንብረት እና የተፈጥሮ ኃብት እየጠራረጉ ወደ አረብ ሐገሮች መላክ ያነሰ ይመስል…አስገድዶ ከሐገራቸው በማስወጣት በባርነት ወደ ባዕድ ሐገር መላክ ግን ማንኛውም እምነት ወይንም ኃይማኖት ተከታይ የሆነ ሰው ልጅ ህሊና የእማይቀበለው እጅግ ወራዳ ድርጊት ነው ። [112]”
ይኽን መሰሉ ፤ ቅርስ ማቃጠል ፣ ከብት መንዳት ፣ ንብረት መዝረፍ ፣ ዜጎችን እያጋዙ በባርነት መሸጥ ፣ ወዘተ ፤ የአንድን ሐገር መሠረት የሆኑ ሕዝብን እና ታሪካቸውን ከማጥፋት ጋር እንጂ ፤ ኃይማኖትን ለመከላከል ወይንም ለማስፋፋት ከእሚደረግ ጅኃድ ጋር አብሮ የእሚኼድ በአለመሆኑ ፤ የግራኝ ጥቃት ቋሚ ግብ በሌለው ‘ዕብድ’ ጀነራል የእሚመራው ጦርነት ነበር ማለት ይቻላል ።
ሌላው ስለ ግራኝ ሊባል የእሚገባው ነገር ነው ብዬ የእማስበው ፤ ግራኝ በጦርነት ሱስ መናወዙ ፤ ወይንም ይኽ ነው የእሚባል የእሚጨበጥ እና ፋይዳ የአለው ወታደራዊ እና ሕዝባዊ ግብ ሰአይኖረው እስኪ ሞት ድረስ መዋጋት መፈለጉ ፤ የእውነተኛው ኃይማኖት ተከታይ በመሆኑ ከአምላክ የተሰጠው ፀጋ አድርጎ ሳይወስደው የቀረም አይመስልም ።
ክርስቲያን ንጉሥ እና የክርስቲያን ሐገርን እየተዋጉ መሞት ክብር ነው ብዬ ሕይወቴን በጦርነት ኖሬ ለማለፍ በእሚል የጦርነት ሱሰኛ የሆንኩት ፤ እውነተኛውን ኃይማኖት ከመከተሌ የተነሳ ‘አምላክ’ የሰጠኝ ፀጋ ነው ብሎ እንደ እሚያምን ብዙ ይስተዋልበት ነበር ።
እላይ ፤ ከልብነ ድንግል ጋር ምርኮኛ እንቀያየር ለማለት በጻፈው ደብዳቤ ላይ ፥ የእማደርገው ጦርነት ጅኃድ ስለሆነ ፤ እውነተኛው ዳኛ እናንተን እንድ አሸንፍ ፈቅዷል ፤ ከአልሆነም እና ከሞትኩም ያለ እርሱ ፈቃድ ነው የመጣኹት ለማለት ‘…ይኽም በአይሳካ እና የእግዚአብሔር ፈቃድ ቢሆን ለመሞት ዝግጁ ነን ፤ ‘በዳኝነቱ ወደር የሌለው እግዚአብሔር ፤ በመካከላችን ይፈርዳል’’ ማለቱ ይኽንን እንደ አሰበ በግልፅ ያሳያል ።
ይኽም ብቻ ሰአይሆን ፤ ግራኝ ይኽን እርሱ ቆራጥነት የእሚለውን እብደት እና ጭካኔ ፤ የእውነተኛው ኃይማኖት ተከታዮች ብቻ የእሚጎናፀፉት የፈጣሪ ፀጋ ነው ብሎ ማመን ብቻ ሰአይሆን ፤ ክርስቲያኖቹን ማሸነፍ የቻለው ፤ ክርስቲያኖቹ እንደ እርሱ እውነተኛውን ኃይማኖት ስለ እማይከተሉ ይኽንን እርሱ ጋር የአለው ለኃይማኖት በእሚደረግ ጦርነት ሰመዓት ለመሆን የመፈለግ ሱስ ስለ ሌላቸው ነው ብሎ አምኗል ።
በግራኝ ስሌት ፦ ጣዖት አምላኪያን ፥ ሲፈልግ አረማውያን ፥ አንዳንዴም ውሾች ፤ እያለ የእሚጠራቸው ክርስቲያኖች ለዕምነታቸው ለመሞት የእሚያበቃ የመንፈስ ጥንካሬ የሌላቸው እውነተኛውን ኃይማኖት ስለ አልያዙ ነው ። ላሊበላን ቤተክርስቲያን ሊያቃጥል ሲል (ውስጡ ያሉትን ቅርሶች) የአደረገው ይህን ያሳያል ፦
“ላሊበላ በእሚባለው ቤተክርስቲያን ጣዖት አምላኪዎቹ ተሰብስበዋል የእሚል ነገር ሲሰማ ፤ ኢማሙ ሊያጠቃቸው አስቸጋሪውን የተራራ መንገድ ወጣ ። ዝናብም ዘነበበት ። በሌሊት ተጓዙ ፤ የእርሱ ሰዎች አንዳንዶቹ ሰውነትን ከእሚበሳ ብርድ የተነሳ ሞቱ ። በደረሰም ግዜ ፤ መነኮሳቱ በቤተክርስቲያኑ ዙሪያ ሆነው ለቤተክርስቲያኑ ለመሞት የተዘጋጁ ሆነው አገኛቸው ። ኢማሙ ከእዚኽ በፊት እንዲኽ ያለ ነገር አይቶ አያውቅም እና ቤተክርስቲያኑን በግርምት አየው ... ከእዚያኽም ቤተክርስቲያን ውስጥ ደረቅ እንጨት እንዲገባ አዘዘ ፤ ለማቃጠል ። እሳት ከለኮሰበት በኋላ ፥ እሳቱ ሲግም ፤ እንዲኽ አላችው ፤ ለመፈተን ፦ ‘እዚኽ እሳት ውስጥ ከእናንተ አንዱ ይገባል ፤ ማን ይኹን ... ዋናቸው እኔ በፈቃደኝነት እገባለኹ አለ ። በእዚያኽም የነበረች ሴት መነኩሴ ፤ ወንጌልን የአስተማረኝ እርሱ ነው ፤ እኔ ዓይኔ እያየ እርሱ አይገባም ብላ ፤ ተነስታ እሳት ውስጥ ገባች ፤ ኢማሙም አውጧት አለ ፤ ግማሽ ፊቷ በእሳት ተቃጥላ ወጣች ።”
“After he had heard that the idol-worshippers had assembled near a church called Lalibala, the imam set out into the mountains, by a difficult route, to attack them. Rain fell on them from above. They marched by night, and still he forced their march. Some of their number died from the piercing cold before he arrived at the church. He found its monks there, milling around and willing to die for its sake. The imam gazed at the church, He had never seen its like. …The imam had the monks grouped together and then ordered firewood to be strewn inside [the church]. He had it set alight, and when the heat intensified he said to them, ‘One of you shall enter it; …,'to find out what they would do; to put them to the test. Their chief said, ‘I shall enter willingly’. Thereupon one of the women rose up, she was a nun, and said, “This is he who taught me the Gospel. Shall he die while I am watching him? So she entered the fire and threw herself down in it. The imam said, ‘Put her out’. So they pulled her out. Part of her face had been burned [34].”
የእዚኽች አማኚት ሴት ፤ የዕምነት ፍቅር ግራኝ ለረዥም ግዜ ይዞ የቆየውን ክርስቲያኖች እምነታቸው ውሸት ስለ ሆነ እንደ ሙስሊሞች ለእምነታቸው የመሞት ቆራጥነት የላቸውም የእሚለውን ዝበት ከስር መሠረቱ ሳያናጋበት አልቀረም ፤ ለእዚያኽም ይመስላል ፥ እሳት ውስጥ በፈቃዱ የእሚገባ ማን አለ እያለ ሲፎክር የነበረው እና እሺ ያሉትንም እሳት ውስጥ ለማስገባት ያላቅማማው ሰው ፤ በቅስበት አውጧት ወደ ማለት እንዲመጣ የሆነው እንጂ ፤ ግራኝ በርኽራኼ የእሚታማ ሰው ስለ ነበረ አይደለም ።
እንደ አየነው ፤ ግራኝ ከኃይማኖታዊ እምነቱ እና ከጦርነት ፍልስፍናው ተነስተን ፤ ግራኝ ከዘመናዊዎቹ የታሊባን ሙጅኃዲኖች ጋር ሳይዛነፍ የእሚገጥም ባሕሪ እንዳለው ከእዚኽም የተነሳ እስልምናን በመንግሥታዊ ኃይል የማስከበር እና የማስፋፋት ፍላጎት የነበረው ሰው መሆኑ ግልፅ ቢሆንም ፤ ኢትዮጵያን በእሚያጠቃበት ወቅት ይኽ ቋሚ መገለጫው እንዳልሆነ እና ይልቁንም የተደራጀ የአደጋ ጣይ ጦርነት አካኻያጅ ባሕሪ በጉልህ የእሚታይበት ሰው እንደ ነበር ይበልጥ ይስተዋላል ።
ከእዚኽ በተጨማሪም ግን ፤ ሰውየው በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ፤ ከሙጅኃዲንነት እና ተራ ጦረኛ ዘራፊነቱም የአለፈ ፤ የዘር ማጥፋት ፣ ሐገር የማውድም አባዜ ተጠናውቶት እንደነበር ግልፅ ነው ።
በአንድ ወቅት ፤ ከሽምብራ ኩሬው ውጊያ በፊት በነበረ ውጊያ ላይ ፤ የእርሱ ሠራዊት ተሸንፎ ከአፈገፈገ በኋላ ፤ የራሱ ወታደሮች ደግመን የኢትዮጵያን ሠራዊት አንገጥምም ብለው እምቢ ስለ አሉት ፤ ዓይኑ እስኪቀላ እንደ አለቀሰ የእርሱ ታሪከኛ ይነግረናል ። በአንድ በአልተገለፀ ምክንያት ፤ ኢትዮጵያዊያን ማዋረድ አለብኝ ብሎ ተነስቷል ፦
“ኢማሙ ተመርሮ ዐይኑ ደም እስኪ ለብስ ነበር ያለቀሰው ፥ በማፈግፈጋቸው እና በአለመስማማታቸው (ለመቀጠል ) ።”
“The imam was desolated, and wept bitter tears until his eyes were bloodshot from the excessive weeping at their returning, and their disagreeableness [34].”
ይኽን መሰል ስብዕና በአለው ግለሰብ እየተመራ እና ከእላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች የተነሳው ፤ የግራኝ ጥቃት በታሪክ አጥኝዎች ተገቢ ሽፋን ከአልተሰጣቸው የኢትዮጵያ ታሪካዊ ክስተቶች አንዱ ይመስለኛል ።
ይኽም በመሆኑ ፤ ይኽ ሲጀምር ፤ አንድ የሽምቅ ተዋጊ የነበረው ግራኝ ፤ ለእራሱ እና ለጠላቶቹ (ለኢትዮጵያ ነገሥታት እና ሰራዊታቸው) አስገራሚ በሆነ ኹኔታ ፤ ከአስር ዓመት ላላነሰ ግዜ ፤ ከእርሱ ይልቅ እጅግ የእሚበዙትን ፣ የረዥም ዓመት የጦርነት ልምድ የአላቸውን እና ወደ በኋላ ላይ በደንብ በእሚያውቁት ፤ የራሳቸው መልከዓ ምድር ላይ ሳይቀር ተደጋጋሚ ድል መቀናጀት ስለ ቻለበት ስለ እዚኽ የግራኝ አህመድ ጦርነት በታሪክ የእሚነገሩ እና ደግመው መጤን አለባቸው ብዬ ከእማስባቸው ኹኔታዎች ፥ ኹለቱን ላንሳ ።
የመጀመሪያው ፦ ስለ ግራኝ ጦርነት በልማድ የእሚነገረው ፤ መድፍ እና ጠመንጃ ይዞ ስለመጣ ፤ የኢትዮጵያ ባሕላዊ ሠራዊት ፤ ይህንን ሲያይ ወይንም የእነዚኽ መሳሪያዎች አስደንጋጭነት ጦሩን ፈታው የእሚባለው ፤ የወቅቱ የኢትዮጵያን መንግሥት እና ሠራዊት ከአለማወቅ የእሚመጣ እንጂ ትክክለኛ ግምገማ እንደ እማይመስል ፤ ስለ ወቅቱ ጦርነት ከተዘገቡ ኹኔታዎች ተነስተን ለማየት እንሞክር ።
አንደኛ ግራኝ መድፍ እና ጠመንጃ በተመረጠ ቦታ ፤ ለምሳሌ ፦ የአምባ ላይ ምሽግ ለማፍረስ ፥ ወዘተ ፤ እንጂ የሜዳ ላይ ጦርነቱን ኹሉ ፤ በጎራዴ ፣ በፈረስ ፣ ወዘተ ፤ ነው ያካኼደው ።
እንደ ተጠቀሰው ከሆነ ፤ ሽምብራ ኩሬ ላይ ለምሳሌ ፦ መድፍ አልተጠቀመም ወይንም ከእዚያኽ በፊት በነበሩት ጦርነቶችም በሙሉ ። እንዲያውም ከእዚያኽ በፊት በነበሩትም ሆነ በሽምብራ ኩሬው ጦርነት ፤ ኢትዮጵያዊያኖች የበለጠ ታጥቀዋል ። የኢትዮጵያ ወታደሮች ፤ በዘመናዊ ቋንቋ አይረን ማን ሆነው ነበር የግራኝን ጦር የእሚገጥሙት ፦ የብረት ቆብ አድርገው ፣ ስስ የብረት ልብስ ለብሰው ፣ ጋሻ ፣ ጎራዴ ፣ ጦር ፣ መርዛማ ቀስት ፣ ወዘተ ፤ ታጥቀው ነው ። ከታች የአለው የሲሀብ ትረካ ይኽን ነው የእሚነግረን ፦
“ከእነዚኽም መካከል ጨቋኙ እና አንገተ ደንዳናው ፥ አመፀኛው ሴይጣን ነበር ። ፋኑኤል ፥ እግዚአብሔር ይርገመው ። ስስ የብረት ልብስ ለብሶ ነበር ፥ በጭንቅላቱም ላይ የብረት ቆብ አድርጎ ነበር ፥ እናም ዓይኑ ብቻ ነበር ከእዛኽ ውስጥ የእሚታየው ፤ ከእርሱ ጋር የነበሩትም እንደ እዛው ።”
“Amongst these was the tyrannical and obdurate patrician, the rebellious Satan. Fanuel, may God curse him. He wore protective armour, and on his head a helmet of irony so that all that could be seen of him were his eyes peering out; and his companions likewise. [34]“
ሲሀብ ሽንብራ ኩሬ ላይ ስለነበረው የንጉሥ ጦርም ሲናገር ፦
“እርሱ ከኹሉ በላይ ታላቁ እግዚአብሔር ብቻ ነው ፤ የብረት ልብሶቻቸውን ፣ የብረት ቆቦቻቸውን ፣ የእገረኛ ወታደሮቹን እና የቆዳ ጋሻቸውን ቁጥር መናገር የእሚችለው ።”
“Only the Most High God knows the number of his coats of mail, helmets, foot soldiers and shields made of hide. [34]“
አጋኖ ነው ከአላልን በስተቀር ፤ በዘገባው መሠረት የወቅቱ የኢትዮጵያ ሠራዊት ፤ በእዚያኽን ወቅት ከነበሩ በጥሩ ኹኔታ የታጠቁ እና የተደራጁ የጦር ሠራዊቶች ተርታ የእሚመደብ ብቻ ሰአይሆን ፤ የሲሀብ አዘጋገብ እንደ እሚያሳየንም በቁጥር የአላቸው ብዛት ለጠላቶቻቸውም የአስገረመ ነው ። አንዳንድ የታሪክ ጽኹፎች እንደ እሚገምቱትም ፤ በሽንብራ ኩሬው ጦርነት የንጉሠ ነገሥት ልብነ ድንግል ሥራዊት ከ200 ሺ በላይ ሲሆን የግራኝ ሠራዊት ግን ከ 15 ሺ አይበልጥም ነበር ።
ይኽም የጦር ሠራዊቱ ብዛት እና አደረጃጀት ፤ ከግራኝ በስተቀር ተከታዮቹን በሙሉ ያራደ እና በእየግዜው እባክህ ይብቃን እንመለስ ብለው ሲወተውቱት የነበረ መሆኑ በተደጋጋሚ በራሱ ታሪከኛ የተመዘገበ ታሪክ ነው ።
ይኽም ብቻ ሰአይሆን ፤ ወደ ሰሜን ሲወጣ ፥ በትግራይ እና በአማሀራ መድፍ እና ጠመንጃ አበሾቹም እንደ ነበራቸው እና ከእዚኽም የተነሳ ግራኝ ተጨማሪ መድፍ ግዢ ውስጥ እንደገባ ይናገራል ፦
“ክርስቲያኖቹ እና የትግራይ ሕዝብ ፤ በኹለት አረቦች የእሚተኮሱ ፥ መድፍ እና ጠመንጃ ነበሩዋቸው ።”
“Now the Christians and the people of Tegre possessed cannon and muskets that two Arabs would fire at the Muslims for them. [34]“
የመድፍ ብልጫ ነበረው ከአልሆነ በስተቀር ፤ ለዓለፉት ብዙ መቶ ዓመታት ከጦርነት ገድፎ የእማያውቀው እና በጨበጣ ውጊያ በሰይፍ እና በጎራዴ ተሞሸላልቆ ለመሞት የእማይሰስት የወቅቱ የኢትዮጵያ ወታደር ፥ ለእዛን ዘመን በፍ በፍ ለእሚሉ መድፍ እና ጠመንጃ ድምፅ ተብረክርኮ ፤ የመድፍ ወይንም የእነዛ ጥንታዊ መስኬቶች ድምፅ ይፈታዋል የእሚባል አይደለም ።
ስለ እዚኽ ፤ የተለመደው የኢትዮጵያ ነገሥታት ሠራዊት በግራኝ አህመድ የተሸነፈው ፤ ሰምቶ የእማያውቀው የመድፍ እና የጠብ መንጃ ድምፅ አስደንብሮት ነው የእሚለው አሳማኝ አይደለም ።
ኹለተኛው ፦ ብዙ ግዜ የእሚዘገበው ሽምብራ ኩሬ ላይ ፤ የወናግ ሰገድ (ንጉሥ ልብነ ድንግል) ጦር ከተፈታ ወዲህ ፤ ግራኝ ፖርቹጋሎቹ በመምጣታቸው እስኪ ገደል ድረስ በነበረው ግዜ ኹሉ ፤ ግራኝ አሳዳጅ እና የኢትዮጵያ ሠራዊት ተሳዳጅ መስሎ የእሚቀርብበት ኹኔታ የወቅቱን የጦርነቱን ግመት (Momentum) በአግባቡ አይገልፀውም ።
ብዙም ርቀት ሳንኼድ ፤ ቢያንስ ለአንድ ሺ ዓመት ፤ በሰፊዋ ኢትዮጵያ ያለ ተቀናቃኝ ሲገዛ የቆየ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ጦር ፤ በአንድ ግንባር ብቻ የእሚሸነፍ እንደ እማይሆን መገመት ብዙም አይከብድም ።
ግራኝ በአልተጠበቀ ኹኔታ ከ200 ሺ በላይ የሆነውን የንጉሡን ጦር በያዘው ከ15 ሺ ጦር ፤ ሽምብራ ኩሬ ላይ ድል በመንሳት ከበተነው በኋላ ፤ ለብዙ መቶ ዓመታት አንድ ቀን እንኳን በእዚኽ መልኩ ተሸንፎ የእማያውቅ ሠራዊትን መበተን በመቻሉ ተደስቶ ወደ ሐረር ተመለሰ እንጂ ወደ ላይ አልገፋም ።
ከሽንብራ ኩሬ ድልም በኋላ ፤ ሐረር ላይ ቢያንስ ለአንድ ወር ያኽል ምንም ዘመቻ ሳያደርግ ቆይቶ ወደ ሰሜን ሰአይሆን ወደ ባሊ ነው የዘመተው ። ይኽ በግልፅ እንደ እሚያሳየን ፤ የሽምብራ ኩሬ ድል ፤ ግራኝ ራሱ ያልጠበቀው ድል እንደሆነ ፣ ከአሸነፈም በኋላ አከባቢውን ለመቆጣጠር የእሚችልበት ኹኔታ የአልነበረ መሆኑን እና እነዚኽም ኹኔታዎችም ፤ ከእላይ ግራኝ ሲጀምር መላው ኢትዮጵያን መቆጣጠር በተግባራዊ እቅድ ደረጃ በአዕምሮው ውስጥም አልነበረም ላልነው መላምትም ሌላ ማሳያ ነው ።
ግራኝ ፥ ሙጅኃዲም ፣ ዘራፊም እና ጀብደኛ ስለ ነበር ፤ የበላይነት ከያዘበት ግንባር ርቆ በመቶ ኪሎሜትር ወደ መጣበት የተመለሰው ፤ በያዘው ጦር አከባቢውን ለመቆጣጠር ፤ በወቅቱ የነበረው የኃይል እና የኹኔታዎች ሚዛን ስለ ከለከሉት መሆኑን መረዳት ይቻላል ።
የግራኝን የሽምብራ ኩሬን ድል ታሪካዊ የአደረገው ፤ ግራኝ አህመድ በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሥ የእሚመራውን ፤ ስለ እዚኽም የመጨረሻው ጠንካራ የእሚባለውን የሐገሪቱ የጦር ሠራዊት መፈረካከስ መቻሉ እንጂ መላውን ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር በእሚያስችልበት ቁመና ወይንም ኹኔታ ውስጥ መገኘቱን አመላካች ስለ ነበረ አይደለም ።
ከሽምብራ ኩሬው ጦርነት በኋላ ግራኝ ወደ ሐረር ተመልሶ ለአንድ ወር ያኽል ያለምንም ዘመቻ ከመቆየቱ በአሻገር ፤ የሽንብራ ኩሬው ጦርነት ኢትዮጵያን የተቆጣጠረበት ጦርነት እንደ አልነበረ ሊያስረግጡ የእሚችሉ ብዙ ማሳያዎች ስላሉ ፤ ኃሳቡን ለማጠናከር የተወሰኑትን ማሳያዎች እንጨምር ።
የንጉሡ ጦር ሽምብራ ኩሬ ላይ ከተፈታ በኋላ ፥ እና ከእዛኽም እጅግ ቆይቶ በኢትዮጵያ በተለያየ ክፍል ግራኝ ሲንቀሳቀስ ፤ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከነበሩ የተለያዩ ቦታዎች በንጉሥ ትዕዛዝ እየተንቀሳቀሱ የግራኝን ጦር የእሚያጠቁ የኢትዮጵያ ነገሥታት ሰራዊቶች ነበሩ ።
በእነዚኽም ወቅት የኢትዮጵያ ንጉሥ ፤ ዘማች ይልክበት ነበር ብቻ ሰአይሆን ፤ የእሚያዘምትበት ሠራዊትም ብዛት እና አቅምም ቀላል አልነበረም ። በአብዛኛው የግራኝ ወረራ ወቅት ፤ የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሥ ፤ ከባሌ እስከ ዳሞት ፣ ከዳሞት እስከ ትግራይ እና አምሀራ ፤ በአጠቃላይ ከመላው ኢትዮጵያ ፤ በተለያየ ወቅት ፤ የተለያየ ዓይነት ሠራዊት ያዘምትበት ነበር ።
ሰውየው ግን ከጦርነት ውጭ እና ውጭ የእሚያስበው ነገር ስላልነበረው እና ይኽንንም መሳይ የተወሰኑ ሰዎች ስለ ከበቡት እረፍት የለሽ ስለ ነበር በኹኔታው አልተበገረም እንጂ ። ከሽምብራ ኩሬ በኋላ ፤ በተለያየ ግዜ ከዘመቱበት ጦሮች ስለ አንዱ የግራኝ ታሪከኛ ሲናገር እንደ እዚኽ ይላል ፦
“ክርስቲያኖች ኹሉ እና አረማዊ ሰራዊቶቻቸው ፤ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሆነው በቤተ አምሐራ ፤ በጥንቃቄ በተሰራ ጥልፈት ከተሰራው ሰንሰላታማ ልብሳቸው እና ከአስገራሚ የጦር መሳሪያዎቻቸው ጋር ተሰበሰቡ ።”
“All the Christians, and the infidel army, with their soldiers assembled in Bet Amhara in untold numbers, wearing armor composed of chain rings set in neatly tiered rows, and with awesome weaponry. [34]“
እንደ ገናም ፤ ስለ ሌላው ግንባር እንዲኽ ይላል ፦
“በመሐል ፥ አዝማች ኡራል ኡትማን የተባለ ከእስልማና ወደ ክርስትና የገባ ፤ ንጉሡ ባደቅ በእሚባለው ቦታ የተለያዩ ፥ እንደ ደዋሮ ሕዝብ ፣ የባሊ ሕዝብ … የፈጠጋር ሕዝብ ፣ የዳሞት ሕዝብ ጦር ፤ የአረማውያኑን ኃይል ሰበሰበ ።”
“In the meantime, the patrician Ura'I ‘Utman the apostate, whom the king had left behind him in Badeqe, gathered together the infidel forces, such as the people of Dawaro, and the people of Bali, the people of Wanag Jadab, the people of Wanag Amba, … the people of Fatagar, the people of Damot [34].”
እነ እዚኽ ደዋሮ ፣ ፈጠጋር ፣ ባሊ ፤ የእሚባሉ ግዛቶች በሙስሊም ሱልጣኔቶች ይመሩ የነበሩ እና ከሸዋ ጋር በነበረ ተደጋጋሚ ግጭት ተሸንፈው በክርስቲያኑ አስተዳደር ስር የገቡ ፤ በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ የእሚገኙ ቦታዎች ናቸው ፤ ዳሞት ታዋዊ የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ግዛት ነው ።
ከሽንብራ ኩሬ በኋላ ፤ ከኢትዮጵያ ከኹሉም አቅጣጫ የእሚነሱ የተለያዩ ሰራዊቶች ይዘምቱበት ነበር ብቻም ሰአይሆን ፤ አንዳንዴም የግራኝ ጦር በእነዚኽ ሰራዊቶች ይሸነፍም ነበር ። የባሊ ክርስቲያኖች ወሰን ሰገድ በእሚባለው በንጉሡ (ወናግ ሰገድ) አዛዥ የእሚመራ ኃይል ፤ በአንድ ወቅት የገጠማቸውን አንዱን የግራኝ ‘ክፍለ ጦር’ ሙሉ በሙሉ ደምስሰውት ነበር ። ይኽ እንግዲኽ ፤ ከሽንብራ ኩሬ በኋላ ነው ፦
“ከእዚኽም በኋላ ወሰን ሰገድ ፥ ከኃያል ጦር ጋር በመምጣት ፥ የበረታ ጦርነት ተደረገ ። አንዳቸውም ሙስሊሞች ሳይሸሹ ፥ ኹሉም በፈረሶቻቸው ላይ እንደ አሉ ተገደሉ ።”
“So after that Wasan Sagad left with a mighty army, and a fierce battle ensued. None of the Muslims fled, and they all were killed on the backs of their horses,. [34]“
አጼ ልብነ ድንግል ፤ ግራኝ ኢትዮጵያን በእሚያውክበት በእዚኽ ዘመን ታሞ በመሞቱ ፤ እርሱን ተክቶ በ18 ዓመቱ የነገሠው ልጁ አጼ ገላውዴዎስም የፖርቹጋሎች እርዳታ ከመድረሱ በፊት በተደጋጋሚ ግራኝን አሸንፎት ነበር ፦
“በአሥራ ስምንት ዓመቱ እ.አ.አ. በ 1540 ዓ.ም. ወደ ንግሥናው ዙፋን የመጣው አጼ ገላውዴዎስ ፤ እጅግ አስቸጋሪ ኹኔታ የገጠመው ቢሆንም ወታደሩን እና ሕዝቡን አስተባብሮ ለመምራት ጥንካሬ አግኝቶ ነበር ። በቫስኮ ልጅ ክርስታቮ ደጋማ የእሚመራው ፤ በጥሩ ኹኔታ የታጠቁት የሙስኬት ጠመንጃ ነፍጠኞች ፤ 400 የፖርቹጋል ወታደሮች እ.አ.አ. በየካቲት 10 ፡ 1541 ዓ.ም. ከመድረሳቸው በፊት ፤ ገላውዴዎስ የግራኝን ጦር ብዙ ሽንፈት አከናንቦት ነበር ።”
“Emperor Galawdewos, who succeeded to the throne in 1540 at the age of eighteen, faced a desperate situation but had the strength to begin to rally his soldiers and his people. He had already dealt Gragn' s armies several defeats when 400 Portuguese, well-armed musketeers under Christovao da Gama, son of Vasco, landed in Massawa on 10 February 1541. [35]“
ከእላይ እንደ አየነውም ፤ ነገሥታቱ በሐገራቸው ኖረው እና የስልጣን መተካከቱ ፤ ወጉን ጠብቆ እየተካኼደ ፤ ለዛውም የስልጣኑ መተካካቱ ወደ አስር አመት ከቆየው የግራኝ ጥቃት ፍፃሜው መቃሪቢያ ላይ ሳይስተጓጎል እየተካኼደ በመኾኑ ፤ ኢትዮጵያ ጦርነት ውስጥ ነች እንጂ በሞላ ተይዛለች ማለት አይቻልም ።
የግራኝ ጦር በእዚኽ ኹኔታ ሐገር እያመሰ በነበረበት እና የኢትዮጵያ መንግሥትም በዋናነት መከላከልን መሠረት የአደረገ አካኼድ በእሚከተልበት ወቅት ፤ ወደ ግራኝ ወረራ ማብቂያ አከባቢ ፤ ማለትም ፦ ግራኝ ለአንድ አስርት ዓመት ያኽል ከተዋጋ በኋላ ፤ የፖርቹጋሉ አጋዥ ኃይል መሪ ክርስታቮ ደጋማ የያዘው 400 ወታደር ፤ ከኤርትራ ወደ ትግራይ ሲያቀና እና ግራኝ ይህንን አጋዥ ኃይል ፤ ወደ መሐል ኢትዮጵያ እንደ አይዘልቅ ለመከላከል በሰሜን እያለ ፤ ይህም ማለት ወደ ግራኝ መሸነፍ እና መገደል የእሚያመራው ጦርነት አጥቢያ ላይ ፤ ንጉሥ ገላውዴዎስ ከእራሱ ጦር ጋር በሸዋ ነበር ።
ይህም ማለት ፤ ግራኝ የአልደረሰበት የኢትዮጵያ ክፍል በአይኖርም ፤ ቅሉ ይዞ ከእሚንቀሳቀሰው ጦር በስተቀር ለግራኝ ተጠሪ የሆነ አንድም የኢትዮጵያ አከባቢ የአልነበረ እንደሆነ እና አይደለም የግራኝ ጦር ድል መንሳት በጀመረበት አከባቢ ፤ ለአስርት አመታት በበላይነት በመላ ሐገሪቱ ከተንጎማለለ በኋላም ይህን ማስካት እንደ አልቻለ ፤ ከእዚኽ ኹሉ በኋላ በወሳኝነት ድል ተነስቷል ሊባል የእሚችለው የኢትዮጵያ ሠራዊት እና የእየ አከባቢው ባለስልጣናት ታማኝነታቸው እና ተጠሪነታቸው ፤ ግራኝ በአሸናፊነት በቆየባቸው ይኽን አስርት ዓመት ኹሉ ፤ መጀመሪያ ለልብነ ድንግል በኋላም በሸዋ ለነበረው ለንጉሥ ገላውዴዎስ መሆኑ ግልፅ ማሳያ ነው ።
የተናጠል ክዳት ቢኖርም ፤ አንድ ሙሉ ግዛት ይዞ ፤ ለግራኝ የአደረ የኢትዮጲያ አስተዳደራዊ ክፍል አልነበረም።
ግራኝ ለየ፟ት እና ጠንከር እንደአለ አደጋ ጣይ ሆኖ ፤ በሐገሪቱ በወርድ እና በስፋቷ ተንቀሳቅሶ ፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በእማይታወቅ መልኩ ከአምስት እስከ አስር አመት ለቆየ ግዜ ሐገር ያለከልካይ አሸብሯል ።
የግራኝ ድል ፤ የሽንብራ ኩሬውን ጨምሮ ፤ ጠቅልሎ ኢትዮጵያን የማሸነፍ ሰአይሆን ፤ በግራኝ ልዩ ስብዕና እና በእሚከተለው የጦርነት ስልት ምክንያት ፤ ይዞ የእሚያንቀሳቀሰውን ከአስር እስከ አሥራ አምስት ሺ የእሚሆን ሠራዊት ፤ ለአስር አመት እያደሰ በመላ ሐገሪቱ እየተንቀሳቀሰ ሐገር ማወክ የቻለ እንጂ መላ ሐገሪቱን የተቆጣጠረ አልነበረም ።
ግራኝ ይዞ በእሚንቀሳቀሰው አስር እና አሥራ አምስት ሺ ወታደረም ፤ ኢትዮጵያን በእምታኽል ሰፊ ሐገር ፣ ይኽ ነው የእሚባል መሠረተ ልማት በሌለበት እና ሕዝባዊ መሠረት ሳይኖረው ፤ ሐገር መቆጣጠር አይችልም ።
ከእዚኽ በተጨማሪም ፤ በታሪኩ እንደ እምናየው ፤ ጦርነቱ ታዋቂ እና ሊሳካ የእሚችል ግብ ያልያዘ በመሆኑ ፤ የያዘው ሠራዊት ፤ ተደጋጋሚ በሆነ ጦርነት የመሰላቸት እና የመክዳት ችግር የነበረበት እና የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎችም በጦርነቱ እንዳይገፋበት የእሚያሳስቡት የነበረ ነው ። ግራኝ ግን ፤ የጦርነት አባዜ የተጠናወተው እልከኛ ስለ ሆነ እና በእየ ግዜው የእሚያገኘው ድል የልብ ልብ ስለ አሉት ፤ እስከ ሽንፈቱ እና መሰዋቱ አጥቢያ ከጦርነት ለመመለስ ፈቃደኛ አልነበረም እንጂ።
ስለ እዚኽ ፤ የግራኝ ጦር በአስር እና አሥራ አምስት አመት እድሜው አልቆረጠም ያለ ቅንጣት ሆኖ በመላው ሐገሪቱ እየተንቀሳቀሰ ፤ ከፍተኛ ውድመት እና ሽብር ያካኼደ ሠራዊት ነበር እንጂ ፤ ሽንብራ ኩሬ ላይ በእነዛኽ ጥንታዊ መድፎች እና ጠብ መንጃዎች ድምጽ የኢትዮጵያን ንጉሥ ሠራዊት ፈቶ ፤ መላ ሐገሪቱን የተቆጣጠረ ነበር ማለት አይቻልም ።
ይኽን ዓይነት ገፅታ የነበረው የግራኝ ጥቃት ፤ በእዚኽ መልኩ ኢትዮጵያን ሲያውክ እና ሲያሸብር ለመክረሙ ዋነኛ የአቅም ምንጭ የነበረለት ፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ፤ በጨካኝ አምባገነኖች እና በሕዝባዊ ኃይሎች መካከል የተደረገው የኃይማኖት እና የንግድ ነፃነትን ለማስከበር የእሚደረገው ትንቅንቅ በመሆኑ ፤ ይኽን ግጭት በድል ለመወጣት ኢትዮጵያ እና ፖርቹጋል ፤ ከእዚኽ ጦርነት አስቀድመው ጀምረውት የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ፤ ኢትዮጵያ በእዚኽ ፈታኝ ወቅት የእሚያግዟት የፖርቹጋል ወታደሮች እንዲመጡ በማስቻሉ ፤ ድሉ ሙሉ በሙሉ ከቱርክ በእሚያገኘው እገዛ ላይ ለተመረኮዘው የግራኝ ጦርነት ፤ የእነ ክርስታቮ ደጋማ መምጣት ፤ በወሳኝ ሰዓት የተገኘ ዓይነተኛ እገዛ በመሆን የኢትዮጵያ ነገሥታት በወቅቱ የእሚያስፈልጋቸውን የኃይል ሚዛን ማስጠበቅ ችሏል ።
ምንም እንኳን ከድል በኋላ ፤ ለእገዛ የመጣው የፖርቹጋሎች እጅ ፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አድራጊ ፍጣሪ ልኹን በማለቱ ፤ ግንኙነቱ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ቢወስደውም።
ከድል በኋላ ፤ ፓርቹጋሎች ስለ አመጡት የተዛባ ፍላጎት ፓል ኼንዝ እንደ እዚኽ ይላል ፦
“ፖርቹጋሎቹ ኢትዮጵያን ከሙስሊሞች ማዳን ብቻ ይበቃል ብለው አልረኩም ፤ ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ፖለቲካዊ ተፅኖ እንዲኖራቸው ፈለጉ ። ሐገሪቱን የሮማዊ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ምሽግ አድርጎ የመቀየር ተስፋ ይዘው ነበር ።“
“The Portuguese were not content with rescuing the Ethiopians--- from the Muslims; some aspired to political influence. They hoped to transform the country into a bastion of Roman Catholicism. [35]“
ያም ሆኖ ፤ የረዥም ዘመን የዲፕሎማሲው ትሩፋት ፤ አራት መቶ በጥሩ ኹኔታ የታጠቁ በወታደራዊ ጀግንነታቸው እንከን የእማይወጣላቸው እና እንደ እነሱው ጀግና በሆነ ወጣት መሪ የእሚመሩ የፖርቹጋል ወታደሮቹን አመጣ ። የእዚኽ የአጋዥ ጦር መሪ ፤ የታዋቂው የባሕር ላይ መንገድ አሳሽ የቫስኮ[9] ደጋማ ልጅ ሲሆን ፤ በጉዞ ወቅት ኢትዮጵያ ለመድረስ የነበረበትን የተለያዩ ብዙ ፈተናዎችን አልፎ ፤ አራት መቶ ወታደሮች ይዞ በእ.አ.አ. በ1541 ዓ.ም. የኢትዮጵያን መሬት ረገጠ ።
ለ10 ዓመት ገደማ ፤ ኢትዮጵያን ግራኝ ከአመሰ በኋላ ፤ ክርስታቮ 400 መስኬት ጠብ መንጃ የታጠቁትን ወታደሮቹን ይዞ በእ.አ.አ. በ1541 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ሲደርስ ፤ ግራኝ ይችኽን የእምታኽል ትንሽ ጦር ይዞ ፤ ከትልቁ የግራኝ ጦር ጋር ሊጋጠም በመምጣቱ የተገረመ አስመስሎ ፥ ሳይዋጋው እንዲመለስ ፤ ማባበያም ማስፈራሪያም መልዕክት ላከበት። ግራኝ የላከውን መልዕክት ኮስቶኖሆ የተባለው በጦርነቱ ላይ ተሳታፊ የነበረ ፖርቹጋላዊ እንደ እዚኽ አስቀምጦታል ፦
“የዘይላ ንጉሥ ፥ በፈረስ ላይ ተቀምጦ ፥ በፊቱ ነጭ ባንድራ የእሚያውለበልብ ልጅ በያዘ የአረብ መልዕክተኛ ለጌታ ክርስታቮ መልዕክት ላከበት ፡ ይኽን አነስተኛ ጦር ይዞ በእርሱ ፊት ለመቆም በመምጣቱ በጣም እንደ ተገረመ እና ለእዚኽም አጉል ድፍረት የተጋለጠው ፥ በሐሜት እንደ ሰማው ልምድ የሌለው ትንሽ እና የዋህ ልጅ ስለ ሆነ እንደ እሚገምት ገልፆ ። ይኽን የአደረገው ተታሎ እንደ ሆነ ስለ እሚረዳ ፤ እንደ እማይወቅሰው ... ምክንያቱም ያታለለችው ያቺኽ ወይዘሮ[10] እንደ ሆነች እና እርሷን ከእዚኽ በኋላ ሊያምናት እንደ እማይገባ ነገሮት ። እርሱ መሐሪ ንጉሥ እንደ መሆኑ ፥ ሊራራለት እንደ እሚፈልግ እና እርሱን ለመግጠም ለአሳየው አጉል ድፍረት ፥ ከፈለገ ከእነ ሙሉ ወታደሩ እርሱ ጋር እንዲመጣ ፤ አይ ከአለም ወደ መጣበት ሐገሩ ቢመለስ ጥፋተኛ አድርጎ እንደ እማያየው እና በእሚመለስበትም ግዜ ምንም ጉዳት እንደ እማያደርስበት ገልፆ … አያይዞም የመኖክሴ ቀሚስ እና መቁጠሪያ አድርጎ ላከ ፤ በምፀት መኖክሴ ናቹኹ ጦርነት አታውቁም ለማለት ነው ፤ ኹል ግዜም መነኩሴ እያሉ ማንጓጠጥ ልምዳቸው ነበር ።”
“The king of Zeila sent a Moor, who came on horseback, with his boy, who carried a white flag on a lance infont of him to D.Christavo with a message : that he marvelled greatly how he had the audacity to appear before him with so a small force; that indeed he seemed to be a mere boy, as rumour said, and innocent without experience. As he had been so deceived, he did not blame him, ...That he knew in fact that that woman had beguiled him, but that he should pay no more attention to her. That he, as a pitiful King, wished to have compassion on him, and for his boldness in facing him (a thing which had not happened 13/14 years in that counrtey), he would pardon his great temerity, on condition that he came over to him with all his Portugese. That if he did not care to join him, that he could return to his country. That he assured him no evil should befall him....With this he sent him a friar’s cowl and a rosary of beads, making us all out friars – for so they cal us. [113]“
ክርስታቮም ከጓደኞቹ ከመከረ በኋላ ፤ አንተ መነኩሴ ብሎ ላለው ግራኝ ፤ አንተ ሴታ ሴት የእሚል መልዕክት ልኮበት ፤ ሊዋጋው እንደ ቆረጠ አሳየው ፦
“ምላሹም ፥ ንጉሡ ራሱ እንዲ ያነብ በአረብኛ የተጻፉ ጥቂት መስመሮች ነበሩ ። በመልዕክቱም ፥ እኔ እዚኽ የመጣኹት ፥ በባሕሩ አንበሳ እና በምድሩ ጌታ በታላቁ ንጉሥ ትዕዛዝ ነው ፤ የተጨነቁትን እና ረዳት የአጡትን ማገዝ ደግሞ ባሕሉ ነው ። እርሱም ፤ የጦር አጋሩ እና የተወደደው የክርስቲያን ንጉሥ ፤ ቀሲሱ[11] ፥ በአረማዊያን እንደ ተሸነፈ እና በካቶሊክ እምነታችን ጠላት ከመንግሥቱ እንደ ተፈናቀለ ስለ ሰማ ፥ ይኽችኽን ትንሽ እገዛ ልኳል ። ይኽችኽ እገዛ ትንሽም ብትሆን ቅሉ ፤ ምክንያት እና ፍትኽን መሠረት የአደረገች በመሆኗ ለማሸነፍ በቂ ነች ፤ ፖርቹጋሎች ምን ያኽል ጠንካራ መሆናቸውን ነገ እርሱ ራሱ በተግባር እንደ እሚያይና ፤ ወደ እኔ ና ላልኸው ፥ በህንድ ፣ በአረብ ፣ በፐርዥያ ፥ በአብዛኛው አፍሪካ ግዛት ላለው የፖርቹጋል ንጉሥ ብቻ እንደ እሚታዘዝ እና እርሱንም ከእነ እዚኽ እንደ አንዱ እንደ እሚያደርገው ነግሮት ከእዚኽም ጋር አያይዞ መቀንደቢያ እና ትልቅ የፊት መስታወት ላከለት ፤ በምፀት ሴት ለማለት ።”
“His answer was a few lines written in Arabic, that the King might read it. This said that he had come here by order of the great Lion of the Sea, who is very powerful on land; Whose custom it is to help those who are helpless and need his assistance. That as he was informed that the most Christian King, the Prester, his brother in arms, had been defeated and driven from his kingdom by the infidels and enemies of our Holy Catholic Faith, he had sent the small succor that was here, which still sufficed against such evil and bad persons; that reason and justice, which were on his side, were enough to defeat them, …That the following day he would see what the Portuguese were worth, and that was not to go over to him; for they obeyed no lord save the King of Portugal, whose vassals all the Kings of India, Arabia, Persia, and the greater part of Africa were; and the same, by the help of our Lord, he hoped to make him. With this he sent him small tweezers for the eyebrows, and a very large looking-glass—making him out a woman [113]“
አንተ መነኩሴ እና ልምድ የሌለህ ልጅ እግር ነህ ስለ እዚኽ ተመለስ በእሚል እና ወንድ ልጅ ይዋጋል እንጂ አይለፈልፍም አንተ ሴታ ሴት በእሚል የቃላት መወራረፍ የጀመረው ፤ የግራኝ እና የክርስታቮ ጦርነት ፤ ከመጀመሪያ ጀምሮ በአሥራዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ በእሚገኘው ልጅ እግሩ ክርስታቮ የበላይነት ነበር የተደመደመው ። የመጀመሪያውን የክራስታቮ እና የግራኝ ግጥሚያ ኮስቶኖሆ እንደ እዚኽ ዘግቦታል ፦
“በጦርነቱ ግመት ፥ እኛ ጥሩ እየተዋጋን አልመሰለንም ነበር ፤ የዘይላው ንጉሡም ስለ ራሱ ጦር እንደ እዛኽ አስቦ ኖሮ ፤ ሠራዊቱን ሊያበረታታ ወደ ራሱ ሰዎች ሲጠጋ ፤ ፈረሱ በጥይት ተመቶ ከስሩ በመውደቁ ፤ ይኽን ያዩት የማፈግፈግ ምልክት የሆነውን የእርሱን ባንዲራ ሦሥት ግዜ ዝቅ ማድረግ በማድረጋቸው ፤ ከወደቀበት በእጃቸው ተሸክመውት ሸሹ ።”
“It appeared to us that we had the worst of the battle, and it appeared to the King of Zeila, who saw it from the outside, the opposite. He therefore advanced to encourage his men, and came so close to us that he was wounded in the thigh by a matchlock bullet, that pierced his horse, which fell dead under him. When they saw him fall, his ensigns lowered the three banners which accompanied him : this was the signal of retreat ; they lowered them three times, and then took him up in their arms and bore him away [113]“
የመጀመሪያው ጦርነት በእዚኽ ኹኔታ ከተቋጨ በኋላ ፤ በኹለተኛው ጦርነት ግን ግራኝ ራሱ ቆስሎ ፤ እነ እዚኽ መነኩሴዎች አይለቁኝም ይዛችኹኝ አምልጡ ብሎ ፤ አከባቢውን በሙሉ ለቆ ለመሸሽ ተገዷል ። ይኽ ኹለተኛው ጦርነት መገባደጃ ላይ ፤ የነበረውን ኹኔታ ፥ በጦርነቱ ተሳታፊ የነበረው ኮስቶኖሆ እንዲኽ አስቀምጦታል ፦
“ቱርኮቹ ማረፍ ሲጀምሩና ፈረሰኛ መላክ ሲያቆሙ ፥ መፈረካከስ እንደ ጀመሩ ጌታ ክርስታቮ ስለ ተረዳ ፤ በፍጥነት በማጥቃት እግሬ አውጭኝ እስኪሉ አሳደድናቸው ። በእዚኽ ቀን ፥ መቶ እንኳን ፈረስ ቢኖረን ኖሮ አሳደናቸው ጦርነቱ ይጠናቀቅ ነበር ፤ ምክንያቱም የቆሰለውን ንጉሳቸውን በሆሳንሳ ተሸክመው በፈረሰኛ ተከበው ተበታትነው እየሸሹ ስለ ነበር ።... በአንዲት ወራጅ ዳር ላይ ስንደርስ ሙሮቹን አየናቸው ፤ የወንዙ ዳር ምቹ ስለ ነበር እና ምሽትም ስለ ቀረበ እና እኛ እንደ እምንከተለው ስለ አላወቀ ማረፍ ፈልጎ ነበር ። እንደ ተከተልናቸው ሲያዩ ግን እንደገና ሽሽት ጀመሩ ። ከእነርሱ ጋር የነበረ አንድ ሐበሻ እንደ ነገረን ፤ ‘እነ እዚኽ መነኩሴዎች አይተውኝም ‘ ይዛችኹኝ ኺዱ አላቸው ። ኹሌም መነኩሴዎቹ ነው የእሚለን ።”
“When the Turks retired, and the horse ho longer came on, D. Christovao saw that they were shaken ; and we attacked them briskly, and drove them before us till they took flight. The victory would have been complete this day had we had only one hundred horses to finish it : for the King was carried on men's shoulders on a bed, accompanied by horsemen, and they fled with no order…….. When we arrived in sight of the stream we saw the Moors halted on its banks, because, when they had crossed it the King thought that we were not in pursuit ; and as it was late and the place suitable, he desired to rest there. They fled when they saw us ; and an Abyssinian who joined us there, and who had been with them, told us afterwards that the King said •' these friars will not let me long alone”—for thus they call us. [113]“
ግራኝ በእነ እዚኽ ኹለት ግጥሚያዎች ፤ በአንድ ግዜ ወደ አምስት መቶ (500) ኪሎሜትር ያኽል ነው የሸሸው ፤ ይኽ ሐገር የተቆጣጠረ ሠራዊት ባሕሪ አይደለም ።
ኮስቶኖሆ እንደ እሚለው ፤ የመቶ ተጨማሪ ፈረስ መኖር ፤ በእዚኽ ወቅት ጦርነቱን ይደመድመው ከነበረ ፤ ኹኔታው የግራኝ የወረራ ዘረፋ ሐገሪቱን ምን ያኽል እንዳራቆታት ዓይነተኛ ማሳያ ነው ። ምክንያቱም ፦ አልቫሬዝ ፤ በንጉሥ ልብነ ድንግል ድንኳን ዙሪያ ፤ እንደ በቅሎዎቹ የበዛ መቶ ሺ እና ሐምሳ ሺ ፈረስ ነበር ብሎ በአይዘግብም ፤ ንጉሡ ሰፈር ሲቀየር በመቁሰላቸው ተትተው የእሚኬዱት ፈረሶች ሰፈሩን ይሞሉት ነበር ስለ አለ ፤ በንጉሡ ድንኳን ዙሪያ ብቻ በሺ የእሚቆጠሩ ፈረሶች ይኖሩ እንደነበር ግልፅ ነው ።
የኮስቶኖሆን የፈረስ አስፈላጊነት እውነት የእሚያስመስለውም ፤ ከእነ እዚኽ ኹለት ግጥሚያዎች በኋላ ፤ የፖርቹጋል ወታደሮች ግራኝ በጣም ርቆ በመኼዱ ፤ በእየ አከባቢው ፈረስ መፈለግ ዋነኛ ሥራቸው ሆኖ እንደ ነበር መታየቱ ነው ።
በአስደናቂ ጀግንነት እና እምነት ይህንን በዋናነት 400 የፖርቹጋል ወታደሮች እና ወደ 15,000 የእሚጠጉ የግራኝ ወታደሮች መካከል የተደረገ ጦርነት ፤ መርቶ ግራኝን ከአንዴም ኹለት ግዜ አሸንፎት እግሬ አውጭኝ ያስባለው ወጣቱ ክርስታቮ ፤ ሳያስበው የግራኝ ወጥመድ ውስጥ ገብቶ ለመማረክ ያበቃውም ፤ ፈረስ ፍለጋ በወጣበት መሆኑ ፤ በወቅቱ ገጥሞዋቸው ለነበረው የፈረስ ችግር ማሳያ ነው ።
ጌታ ክርስታቮ ፤ ከ 100 ትንሽ የእሚበልጡ የእርሱን ሐገር ወታደሮች ይዞ ፤ የወቅቱ እጅግ አስፈላጊ የጦር መሳሪያ የነበሩትን ፈረሶች ፍለጋ በኼደበት ፤ ሳያስበው የግራኝ ጦር ወጥመድ ውስጥ ገብቶ ተያዘ ። ግራኝም ይዞ ፤ ጺሙን ሰም ነክሮ እየጠቀለለ ፊቱን ከአቃጠለ እና ወታደሮቹ እና እርሱ ራሱ ከአንጓጠጡት በኋላ ፤ ራሱ አንገቱን በሰይፍ ቀልቶ ገደለው ። ክርስታቮ ተይዞ ፤ ግራኝ ፊት ከቀረበ በኋላ የአለውን ኹኔታ ኮስቶኖሆ እንዲህ ገልፆታል ፦
“ጌታ ክርስታቮ የግራኝ ድንኳን ጋር ሲደርስ ፥ ያ ውሻ ፤ አንገታቸው የተቆረጠውን የፖርቹጋል ጭንቅላቶች እንዲናደድ እያሳየው የማን ናቸው አለው ፤ ከእዛኽም እነዚኽን ይዘኽ ነው ሐገሬን ልትወር የመጣኸው ፤ ይኽም የእብደትህ ማሳያ ነው ብሎ ተሳለቀበት ።…ከእዛኽም እጁን ወደ ኋላ አስረው ፤ ራቁቱን አቁመው በአሰቃቂ ኹኔታ ገረፉት ፤ ከእዛኽም የጺሙን ፀጉር በሰም ጠቅልሎ አቃጠለው ፤ ከእዛኽም በእየ ወታደሮቹ ድንኳን እያስዞረ ፤ በላከለት መቀንደቢያ ፥ እስከ ዛሬ ለአንተ ብዬ ነው ያስቀምጥኹልህ ብሎ ፤ ሽፋሽፍቱን ከአስነቀለበት በኋላ ፤ የስድብ ናዳ እያወረዱ ተሳላቁበት ። ጌታ ክርስታቮም ይኽን ኹሉ በትዕግስት እና 550 ኪ.ሜ ርቀት የአለው የእሚያኽል የክርስቲያን መሬት ማስለቀቅ ስለ ቻለ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ተቋቋመው ። በእዚኽ መልኩ አሰቃይተውት ሲጨርሱ ፤ ወደ ንጉሡ ድንኳን መለሱት ፤ ንጉሡም ሌላ ሰው ሰአይሆን ራሱ ሊገድለው ስለ ፈለገ ፤ ንጉሡ ራሱ አንገቱን ቀልቶ ገደለው ።”
“When D. Christovao reached his tent, that dog ordered the heads of the Portuguese to be shown him, to grieve him ; telling him whose they were, and that here were those with whom he had designed to conquer his country, and that his madness was clear in his design ; …. This was to order him to be stripped, with his hands tied behind him, and then cruelly scourged, …; of his beard he made wicks, and covering them with wax lighted them ; with the tweezers that he had sent him, he ordered his eyebrows and eyelashes to be pulled out : saying that he had always kept them for him, as he and his followers did not use them. After this, he sent him to all his tents and his Captains for his refreshment, where many insults were heaped on him, all of which he bore with much patience: giving many thanks to God for bringing him to this, after allowing him to reconquer one hundred leagues of Christian country. After they had diverted themselves with him they returned to the King's tent, who with his own hand cut off his head, it not satisfying him to order it to be cut off [113]“
ከእዚኽ በኋላ ፤ አስቀድሞም በተለያየ ግንባር ተከታታይ ሽንፈት አከናንቦት የነበረው ንጉሥ ገላውዲዎስ ፤ በእየ አከባቢው ከአለ፟ው ኃይል ጦሩን ሰብስቦ ፤ የቀሩትን ከመቶ ትንሽ የእሚበልጡትን የፖርቹጋል ወታደሮች ይዞ ፤ የመጨረሻውን ግራኝ የተገደለበትን ጦርነት አደረገ ፤ ኮስቶኖኾም ይኽንን ግራኝ የተገደለበትን የመጨረሻ ጦርነት የመጨረሻ ሰዓት እንዲኽ አስቀምጦታል ፦
“ከእኛ ጋር ኹለት መቶ ሐምሳ ፈረሰኛ እና ሦሥት ሺ እግረኛ ፤ ከኋላ ቀሲስ ዮሐንስ (ገላውዲዎስ) እንደዚኹ ኹለት መቶ ሐምሳ ፈረሰኛ እና የቀረው እግረኛ ሆነን ወጣን ። የዘይላ ንጉሥም (ግራኝ) ... ጠብ መንጃ ተኳሽ ኹለት መቶ ቱርኮች ፤ ስድስት መቶ ፈረሰኞች እና ሰባት ሺ እግረኛ ይዞ በኹለት ረድፍ መጣ ... ንጉሡ (ግራኝ ) የእርሱ ወታደሮች እያፈገፈጉ መሆኑን ሲያይ ፤ አብሮ ከእሚያግዘው ልጁ ጋር ሆኖ ፤ ወደ ውጊያው ተጠግቶ ጦሩን ሲያበረታታ ፤ ግራኝ መሆኑን የለየው የፖርቹጋል ወታደር ተኩሶ ደረቱን መታው … ሲመታም ከፈረስ ወደቀ ። የእርሱ ተከታዮችም ሙውታዊ ቁስል እንደ ቆሰለ ሲያዩ ሸሹ ። … ጦርነቱ አልቆ ምርኮ ከተከፋፈለ በኋላ ፤ ከንጉሡ (ገላውዴዎስ) ባለሙዋሎች አንዱ የሆነው ፤ አዝማች ሳላይት የእሚባል ሰው ፤ የግራኝን የተቆረጠ ጭንቅላት በጥርሱ ይዞ መጣ … ከታላቅ ደስታ ጋር ። የሆነው ምንድነው ፤ ግራኝ ከወደቀ በኋላ ፤ ይኽ ወጣት እና በሐረነጋሹ (ግራኝን የእሚያውቀው የኤርትራ ገዢ) ወደ ወደቀበት ተከተሉት ፤ ይኽም ወጣት ቀድሞ ደረሰና ግራኝን ጨርሶት ፤ አንገቱን በመቅላት ፤ ሽልማት ይሰጣል ስለ ተባለ በደስታ ቀሲስ ዮሐንስ (ገላውዲዎስ ) ጋር መጣ ።”
“With us were two hundred and fifty Abyssinian horse and three thousand five hundred foot ; in the rear came the Prester with another two hundred and fifty horse, and with all the rest of the foot. In this order we attacked the enemy, who also advanced in two battles, the King of Zeila in person .., with two hundred Turks, matchlock men, six hundred horse and seven thousand foot.…When the King saw that his men were losing ground, he in person led them on, encouraging them, and with him was his son, a young man, helping him ; they came so near that he was recognized by the Portuguese, who, seeing him close, fired at him with their matchlocks. … and he fell over his saddlebow and left the press ; when his followers knew that he was wounded to the death, they lost heart and took to flight. …. After the booty had been se ured, there came to the Prester one of his Captains, by name Azemache Calite, a youth, with the head of the King of Zeila in his teeth, …with great pleasure ; for this youth and the Barnaguais, who knew him [the King of Zeila] best, followed him, and this youth got up to him first and finished killing him, and cut off his head ; he took his head so eagerly to the Prester on account of the promises he had made, which were great : [113]“
ለዘመናዊ ኢትዮጵያዊያን ፤ እንደ እየ ኃይማኖታቸው በእዚኽ መልክ ተጀምሮ የተደመደመው የግራኝ ጦርነት የተለያየ እንደምታ አለው ። ክርስቲያን ለሆኑት ፤ የአልተሳካ ኢትዮጵያን በሰይፍ የማስለም ጥረት አካል አድርገው ስለ እሚያዩት በአብዛኛው አሉታዊ እይታ ነው የአላቸው ። ከእላይ ለማየት እንደ ሞከርነው ግን ፤ የግራኝ ጥቃት ምንም እንኳን ኃይማኖታዊ መልክ የነበረው ቢሆንም ፤ በዋናነት ግን የዓለም ዓቀፉ የኃይል ግብግብ ተቀፅላ የሆነ እና ዋናው ግቡም ኢትዮጵያን ፥ ከኃይማኖት ስሌት ውጭ ምንም እንኳን ኃይማኖት በሽፋን ታሪክነት ቢቀርብም ፤ አንኮታክቶ ከዓለም ዓቀፉ መድረክ ተሳታፊነት ማስወጣት የነበረ ነው ። ስለ እዚኽ ጦርነቱ ፤ ከኃማኖታዊ ጦርነት ይልቅ ፀረ ኢትዮጵያ ወይንም ፀረ ሉዓላዊት ኢትዮጵያ የሆነ ጦርነት ነበር የእሚለው የበለጠ ትክክል ይመስላል ።
ለእስልምና እምነት ተከታይ ሙስሊሞች ደግሞ ገሚሶቹ ፤ ጦርነቱ ግራኝ በኢትዮጵያ ላይ ለመንገሥ ከነበረው ፍላጎት የመጣ ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ በክርስቲያን ነገሥታት ለዘመናት በሙስሊም ማሕበረሰብ ላይ ሲደረስ ለነበረ በደል የተሰጠ አፀፋዊ ምላሽ አድርገው ያዩታል ።
ግራኝ በኢትዮጵያ ለመንገሥ ፈልጎ ነበር የእሚለው ፤ ምን አልባት ኢትዮጵያዊያን በሌሉባት ኢትዮጵያ ለመንገሥ ፈልጓል በእሚል ከአልተስተካከለ በስተቀር ፤ በእየደረሱበት ፦ መንደር እያቃጠሉ ፣ ቅርስ እያወደሙ ፣ ከብት እየነዱ ፣ ነዋሪን ማርኮ በባርነት እየሸጡ ፣ ወዘተ ፤ ይኽን በእሚያደርጉበት ሐገር/ሕዝብ ላይ መንገሥ እፈልጋለሁ ማለት አይቻልም ፤ ስለ እዚኽ ፦ ጦርነቱን የአካኼደው ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ ለመሆን ፈልጎ ነው የእሚባለው ብዙም ተቀባይነት የለውም ።
በአንዳንድ ሙስሊሞች እንደ እሚባለው የግራኝን ጥቃት በሙስሊም ማሕበረሰብ ላይ በኢትዮጵያ ክርስቲያን ነገሥታት ለተፈፀመ ጥቃት እንደ ተሰጠ ታሪካዊ እና ተገቢ አፀፋ አድርገው ለእሚወስዱት ሰዎች ወይንም ይህንን መከራከሪያ ለእሚያቀርቡ ኃይሎች ፤ የተወሰነ ታሪካዊ እይታ ማስቀመጥ ተገቢ ይመስላል ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ እና የአረብ ወሽመጥ (Arabian Peninsula) ፤ በጉርብትና ፣ በታሪክ እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የቆየ ግንኙነት የአላቸው ናቸው ።
ምንም እንኳን ፤ በዘመነ አክሱም ትንሽ ባፈነገጠው አብረኃ ፤ ከተለመደው የኢትዮጵያ ነገሥታት አካኼድ ወጣ በአለ መልኩ ፤ ከእስልምና በፊት ከአረቡ ዓለም ጋር በኃይማኖት ጉዳይ ኢትዮጵያ ብትጋጭም ፤ ፅንፈኛ የተባለው አብረኃ እንኳን ከልክ ሲያልፍ አይታይም ።
በእርግጥ ነብዩ መሐመድ ራሱ ፤ ኢትዮጵያን እና ነገሥታቶቿን ፤ በስም ብቻ ሰአይሆን ፤ በአካል ተገኝተው ኢትዮጵያን እንደ እሚያውቁ የብዙ ሰዎች እምነት ነው ፦
“ ቁራን መሐመድ ኢትዮጵያን ያውቅ እንደ ነበር መረጃ ይሰጣል ፤ ከኹለት መቶ በላይ የእሚሆኑ ቃላቶች ከግዕዝ የተወሰዱ ይመስላሉ ።”
“The Koran provides evidence of Mohammed’s knowledge of Ethiopia and contains over 200 words which appear to be derived from Ge’ez. [35]“
ለእዛኽም ይመስላል ፤ በስማ በለው ሰአይሆን ፤ በአካል ኢትዮጵያን ስለ እሚያውቁ ፤ የሐገራቸው ሰዎች ሲሰደዱ ኢትዮጵያ ኺዱ የአሉት ። ወደ ኢትዮጵያም መጥተው የኼዱ የነብዩ መሐመድ ሰዎች ፤ ስለ አክሱም መልካም እንጂ ክፉ ሲናገሩ አልተሰመሙም ።
የመጀምሪያው ሒጅራ በእሚባለው ፤ ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው ከመጡ የነብዩ መሐመድ ተከታዮች መካከል ከነበሩት እና በኋላ የነብዩ መሐመድ ሚስት የሆነችው ኡም ሐቢባ ፤ ከአክሱም ስትመለስ በአክሱም ለነበሩ የህንፃ ላይ ስዕሎች የነበራትን አድናቆት በተጠቃሽ መልኩ በመልካም አድርጋ እንደ ገለፀችው ይነገራል ፦
“ለአክሱማዊያን ስዕሎች ፤ በኋላ ላይ የነብዩ መሐመድ ሚስት የሆነችው ፤ ኡም ሐቢባ ፤ እ.አ.አ. በ620 ዓ.ም. ተደርጎ በነበረው ስደት ለአስርት ዓመታት በአክሱም ቆይታ ስትመለስ ፤ በአክሱም ካቴድራል ግድግዳዎች ላይ ተስለው ስለ ነበሩት ስዕሎች ከአቀረበችው የአድናቆት ሪፖርት በላይ የጎላ ሪፖርት እስካኹን አልቀረበም ።”
“No significant example of Aksumite painting has come to light but one of the Prophet Mohammed’s later wives, Umm Habiba, is reported to have returned from exile in Ethiopia during the decade following 620 parasing the walls covered with paintings in the cathedral at Aksum. [35]“
ምንም እንኳን ፤ በእዚኽ በተባለው በእ.አ.አ. 620 ዓ.ም. የመጡት የመሐመድ ተከታዮች ፤ ከፊሎችም ተመልሰን አንኼድም ብለው በክርስቲያን አክሱም መቅረታቸው እና በእዚኽ መቀበራቸውን ፤ ኡም ሐቢባ ያደነቀቻቸው ስዕሎች የነበሩባቸው ሕንጻዎች ካቴድራል መሆናቸው እና በስደት የመጡት የነብዩ ተከታዮች ፤ በአክሱሙ ንጉሥ ፊት በቁሬሾች ተከሰው በቀረቡበት ወቅት እምነታቸውን የተከላከሉበትን መንገድ ስናይ ፤ ንጉሡ የተቀበላቸው ክርስቲያን በመሆናቸው ምክንያት የተሰደዱ መስሎት ቢያስመስለውም ፤ በኃይማኖት እምነት ምክንያት መሰዳደቸውን አውቆ ግን በሰብዓዊነት እንደ አስጠለላቸው ግን ምንም ጥያቄ የለውም ።
የቁሬሽ ገዢዎች ፤ እነ እዚኽን አመፀኞች አታስጠልል ፤ አሳልፈህ ስጠን ሲሉት ፤ የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሥ ፦ ጳጳሶችን ፣ ወንጀለኛ ያሉዋቸው የመሐመድ ተከታዮች ታልፈው እንዲሰጡዋቸው የጠየቁት የመካ አምባሳደሮች ፣ እንዲኹም ተከሳሾቹ የነብዩ መሐመድ ተከታዮች ፤ ሰብስቦ በጉዳዩ ላይ ችሎት ከተቀመጠ በኋላ ፤ ጃፋር የእሚባለው የስደተኞቹ ወኪል ፤ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን እና የመንፈስ ቅዱስ ልጅ መሆኑን ሲነግረው እና ስለ ማሪያም ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈውን ሲጠቅስለት ፤ ንጉሡ ስሜቱ ተነክቶ እምባው በጺሙ እንደ ወረደ እንዲኹም ጳጳሳቱ መጽሐፍት ላይ ተደፍተው እንደ አለቀሱ ይነገራል ።
የነብዩ መሐመድ ተከታይ በመሆናቸው ፤ በስደት ወደ አክሱም የመጡት ሰዎች መሪ የነበረው ፤ ጃፋር ቢን አቡ ጣሊብ (የጣሊብ አባት ልጅ ጃፋር) በእዚኽ ንጉሡ በተገኘበት ችሎት ላይ ፤ ከከሳቾቹ ቁሬሾች ለቀረበበት ክስ የእሚከተለውን መልስ ሰጥቷል ፦
“ንጉሥ ሆይ ፤ እኛ አረማዊ ሕዝብ ነበርን ፤ ጣዖት የእሚያመልኩ ፣ የሞተ ነገር የእሚበሉ ፣ አሳፋሪ ድርጊት የእሚፈፅሙ ፣ የደም ዘመዶቻችንን የእምንገድል ፣ ለባለንጀራችን የአለ፟ንን ኃላፊነት የዘነጋን ፣ ጉልበተኛው ደካማውን የእሚበዘብዝበት ። ይኽ ነበር የእኛ ኹኔታ እግዚአብሔር ሐዋሪያ እስኪ ልክልን … እኛም ቃሉን አምነን ተቀብለን እግዚአብሔር በእርሱ የላከልንን ትምህርት ተከተልን …”
“O King, we were a barbarous nation, worshiping idols, eating carrion, committing shameful deeds, killing our blood-relations, forgetting our duty towards our neighbors, the strong amongst us devouring the weak. Such was our state until God sent us an apostle, …. So we trusted in his word and followed the teachings he brought us from God…. [96]“
ይኽን መሰል ከክርሥትና የሰብዓዊነት ፣ የፍትህ እና የተራማጅነት ጋር ተቀራርቦ የአለ፟ውን ማብራሪያ ጃፋር ከሰጠ በኋላ ፤ በጣም በጥበብ የተሞላ አመላለሱ ፤ ክርስቲያን መሆኑን በግልፅ የአሳየ ስለ አልነበረ ፤ ንጉሡ በዘመኑ የክርስትና ክርክር የእምነት መግለጫ የሆኑትን የእሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠየቀው ፦
“ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ታምናለህ ብሎ ጠየቀው ፤ ጃፋርም ሲመልስ … ‘ክርስቶስ ኢየሱስ ፤ የማርያም ልጅ ፤ የእግዚአብሔር ሐዋሪያ ፤ በማርያም ውስጥ የተፀነሰ የእርሱ (የእግዚአብሔር) ቃል እና ከእርሱ (ከእግዚአብሔር) የወጣ መንፈሱ ነው ። ከእዚያኽም ንጉሡ ስለ ማሪያም ሲጠይቀው … ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማርያም የተናገረችውን ‘ነፍሴ በአምላኳ ሐሴት ታደርጋለች … ‘ጠቀሰ ፤ ንጉሡም ይኽን ሲሰማ ‘እምባው በጺሙ ላይ እስኪ ወርድ አለቀሰ ፤ ጳጳሶቹም መጽሕፍታቸው በእንባ እስኪርስ አለቀሱ …”
“On further questioning by the king on what they believed about Jesus Christ, Ja’far proceeded …. ‘verily Christ Jesus, son of Mary, is the apostle of God and his word which conveyed into Mary and a spirit proceeding from him’. And when the Emperor asked him about Mary, he recited … from the Gospel ‘And my spirit hath rejoiced in God, my Savior … “When the emperor heard that, he ‘wept so that his beard was wet with his tears, and his bishops wept with him until their books were wet with tears. … [96]“
ከእላይ እንደ አልነው ፤ ምንም እንኳን እነ እዚኽን የመጀመሪያ የነብዩ መሐመድ ተከታዮች የኢትዮጵያ ንጉሥ የአስጠለላቸው የክርስቲያን እምነት ተከታይ የሆኑ እንደ ሆኑ አምኖ መሆኑ ከችሎቱ ክርክር በግልፅ የእሚታይ ቢሆንም ፤ የኢትዮጵያው ንጉሥ አረብነታቸው ወይንም የቋንቋ ልዩነታቸው ሳይገድበው ፤ በሰብዓዊነታቸው ተቀብሎ መከላከሉ በዘመናት መካከል የተንፀባረቀውን የኢትዮጵያዊያን ነገሥታት የፍትኽ አካኼድ የእሚያሳይ ነው ። ከእላይ እንደ አልነው ፤ ነብዩ መሐመድም ወደ ሐበሻ ምድር ኺዱ የአሉት ፤ በወቅቱ ኢትዮጲያ ውስጥ የነበረውን ፍትኃዊ የአስተዳደር ስረዓት ስለ እሚያውቁት ነው።
የኢትዮጵያ የክርስቲያን ነገሥታት እና የሸዋውን ንግሥና ተከተለው የተመሠረቱት የተለያዩ የሙስሊም ሱልጣኔቶችም ፤ በታሪክ የተመዘገበ ረዥም ጦርነት አድርገዋል ። ማንም ታሪኩን በቅርበት የመረመረ ሰው በግልፅ ሊረዳው እንደ እሚችልው ግን ፤ ምናልባት የሙስሊም ሱልጣኔቶቹ ሽንፈት ሲበዛባቸው የጅኃድን ካርድ ለመምዘዝ በተለያየ ግዜ ይጥራሉ እንጂ ፤ የኢትዮጵያ ነገሥታት ይኽ ጦርነት በተካኼደበት ምሥራቁ ክፍል የኃይማኖት ጦርነት ሲያካኺዱ ታይቶ አይታወቅም ወይንም ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በተለየ ኹኔታ በእዚኽ አከባቢ አስተዳደራዊ በደል ሲያደርሱ አይታወቅም ።
እንዲያውም ፤ በሰው ሐገር መጥተው መስኪድ እየሰሩ ፤ በእኛ አከባቢ ለምን ቤተክርስቲያን ተሰራ ፣ ገዳም ተቋቋመ ፣ ወዘተ ፤ ብለው ኢፍትኃዊ ጥያቄ በማንሳት ፤ እነርሱው ቤተክርስቲያን ከአላቃጠልን ፣ መነኩሴ ከአላበረርን ይሉ ይሆናል እንጂ ፤ ነገሥታቱ የእሚያስፈልጋቸውን መስኪድ ለምን ሰራችሁ ብለው ፤ ወይንም ሌላ ኃይማኖታዊ ክልከላ በቋሚነት ሲያደርጉባቸው አይታይም ።
አይታይም ብቻ ሰአይሆን ፤ በራሳቸው የታሪክ ጸኃፍት ምስክርነት ፤ በኢትዮጲያ ላይ ጦርነት ከጦርነትም በአሻገር የኃይማኖት ጦርነት (ጅኃድ) አዋጅ አውጀው ነገር የጀመሩት ራሳቸው በአከባቢው ሰፍረው ሱልጣኔት የመሠረቱ አረቦች መሆናቸው የተመዘገበ ታሪክ ነው ፦
“የመጀመሪያ ጥቃት ሰንዛሪዎች መስሊሞች ናቸው። በአሥራ አራተኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ ላይ ኃቅ አድ አዲን የተባለ የኢፋት ሱልጣን ፤ ከእርሱ ቀደም በነበሩት ሱልጣኖች ይደረጉ የነበሩ በተለያዩ ቡድኖች እና በእየግዜው የእሚደረጉ የዘረፋ ጥቃቶችን ወደ ለየለት የተቀናጀ ጥቃት ቀይሯል እናም በእኔ እጅ በእሚገኝ እንደ ዘይላ ዜና መዋዕል ጸሐፊ ለመጀመሪያ ግዜ ጥቃቱን በከኃዲዎች (አረማዊያን ወይንም የኢትዮጲያ ክርስቲያኖች) ላይ የእሚደረግ ጦርነት አድርጎ አውጇል።
መጀመሪያ ላይ ሙስሊሞች በግሩም ኹኔታ ስኬታማ ነበሩ። የክርስቲያኑን አከባቢ ወረዋል ፣ ቤተክርሲቲያን አፈራርሰዋል ፣ እና ክርስቲያኖችን በሰይፍ አስገድደው አስልመዋል።”
*The initiative was first taken by the Muslims. Early in the fourteenth century Haq Ad-Din, Sultan of Ifat, turned the sporadic and disjointed forays of his predecessors into a full-scale war of aggression and, according to an Arab chronicle of Zeila in my possession, for the first time couched his call to arms in terms of a religious war against the infidels.
At first the Muslims were remarkably successful. Christian territory was invaded, churches were razed, and Christians forced to apostatize at the point of sword. [100]”
ክፍል አራት በአልነው የታሪክ ዘገባ ላይ እንደ አየነው ፤ የሙስሊም ሱልጣኔቶች መሰረታቸው ራሱ ይኩኖ አምላክ ይሰጣቸው የነበረው ከለላ እንደ ነበር አስቀምጠናል ።
ከእዛኽም በኋላ እነዚኽ ሱልጣኔቶች እየጠነከሩ ሲኼዱ እና ግጭት ሲበረታም ፤ የክርስቲያን ነገሥታቱ አንዱን ሱልጣን አውርደው ዘመዱን ወይንም ወንድሙን ይሾማሉ እንጂ በጦርነት አሸንፈዋቸው እንኳን ሌላ ሰው አይሾሙባቸውም ነበር ። በእርግጥ የሱልጣኖቹ የጠብ ምክንያት በእዚኽ ዓይነት አካሔድ አልፈታ ሲል ፤ ነገሥታቱ ሱልጣኔቶቹን ወደ ዘይላ በመግፋት የእነርሱን አከባቢ በክርስቲያን አስተዳደር ስር ቢያደርጉም ፤ ይኽ ግን ከኃይማኖታዊ ጥላቻ ሰአይሆን ፤ የወቅቱ ሙስሊሞች ድርድር ሰአይሆን ማሸነፍ ወይንም መጥፋት የእሚል ዓይነት ፅንፈኛ አካኼድ በመከተላቸው ፤ የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ፤ በእዚኽ አካኼዳቸው ተሸናፊ በመሆናቸው የመጣ ነው ።
ስለ እዚኽ ፦ በእዛኽ ዘመን የነበረው ግጭት ፤ የራሳቸው የወቅቱ ሙስሊሞች የፖለቲካ ምርጫ ውጤት እንጂ የክርስቲያን ነገሥታቱ ለእስልምና ኃይማኖት የአላቸው ጥላቻ ውጤት እንደ አልሆነ ግልፅ ማሳያ ነው ።
በጠቅላላው ሲታይ የኢትዮጵያ ነገሥታት ፤ ክርስቲያን ቢሆኑም እና በየትም ቦታ ክርስቲያን በኃይማኖቱ ሲጠቃ ለመከላከል ቢቀኑም ፤ አረቦችን በሕዝብነታቸው አክብረው ፤ በፍትሕ መርህ ከኃይማኖት በአሻገር በሰውነታቸው አክብረው ከመቀበል በቀር ፤ ክርስትናን ተቀበሉ ብለው ሰይፍ ያነሱበት የታሪክ አጋጣሚ የለም ። ለእዚኽም ይመስላል ፦ ነብዩ መሐመድ ራሳቸው ጠብ ከአላጫሩ ሐበሾችን በሰላም ተውዋቸው የአሉት። ይኽን የነብዩ መሐመድ ምክር ፤ ፓል ሔንዝ እንደ እዚኽ አስቀምጦታል ፦
“ ‘ሐበሾችን በሰላም ተውዋቸው እነርሱ ጠብን እስካልፈለጉ ድረስ’ እንዳሉ ይነገራል ።”
“‘Leave the Abyssinians in peace,’ he is reported to have said, ‘as long as they do not take the offensive.’ [35] “
ያው ሰላም በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ የእማይመጣ ሆነና ፤ ማሸነፍ ወይንም መጥፋት የእሚለውን አማራጭ አድርገው የወሰዱት ሱልጣኖች ፤ ሰላምን እድል ነሷት እንጂ ።
ይኽን መልክ የነበረው ፤ የግራኝ አይበገሬነት አስማት በእዚኽ መልኩ ከከፈሸፈ በኋላ ፥ በአዳል ሱልጣኔት እና በሸዋ መንግሥት መካከል የነበረው ግጭት ፤ የቀጠለ ቢሆንም እና አንዳንዴ የነገሥታቱን ህይወት ኹሉ የቀማበት ወቅት ቢኖርም ፥ ከግራኝ በኋላ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አካኼድ የእሚወስኑ ነገሮች መካከል አልነበረም ። ከግራኝ ወረራ በኋላ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ አቅጣጫ የወሰኑት ሦሥት ክስተቶች ፦
ናቸው ።
ኃይማኖታዊ ይዘት የአለው የእርስ በእርስ ጦርነት እና የቱርክ ጥቃት
ከፍተኛ ኃይማኖታዊ እውቀት በነበራቸው የወቅቱ የኢትዮጵያ ነገሥታት ፣ የወቅቱ የፖለቲካ ሊህቃን እንዲኹም የኃይማኖት አባቶች ተቀባይነት አጥቶ ፤ በኢትዮጵያዊያኖች እና በጀስዊቶች መካከል ልዩነትን በማባባስ ወደ ግጭት እንዲያመሩ የአደረጉዋቸው እና ኢትዮጲያ በእዚኽኛው የታሪካችን ክፍል ከገጠሙዋት የህልውና አደጋዎች ኹለተኛ የሆነው ፤ የኃይማኖት ልዩነት ምክንያት የሆኑት ዋና ዋናዎቹ የልዩነት ነጥቦች ፤ ከእዚኽ በታች የአሉ፟ት ናቸው ፦
ይህ የጀስዊቶቹ አካኼድ ቤተ መንግሥቱን ለኹለት ከፈለው ።
በእዚኽ የጀስዊቶቹ አካኼድ በተፈጠረው በኹለቱ የቤተ መንግሥት ጎራ መካከል የነበረውን ልዩነት ጠቅለል አድርገን ብናስቀምጠው የእሚሆነው ፦ በአንዱ ወገን ዕቡያኑ የጀስዊት ቄሶች ታግሰን ከሮም ጋር ብናብር (የጀስዊቶቹን ቀኖና በግልፅም በስውርም የተቀበሉ የቤተመንግሥት ሰዎች የነበሩ መሆኑ እንደ አለ ሆኖ) ፤ በመንፈሳዊ ህይወታችን ብዙም አናጎድልም በወታደራዊ እና በኢክኖሚያዊ መስኩ ደግሞ እጅግ ብዙ እናተርፋለን የእሚል ነው ። የንግሥት እሌኒ እና የንግሥት ሰብለወንጌል አቋም በአብዛኛው ይኽ ነበር ፤ ከተወሰኑ አማካሪዎቻቸው እና ባለ ስልጣናት ጋር ።
ከእዚኽ በተቃራኒ ደግሞ ፤ ከእምነታችን አንዲት ጋት እንኳን አናፈገፍግም ፤ የተሻለ መንፈሳዊ መረዳት ከአላቸው ያሳምኑን ይሆናል እንጂ የእሚከፈለውን ዋጋ በሙሉ ከፍለን የእምነት ነፃነታችንን እናስከብራለን የእሚል ፤ በዋናነት በነገሥታቱ የእሚራመድ የአርበኝነት አቋም ነበር ። በእዚኸኛው ጎራ አጼ ልብነ ድንግል ፣ አጼ ገላውዴዎስ ፣ አጼ ምናሴ ተጠቃሽ ናቸው ፤ በኋላ ዘ ድንግል እና ሰሶኒዮስ አዲስ አቅጣጫ እስኪ ከተሉ ።
አብዛኛዎቹ ነገሥታት ይኽን አቋም ሲይዙ ፤ እንደው በማን አለብኝነት እና በከንቱ ጀብደኝነት ስሜት ሰአይሆን ፤ ምንም እንኳን በድርጅታዊ መዋቅር እና በአንዳንድ ስነ ምግባራዊ ጉዳዮች የወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የእሚሻል አሰራር አለኝ ብላ ማሳየት የእምትችል ቢሆንም ፤ ለመንፈሳዊም ሆነ ለምድራዊው ተቋም መሠረት በሆነው ቀኖና ጉዳይ ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ከሮማው ካቶሊክ የእማያንስ ምናልባትም የእሚሻል ደረጃ ላይ የእምትገኝ እንደ ነበር ፤ በነገሥታቱ እና ከፖርቹጋል እንዲኹም ከስፔን በተለያየ ግዜ ከእሚመጡት ቄሶች ጋር በተደረገው ውይይት የእሚታይ ነው ።
ይኽ መከፋፈል ፤ ከቱርክ ስጋት ጋር ተደማምሮ የወቅቱን የኢትዮጵያን ፖለቲካ በአሉታዊ መልኩ ያጋመበትን አግባብ በዝርዝር ለማየት እንሞክር ።
ቤርሙዴዝ ፥ ለእገዛ ከተነሱበት አንስቶ ፤ የጦርነቱን በድል መጠናቀቅ ጨምሮ ከኢትዮጵያ ነገሥታት ጋር እስከ ገባበት አለመግባባት በነበረው ኹኔታ ላይ ለፖርቹጋሎች በጻፈው ሪፖርት ላይ ፤ ያለ መግባባቱ መነሾ የሆነውን ለአጼ ገላውዴዎስ ፥ ከአሌክሳንደሪያ ወደ ሮም እንዲዞር ያቀረበለትን ግብዣ እንዲኽ አስቀምጦታል ፦
“ወደ ንጉሡ ድንኳን ስንደርስ ከእናቱ ጋር ሆኖ ሳለ አገኘኹት ፤ በጣም ደስ አለኝ ፤ ጥሩ ሦሥተኛ ሰው እንደ እምትሆነን ስለ አወቅኩሁ ። በታላቅ ክብር እና በደህና አቀባበል ተቀበለኝ ። ላቀድኹት ነገር ኹኔታው አመቺ መስሎ ታይቶኛል እና እንደ እዚኽ አልኹት ፦ በክርስቶስ እጅግ የተወደድኸው ልጅ ፤ እንደ እምታውቀው አኹን በክብር የአለው ፅኑው ክርስቲያን አባትህ ፤ ስለ ራሴ እና ስለ እርሱ ወደ ሮማው ጳጳስ ኼጄ ለሮማው ጳጳስ ታዛዥነታችንን እንድ አሳውቅ ልኮኝ ነበር ፤ ምናልባት ግን አንተ ልጅ ስለ ነበርኽ ኹኔታውን ረስተኸው ከሆነ ፤ አባትህ ወደ ሮም ሲልከኝ የሮማው ጳጳስ እንዲያምነኝ የሰጠኝን በራሱ እጅ የተፈረመ ደብዳቤ ለማስረጃ ይኸው ፤ እኔ እያልኹ ያለኹት ነገር እውነት መሆኑን በእዚኽ ማረጋገጥ ትችላለህ ። የደብዳቤውም ይዘት ፤ አባትህ የሮማውን ጳጳስ ፤ የክርስቶስ ሐዋሪያቶች የበላይ የሆነው የሐዋሪያው ጴጥሮስ ወራሽ መሆኑን እንደ እሚቀበል እና የዓለም ዓቀፏ ቤተክርስቲያን የበላይ ካህን መሆኑን እንደ እሚያውቅና ፤ በዓለም ላይ በየትም ቦታ ቤተክርስቲያን ስትመሠረት በእርሱ ስር መሆን የአለ፟ባት መሆኑን በመገንዘብ ፤ ራሱን እና በስሩ የአሉ፟ት በላመዋል ጌቶቹ በሙሉ ፤ ኹላችንም ታማኝ እና ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖች በመሆናችንን ፤ የእርሱን መንፈሳዊ አባትነትን የእሚቀበሉ መሆናቸውን የእሚገልፅ ነበር ። አባትህም ፥ ይህን ምድራዊውን ህይወት ለቆ ኼዷል ፤ አንተም በእግዚአብሔር ፀጋ ፤ መንግሥቱን እና ዘውዱን ወርሰኃል ፤ ይኽም ደግሞ የአባትህን ብስለት ፣ መልካም ጠባይ እና ፈርኃ እግዚአብሔር አብረህ እንድትወርስ የበለጠ አስፈላጊ ያደርግብኻል ። ጥሩ የእግዚአብሔር አገልጋይ ለመኾን ፥ የእርሱን እውነተኛውን እምነት ፥ ከሐይማኖቱ እና ከሕግጋቱ ጋር መጠበቅ አለብህ ። እግዚአብሔርም ፤ አንድ ብቻውን አምላክ እና የቤተክርስቲያኑ ራስ እርሱ ስለ ሆነ ፤ ኹሉም በአንድ ፍቅር እና ፍላጎት ፥ አንድ የኃይማኖት እና እምነት አካል እንዲሆኑ እንጂ በመካከላቸው መከፋፈል እንዲኖር አይፈልግም ። አንተም ፥ የአባትህን ጥበብ እና መልካም ጠባይ ወርሰህ ፤ ለቅዱስ አባታችን እና ለሮማው ሊቃነ ጳጳስ ታዘዝ ፤ በእዚኽም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ትፈፅማለህ ፤ በእዚኽም የፖርቹጋሉን ንጉሥ እና የእርሱን ወዳጆች እና አጋሮች ለአንተም የእሚያግዙህ ወንድሞች ወዳጆች እና ረዳቶች ይሆኑኃል ። እንዲኽ ብዬ ለአቀረብኩለት ግብዣም ፤ እንደ ልጅነቱ መጠን ምን እየመለሰ እንደ ሆነ ሳያገናዝብ ፦ አንተ የእኛ መንፈሳዊ አባት አይደለህም ፥ የአንተ አባትነት ለፍራንኮች ነው ፤ አሪያናዊ (የአርዮስ ተከታይ) በመሆንህ እና አራት አምላክ አለ ብለህ የእምታምን በመሆንህ ከእዚኽ በኋላ እኔ የአንተ መንፈሳዊ አባት ነኝ ስትል እንዳልሰማህ ፤ ብሎ መለስለኝ ። እኔም መለስ ብዬ ፤ ሀሰት ተናገርኽ እኔ አሪያናዊ አይደለኹም ፤ አራትም አምላክ የለኝም ፤ ለቅዱሱ አባት አልታዘዝም እያለ ስለ ሆነ ምንም ማድረግ አልችልም ፤ ልረግመው እና ላወግዘው እንደ ሆነ እና ከእዚኽ በኋላ እርሱን ለመመለስም ሆነ በሌላ ጉዳይ ላናግረው እንደ እማልፈልግ ነገርኹት እና ለመኼድ ስነሳ ፤ እንደ እዚኽ አለኝ አንተው ራስኽ ትወገዛለኽ እንጂ እኔ አልወገዝም አለኝ ።”
“When we arrived at the King's tent I found him with his mother, which pleased me much, as I knew she would make a good third. He received me with much honor and welcome. Seeing that the opportunity was suitable for my intention, I said to him these words: “Much beloved son in Jesus Christ, you are aware that the most Christian King your father, now in glory, asked me to go to Rome, for himself and for myself, to give submission to the High Pontiff: should you by reason of your youth not remember this, you may see here a letter signed by him which he gave me,^ that the High Pontiff might believe me, and know that what I said on his behalf was correct ; which was, as I say, that your father recognized him as the successor of St. Peter, chief of the apostles of Christ, and Vicar of His universal Church, in whatever part of the world it may be established; and that he considered himself subordinate to him, with all his kingdoms and lordships, as were all the faithful and orthodox Christian Kings. He, your father, has passed from the present life, and you by the grace of God have inherited from him the crown and governance of these kingdoms, which is also a reason that you should inherit from him his intelligence, virtues, and fear of God. To be a good servant of God you must maintain His true faith and keep His religion and law. He requires that all His should live in one love and desire, and make one body in faith and religion; and that there should be no divisions among His people, just as He is sole God and Head of His Church. Therefore, conforming yourself with the will and rule of God, and imitating the virtue and intelligence of your father, you should submit yourself to the Holy Father the Roman Pontiff, as thus you will do what God orders, and will have for friends, brothers, and helpers in your necessities, the King of Portugal and all the other Kings, his brothers and friends.” To which he, not considering what he was saying, like a young boy, replied as follows: “ You are not our father, nor a prelate, but Patriarch of the Franks, and you are an Arian, for you have four Gods, and you are not in future to call yourself my father.” I turned and told him he lied, for I was not an Arian, and had not four Gods; and that as he would not obey the Holy Father, I held him to be excommunicate, and accursed; and that I would no longer be with him, or speak to him; and with that I got up to go. He replied that I was excommunicated, not he [113]“
በእዚኽ ስፍራ ላይ ፤ ቤርሙዴዝ ንጉሥ ልብነ ድንግል የሮማውን ጳጳስ መንፈሳዊ አባቱ አድርጎ የተቀበለበት ብሎ በማስረጃነት የእሚጠቅሰው የልብነ ድንግል ደብዳቤ ፤ ምናልባት ቤርሙዴዝ በስሕተት ተረድቶት ይሆናል እንጂ ፤ ከአሌክሳንደሪያ ወደ ሮም ዞሪያለኹ የእሚል ዓይነት እንደምታ የአለው ደብዳቤ እንደ አልነበር ፤ በጉዳዩ ላይ የጻፈ ማቲዮ ሳልቫዶር (Matteo Salvadore) የእሚባል ተመራማሪ እንደ እዚኽ ብሏል ፦
“ሆኖም ግን ፥ በወቅቱ በነበረው ግንኙነት አውድ ከተነበበ ፤ የልብነ ድንግል ደብዳቤ የቅርብ ትብብር ፍላጎት መግለጫ ብቻ እንጂ በሌላ መልኩ ምንም ዓይነት ትርጉም ያልአዘለ ነበር ።”
“However, Lebna Dengel’s letter was only an expression of interest for a close association and, if properly read in the context if the encounter, it cannot be interpreted otherwise. [32]”
ስለ እዚኽ ፦ ቤርሙዴዝ ለገላውዴውስ የእሚያቀርበውን ግብዣ ፤ ገላውዴዎስ እንዲቀበለው ብሎ ፤ አባትህ ልብነ ድንግልም የሮማውን ካቶሊክ መንበር ሊቀላቀል ዝግጅት ላይ ነበር ፤ ለእዚኽም ማሳያው ይኽንን ፍላጎቱን ለማሳካት እኔን መልዕክተኛ አድርጎ የላከበት ደብዳቤ ነው ብሎ ለገላውዴዎስ የእሚያቀርብለት ደብዳቤ ፤ ልብነ ድንግል ወደ ካቶሊክ መንበር መቀላቀል መፈለጉን የእሚገልጽ ደብዳቤ ሰአይሆን ፤ መደበኛ እና የተለመደውን የትብብር ፍላጎት እና ጥያቄ የእሚያቀርብ በመሆኑ ፤ ቤርሙዴዝ ገላውዴዎስን የአባትህን ምሳሌ ተከተል ሲለው ፤ በስህተት ፥ ስህተት ከአልሆነም በተራ የማጭበርበር አካኼድ ፤ ሊያሳምነው እየፈለገ መሆኑ ይታያል ።
እነ ቤርሙዴዝ ፤ በእዚኽ መልኩ ከንጉሥ ገላውዴዎስ ጋር ተደጋጋሚ ክርክር አድርገው መግባባት ሳይችሉ ሲቀሩ እና ይኽ አካኼዳቸው በመሐል ሐገር በእሚሆኑበት ግዜ የወቅቱን ሹማምንት መከፋፈል ሲጀምር ፤ እንደ ተለመደው ርስት ፣ አገልጋይ እና በጀት እየተመደበላቸው በተለያየ ቦታ እንዲቀመጡ ለማድረግ የተሞከረው ጥረት ከእዚኽ መሰል እንቅስቃሴያቸው ስለ አል አገዳቸው ፤ በስተመጨረሻ ፤ ከሌላው የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ተነጥለው ፤ ማይጓጓ የእምትባል አድዋ ትግራይ ውስጥ የእምትገኝ ቦታ ላይ ሰፈራቸውን በማድረግ እንዲወሰኑ ፤ ማይጓጓ በኢትዮጵያ የካቶሊክ ሰፈር እንድትሆን ተሰጠቻቸው ።
በኋላ ላይ እነርሱ ማይ ጓጓን ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሥራች አባት የሆነውን ፍሬምናጦስ አባ ሰላማን ለመዘከር በማሰብ ማይ ጓጓን ፍሪሞና ብለው ቢስይሙዋትም ፤ በዕቡይ አመፀኝነታቸው ጠቅልለው ከኢትዮጵያ ምድር በንጉሥ ፋሲለድስ ከተባረሩ በኋላ ፤ ቦታዋ አኹን ላይ እንዴት-ነበርሽ ተብላ ሰአትሰየም አትቀርም። በእዚኽ ዘመን የጀስዊት ቄሶች ተያይዘውት የነበረውን ወትዋችነት ፖል ሔንዝ እንደ እዚኽ አስቀምጦታል ፦
“ቤርሙዴዝ ፤ ንጉሥ ገላውዴዎስን ፤ ከንግሥት እናቱ (ሰብለ ወንጌል) ከተቸረው እገዛ ጋር አስተባብሮ ፤ ለሮማው ጳጳስ እንዲገዛ ጫና ለማሳረፍ ቢሞክርም ፤ ተቀባይነቱን አጥቶ ከቤተ መንግሥት ተባረረ ። ከቤተ መንግሥት እንደ ወጣ ትግራይ ነበር የተላከው ፤ በእዛኽም ደግሞ ነገር ማቀጣጠሉን ስለ አላቆመ ከእዚያኽም ተባረረ ። እ.አ.አ. በ1556 ዓ.ም. ሌሎች ኹለት የካቶሊክ ቄሶችን በእርሱ ምትክ ይዛ በመጣች መርከብ ከምፅዋ ወደ ፖርቹጋል በጎዋ (ህንድ ውስጥ ያለ ቦታ) አድርጎ ኼደ ። ከእዚኽ በኋላ ለ70 ዓመታት ፤ በጀስዊቶች መሪነት በቆራጥነት ኢትዮጵያን ከአሌክሳንደሪያ አቆራርጦ ከሮም ጋር ለማስተሳሰር የእሚደረገው ጥረት ተጀመረ ። … ገላውዴዎስ እና ከእርሱ በኋላ የመጡት ሦሥት ተተኪዎቹ ፤ ለፖርቹጋሎቹ ኢትዮጵያዊያን የተዋህዶ ክርስቲያን እምነታቸውን እና ባህላዊ የእምነት ልምምዳቸውን ሊተው የእሚችሉበት አጋጣሚ የሌለ መሆኑን አሳይተዋቸዋል ።”
“Bermudez, apparently for trying to press Galawdewos to acknowledge submission to the Pope, fell out of favor and was exiled from the court in spite of support from the Queen Mother. He was sent to Tigray where he provoked further trouble. He left Massawa in 1556 on a Portuguese vessel that brought in two more priests while he made his way back to Portugal via Goa. Thus, began more than 70 years of determined efforts, dominated by Jesuits, to persuade the Ethiopian church to sever its connection with Alexandria and accept submission to Rome. … Galawdewos and his next three successors gave the Portuguese no reason to believe that they were susceptible to abandoning Monophysite Christianity and their traditional religious practices. [35]“
ጀስዊቶቹ ግን በራሳቸው ምክንያት ፤ ከፈለጋችሁ በእዚያው በተሰጣችሁ መንደር ፥ በማይጓጓ ልክ ነው በእምትሉት መንገድ እምነታችሁን አካኺዱ እንጂ በእኔ መንገድ ከአል አመለካችሁ በእሚል ሐገር አታበጣብጡ የእሚለውን ንጉሣዊ ብያኔ በፀጋ በአለ መቀበል ፤ ከማይ ጓጓ እየተነሱ በመምጣት ፤ የኢትዮጲያን ዖርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከአሌክሳንደሪያ አፋተው ከሮም ጋር ለማሰተሳሰር ተደጋጋሚ ጥረት ማድረግ ውስጥ ገቡ ።
ከቤርሙዴዝ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ፤ በቤርሙዴዝ የተጀመረውን የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከአሌክሳንደሪያው መንበር አላቆ ወደ ሮሙ መንበር የማምጣቱን ጥረት የቀጠለው ኦቭዬዶ በመባል የእሚታወቀው የካቶሊክ ቄስ ነው ።
በኦቭዬዶ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ለቀረበው ትችት ፤ ገላውዴዎስ እንደ ከእዚኽ ቀደሙ በቃላት ብቻ የተወሰነ ሰአይሆን በጽሑፍ የተቀመጠ መልስ የሰጠበትም ነበር ። ገላውዲዎስ ለኦቭዬዶ ምላሽ የሰጠበት ይኼ ጽሑፍ ፤ በታሪክ አጥኝዎች ፤ የገላውዴዎስ የእምነት መግለጫ በመባል ሲታወቅ ፤ ይዘቱም ፦ የወቅቱን መንፈሳዊ ጥያቄ በአግባቡ የተረዳ እና ለጥያቄዎቹም ጥሩ የእሚባል መልስ የሰጠበት እንደ ሆነ ነው የእሚታመነው ።
ይኽም የገላውዴዎስ መድብል ፤ የነገሥታቱን የአዕምሮ ብስለት እና በጉዳዩ ላይ አቋም ሲይዙ ፤ እንደው በግድ እና በእልኽ ሰአይሆን ፤ በመረዳት ለመሆኑ ፤ ኹለተኛ ትልቅ ማሳያ ሲሆን የጀስዊቶቹን አላቆም ያለ ጠብ አጫሪነት እና እቡይነትም የእሚያሳይ ነው ፦
“የጀስዊቶቹ ጳጳስ አንድሬ ዳ ኦቪዬዶ ፤ በአምስት ሌሎች ቄሶች እና በተወሰኑ አገልጋዮች ታጅቦ አርኪኮ[12] ላይ እ.አ.አ. በመጋቢት 1557 ዓ.ም. ከደረሰ በኋላ ፤ ራሱን የኢትዮጵያ ኢጵስ ቆጶስ ብሎ ሰይሞ መጀመሪያ ወደ ትግራይ ከእዛም ወደ ንጉሡ ግቢ መጣ ። ገላውዲዎስ በወሎ (አንጎት) ተድባባ ማሪያም የእምትባል ታዋቂ ደብር አቋቁሞ እንደ ተነሳ የደረሰው ኦቭዬዶ ፤ ከአይኹድ ጋር የተቀየጠ ክርስትና ነው የእምታካኼዱት ብሎ ቢከሰውም ገላውዴዎስ አንዱንም ክስ አልተቀበለም ። ይልቁንም ገላውዴዎስ አስደናቂ ሰነድ (መድብል) አዘጋጅቶ የተዋህዶ ኦርቶዶክስን እምነት ተከላከለ ፤ ይኽም ገላውዴውስ ያዘጋጀው ጽሑፍ ፤ የገላውዴውስ የእምነት መግለጫ በመባል ይታወቃል ።”
“Jesuit Bishop Andre da Oviedo accompanied by five priests and a small party of servants landed at Arkiko in March 1557 and designated himself Archbishop of Ethiopia, moving up into Tigray and on to the Emperor's camp. Galawdewos, who had just founded and dedicated an important church in Wollo, Tedbaba Maryam, made no concessions in discussions with Oviedo, who accused the Ethiopians of practicing a false form of Christianity contaminated with Judaism. Galawdewos composed an impressive document defending monophysite orthodoxy which became known as his Confession. [35]“
በእርግጥ ገላውዴዎስ ብቻ ሰአይሆን ፤ ስጋ ዘዓብ የእሚባል እና በአጼ ልብነ ድንግል ዘመን ከእነ ቄስ አልቫሬዝ ጋር በመኼድ በፖርቹጋል የኢትዮጵያ አምባሳደር የተደረገ ሰው ፤ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተከታይነቱን በመንቀፍ ፤ ከገላውዴስ ቀደም ብሎ በፖርቹጋል አንተ ክርስቲያን አይደለህም ቁርባን መውሰድ የለብህም ሲባል ፤ ተመሳሳይ በሳል ጽሑፍ አዘጋጅቶ የወቅቱ የካቶሊክ አማኞች ያለባቸውን ዝበት የነቀፈበት ግዜም ነበር ፦
“በቤተመንግሥት (በፖርቹጋል) ታውሎግያ ተመራማሪዎች ማንጓጠጥ ከደረሰበት እና ስጋ ወደሙ እንደ አይወስድ ከተከለከለ በኋላ ፤ ኢትዮጵያዊው ለመጀመሪያ ግዜ እ.አ.አ. በ1540 ዓ.ም. የታተመውን ‘የኢትዮጵያዊኖች እምነት’ የእሚለውን ጽሑፍ ለመድረስ ወሰነ ። ሐተታውም ፤ ኑፋቄ ተብሎ የቀረበበትን ክስ በጥልቀት ማስረዳት የእሚቃወም ፣ የኢትዮጵያን ክርስቲያናዊ እምነት ጤናማነት የእሚያስረግጥ እና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የአዕምሮ ጥበት የእሚያወግዝ ነበር ። ከእዚኽም በተጨማሪ ከእዚኽ በሚሰፉ ፤ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር የአላ፟ትን ግንኙነት በመዳሰስ ፤ በአውሮፓ ለአ፟ሉ የተኻድሶ ቤተክርስቲያኖች ሆደ ሰፊነት እንዲኖራት የእሚመክር ነበር ። እንዲያውም ስጋ ዘአብ ፤ የፀረ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ተቺ የእሚባለው ቃል ራሱ ሳይፈጠር ፤ የፀረ ተሀድሶ እንቅስቃሴ ተቺ ተብሎ መወሰድ የእሚችል ሰው ነው ። ከእዚኽም የተነሳ ፤ ዳሚያዖ ዲ ጎይዝ የእሚባለው ፤ በኤራስመስ ባሕል መሠረት የክርስቲያናዊ ሰብዓዊነት አግባብ የሰለጠነው የፖርቹጋል ሊህቅ እና የቤተመንግሥት ታሪክ ጸሐፊ ድጋፍ አግኝቷል ።”
“After suffering the scorn of court theologians and being denied communion, the Ethiopian decided to author The Faith of the Ethiopian, first published in 1540. The account was a thorough refutation of the accusation of heresy, affirmed the theological soundness of Ethiopia’s Christian traditions, and denounced the narrow-mindedness of the Catholic Church. It also speaks to the broader issue of Catholic relations with other Christians and suggests an accommodating attitude vis-à-vis the reformed churches in Europe. Zaga Za’ab can in fact be considered an ante-litteram critic of the Counter-Reformation: as such, he found the support of Damiao de Gois, Portugese intellectual and foremost court historian trained in the Erasmian tradition of Christian humanism. [32]“
ከላይ እንደ አለው እንደ ማቲዎ ሳልቫዶር ገለጻ ከሆነ ፤ ስጋ ዘዓብ በእዚኽ ጽሑፉ ያሳየው ልህቀት ፤ የአውሮፓ ህዳሴ የማዕዘን ድንጋይ የሆነውን ሰባዊነት (Humanism) በጽሑፉ ውስጥ በማንፀባረቁ የአውሮፓ ህዳሴ መኃንዲሶች ጋር የእሚመደብ ልህቀት የዓሳየ ሰው ነበር ማለት ነው ።
ከአልቫሬዝ ጀምሮ እስከ ቤርሙዴዝ እና ኦቪዬዶ ድረስ ከአሉ፟ት የካቶሊክ ቀሳውስት ጋር በተደረገው መንፈሳዊ ክርክርም ብቻ ሰአይሆን የነገሥታቱ መልካምነት የእሚታየው ፤ በስብዕናቸውም የተመሰከረላቸው ሰዎች ስለመሆናቸው በታሪክ አጥኝዎችም የእሚወደሱ ነው የነበሩት ። እንደ ሰው የተከበሩ እና ጨዋ ዓይነት ብቻም ሳይሆኑ ፤ ምንም እንኳን በካቶሊክ ቀኖና በአያምኑም ፤ የዛሬ 400 ዓመት ቀደም ብሎ የኃይማኖት ነፃነት እንግዳ ብቻ ሰአይሆን አስፈሪ በነበረበት ዘመን ፤ ልክ አይደለህም የእሚሉዋቸውን ካቶሊኮች ፤ በግዛታቸው የራሳቸውን ቤተክርስቲያን በነፃነት አቋቁመው እንዲንቀሳቀሱ የፈቀዱ ነበሩ ። ሉዶልፍ ስለ ገላውዴዎስ እንደ እዚኽ ይላል ፦
“ገላውዲዮስ የልዑል ባሕሪ የተላበሰ ነበር ። በውጭ በተክለ ሰውነት ከተላበሰው ፀጋ በአሻገር ፤ የመልካም አዕምሮም የታደለ ሰው ነበር ፤ ይኽም በኹሉም መመዘኛ የተገባ ንጉሥ መሆኑን ያሳያል ። የመንፈሳዊ አባቶቹ (ካቶሊኮቹ) በሙሉ ዓስተዋይ ልዑል መሆኑን የመሰከረሉት ነው ፤ ምንም እንኳን እነርሱ እንደ እሚፈልጉት ለሮማው መንበር አክብሮታዊ ፍቅር ስለ ሌለው ቅር ቢያሰኛቸውም ። የላቲኗ ቤተክርስቲያን በለመደችው መንገድ እንድ እታመልክ ወይንም የሮም ቀሳውስት ሐይማኖታቸውን በነፃነት እንደአያካኺዱ አልከለከለም ።”
“Claudius was a man of a most Princely Port. For besides the outward Grace of his Person, he was Endued with many Virtues of the Mind, which made him judged by all worthy of the Royal Dignity. The Fathers of the Society applauded him for a most Prudent Prince, though otherwise not so well pleased with him, because he had not shewed that Affection to the Roman See, as they required. Though he did not prohibit the Divine Worship of the Latin Church; nor hindered the Roman Priests from the free exercise of their Religion. [104]“
ገላውዴውስ ይኽን መሰሉን የኃይማኖት ነጻነት ፤ በአመዛዝኖ ፍርድ ያከበረው ፤ የአውሮፓ የፖለቲካ ሊህቃን የኃይማኖትን ነጻነት አስመልክተው ብዙ ከማለተቻው አስቀድሞ መሆኑ ፤ ጉዳዩ ስለ ኢትዮጲያ ነገሥታት የእሚለው ብዙ ነገር አለው።
ስለ እዚኽ ፦ የነገሥታቱ አካሔድ ከከንቱ ትምክህት የመነጨ ሰአይሆን ፤ ጤናማ የአዕምሮ ፍርድ የእሚቀበለው የነፃነት መርህን የተከተለ ነበር ። ጥያቄው ፦ ከተደቀነብን ከእዚኽ ዓለም ዓቀፍ ይዘት ከነበረው ፦ በግራኝ ጥቃት ከደረሰው ውድመት ፣ የውስጥ መከፋፈል ፣ የቱርክ መጠጋት እና የዖሮሞ ሰፊ ሰርጎ ገብነት ፤ አደጋ ለመውጣት ፤ በግዜያዊነትም ቢሆን ፤ ከዕቡይነት ውጭ (አብዛኛዎቹ) ክርስቲያናዊ መርህ የእማይገዛቸውን የወቅቱን የካቶሊክ ዕምነት ቄሶች መታገስ ነበረባቸው ወይንስ አልነበረባቸውም የእሚል ነው የእሚሆነው ።
በእዚኽ ጉዳይ ላይ የአለው የስልት ልዩነት ፤ ለኹሉም ሰው እንደ እየ ምርጫው ትተነው ፤ እ.አ.አ. በ1603 ዓ.ም. ምፅዋ ከደረሰው ፤ ስፔናዊ ፔድሮ ፓኤዝ በስተቀር ፤ ከቤርሙዴዝ ጀምሮ መጨረሻ እስከ ተባረሩት እነ ሜንዴስ ድረስ የነበሩት ፤ በጀስዊት ሚሽነሪዎች ለ70 ዓመት የተካኼዱት ፤ ከአሌክሳንድሪያዋ መንበር ወደ ሮም መንበር ተዛወሩ የእሚል የነበረው ውትወታዎች ፤ በተነጻፃሪ ደከም ያለ ተቋም ከሆነው ፤ ነገር ግን እጅግ ግዙፍ እና ታሪካዊ በሆነው የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ፤ ከኢትዮጵያዊ ካህናት ለመቀማት የመፈለግ ፤ ዕብዩ የክህነት ሌብነት እንጂ ፤ ንፁህ ኃይማኖታዊ ቅናት እንደ አልሆነ ከድርጊታቸው መረዳት ይቻላል ።
ይኽ ኃይማኖታዊ ካባ የአለው ነገር ግን በዋናነት የመንበር ስግብግብነት የእሚነፀባረቅበት የጀስዊቶች ዝብዘባ ፤ ምንም እንኳን ኢትዮጵያዊያን ፤ ከገላውዴዎስ አንስተው ፤ ለወታደራዊ እና ቴክኒካዊ ድጋፍ ሲባል ከኃይማኖታዊ እምነታችን አንድም ጋት እንኳን አናፈገፍግም የእሚለውን የፀና አቋማቸውን ይዘው ፤ ከቤርሙዴዝ ጀምሮ የነበሩትን የጀስዊት ቀሳውስቶች በማይ ጓጓ እንዲ ወሰኑ በማድረግ ቢፀኑም ፤ መሰል ቆራጥነት በጀስዊቶቹም ዘንድ በመኖሩ ፤ በሰላማዊ መንገድ የሞከሩት የቅስና መንበር ቅሚያ አልሳካ ሲላቸው ፤ ራሳቸውን ወደ ኃይማኖታዊ ሸማቂ በመቀየር ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ፖለቲካዊ መሰንጠቅ በመፍጠር የካቶሊክን ቤተክርስቲያን እምነት በኢትዮጵያ ለማንገሥ ፤ ከኃይማኖት ሰባኪነት ወደ ፖለቲከኛ ሸማቂነት መቀየር ጀመሩ ።
ከቤርሙዴዝ መሰናበት በኋላ የመጣው ኦቭዬዶ ፤ ወደ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ለመስረግ ከአጼ ገላውዴዎስ ጋር የአደረገው ክርክር ፤ ከእላይ ንጉሥ ገላውዴውስ እንደ ጻፈው በጠቀስነው የገላውዴዎስ የእምነት ኑዛዜ ተመክቶ ፤ ኦቪዬዶ በቤተ መንግሥት ተቀባይነት አጥቶ ሳለ ገላውዴዎስ በአዳል ጦርነት ላይ በመሞቱ ፤ አጼ ገላውዴዎስን ተክቶት የነገሠው ወንድሙ ምናሴ ፤ ወንድሜ የተገደለው ጀስዊትሶችን ከማይ ጓጓ እየወጡ መሰል ክርክር እንዲያደርጉ ስለ ፈቀደላቸው ነው ብሎ ስለተቆጣ ፤ ኦቭየዶን መልሶ ወደ ማይ ጓጓ (ፍሬሞና) ሰደደው ። እንደ ሉዶልፍ ከሆነ ፤ ንግሥቲቱ እና ሌሎች ባለስልጣናት መሐል ገብተው በአያበርዱት ኖሮ ፤ ወደ እሚቀጥለው ዓለምም ያጓጉዘው ነበር፦
“ንግሥቲቱ እና የተወሰኑ መኳንንቶች ባይከለክሉት ኖሮ ፤ ጳጳሱን ያለምንም ጥርጥር ወደ ሌላኛው ዓለም ይልከው ነበር ።”
“… unless the Queen, and some of the chief Nobility had prevented him, had undoubtedly dispatched the bishop to the other World. [104]“
በእዚኽ ሰጣ ገባ ከመሐል ሐገር ተባሮ በማይ ጓጓ እንዲወሰን በመደረጉ የተበሳጨው ኦቭዬዶ ፤ የባሕርመላሽ (ኤርትራን) ባሕረ-ነጋሽ ይስሐቅን ፤ በገላውዴውስ ወንድም በምናሴ ላይ አሳመፀ ፦
“ኦቪዬዶ ከይስሐቅ ጋር አጼው ላይ በማሴር ወደ ሮም እና ሊዝበን ወታደራዊ እርዳታ እንዲደረግለት ተደጋጋሚ ጥያቄ አቀረበ ። ነገር ግን ፤ የፖርቹጋል አልጋ ወራሽ ፤ ልዑል ሔነሪ ፤ ጥያቄውን እምቢታ መልስ በመስጠት የሮማውን ጳጳስ ኦቪዬዶን ከኢትዮጵያ ደብሩ አንስተው ወደ ኤስያ እንዲሉኩት ምክር ሰጣቸው ፤ ቢሆንም ኦቪዬዶ ከደብሩ መቆየት ችሎ እ.አ.አ. በ1577 ዓ.ም. በእዚያው ሞተ ።”
“Oviedo schemed with Yishaq against the emperor and made repeated appeals to Rome and Lisbon for military support, but the Portuguese regent, Prince Henry, refused and advised Pope Pius V to relieve Oviedo of his Ethiopian bishopric and send him into Asia. Oviedo nevertheless managed to stay on until his death at Fremona in 1577. [35]“
በኃይማኖት ቀኖና አለመግባባት የጀመረው ፤ የጀስዊት ቄሶች እና የኢትዮጵያ ነገሥታት ልዩነት ፤ በእዚኽ መንገድ በግዜ ኺደት እንደ እሚታየው ወደ ለየለት ፖለቲካዊ ልዩነት እያደገ መጣ ።
ይኽ በእንዲኽ እንዳለ ፤ የቆየ ኢትዮጵያን የማዳከም አቅጣጫ ሲከተሉ የነበሩት የዖቶማን ተርኮች ፤ ግራኝ አህመድን በማገዝ ኢትዮጵያን የማጥቃት እቅዳቸው በግራኝ መሸነፍ እና መደምሰስ ሲከሽፍባቸው ፤ በእዚኽ የኢትዮጵያ የታሪክ ክፍል ኢትዮጵያ በሦሥተኛነት አጋጠማት ያልነው ፤ ቱርኮች በራሳቸው ፥ በቀጥታ ተንቀሳቅሰው የኤርትራን ወደቦች የያዙበትን ኹኔታ አስከተለ። ይኽን የቱርኩቹን ኹለተኛ ዙር ጸረ ኢትዮጲያ እንቅስቃሴ ፤ ፓል ሔንዝ እንደ እዚኽ ያስቀምጠዋል ፦
“ግራኝን ድል በነሱ ማግስት ኢትዮጵያዊያኖች የገጠማቸው መጥፎ እድል እነ እዚኽ ብቻ አልነበሩም ። ፓሻ (ባሻ) ኦዝደምር በእሚባለው ሰው የእሚመራው የኦቶማን ተርኮች ጦር ምፅዋን እና አርኪኮ ወደቦች እ.አ.አ. በ1557 ዓ.ም. በመያዝ ፤ ከእዚያኽም አልፎ ገፍቶ በመምጣት ሐማሴን ውስጥ ፤ ከአስመራ በስተደቡብ ደብራዋ በእሚባል ቦታ ላይ ምሽግ ሠራ ። ትግራዮች የቱርኩን ጦር ገፍተው ከዋናው ምድር ቢያስወጡም ፤ ከስዋኪን ፣ ምፅዋ እና አርኪኮ ወደቦች ሊያስለቅቁዋቸው አልቻሉም ፤ ቱርኮቹም በቀረው የምዕተ ዓመቱ ዓመታት ፤ በተለይ የአጼዎቹን ተቃዋሚዎች እየያዙ ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው በተደጋጋሚ ገብተዋል ።”
“These were not the only misfortunes the Ethiopians experienced in the wake of Gragn' s defeat. The Ottoman Turks under Ozdemir Pasha seized Massawa and Arkiko in 1557 and fought their way up into Hamasien where they built a fortress at Debarwa, south of Asmara. This provoked strong Tigrayan resistance. The Tigrayans drove the Turks back toward the coast but could. not dislodge them from Suakin, Massawa and Arkiko, and the Turks made repeated incursions into northern Ethiopia during the remainder of the century, at times gaining the support of rivals of the emperors. [35]“
ቱርኮች የኤርትራን ወደቦች በመያዝ ብቻ መወሰን ሰአይሆን ፤ ልክ እንደ ጀስዊቶቹ በኢትዮጵያ ውስጥ የአለውን ፖለቲካዊ መከፋፈል በመጠቀም ፤ በመዓከላዊው መንግሥት ላይ መነሳት የእሚፈልጉ ሸመኞችን ወደ ማስተባበር እና ወደ ማገዝም ገብተዋል ። ወይንም በቀላል አገላለጽ ፤ አማጺዎች ፣ ሸማቂዎችን እና ቅጥረኞችን ፤ መመልመል ፣ ማስታጠቅ እና ከለላ መስጠት ውስጥ ገብተዋል።
የኤርትራው ባህረነጋሽ ይስሐቅ ፤ የክርስታቮ ደጋማ ጦር በሰላም እንዲደርስ ከማድረግ አንስቶ ፤ ግራኝ በተገደለበት ጦርነት ላይ በቀጥታ በመሳተፍ ወሳኝ ሚና የተጫወተ ዓይነተኛ ኢትዮጵያዊ አርበኛ የነበረ ቢሆንም ፤ በጥቂት አመታት ውስጥ አካኼዱን ቀይሮ ፤ በዋናነት በውጭ ኃይሎች መካሪነት የመሐሉን ፖለቲካ ለመቆጣጠር በማሰብ ፤ መጀመሪያ እላይ እንደ አልነው ከኦቪዶ ጋር አብሮ ከፖርቹጋል ወታደር አስመጥተው በኢትዮጵያ ነገሥታት ላይ ለመዝመት ያቀረቡት የወታደር ይላክልን ጥያቄ በፖርቹጋል መንግሥት እና በሮማው መንበር ዝምታ ሲከሽፍ ፤ የቀይ ባሕርን ወደቦች በራሳቸው ወታደር ተቆጣጥረው እና የራሳቸውንም ወታደር ወደ መሐል ኢትዮጵያ ለማዝመት ከእሚፈልጉት ቱርኮች ጋር በማበር ፤ የእሚፈልገውን ሰው በኢትዮጵያ ላይ በማንገሥ ፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ዘመነ መሣፍንት የእሚባለውን ዘመን ፈር ቀዳጅ ሊያስብለው የእሚችለውን ፖለቲካዊ አቅጣጫ ተከትሏል።
ባሕረ ነጋሽ ይስሐቅ ከወቅቱ ሴረኞች ቱርኮች ጋር በማበር የአደርገውን መሳፍንታዊ አመጽ ፤ ፓል ሔንዝ እንደ እዚኽ ዘግቦታል ፦
“ … ባህረ ነጋሽ ይስሐቅ ፤ ቀይ ባሕርን የእሚያካትተውን አከባቢ ገዥነት ስልጣን የአለው ፤ ራሱን ከኦቶማን ተርኮች ጋር በማስተባበር ፤ የአጼ ምናሴን የወንድም ልጅ አነገሠ።”
“… Bahr Negash Yishaq, bearer of the title of the ruler of the regin along the sea, allied himself with Ottomans and crowned a nephew of Minas aa a rival emperor. [35]“
አጼ ምናሴም ፤ ይኽን አመፅ ለማስቆም ቢሞክርም ፤ ከተርኮች ጋር የአበረው ይስሐቅን ማሸነፍ ሳይችል ቀርቶ በጥቂት ግዜ ውስጥ ታሞ ህይወቱ አለፈ ። ይኽን አዲስ ዓይነት ፤ በባህረ ነጋሽ ይስሐቅ የተጀመረ ፖለቲካዊ አመፅ ማክሸፍ የቻለው የምናሴ ልጅ የሆነው እና በእዚኽ ዘመን ለ34 ዓመታት ሐገር አረጋግቶ መምራት የቻለው ፤ ምናሴን ተክቶ የነገሠው አጼ ሰርፀድንግል ነው ፦
“ ሰርፀ ድንግል ፤ ምንም እንኳን ከኦሮሞ ፤ ከአዳል እና ከፈላሾች ጋር የእማያባራ ጦርነት ውስጥ ቢሆንም ፤ እ.አ.አ. በ1576 ዓ.ም. ወደ ትግራይ ዘምቶ ተርኮችን አሸንፏቸዋል ፤ በጦርነቱም ይስሐቅ እና ኦዝደምር ፓሻም ተገድለዋል። “
“Sarsa Dengel, who meanwhile was involved in constant fighting with the Oromo, Adal and the …, marched into Tigrayin 1576. He defeated the Turks and both Yishaq and Ozdemir Pasha were killed. [35]“
በእዚኽኛው የታሪክ ክፍል ፤ እንደ እሚታየው ፤ የግራኝ ጥቃት ሲከሽፍ ፤ ፖርቹጋሎች በኃይማኖት አሳበው ሐገር ለመቆጣጠር ፈለጉ ፤ ይኽ ሳይሳካላቸው እና በማይጓጓ እንዲወሰኑ ሲሆን ፤ ከፖርቹጋል ድረስ ጦር አስመጥተው በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ለማዝመት ቢፈልጉም ጥያቄያቸው መልስ አጥቶ ሳይሳካላቸው ቀረ ።
ፖርቹጋሎቹ ለግዜው በእዚኽ ጋብ ሲሉ ፤ ዖቶማን ተርኮች በእዚኹ ግዜ የኤርትራን ወደቦች ተቆጣጥረው ፤ በመንግሥት ላይ ቅሬታ የአላቸውን ሰዎች በማፈላለግ እና በማስተባበር ወደ መሐል ሐገር ለመዝለቅ ተደጋጋሚ ጥረት ወደ ማድረግ ገቡ ።
ይኽም የእሚበቃ አይመስል ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ፤ የኹለት የወቅቱ የዓለም ኃያላን መንግሥታት በሰሜን በእዚኽ መልኩ እረፍት እየነሱት ሳሉ ፤ በእዚኽ ዘመን የኢትዮጵያን ፖለቲካ የገጠመው አራተኛው ፈተና የአልነው ፤ የዖሮሞ ሕዝብ ፤ አዲስ የገዳ ስረዓት የእሚባል ተዋውቆ ፤ ይኖርበት ከነበረው ከሶማሊያ ተነስቶ ባሌን እና ደቡባዊ ኢትዮጵያን ማጥቃት እና ወደ መሐል ኢትዮጵያ መስረግ ጀመረ ።
የኢትዮጵያ መንግሥትም የተቀናጀ በእሚመስል መልኩ ፤ በእነዚኽ በሰሜን እና በደቡብ በተጋረጡበት ጥቃት ውስጥ እያለ ፤ በባህረ ነጋሽ ይስሐቅ የተጀመረው የመዓከላዊውን መንግሥት በከባቢያው መኳንንቶች የእጅ አዙር አመራር ውስጥ የማስገባት ፍላጎት ዓይነት አካኼድ ወደ ቤተ መንግሥት ውስጥ በአልተጠበቀ አኳኋን በመግባት መኳንንቶቹ የንጉሡ በአለመዋል ከመሆን ይልቅ አንጋሽ እና አፍራሽ እንዲሆኑ በማደረግ አዲስን አካኼድ ጀመሩ ። ይኽ ከሆነበት ፤ ከእዚኽ ግዜ አንስተን ፤ በባሕረ ነጋሽ ይስሐቅ ፋና ወጊነት ፤ በኢትዮጵያ ዘመነ መሣፍንት በጋህድ ተጀመረ ማለት የእምንችል ይመስለኛል ።
ከቤተ መንግሥት ውጭ በነበረው ባህረ ነጋሽ ይስሐቅ የተጀመረውን ይኽን የመኳንንቱን አንጋሽ እና አፍራሽነት ልማድ በአዲስ መልኩ ቤተመንግሥት ውስጥ የአስገባው ደግሞ ፤ የሰርፀ ድንግል የስልጣን ተተኪውን የመምረጥ ኑዛዜ ፤ ከእቴጌይቱ እና ከመኳንንቶቹ ምርጫ ጋር በአለመግጠሙ ነው ።
ስለ እዚኽ ኹኔታ ፤ ኢዮብ ሉዶልፍ ፤ አጼ ሰርፀ ድንግል ፤ ወደ እድሜው መጨረሻ ላይ ሲደርስ ፤ ማን ሊተካው እንደ እሚገባ ለመግለፅ ፤ የአደረገውን የእሚከተለውን ኑዛዜ ዋቢ በማድረግ ያስቀምጥልናል ፦
“የህይወቴ መጨረሻ እየተቃረበ ስለሆነ ፤ ከነፍሴ መዳን ቀጥሎ በጣም ከእሚያስጨንቁኝ ነገሮች ቀዳሚው የመንግሥቴ ጉዳይ በመሆኑ ፤ የመንግሥቴን ጉዳይ ከነፍስ ድህነቴ ጉዳይ ያልአነሰ አትኩሮት ስሰጠው ኖሪያለኹ ። እውነት ነው ከእርሱ ውጭ ሕጋዊ ወራሽ ስለ ሌለኝ ያዕቆብን ኹሌም ወድጄዋለሁ ። ለእንደ እዚኽ ዓይነት የከበረ ውርስ የእማያበቃ የአዕምሮ ጉድለትም ስለ አላየኹበት ፤ ወራሼ መሆኑን ቆርጬ የወስንኩት ጉዳይ ቢሆን ኖሮ እና እናንተም ብትታዘዙት የእምፀፀጥበት ነገር አይሆንም ነበር ። ሆኖም ግን በእዚኽ ጉዳይ የሐገሬን ፍቅር እና የመንግሥቱን ሕግ በግል ከአለ፟ኝ ፍቅር ስለ እማስበልጥ ፤ የወንድሜ ልጅ እና የቅርብ ዘመዴ ለሆነው ፤ በጦርነት ጀግና ፣ በእድሜ ብስል ፤ መልካምነቱ ለኹሉም የእሚታይ እና በእነ እዚኽ መልካም በኻሪዎቹ በውልደት የአገኘውን ይኽ ክብር የእሚገባው ስለ ሆነ ፤ ለዘድንግል እንድ ትታዘዙ እላለኹ ። ይኽን ኑዛዜ ከአደረገ ከጥቂት ግዜ በኋላ ሞተ ።”
“Seeing that the end of my life approaches , I thought that next the Care of my Soul, that of my kingdom was the chiefest , the safety of which 1 bate always held no less dear tome, than the Salvation of my own Soul. True it is, that having none Legitimate, I always loved Jacob as my own. And l have observed in him Endowments of Mind not unworthy so fair an Inheritance; so that I could not have had any reason to repent, had I Established him my Successor; nor, you, had you yielded him Obedience. 'But now I prefer the Love of my Country, and the Laws of the kingdom before my private Affection. Therefore, it is, that I recommend to your Allegiance Z Denghel my Brothers Son, my nearest Kinsman, flout in War, Mature in years, conspicuous for his virtues, and one that by those virtues Merits the high Dignity which is due to him by Birth. Having thus said, in a short while after he expired. [104]“
እንደ ሉዶልፍ ይኽ ኑዛዜ ፤ ቤተመንግሥቱን ለኹለት ከፍሎ ፤ አለመረጋጋትን በሐገሪቱ ፈጥሮዋል ።
ጉዳዩን ሉዶልፍን ዋቢ አድርገን ስናየው ፤ የነገሩ አጀማመር ፥ የንግሥናው መሐል ላይ ፤ ሰርፀ ድንግል ከራሱ ልጅ ያዕቆብ ይልቅ የወንድሙ ልጅ ዘ ድንግል ላይ ለንግሥና የእሚያበቃ መልካም ጠባይ ያይበት እና የእሚተካው እርሱ ሊሆን እንደ እሚገባው ይላል ። ይኽ ኹኔታ ግን የዘ ድንግል ልብ አስታብዮ ፤ ሰርፀ ድንግልን መናቅ ሲጀምር ፤ በኹኔታው የተናደደው ሰርፀ ድንግል ኃሳቡን ይቀይራል ።
ስለ እዚኽ ፦ መኳንንቱም ሆኑ እቴጌይቱ ፤ ያዕቆብ እንደ እሚነግስ እርግጠኞች ሆነው ፤ በእርሱ ንግሥና እሳቤ ራሳቸውን አደላድለው ሳሉ፟ ፤ ሰርፀ ድንግል በድንገት ታሞ ሊሞት ሲል ፥ ከእላይ የአስቀመጥነውን ውብ ኑዛዜ በማድረግ ፤ ያዕቆብ ልጄ ቢሆንም ፤ ለቦታዉ የእሚመጥነው የወንድሜ ልጅ ዘ ድንግል ነው እና እርሱን አንግሱት ብሎ ይሞታል ።
ይኽ ያልተጠበቀ ኑዛዜ ዱብዳ የሆነባቸው የያዕቆብን መንገሥ ታሳቢ አድርገው ስሌታቸውን የሰሩ መኳንንቶች እና የእቴጌነቷንም ቦታ ልታጣ ያለቸው የያዕቆብ እናት ፤ አንድ ላይ አሲረው ፤ ከሰረፀ ድንግል ሞት በኋላ ፤ ያዕቆብን አንግሰው ፤ ዘ ድንግልን ፤ ከአምባ አምባ እያዞሩ ያስሩታል ፤ አንድ ቦታ ከተቀመጠ ደጋፊ ሰብስቦ ይዘምትብናል ብለው ስለ አሰቡ ።
በእዚኽ ኹኔታ ፤ የጌታቸውን የንጉሥ ሰርፀ ድንግልን ኑዛዜ ችላ ብለው ፤ ተገቢውን ወራሽ አስረው ፤ ለአቅመ አዳም ያልደረሰውን ያዕቆብ አንግሰው ወይንም አሻንጉሊት አድርገው ፤ መኳንንቱ እና እቴጌይቱ የስልጣን ባለቤት በሆኑበት ኹኔታ ፤ ያዕቆብ ትንሽ ከፍ ሲል ፥ ወደ 11 ዓመቱ ገደማ ፤ ልክ እንደ አቤቶ እያሱ እኔ ካል አዘዝኩ ማለት በመጀመሩ ፤ የስልጣን ፍትጊያው ሲበረታ ፥ መኳንንቱ በእርሱ ላይ በመነሳታቸው ፤ ከትንሽ ጠባቂዎቹ ጋር ሸሽቶ ፤ ዘ ድንግል ወደ ታሰረበት አምባ ይመጣል ።
ንጉሥ የተበላባቸው ፥ አንጋሽ እና አፍራሽ መኳንንቶቹ ፤ በወቅቱ የፖለቲካ ስሪት መሠረት የነጋሢ ዘር በሌለበት ፖለቲካቸው መቀጠል ስለ እማይችል ፤ ዘ ድንግልን ከታሰረበት አምባ መልሰው ንጉሥ ያደርጉታል ። ዘድንግልም ፤ ያዕቆብን በእናርያ እንዲታሰር አድርጎ ፤ ወደ ንግሥናው ይገባል ።
የቤተ መንግሥቱ ኹኔታ እዚኽ ላይ እንደ አለ ፤ የቱርክ መሠረተ ሰፊ ጥቃት ፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማጀት ውስጥ የአስገባቸው ጀስዊቶች ፤ ከእኛ በላይ ክርስቲያን ለአሳር በእሚል ዕቡይነት የኢትዮጵያ መንፍሳዊ ሊቃውንት በሙሉ ለእኛ ሰጥ ለጥ ብለው ሊታዘዙ ይገባል የእሚለው አካኼዳቸው ፤ ከቤርሙዴዝ እስከ ኦቭዬዶ በዙ እርቀት አልወስዳችኹ ብሎዋቸው በማይጓጓ እንዲቆዩ ከተደረጉ በኋላ ፤ የኦቪይዶን መሞት ተከትሎ የመጣው ፔድሮ ፓኤዝ አማርኛ እና ግዕዝ አጥንቶ ፤ ራሱን ‘ኢትዮጵያዊ’ አድርጎ መቅረቡ የአዲሱን ነጋሢ ዘ ድንግልን ስለ ሳበው ፤ የካቶሊክ እምነት ተከታዮቹ ጀስዊቶች ኃሳብ ለመጀመሪያ ግዜ በአጼ ዘድንግል ተቀባይነት በማግኘት ፤ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ መከፋፈል እና የመንግሥትን መዳከም እንደ ገና ወደ አንድ ከፍ የአለ ደረጃ ወሰደው ።
በሐገራቸው መንግሥት እንኳን ፤ አካኼዳችኹ ልክ አይደለም እና እረፉ ተብለው ፤ ለማረፍ እምቢተኛ የሆኑ ጀስዊቶች ፤ ኦቪየዶ በፍሬሞና (ማይጓጓ) ከሞተ በኋላ ፤ እ.አ.አ. በ1603 ዓ.ም. ፔድሮ ፓየስ የተባለ ፤ የስፔን ዜግነት የአለው ጀስዊት መጣ ፦
“ከእዚኽ በመቀጠል ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ፤ የስፔን ሰው የሆነው አባ ፔሮ ፓየስ (ፔድሮ ፓኤዝ) ነው ።… ሲመጣ እድሜው ገና በሰላሳዎች ውስጥ ነበር ። በቱርኮች ተይዞ ዶፋር እና የመን ላይ መታሰር እና በዙ አስቸጋሪ መጥፎ ገጠመኞችን አልፎ ነበር ወደ ሐገሪቱ የመጣው ። በስተመጨረሻ ራሱን የአርመን ነጋዴ አስመስሎ እ.አ.አ. በ1603 ዓ.ም. ምፅዋ ከደረሰ በኋላ በደብረዋ አድርጎ ፍሬሞና ደረሰ ። ፔድሮ ሲደርስ ፤ ሰርፀ ድንግል ሞቶ ሐገሪቱ ለቀጣዩ አስር አመት በስልጣን ሽግግር ችግር ግራ መጋባት ውስጥ ነበረች ። … ፍሬሞና ላይ ለብዙ ወራት ቁጭ ብሎ ሲጠባበቅ በነበረበት ወቅት ፤ አማርኛ እና ግዕዝ አጥንቶ ሳለ፟ ፤ ዙፋን ላይ በነበረው በወጣቱ ዘድንግል … ኦሮሞዎችን በዳሞት ወግቶ ተመልሶ ከሰፈረበት ወደ ደንካዝ እንዲመጣ ተጠራ ።
ፓኤዝ ከኦቪየዶ የተለየ ሰው ነበር ፦ ጭምት ፣ የተማረ ፣ ለሌሎች ስሜት የእሚጠነቀቅ ። ግዕዝ እና አማርኛ በፍጥነት በማቀላጠፍ ፤ ስለ ኢትዮጵያ ባህል ፣ የካቶሊክ እምነት እና አደራረግ ለዘድንግል በጥንቃቄ በማስረዳት ዘድንግልን አስደሰተው ። በእዚኽም ዘድንግል እና ከአጀቡ መሐል የተወሰኑት ፤ ካቶሊክ ለመሆን ወሰኑ ፤ ምንም እንኳን ፓየዝ ቸኩለህ በአደባባይ አታውጅ ብሎ ቢያስጠነቅቀውም ።”
“Next to arrive in Ethiopia was the Spanish-origin Father Pero Pais (Pedro Paez). …, he was still in his thirties. He had to endure a series of acute misfortunes, including capture by Turks and imprisonment in Dhofar and Yemen, on his first attempt to reach the country. ….He finally succeeded in landing at Massawa in 1603 disguised as an Armenian merchant and proceeded to Fremona by way of Debarwa. Sarsa Dengel had died and the country had fallen into a ten-year period of confusion over the succession. ... After waiting at Fremona for several months during which he studied Amharic and Ge'ez, Pais was summoned by the young emperor then on the throne, Za Dengel, … to come to Dankaz near Lake Tana, where he had returned from fighting against the Oromo in Damot.
Pais was a very different kind of man from Oviedo: gentle, learned, considerate of the feelings of others. He quickly mastered Ge’ez and Amharic and so impressed Za Dengel with his knowledge of Ethiopian customs and his careful explanations of Catholic belief and practice that the young emperor decided to convert, as did some members of his retinue, though Pais cautioned him against declaring himself openly to quickly. [35]“
ዘድንግልም ፤ በእዚኽ መልኩ ፔድሮ ፓየዝ የእሚባለው ፤ የካቶሊክ እምነትን ለማስፋፋት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት ጳጳሶች ፤ የሦሥተኛ ዙር የሆነው ሰው ተፅኖ አድርጎበት ፤ የመጀመሪያው የካቶሊክ እምነትን የተቀበለ የኢትዮጵያ ንጉሥ ይሆናል ።
ዘድንግል ካቶሊክ መሆኑን ምክንያት በማድረግ ፤ የተወሰኑ መኳንንቶቹ ፥ ለዘመቻ በወጡበት ፤ ጦራቸውን እየሰበሰቡ ስለ ከዱት ፤ በእዚኽ የተበሳጨው ዘድንግል ፤ አብረውት የነበሩትን የፖርቹጋል ወታደሮች እና ወደ 15 ሺ የእሚሆን የራሱን ጦር ይዞ በመኳንንቶቹ ላይ ይዘምታል ። ፖርቹጋልቹ ምንም መሬት ይዘው ቢዋጉም ፤ አብረውት የዘመቱት የሐገሬው ጦር በድጋሚ ስለ ከዳው ፤ በሰልፉ ሜዳ ላይ በጦር ከተወጋ በኋላ ፤ ንጉሥ ነው ብለው ስለ አከበሩት ፤ በሰይፍ እንደ አይገድሉት ፤ ከርቀት በቀስት ደብድበው ገደሉት ።
ዘ ድንግል በእዚኽ መልኩ ሲገደል እና ዙፋኑ ሲለቀቅ ፤ የእዛን ወቅቱ ፖለቲካ ያለ ንጉሥ አይሆንምና ፤ መኳንንቶቹ በእናርያ ግዞት ላይ የነበረውን ፤ ብላቴናውን ያዕቆብን በድጋሚ አምጥተው አነገሡት ።
ያዕቆብ በድጋሚ ከነገሠ በኋላ ፤ ከያዕቆብ ጋር በተያያዘ ኹለት አስገራሚ ክስተቶች ስለ ተከሰቱ ፤ እገረ መንገዳችንን ተመልክተናቸው እንለፍ ።
ያዕቆብ ከነገሠ በኋላ ፥ ለሰሶኒዮስ የዛሬዎቹን ጎጃም ፥ ሸዋ እና ወሎ (አንጎት) ግዛ እኔ ግን ንጉሠ ነገሥት ነኝ ቢለው ፤ ሰሶኒዎስ ይኽን አልቀበለም ስለ አለ ፤ ኹለቱ የሰለሞናዊው ስርወ መንግሥት ዘር የአለ፟ባቸው ሰዎች ፤ ዙፋኑ ለእኔ ነው የእሚገባኝ የለም ለእኔ ነው የእሚገባኝ በእሚል ወደ ጦርነት አመሩ ። በእዚኽ ጦርነት ያዕቆብ የተሸነፈ ሲሆን ፤ ያዕቆብን የገደለው ሰው ደፍሮ እኔ ነኝ ማለት ስለ አልቻለ ፤ አንዱ እኔ ያዕቆብ ነኝ ብሎ ፤ በጦርነት በጣም ስለቆሰልኩ ፊቴን እሸፍናለሁ ብሎ ፤ ፊቱን ሸፍኖ ፤ ሸፈተ ።
ይኽም ፤ ሕዝቡ ያዕቆብ አልሞተም ብለው እንዲያምኑ እና ተገቢው ንጉሥ ሌላ ነው በእሚል ፤ የሶስንዮስ ስልጣን አጣብቂኝ ውስጥ እንዲ ገባ አደረገው ። ይኽም አስመሳይ ሰው ጦር አደርጅቶ ፤ እኔ ነኝ እውነተኛው ንጉሥ እያለ ፤ ለረዥም ግዜ ከአስቸገረ በኋላ ፤ የትግራይ ሰዎች አድነው ይዘው ገደሉት ፤ በእዚኽም ፊቱ እንዳልቆሰለ እና እውነተኛ ያዕቆብ እንዳልሆነ ስለ ታወቀ ሰሶንዮስ ተቀናቃኝ የሌለው ነጋሢ ሆነ ።
ከአጼ ያዕቆብ ጋር የተያያዘው ኹለተኛው ክስተት ፤ ሉዶልፍ እንዳለው ፤ የያዕቆብ ታሪክ በእዚኽ መልኩ ከአበቃ ከጥቂት ግዜ በኋላ ፤ ሌላ ኢትዮጵያዊ አውሮፓ ኼዶ ፤ የተገደለው የንጉሥ የያዕቆብ ልጅ ነኝ ብሎ ፤ ራሱን በማቅረብ እና እነርሱም የንግሥት ሳባን ታሪክ ተከትለው የመጽሐፍ ቅዱሱ የንጉሥ ሰለሞን የልጅ ልጅ ነው ብለው እያከበሩት እና በጀት መድበው ሲያኖሩት ከርሞ በእዚያው ሞተ ። ከሞተ በኋላ ግን ፥ ንጉሥ ያዕቆብ በ20 ዓመቱ እንደ ሞተና ልጅ እንደ አልወለደ ስለ ሰሙ ፤ ሲጠራጠሩ ኖረው መቃብሩ ላይ እንዲኽ ብለው ጽፈው አስቀምጠዋል ፦
“በእዚኽ የኢትዮጵያ ንጉሥ አርፏል፥
እውነተኛው ፥ ወይንም ግልባጩ ።”
“Here lies the King of Ethiopia,
The Original, or else the Copy”
ወደ ዋናው ታሪካችን እንመለስና የኢትዮጵያን የመሐል ፖለቲካ በማፈረካከስ ፤ በብዙ ፈተና ውስጥ የነበረውን ፖለቲካ ወደ ባሰበት ውጥንቅጥ ውስጥ የአስገባው ፤ የእቡያኖቹ የጀስዊት ቄሶች እና የመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ነገሥታት እና መኳንንቶች ልዩነት ፤ በይዘቱ ይኽን ያኽል ችግር ሊያስከትል የእሚገባውም ችግር አልነበረም ከመጀመሪያውም ።
ምንም እንኳን አስቀድሜ እንደ አልኹት ፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ጀስዊቶቹ ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ይዘወተሩ የነበሩ አንዳንድ ጎጂ ልማዶችን ነቅሰው ማውጣት ቢችሉም ፤ ዓይነቱ ይለይ እንጂ ተመሳሳይ ስህተት ከራሳቸው ከካቶሊኮቹ እምነት ውስጥም ስለ ነበረ ብቻም ሰአይሆን ፤ ከአደራረግ ውጭ በቆኖና ጉዳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች በቂ እውቀት የነበራቸው በመሆኑ ፤ በተወሰኑ ሰዎች የባሕሪ አለመጣጣም እንጂ የተወሰኑ መጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም እና ልማድ ላይ ያሉ ልዩነቶች ፤ ለእዚኽ መሰል ግጭት መዳረግ አልነበረበትም ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ኃይማኖት ወዳጅ እና ሰሶንዮስን የተካው አጼ ፋሲለደስ ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና በሮማው ካቶሊክ መካከል ትርፍ በሆኑ ፦ እንደ ቁርባን ስረዓት ፣ የመነኩሴነት አስተዳደር ፣ ወዘተ ፤ ከአልሆነ በስተቀር በክርስትና ኃይማኖት የዕምነት አዕማዶች ላይ መሠረታዊ ልዩነት የሌለ መሆኑ እና ጠቡ እዚኽ መድረስ እንዳልነበረበት እንዲኽ ብሏል ፦
“ … ፋሲለደስ ፤ የአባቱ አማካሪ የነበሩትን መኳንንቶች እና አለቆች ከሰበሰበ በኋላ ፤ የእሚከተለው ድምዳሜ ላይ ደረሱ … በዕምነት ጉዳይ ሮም እና አሌክሳንድሪያ አንድ መሆናቸው ፤ ኹለቱም ክርስቶስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ መሆኑን የእሚቀበሉ መሆናቸው እና እነ እዚኽ ደግሞ በአንድ ተፈጥሮ ነው ወይስ በኹለት ተፈጥሮ ውስጥ ነው የእሚለው ክርክር ብዙም ዋጋ የሌለው የቃላት ክርክር በመሆኑ ፤ በእዚኽ ልዩነት ሐገር ማፍረስ እንደ እማይገባ አስቀመጡ ።”
“Basilides, after he had summoned the nobility and chiefs of his father’s Counsellors together, held a Council, wherein it was concluded … the Romanists and Alexanderians were of the same Opinion in points of Faith, That both affirmed that God was true Christ, and true Man, as for the asserting of One or Two Natures, they were words of little Moment, and not worth of the Ruin of a Mighty Empire. [104]“
ሆኖም ግን ፤ ከፓኤዝ በፊት የነበሩት ጀስዊቶች ዕቡይነት አግዶት የነበረው የካቶሊክ እምነት ፦ በግራኝ ጥቃት የደረሰው ውድመት ፣ የቱርኮች የባሕር በሮችን መዝጋት ፣ ቀጥታ እና የተልዕኮ ጦርነቶችን ማድረግ ፣ በደቡብ የአለው ከኦሮሞ መስፋፋት ጋር የአለው ጦርነት ፤ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በአዲስ መልክ ኢከነሚውን እና ወታደሩን ከአልገነባ አደጋ እንደ ተደቀነባችው የተረዱት ነገሥታት ፤ ራሳቸውን ለካቶሊክ ክፍት ወደ ማድረግ እንዲመጡ በማድረጉ ፤ ይኽም የነገሥታቱ አካኼድ ሕዝቡ በውቅቱ በነበረው መረዳት እጅግ ከፋፋይ ሆኖ ጦር ወደ መማዘዝ እንደ እናመራ ለአደረገው ፤ ለጀስዊቶቹ ከአሌክሳንደሪያ ወደ ሮም መዞር አለባችሁ ለእሚለው ዝብዘባ እንደ ገና አዲስ በር የከፈተለት ይመስላል ።
በእዚኽም መሠረት ፤ ከላይ እንደ አልነው ዘደንግል በአስተዋዪ ፓኤዝ ካቶሊክ ለመሆን ከወሰነ በኋላ ፤ የራሱ ሰዎች ገሸሽ ስለ አሉበት ፤ በጦርነት ላይ ሞተ ። እርሱንም ተክቶ የነገሠው ያዕቆብ ከሰሶኒዎስ ጋር ፤ እኔ ነኝ ዙፋኑ የእሚገባኝ ፤ የለም እኔ ነኝ የእሚገባኝ በእሚል ተለያይተው ወደ ውጊያ በማምራታቸው ፤ ጠንካራ ጦር የነበረው ሰሶኒዎስ በውጊያው አሸንፎ ነገሠ ።
ሰሶኒዎስም በንግሥናው ማግስት ፤ ከዘድንግል ሞት በኋላ ወደ ፍሬሞና የተመለሰውን ፓኤዝን ጠርቶ ፤ ከሮም ጋር ግንኝነቱን በማደስ ፤ ራሱን በግልፅ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ብሎ እና የኢትዮጵያም መንግሥታዊ ኃይማኖት ካቶሊክ ነው ብሎ ለማወጅ ዝግጅት አደረገ ።
ይኽ ነገሥታቱ የካቶሊክን እምነት የመቀበል አዲስ አቅጣጫ ግን ፤ ምናልባትም ፦ በእሚከተሉት ሦሥት ምክንያቶች አተገባበሩ መሠረታዊ ስህተት የያዘ በመሆኑ ፤ የሰሶኒዎስን ስልጣን በፈቃድ መልቀቅ ያስከተለውን ጦርነት በማምጣት በአሳዛኝ ኹኔታ ፍፃሜውን አግኝቷል ።
የመጀመሪያው እና ትልቁ ነገር ፤ በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ ፤ ብሎም በአብዛኛው ክርስትና ተከታዮች መካከል የአለው ልዩነት ፤ መሠረታዊ የእምነት ዓዕማዶችን የእሚነካ ዓይነት ልዩነት ሰአይሆን ፤ በመጽሐፉ ህደግ ላይ የአሉ፟ ጉዳዮች በመሆናቸው ፤ በኹለቱም ጎራዎች ሊኖር የእሚገባው ዓመለካከት ፤ ልዩነቱን አካሮ ከመጋጨት ይልቅ በእሚስማሙበት ላይ አተኩሮ ፤ እነ ገላውዴዎስ እንደ አደረጉት ፤ ካቶሊኮቹ በነፃነት እምነታቸውን ከማራመድ ውጪ የኢትዮያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለማጥቃት ሰአያስቡ ፤ ኹሉም በተረዳበት መልኩ መንቀስቀሱ ነበር የተሻለው መንገድ ።
ጀስዊቶቹ ግን ይኽ ነው የእሚባል የተሻለ ቀኖና ይዘው በአይመጡም ፤ እንዲያውም በወቅቱ ነገሥታቱን ጨምሮ የኢትዮጵያ ሊህቃን የነበራቸው የእምነት እውቀት ጀስዊቶቹን የእሚያስከነዳ ቢሆንም ፤ ጀስዊቶቹ በከኃዲነታቸው ፤ በኢትዮጵያ በጠቅላላ ይታይ የነበረው ተጋላጭነት ፤ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመው ፤ እኛ ብቻ ልክ ነን እና እኛን ብቻ ስሙን የእሚለው የንቀት አመለካከት በመያዛቸው ነገሩን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ወሰደው ።
ኹለተኛው ፤ ይኽንን ቁልፍልፍ የፔድሮ መምጣት መፍታት ሲጀምር ፤ ትልቁ የዓዕምሮ ገደብ የተነሳላቸው ነገሥታት ፤ ነባራዊውን የቤተክርስቲያን እና የመንግሥት መዋቅር ህልውና በእሚያሰጋ መልኩ ፤ በአንድ ለሊት ሐገር ምድሩን ካቶሊክ አድርገን ካል አደርን ወደ የእሚል ክንፈት ውስጥ የገቡ ይመስላል ።
ካቶሊክ መሆን ኃይማኖትን መካድ አይደለም ብለው የአመኑት ነገሥታት ፤ ከአውሮፓ በእሚመጣ የመሳሪያ እና የእውቀት እገዛ ፤ በእየ አከባቢው እረፍት የነሳቸውን ድህነት እና ጦርነት ማሸነፍ የእሚችሉበት ትልቅ በር ስለታያቸው ፤ በፍጥነት እድሉን ለመጠቀም መቸኮላቸው ፤ አዲሱ መዋቅራዊ ለውጥ በነዋሪው መዋቅር ላይ ከፍተኛ ቅራኔ እና ስጋት ፈጠረ ።
ለምሳሌ ፦ ሰሶኒዎስ ፤ የቱርኮችን የኤርትራ ባሕር እገዳ ለማሳበር ማልንዲ የእምትባለውን ከሞንባሳ ወደብ አጠገብ ያለችውን ወደብ አዲስ የኢትዮጵያ ወደብ በማድረግ ለመጠቀም በማሰብ ፤ በስውር የፖርቹጋል ቃኝ ወደ ደቡብ ልኮ ነበር ፦
“ሰሶኒዮስ አንቶንዮ ፈርናንዴዝ በእሚባል ቄስ ፤ በኢትዮጵያ በስተ ደቡብ አድርጎ በኬንያ ማልንዲ የባሕር በር አድርጎ ወደ አውሮፓ መንገድ በማግኘት ፤ ከሮማው ጳጳስ እና ከፖርቹጋል እርዳታ ለማፈላለግ እንዲኼድ ታስቢ ነበር ።”
“Susenyos dispatched a mission led by the priest Antonio Fernandes which was to travel via southern Ethiopia to Malindi on the coast of Kenya and then make its way to Europe to seek support from Portugal, Spain and the Pope. [35]“
ሆኖም ግን ፤ ይኽ የሰሶኒዮስ አካኼድ ኃይማኖታዊ እና ክህነታዊ ስጋት የፈጠረባቸው መነኮሳት ፤ የአላቸውን መንፈሳዊ ተፅኖ እየተጠቀሙ ፤ መንግሥት ከካቶሊኮች ጋር የእሚያደርገውን ትብብር በስውር ወደ ማፋረስ ውስጥ እንደ አስገባቸው በወቅቱ ታሪክ ይዘገባል። ጀምስ ብሩስ የተባለው ሰው ፤ ሰለ እዚኽ ጉዳይ እንደ እዚኽ ይላል ፦
“አምባሳደሩ እና ፈርናንዴዝ ፤ በቤኒሮ[13] ጥርጣሬ የሞላበት ቀዝቃዛ ነገር ግን የስልጡን አቀባበል ተደረገላቸው ። በኋላ ላይ የእዚኽ ቀዝቃዛ አቀባበል ምክንያት ፤ በልዑሉ ግቢ የነበረ አንድ መሰሪ የሆነ የሐበሻ መኖክሴ ፤ ለቤኒሮው አምባሳደሩ እና መልዕክተኛው ወደ ህንድ ይዘው የእሚኼዱት ጥያቄ ፤ በእዚኽ በእሚከፈተው አዲሱ መንገድ የፖርቹጋል ወታደር ላኩልን የእሚል በመሆኑ ፤ ወታደሮቹ ከመጡ ፤ እናርያ መጥፋቷ አይቀርም ፤ እንዲያውም ለእዚኽ አዲስ መንገድ ቅርብ በመሆኗ ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ግዛት ቀድማ ጠፊዋ ልትሆን ትችላለች ብሎ ሹክ በማለቱ እንደ ሆነ ደረሱበት ።”
“The ambassador and Fernandes were received by the Benero with an air of constraint and coolness, though with civility. They afterwards found, that the cause of this was the insinuation of a schismatic Abyssinian monk, then at the court of that prince, who had told him, that the errand of the ambassador and missionary to India was to bring Portuguese troops by that way into Abyssinia, which would end in the destruction of Narea, if it did not begin with it. [111]“
ከእዚኽ ኹኔታ እንደ እምንረዳው ፤ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቀሳውስት እና በካቶሊክ ጀስዊት መካከል የተደረገው ግብግብ ፤ በዋናነት ‘የርስት’ ግብግብ እንጂ የኃይማኖታዊ ቀኖና አይመስልም ። ጀስዊቶቹ ከጀብደኝነት ስሜት ወይንም ከተራ ምንደኝነት ተነስተው ፤ የኢትዮጵያን ቀሳውስት ኹሉ ዝቅ ዝቅ አድርገው ፤ ትልቋን እና ታላቋን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መውርስ ፈልገዋል ።
የኢትዮጵያ ቀሳውስት ደግሞ ፦ ያለ አግባብ ስለተገፉ ተቆጥተው እና የሐገራቸውንም ክብር አሳልፈው ለአለመስጠት በአደረጉት ግጭት ፤ መንፈሳዊው አቅጣጫ እና ተገቢው የመንግሥት ፖሊሲ ሊታረቁ በእማይችሉ ኹለት ፅንፎች በመወጠሩ ፤ ውሎ አድሮ መነኮሳቱ በወቅቱ እጅግ ጠንካራ ጦር በነበረው ሰሶኒዮስ ላይ ሐገሬውን በማሳመፃቸው ያ አሳዛኝ ጦርነት ተከስተ ።
ምንአልባት ፦ በወቅቱ ፋሲለደስ እንደ አለው የቀኖናውን ችግር መፍታት የእሚቻል ከነበረ ፤ እኛ የአልነው ከአልሆነ ፖለቲካዊ እና ኢከነሚያዊው እገዛ አይመጣም ብለው ደንቃራ የሆኑት ዕቡያኑ ጀስዊቶች ለማለፍ መንግሥት ሊከተለው ይገባ የነበረው አቅጥጫ ፤ ትልልቆቹ የኦርቶዶክስ አባቶች የካቶሊክን ቀኖና ተቀብለው ፤ ተሐድሶው ከውስጥ የእሚመጣ እና በቤተክርስቲያኒቱ ነባራዊ መዋቅር የእሚተገበር እንጂ ተኃድሶው ፤ በጀስዊቶች የእሚመራ እና ቄስ በሞላበት ሐገር ፤ ከውጭ ሐገር ቄስ የእሚያስገባ ተሐድሶ መሆን አልነበረበትም ።
በእዚኽ ኹኔታ በእየ አቅጣጫው በተወጠረው የወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሆኖ ፤ ከውጭ ሐገር በእሚገቡ እቡይ ቄሶች ካቶሊሲዝምን በሕዝብ ላይ ጭኜ ፤ የተደቀነብኝን ፖለቲካዊ እና ኢከነሚያዊ የህልውና አደጋ አልፋለኹ የአለው ሰሶኒዎስ እ.አ.አ. በ1624 ዓ.ም. አክሱም ላይ ኼዶ ፤ ካቶሊክ ሆኛለው ብሎ ከአወጀ በኋላ ኹኔታው ወደ ለየለት ጠብ አመራ ።
ለእዚኽ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ፤ ዘድንግልን እና ሰሶኒዎስን ፤ በመልካም በኃሪው ማርኮ ፤ ወደ ካቶሊክ ያመጣው ፓኤዝ ፤ ሰሶኒዎስ ኢትዮጵያ የካቶሊክ ክርስቲያን እምነት ተከታይ ሆናለች ብሎ በአወጀ በኹለተኛው ዓመት እ.አ.አ. በ1626 ዓ.ም. ስለሞተ ፤ በካቶሊክ እምነት አዲስ የኢትዮጵያ ኢጲስ ቆጵስ ሆኖ የመጣው አልፎንሶ ሜንዴስ ፤ የተለመደውን የጀስዊቶች ዕቡይነት በመከተል ፤ የካቶሊክ እምነትን ማስፋፋት ሰአይሆን ፤ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሐገሯ ላይ ወደ ማሳደድ በመግባቱ ነው ፦
“እርሱም (ሜንዴዝ) እጅግ አስቸጋሪ የሆኑ እና በአስቸኳይ በሐገሪቱ በሙሉ ተፈፃሚ ሊሆኑ ይገባቸዋል የአላቸውን ፤ የተለመደውን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልማድ የእሚያግዱ አዋጅ አወጣ ። ይኽ ታላቅ ክስተት የእዛው ዘመን ቀውስ መጀመሪያ ነበር ።”
“He proclaimed a series of onerous restrictions on continuation of any Orthodox practices and decreed their immediate imposition throughout the provinces. This grandiose occasion was the beginning of a troubled period. [35]“
ይኽ ኢፍትሓዊ ግፊያ ፤ ምናልባትም በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ ፤ አብዛኛው ሕዝብ በንጉሥ ላይ ጦር ያነሳበትን ኹኔታ ፈጠረ ። እንደ እሚታወቀው ፤ ሰሶኒዎስ የደረጀ ኃይል ስለ ነበረው ጦርነቱን ቢያሸንፍም ፤ የገደለው የሐገሩን ሕዝብ በመሆኑ ፤ ስልጣኑን ለልጁ ለፋሲለደስ አስረክቦ እንዲ ወርድ በኹኔታው ተገዶ ፤ የተፈጠረው ክስተት መጀመሪያውንም ባየነው መልክ ተወሳስቦ የነበረውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ የባሰ አጨለመበት ፦
“የስምንት ሺ ሰው ነፍስ ገብሮ ሰሶኒዋስ አሸነፈ ። በማግስቱም ጦርነቱ በተካኼደበት ሜዳ ላይ አብረው ሳሉ ፤ ልጁ ፋሲለደስ እንዲህ አለው ይባላል ፦
እዚኽ ሞተው የእምታያቸው ሰዎች ፤ በሞታቸው ደስ የእሚለን አረማዊያን ወይንም ሙስሊሞች አይደሉም ፤ ይልቁንም የአንተው ሕዝብ የሆኑ ክርስቲያኖች እና አንዳንዶቹ ዘመዶችህ ናቸው ። ይኼን እንደ ተቀዳጀነው ድል ልናየው አንችልም ፤ ሰይፋችንን የራሳችንን ሰውነት ወግተንበታል እና … ይኽንን ጦርነት በማካኼድ እና የአባቶቻችንን እምነት በመተው ፤ በአረማዊያን እና በአረቦች ዘንድ መዘባበቻ ሆነናል …”
“Susenyos defeated it at the cost of 8,000 killed. The day after the battle his son Fasilidas is reported to have said to him as they walked on the battlefield: The men you see lying dead here were neither pagans nor Muslims over whose deaths we could rejoice, but Christians, your subjects and fellow countrymen, and some of them were your kin. It is not victory that we have gained, for we have driven our swords into our own bodies. ... Through carrying on this war and abandoning the Faith of our ancestors, we have become a byword among the pagans and Arabs ... [104]“
ከእዚኽ በኋላ ፤ ሰሶኒዎስ ስልጣኑን ለፋስለድስ ሲያስረክብ ፤ ፋሲለደስ በአዲስ አዋጅ ፤ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እንደ ሆነች አውጆ ፤ አልፎንሶ ሜንዴስ እና ጓደኞቹን ፤ ወደ ፍሪሞና (ማይ ጓጓ) ላካቸው ።
የጀስዊቶቹ ዕቡይነት ግን ልክ ስለ አልነበረው ፤ እንደ ኦቪየዶ ወታደር ላኩልን ብለው ወደ ሐገራቸው ያልተሳካ መልዕክት ላኩ ። ከእዚያኽም በኋላ እንደ አኹኑ ስልክ በአይጠልፉም ፤ መረጃ የእሚጠልፉበት የራሳቸው መንገድ የነበራቸው የዘመኑ ነገሥታት ፤ አኹን በኬንያ የአለው የሞንባሳ ወደብ በፖርቹጋል መርከበኞች ተደበደበ የእሚባል ወሬ አጼ ፋሲለደስ ሲሰማ ፤ ሜንዴዝ በደቡብ አዲስ ትንኮሳ ሊጀምር ነው ብሎ ስለ አሰበ ፤ ፍሬሞና ወይንም እንዴት-ነበርሽ የተባለችውን ፤ ገላውዴውስ ለጀስዊቶች የሰጠውን መንደር ዘግቶ ፤ ጀስዊቶችን ጠራርጎ ከሐገር አስወጣቸው ፦
“ … ፋሲለድስ የፖርቹጋል ባሕር ኃይል ሞምባሳን ደበደበ የእሚል መረጃ ሲደርሰው ፤ ሜንዴዝ በደቡብ አዲስ ጥቃት አስጀምሯል ብሎ በማሰብ ፤ እርሱና እና ኹሉም ጀስዊቶች ኢትዮጵያን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ አዘዘ ።”
“… But when Fasiledes received word that a Portugese fleet had bombarded Mombasa, he assumed Mendes had instigated an attack from the south and ordered him and all the Jesuits to leave Ethiopia immediately. [35]“
እብደት ይሆን ሞኝነት ወይንም እልኽ ያልለየለት የጀስዊቶቹ ጥረት በእዚኽ ሰአያበቃ ፤ ከፊልም ነገሥታቱ ተቀብለውናል ቀሳውስቱ ናቸው የጠሉን ከእሚል ስሌት ይመስላል ፤ በተለያየ መንገድ እያሳበሩ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ቀጥለው ፤ በስተመጨረሻ የሆኑቱ ፤ ሳውኪን (አኹን የሱዳን ወደብ የሆነ ) ደርሰው ፤ ኑ እንዲላቸው በማሰብ ፤ ለፋሲለደስ ፤ ሳዊኪን ደርሰናል ብለው ደብዳቤ ላኩለት ፦
“ … የተሻለ እድል ይገጥመናል ብለው ፤ አንድ የመጨረሻ ሙከራ ሊያደርጉ ተነሱ ፤ እናም ሳውኪን ሲደርሱ ፤ ምን ዓይነት ምክር ሰምተው እንደ መጡ አላውቅም ፤ ልክ እንኳን ደስ ያለህ መጥተንልኃል መልዕክት የላኩ መስሏቸው ፤ መድረሳቸውን ለአቢስንያው ንጉሥ ደብዳቤ ላኩለት ። ንጉሡም ይኽን ደግነታቸውን ለመመለስ ፤ ምላሹን ደብዳቤ ለእነርሱ ሰአይሆን ለሳውኪኑ ባሻ ፤ ሰዎቹን ተውና ጭንቅላታቸውን ብቻ ላክልኝ ብሎ ጻፈለት ፤ ባሻውም እሸለማለኹ ብሎ አስቦ ፤ በፍጥነት እንዲያውም ከተጠየቀው በላይ አድርጎ ፤ አንገታቸው እንዲቀላ ከአደረገ በኋላ ቆዳቸው እንዲገፈፍ አድርጎ ፤ ሰዎቹ ፈረንጆች መሆናቸውን በቆዳቸው እና ቄስ መሆናቸው በፀጉር አለጫጨታቸው እንዲለዩ ላከለት ።
ከቆይታ በኋላም በርናርድ ኖግዌራ ፤ የተባለው የመጨረሻው ቄስ ተይዞ ፤ በፍትኃዊ መንገድ በስቅላት ተቀጣ ።”
“… in hopes of better Fortune, resolved to make one tryal more, who when they arrived at Suaqena, I know not by what advice, wrote letters to the Abyssine King, as if it were to congratulate him upon Their arival. But the King to retaliate their Kindness, wrote back to them, but to the basha of Suaqena, to send him only their Heads; which the Basha in hopes of Reward, very readily did, with a more than ordinary Ceremony. For after he had caused their Heads to be strucken off, he ordered their Skin to be Shead off, and to sent them to the King; that by their Colour he might know them to be Franks, and by their Shavings to be Priests.
At length also Bernard Nogueira was apprehended, the last of all the Fathers, and fairly hanged. [104]“
ለመቶ እና ከእዛኽ በላይ ዓመታት ፤ የብዙ ሰዎች ላብ እና ደም የተከፈለበት ፤ ኢትዮጵያን የአውሮፓ ህዳሴ አካል ማድረግ ጥረት ፤ ዕብሪት ልቦናቸውን በከደነባቸው ስግብብ የካቶሊክ ቄሶች በእዚኽ መልኩ ተሰነካክሎ ፤ ኢትዮጵያን እንደ ሐገር አራቁቶ ፣ በስንት ችግር የተገነቡ ነግሮች በሙሉ አውድሞ ፤ የእየ ወቅቱ ፣ የእየ አከባቢው ኃያላን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ፤ ከጠባቡ ከባቢያዊ ፍላጎታቸው አንፃር ሐገራዊ ፖለቲካውን የእሚዘውሩበትን ፤ አዲስ አሉታዊ ፖለቲካዊ ልማድ ፤ በእዚኽ መልኩ ለቀጣዩ ኹለት መቶ እና ከዛ በላይ ለሆኑ ዓመታት ፤ በኢትዮጵያ አነገሠ ።
የሕዝብ ስብጥርን መቀየር ዋነኛ ስልቱ የአደረገው የዖሮሞ ስፋት የአለው ሰርጎ ገብነት
መንግሥትን በእዚኽ መልኩ አዳክሞ ዘመነ መሣፍንትን ለማፋፋም ያገዘው ፤ በእዚኽ የታሪካችን ክፍል የተከሰተው አራተኛው እና የመጨረሻው ክስተት ፤ በ10ኛው ምዕተ ዓመት ይኖርበት ከነብረው የብሪትሽ ሶማሊያ (ምስል 9 : የሶማሊ ጎሳዎች ስርጭት በሱማሊያ። [100] ይመልከቱ) ፤ ከሶማሌ ሕዝብ ፥ በኋላም በዛሬው ሶማሌ ከኦሮሞ እና ከሶማሌ በፊት ነዋሪ በነበሩ የባንቱ ሕዝብ ጦርነት እንዲኹም በአረብ ሱልጣኖች ሴራ ከስፍራ ስፍራ እንዲሰደድ ተገዶ የነበረው የኦሮሞ ሕዝብ ፤ ከመኖሪያው ከዛሬዋ ሶማሊያ ተነስቶ እንደ ባሊ ያሉ ደቡብ ምዕራባዊ የኢትዮጵያን ግዛቶች ማጥቃት እና ወደ መሐል ኢትዮጵያ በስፋት መስረግ መጀመሩ ነው ።
የኦሮሞ ሕዝብ በእዚኽ መልኩ የእዚኽ ዘመን አራተኛ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ትኩሳት የሆነበትን አግባብ ለማየት ፦
የኦሮሞ እና የሱማሌ ሕዝብ ከፍተኛ ታሪካዊ ቁርኝት የአላቸው እና ምን አልባትም ፤ የሶማሌ ሕዝብ ይበልጥ በአረብ ባሕል ተጽኖ ስር እየገባ በመኼዱ ኹለቱ ሕዝብ የተለያየ ባሕላዊ ማንንነት እያዳበሩ ሳይኼዱ በፊት አንድ ሕዝብ ሊሆኑ እንደ እሚችሉ ይገመታል፦
“ሶማሊዎች የተለዩ እና ራሳቸውን የቻሉ ካማዊ ሕዝብ ይኹኑ ወይንስ ከፍተኛ የአረብ ተጽኖ የአለባቸው የሌላው እና በጣም የቀረበ ታሪካዊ ትስስር ከአላቸው ትልቅ ምሥራቃዊ ካማዊ ሕዝብ የጋላ ሕዝብ አንድ ወገን ይኹኑ በእርግጠኝነት መናገር ያስቸግራል።”
“But it is impossible to determine yet whether the Somali are to be regarded as an independent Hamitic stock, or whether rather they are to be considered as a heavily arabicized segment of the great branch of the Eastern Hamites, the Galla, with whom they are closely connected historically. [100]”
በእርግጥ ሶማሊ የእሚለው ስም ራሱ እስከ 15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የእማይታወቅ በመሆኑ ፤ ይኽ ግምት የተወሰነ ቦታ ሊሰጠው ይችላል ፦
“በእርግጥ ሶማሌ የእሚለው የነገድ ስማቸው ከ15ኛው ምዕተ ዓመት አስቀድሞ ተጥቅሶ አይገኝም ፤”
“Indeed the ethnic name ‘Somali’ itself is not recorded until the fifteenth century, [100]”
ኹለቱም ሕዝብ ከብት አርቢ እና ተንቀሳቃሽ ሕዝብ መሆናቸው ፣ ወደ ዛሬዋ ሶማሌ አከባቢ በአንድ ዘመን ላይ መስፋፋታቸው ፣ ከእስልምና በፊት ዋቄ በእሚለው አምልኮ ስር መኖራቸው ፤ በእነ እዚኽ ኹለት ሕዝብ መካከል የቆየ ግንኙነት መኖሩን ሌላው አሳዪ ነው።
አብዛኛውን የውትድርና ዘመናቸውን በምሥራቁ የኢትዮጵያ ግንባር ላይ ያሳለፉት እና ስለ ሶማሊያ ሕዝብ ተግባራዊ እውቀት የአላቸው ፤ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ፤ የገዳ ስረዓት እና የዋቄ ፈታ አምልኮ የሶማሌ ሕዝብ እና የኦሮሞ ሕዝብ የጋራ ባሕል እና እምነት እንደ ሆነ እንዲኽ ይላሉ ፦
“በሐገራችን በኢትዮጵያ ጥንታዊው የኦሮሞ ማሕበረሰብ ይመራበት ወይንም ይተዳደርበት የነበረውን ዓይነት የገዳ ስረዓት የመሰለ የጎሳ መተዳደሪያ ስረዓት አላቸው (ሱማሌዎች)። [112]”
የኦሮሞ ሕዝብ በታሪክ በጣም ከእሚዛመደው የሶማሌ ሕዝብ ጋር ትክክለኛ ምንጫቸው ከየት እንደ ሆነ የእሚያሳይ ታሪካዊ ዘገባ በአይገጥመኝም ፤ ቢያንስ ከ10ኛው ምዕተ ዓመት ጀምሮ ፤ በኤደን ሰላጤ የሶማሌ ሕዝብ ታጁራ የእሚባለው እና የኦሮሞ ሕዝብ ደግሞ አኹን ሱማሊላንድ ወይንም ቀድሞ የእንግሊዝ ፕሮክቶሬት የእሚባለው አከባቢ መኖር እንደ ጀመሩ ይገመታል።
ይኽንን ታሪክ ይልማ ደሬሳ በእዚኽ መልኩ ያስቀምጡታል ፦
“ታሪክ ሲነጋጋ የኦሮሞ ሕዝብ ከአደን ሰላጤ እና እስከ ቅርብ የእንግሊዝ ሱማሌ በእሚባለው የሱማሌ ሪፐብሊክ አውራጃ መካከል ከእሚገኘው የአፍሪካ ቀንድ በተባለው አገር ሲኖሩ ታዩ። … እነሱም ሳይሰፍሩበት በአፍሪቃ ቀንድ የነበረው ጥንታዊ ሕዝብ የትኛው ነገድ እንደ ነበረ አናውቅም። [102]”
እንደ ገናም ይልማ ደሬሳ ቀጠል አድርገው ፦
“አየሩ እንደ እሳት ከእሚያቃጥል ከሕንድ ውቅያኖስ ወደብ ለቀው የመጡት ሕዝብ (ኦሮሞዎች)ለምለምና ቀዝቃዛ በሆነው ወይና ደጋ ጤናማና አካለ ብርቱ የሆነ ትውልድ ሆነው ለመራባት ደረሱ። [102]”
ታጁራ እና የእንግሊዝ ሱማሌ የእሚለውን ቦታ በዛሬዋ ሶማሊያ ካርታ ላይ ለማየት ይኽንን ፦ ምስል 9 : የሶማሊ ጎሳዎች ስርጭት በሱማሊያ። [100] ይመልከቱ።
ይልማ ደሬሳ ኦሮሞ በአፍሪካ ቀንድ ወይንም የዛሬዋ ሶማሊያ የእንግሊዝ ሱማሌ በእሚባለው ቦታ ከመታየቱ በፉት የዛሬው ሶማሊያ ነዋሪ ነገዶች ማን እንደ ነበሩ አይታወቁም ቢሉም ፤ ሌሎች ጥናቶች ከኦሮሞ በፊት በሶማሊያ የነበሩት ማን እንደነበሩ ይነግሩናል።
“ከካም ወገን የሆኑት ጋላ እና ሶማሊ ወደ ደቡባዊ ሶማሊያ ሰርገው ከመግባታቸው በፊት ፤ ቢያንስ በኹለቱ ወንዞች መሐከል ፤ አከባቢው ቢያንስ የራሳቸው ኹለት ባሕላዊ ይዘት በአላቸው ፤ የጥንት አረብ ጂኦግራፈርስ ‘ዘንጊ’(ጥቁሮች) ብለው የእሚያውቁዋቁዋቸው የጥቁር እና የባንቱ ሕዝብ ቅይጥ መኖሪያ ነበር። … ሌሎቹ ከእነ እዚኽ ካማዊያን ቀደም ብለው በቦታው ይኖሩ የነበሩት ሕዝብ … በጠቅላላው ሪቢ (ወይንም ዋሪቢ) እና ቦኒ (ወይንም ዋቦኒ) ተብለው የእሚታወቁ ናቸው።”
“Before the incursions from the north of the Hamitic Galla and Somali, southern Somalia, at least between the rivers, was occupied by a mixed negroid or Bantu population which seems to have contained at least two main cultural elements and which was known to the early Arab geographers as the ‘Zengi’ (Blacks)…The Second pre_Hamitic population;….generally known as Ribi( or WaRibi) and as Boni (or WaBoni). [100]”
ከእላይ ይልማ ደሬሳ እንደ አሉትም ሌዊስ የእሚባለው ጸሐፊ የዛሬው ሶማሊላንድ ከሶማሊዎች በፊት የኦሮሞዎች መኖሪያ ለመሆኑ እንደ እዚኽ ይላል ፦
“ሰሜናዊ ሱማሊላንድ ኹሉም ወይንም አብዛኛው ስፍራ ከሱማሌዎች በፊት የጋሎች መኖሪያ መሆኑ የብዙዎች እምነት ነው። በቅርቡ የተደረጉ ጥናቶችም ይኽን እምነት የእሚያጠናክሩ ናቸው። ለእዚኽም ማጠናከሪያ እጅግ ጥሩ ከእሚባሉ ማስረጃዎች መካከል ፦
ናቸው።”
“It has generally been assumed that the Galla occupied much if not all of northern Somaliland prior to the Somali. And recent research has lent firm support to this view. The best evidence for this depends upon Somali oral tradition, upon the presence today of residual pockets of Gall amongst the northern Somali – especially in the west and Ogaden region, and the fact that a number of place-names in the British Protectorate are almost certainly of Galla origin. [100]“
ኦሮሞዎች በእዚኽ የእንግሊዝ ሱማሌ በእሚባለው አከባቢ ከታዩ በኋላ ፤ የሱማሌ ሕዝብ ታጁራ ከእሚባለው አከባቢ እየተነሳ ስለ ወጋቸው ይኽንን አከባቢ ለቀው መጀመሪያ ወደ ደቡባዊ ምሥራቅ ሶማሊያ እንደ ሸሹ ከእዛም ከሱማሌ እና ከባንቱ ሕዝብ በድጋሚ በደረሰባቸው ውጊያ ከእዚያኽም ሸሽተው ዲናብር በእሚባለው በሶማሊያ ውስጥ በጁባ እና ዋቢ ሸበሌ ወንዞች አከባቢ እንደ ኖሩ ይልማ ደሬሳ እንዲኽ ይላሉ ፦
“… ሱማሌ የተባለው ነገድ ከታጁራ ቤይ አቅጣጫ ተንቀሳቅሶ በኦሮሞዎች ላይ ጦርነት በአደረገ ግዜ መጀመሪያ የእንግሊዝ ሶማሌ የነበረውን አገር ለቀው ወደ ምሥራቅ ደቡብ መጓዝ እንደ ጀመሩ ታውቋል። ኋላም የአፍሪካ ቀንድ ከእምትባለው ሦሥት ማዕዘን ወረዳ ተነስተው በዋቢ ሸበሌና በጁባ ወንዞች መካከል ቤናዲር በተባለው አውራጃ ሰፍረው ከዚያ ብዙ ዘመን እንደ ኖሩ በኦሮሞዎች አፈ ታሪክ ሲነገር የኖረ ነው። [102]”
ይኽም ማለት የኦሮሞ ሕዝብ የእንግሊዝ ሱማሌ አከባቢ ከታየ በኋላ ከሶማሊዎች በደረሰበት ጦርነት ሸሽቶ ፤ መጀመሪያ ወደ ደቡብ ምሥራቅ ሶማሊያ (ሞቃዲሾ አከባቢ) ከእዛም ወደ ሶማሊያ ሰሜን ምዕራብ ዴናቢር የእሚባለው አከባቢ ገብቷል። ይኽን የይልማ ደሬሳ ታሪክ ሊውስ የተባለው ሰው ፤ በአረቡ ቁጥጥር ስር እየዋሉ የመጡት ሱማሌዎች ወደ 12ኛው ምዕተ ዓመት አከባቢ ኦሮሞዎችን መውጋት እና ከአከባቢው ማፈናቀል ጀመሩ ብሎ በማስቀመጥ የይልማ ደሬሳን ታሪክ ያጠናክረዋል ፦
“….በ12ኛው ምዕተ ዓመት ድር እና ዳሮ ወደ በኋላም ላይ ኢሳቅ የጋላ ጎሮቤቶቻቸው ላይ ጫና በማሳረፍ ፤ ጋላው በእየግዜው እንዲሸሽ እና አከባቢውን በስተመጨረሻ እንዲለቅ የአደረገው ኺደት ተጀመሯል ማለት ይቻላል።”
“ … about the twelfth century the Dir and Darod, and later the Isaq, were pressing upon their Galla neighbors and great series of movements which finally disestablished the latter can be said to have begun. [100]”
እነ እዚኽ ድር ፣ ዳሮድ እና ኢሳቅ የእሚባሉት የሱማሌ ጎሳዎች ከ10ኛው ምዕተ ዓመት በኋላ በመሰረቷቸውን እና የአረብ ሱልጣን ሆነው በእሚመሯቸው ሼክ ድር ፣ ሼክ ዳሮድ ፣ ሼክ ኢሳቅ ስም የእሚጠሩ ጎሳዎች ወይንም የሼኮቹ የግል ጦር ሰራዊቶች ናቸው።
በሶማሌ ሕዝብ በኦሮሞዎች ላይ ጦርነት ከተከፈተባቸው እና የመጀመሪያ መኖሪያቸው የሆነው ሶማሊላንድ ከለቀቁ በኋላ በ13ኛው የሶማሊያ የሕዝብ ስብጥር ምን መልክ እንደ ያዘ ሊውስ እንደ እዚኽ ያስቀምጠዋል ፦
“… በእዚኽ ምዕተ ዓመት (በ13ኛው) በአከባቢው የነበረው የሕዝብ ስርጭት ይኽን ነው የእሚመስለው ፡ ሀውዬ ስማሊ ኢታላ እና መርካ በእሚባሉት የባሕር ጠረፎች ላይ ፤ ከእዚያ ወደ ደቡባዊ ውስጥ ሲወርዱ ጅዱ ፤ እና በእስተ ምዕራብ ጋላ።”
“…it seems that by this century the local distribution of peoples was as follows : the Hawiye Somali in the coastal region between Itala and Merca; further south and towards the interior the Jidu; and finally to the west the Gala. [100]”
ምስል 9 : የሶማሊ ጎሳዎች ስርጭት በሱማሊያ። [100]
ይኽ በዛሬው ሱማሊያ በ13ኛው ምዕተ ዓመት ላይ የነበረው የጋላ እና የሱማሌ ስብጥር የእሚመለከት ነው።
ሊውስ በተጫማሪ ኦሮሞ በሶማሊያ በጁባ እና በዋቢ ሸበሌ ወንዞች መካከል ይኖሩ እንደ ነበር ይኽን ማስረጃ ያቀርባል ፦
“ጋሎች ቀድመው በእዚያ ይኖሩ እንደ ነበር ፤ በሸበሌ እና ጁባ መካከል በእሚኖሩት በራሃንዊን እና ድግል ሶማሊ ሕዝብ መካከል የተዋቸው አናሳ ወገኖቻቸው ፤ የፀና ማስረጃ ሆነውላቸዋል።”
“But they left behind them secure evidence of their former presence in the many Galla minority groups today found amongst the Rahanwin and Digil Somali of the Shebelle and Juba regions. [100]”
የኦሮሞ ሕዝብ በሶማሊያ ውስጥ በነበረበት ወቅት ከሶማሌዎች ብቻ ሳይሆን ባንቱ ከእሚባሉት ሕዝብ ተመሳሳይ ጦርነት ይደረግበት ነበር። ይልማ ደሬሳ ይኽን እንዲኽ ይገልጹታል ፦
“ኦሮሞዎች ጥንታዊ አግራቸውን ለቀው በቤናዲርና በቆላው ባሌ ከሰፈሩ በኋላ የጸጥታ ኑሮ ለማግኘት አልቻሉም። ከሰሜን ወደ ደቡብ በተጓዙ ግዜ በሰፈሩበት አገር በስተ ደቡብ ባንቱ የእሚባሉ አርበኛ ነገድ ጎረቤት ሆኗቸው። ስለ እዚኽ ፦ ከሰሜን የሱማሌዎች ከደቡብ ባንቱዎች የእሚያደርጉባቸው ጦርነት ምንም ግዜ ምንም ሰላም የሰጣቸው አይመስልም። [102]”
ኦሮሞዎች በእዚኽ መልኩ ከ10ኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ ከ4 መቶ ለአላነሱ አመታት በሶማሊያ ውስጥ በነበሩበት ዘመን ፤ ከሶማሌዎች እና ከባንቱዎች በገጠማቸው በጦርነት ምክንያት ከሶማሊላንድ ወደ ደቡብ ምሥራቅ ሶማሊያ ከእዛም ቤናድር ወደ እሚባለው ሰሜናዊ ምዕራብ ሱማሊያ ቦታ ሲቀይሩ ከቆዩ በኋላ ነው ፤ በ16ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አከባቢ በግራኝ ጦርነት ምክንያት በመዳከሙ ምክንያት ድንበሩን መቆጣጠር ወደ አልቻለው የኢትዮጲያ መንግሥት ግዛት በባሌ በኩል አድርገው መግባት የጀመሩት ።
የወቅቱ የኢትዮጲያ መንግሥት በግራኝ አህመድ እና በእርሱ ተከታዮች በደቡብ ምሥራቅ ፣ በቱርኮች በሰሜን ምሥራቅ እና በጀስዊት ቄሶች ምክንያት በውስጥ በእርስ በእርስ መከፋፈል ተወጥሮ በእነ በረበት በእዚኽ የ16ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የኦሮሞ ሕዝብ ፤ ከሶማሊያ ተነስቶ በመጀመሪያ በባሊ ከእዛም በግዜ ኺደት ወደ አብዛኛው የኢትዮጲያ ደቡባዊ ምዕራብ እንደ ተሰራጨ በቡዙ የወቅቱ እና ከእዛ በኋላ በአሉ የታሪክ መጽሐፍት ተመዝግቦ የእሚገኝ ነው።
የግራኝ ጦርነት ተገባዶ ፤ የፖርቹጋሎች ኢትዮጵያን ካቶሊክ የማድረግ የመጀመሪያው ጥረታቸው ከስሞ ፤ በእየ ሐገሩ ርስት እየተሰጣቸው እንዲሰፍሩ የተደረጉት ፖርቹጋሎች ፤ ባሌ ላይ ርስት ተስጥቶዋቸው በተቀመጡበት ወቅት ፤ መኖሪያቸው የዛሬዋ ሶማሊያ አካል ከሆነው መቋዲሾ እየተነሱ ጥቃት ከእሚሰነዝሩት የዖሮሞ ሕዝብ የገጠማቸውን አደጋ የዘገበበት ኹኔታ ፤ የመጀመሪያው የኦሮሞ የኢትዮጲያ ወረራ እንቅስቃሴ ያሳያል ፦
“ … ይኽም ከሆነ በኋላ ፤ ጋላዎች በድንገት ሊያጠቁን በዝግጅት ላይ በመሆናቸው እንድ እንጠነቀቅ መልዕክት ላከብን ። ምክንያቱም ፦ በወቅቱ እነርሱ ወይንም ሌላ የቀሲስ ዮሐንስ ጠላት ሊያጠቃን ቢመጣ ራሳችንን በራሳችን ከመከላከል ሌላ አጋዥ እንደ ሌለን ስለ አወቁ ፤ ሊያጠፉን ቆርጠው ነበር ። ጋሎች ሞቃዲሾ በእሚባለው ቦታ አከባቢ የእሚኖሩ ሲሆን ፤ በአጎራባች ሐገሮች ላይ ሰውን ለማጥፋት እና ባድማ ለማድረግ ሲሉ ብቻ ጦርነት የእሚያደርጉ ፤ ጨካኝ እና ኃይለኛ ሕዝብ ናቸው ። አሸንፈው በያዙት ቦታ ፤ ወንዱን ኹሉ ይገድላሉ … እድሜያቸው የገፋ ሴቶችን ይገድላሉ ፤ ወጣቶቹን ሴቶች ሊጠቀሙባቸው እና እንዲያገለግሉዋቸው ይወስዳሉ ።”
“…at the end of which time the King sent word to us that we should be on our guard, as he had learned that the Gallas were going to attack us suddenly: because they were determined to destroy us in any possible way, in as much as neither they nor any other enemies of the Prester John had any hindrance save that we caused them. These Gallas lived in the country near Magadoxo; they are a fierce and cruel people, who make war on their neighbors, and on all, only to destroy and depopulate their countries. In the places they conquer they slay all the men, … kill the old women, and keep the young for their own use and service. [113]“
ከእዚኽ በተጨማሪውም ፤ የኦሮሞ ሕዝብ ከእሚኖርበት ሶማሊያ ፤ ከሶማሌ ሕዝብ የደረሰበትን ጦርነት ሽሽት ከግራኝ ወረራ በኋላ በመዳከሙ ምክንያት ድንበሩን መከላከል በተሳነው የኢትዮጲያ መንግሥት ግዛት ውስጥ በ16ኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ አከባቢ ጥሶ መግባት እንደ ጀመረ ሌዊስ የእሚባል ሰው እንዲኽ ይላል ፦
“የአህመድ ጥቃት የአብሲኒያኖቹን በደቡብ ምዕራብ የመከላከል አቅም ስለ አዳከመው ፤ በ16ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አከባቢ ሱማሌው ያስጨነቃቸው ጋሎች በብዛት ዘልቀው እንዲገቡ አስችሏቸዋል።”
“Ahmad’s attacks to a corresponding weakening of Abyssinian resistance in the south-west where the Galla, pressed by the Somali, were able to penetrate in very large numbers early in the sisteenth century. [100]”
እንደ ገናም ፤ በኦሮሞዎች ቋንቋ ጋላ ማለት ‘ስደተኛ’ የእሚል በመሆኑ ፤ ሐበሾች እና አረቦች ናቸው ጋላ የእሚሉዋቸው እንጂ ፤ ጋሎች ራሳቸውን በቋንቋቸው ጠንካራ ፣ ጀግና ወይንም ‘ኦርማ’ ብለው ነው የእሚጠሩት ብሎ ፤ ኦሮሞዎች የጣዖዎት አምልኮ የሌለባቸው ስለ ሆኑ ፤ ወረው የሰፈሩበትን የአበሻ ክልል ኦርማኒያ ብለን ሰይመን ፤ በአውሮፓ ባህል እና በክርስትና ከቃኘነው ፤ አውሮፓዊያንን ወደ እዛ በማሰደድ ትልቅ ስልጣኔ መፍጠር እንችላለን የእሚለው ፤ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1840 ዓ.ም. አከባቢ በኢትዮጵያ የነበረው ሚስዮናዊ ፤ ኦሮሞዎች ከሸዋ በስተደቡብ የያዙት አከባቢ ከአበሾች በእዚኽ ዘመን የወረሩት እንደ ሆነ ይነግረናል ፦
“በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ግራኝ አህመድ ምድሪቱን ወገቶ ከአወደማት በኋላ ፤ … ጋሎች የአበሾቹን ምርጥ ቦታዎች ያዙ።”
“When in the sixteenth century Mohammed Gragn overran and destroyed the land, coming from the south … the Gallas seized on some of the finest portions of Abyssinia. [114]“
እ.አ.አ. 1593 ዓ.ም. የጻፉት መጽሐፋቸው በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የእሚነበብላቸው አባ ባሕሪም ኦሮሞ መጀመሪያ ወደ ኢትዮጲያ የገባው በ16ኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ አከባቢ እንደ ሆነ እንዲኽ ይላሉ ፦
“የእዚኽ መጽሐፍ ባለቤት እንዲኽ ይላል ፡ ጋላው በአጼ ወናግ ሰገድ ዘመን ከምዕራብ ወጥቶ ገለና የእሚሉትን የሐገሩን ወንዝ ወደ ባሊ ዳርቻ ተሻገረ። እርሱም በረይቱማ እና ቦረን የእሚባለው ኹለት ነገድ ነው። [115]”
ወናግ ሰገድ በ1500-1533 (የፈረንጆቹ) የነገሠው የልብነ ድንግል የንግሥና ስም መሆኑን እና ልብን ወይንም ስሂን በግዕዝ ዕጣን ማለት ስለሆነ ፤ ልብነ ድንግል ወይንም ስሂነ ድንግል ማለት ዕጣነ ድንግል ማለት መሆኑን እና ወናግ አንበሳ ማለት በመሆኑ ወናግ ሰገድ ማለት አንበሳ ሰገድ ማለት ነው ብለው አባ ባሕሬይ አጼ ወናግ ሰገድ ሲሉ አጼ ልብነ ድንግል እያሉ መሆኑን ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ በመጽሐፋቸው [115] ግርጌ ላይ ያብራራሉ።
ስለ እዚኽ ኹኔታ ፤ ይልማ ደሬሳም ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ በ16ኛው ክፍለ ዘመን በእሚለው መጽሐፋቸው ላይ ፤ በ1524 ዓ.ም ዖሮሞዎች የዛሬ ኬንያ እና ሶማሌ ውስጥ ከአሉ አከባቢዎች እየተነሱ ፤ በባሊ የአለውን የንጉሡን ግዛት ያጠቁ ነበር ፤ በእሚል አስቀምጠውታል ፦
“ … የዖሮሞ ነገድ በ1524 ዓ.ም ከደቡባዊ መኖሪያው መንቀሳቀስ ጀመረ … ታላቁ ወረራ ግንባር ቀደም ለመሆን ዕድል የመረጣቸው ጃዊ የተባሉት የባርቱማ ክፍል ጎሳዎች ናቸው ። … የጃዊ ጎሳ ከደቡብ ተጉዞ የዌብን ወንዝ ከተሻገረ በኋላ ባሌን ወረረ ። … በእዚኹ ዘመን አዝማች ፋሲልን በመተካት በባሌ ግንባር ለመከላከል ኃላፊነት የተሰጠው ሐመልማል ለተባለው ለስመ ጥሩ የጦር አዛዥ ነበር ። ጃዊዎች ዋቢን ተሻግረው ባሌ መግባታቸውን በሰማ ግዜ አዝማች ሐመልማል በትረ አሞራንና ሌሎችንም በባሌ ውስጥ የእሚገኙትን የንጉሠ ነገሥት ሠራዊት አስከትሎ ወደ ደቡብ ገስግሶ ገጠማቸው ። [102]”
ከእዚኽም በኋላ ፤ የሐመልማል ጦር ዖሮሞዎችን ሊያቆማቸው ስለ አልቻለ ፤ ባሌን ከወረሩ ከወደ 40 ዓመታት ገደማ በኋላ ከረዩ ፤ የዖሮሞ ጎሳ ከባሌ ወደ ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ እንደ ተስፋፋ እንዲህ ይላሉ ፦
“ታላቁ የዖሮሞ ወረራ ባሌ ውስጥ በተጀመረ በአምስተኛው ገዳ … የከረዩ ነገድ በስተ ምሥራቅ የእሚገኘውን ደጋ ወይና ደጋ አጠቃሎ ያዘ ። [102]”
በባሌ የጀመረው ታላቁ የዖሮሞ ወረራ ፤ በግራኝ የተዳከመው ሕዝብ ፣ በሰሜን የቱርክ ወረራ የተወጠረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፣ የጀስዊት ቄሶች በጫሩት ልዩነት ተከፋፍሎ መንግሥት የመከላከል አቅሙ ስለተዳከመ ፤ ኦሮሞ በጥቂት ግዜ ሸዋ ደርሶ ነበር ፦
“አጼ ሠረፀ ድንግል ጃዊዎችን ለመውጋት ወደ ዋግ ሲገሰግሱ በምዕራብ በኩል ሜጫዎች ተሻግረው ዳሞትን ወረው ዘረፉ ። በስተ ምሥራቅ ደግሞ ቱሉማዎች ሸዋን እንደ ገና ወረሩ ። [102]“
የኦሮሞዎች ብሎም የሱማሌ ሕዝብ መጀመሪያ ላይ ከታዩበት ከሐሩራማው የሶማሊላንድ እና የታጁራ አከባቢ ተነስተው መጀመሪያ ላይ በመላው ሱማሊያ ላይ በኋላም እርስ በእርሳቸው ቢጋጩም በኢትዮጲያ እና በኬንያ ላይ እንዲሰራጩ የአደረጋቸው ዋናው ምክንያት የእሚመስለው በመካከላቸው ሰፍረው ኃይማኖታዊ እና የንግድ አጀንዳ የአላቸው የአረብ ሰፋሪ ሱልጣኖች ናቸው ፦
“በተዘዋዋሪ እንዲያውም በቀጥታ ሊሆን ይችላል አረቦችን በውስጡ ማስገባቱ የሱማሌ እና የጋላ ሕዝብ ዛሬ ለያዘው ስርጭት መነሻ ምክንያት ነው።”
“And indirectly if not directly the absorption of Arabian settlers stimulated the movements of expansion of the Somali and Galla. [100]”
ከእዚኽ የተነሳ ይመስላል ፤ ተሳዳጅ እና ይኽ ነው የእሚባል የተደራጀ ማሕበራዊ መሠረት እና ስረዓት ያልነበረው ሕዝብ ፤ በድንገት የሕዝብን ፖለቲካዊ ማንነት ደምስሶ ማሕበራዊ ህልውናን የእሚያጠፋ ፤ ገዳ የእሚባል ስረዓት አራማጅ የሆነው።
የኦሮሞ ሕዝብ ከገዳ ስረዓት ጋር የተዋወቀው ከ15ኛው ምዕተ ዓመት በኋላ እንደ ሆነ በታሪክ የተመዘገበ ነው ፦
“ኦሮሞ ከገናሌ ፣ ጋላና ዱሊ እና ጃላና ሳጋን ወንዞች ተፋሰስ ተከትለው ከመንቀሳቀሳቸው በፊት (እነ እዚኽ ወንዞች ሱማሊያ እና ኬንያ ውስጥ በኢትዮጵያ ድንበር ላይ የእሚገኙ ናቸው) ፤ የጉጂ እና ቦረና ከብት አርቢዎች አከባቢውን ይኖሩበት ነበር ። በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኦሮሞ ሕዝብ ፤ በወረራ በእሚይዛቸው ሕዝብ ላይ የእሚጭነውን የገዳ ስረዓትን አስተዋወቀ ።”
“Before the Oromo moved along the three river basins of Ganale. Galana Duli and Jalana Sagan, the Borana and Guji pastoralists settled these areas. In the fifteenth century, the Oromo developed the Gada system, which was later imposed on the people in the conquered territories. [116]“
ከእነዚኽ ዘገባ እንደ እምንረዳው ፤ ፖርቹጋል እና ዖቶማን ተርኮች ፤ የግራኝ ወረራ በከሸፈ ማግስት የኢትዮጵያን መንግሥት በሰሜን ወጥረው በያዙበት በእዚኽ ወቅት ፤ የዖሮሞ ሕዝብ የሕዝብን ስብጥር በመሠረታዊነት የእሚቀይር የገዳ ስረዓት የእሚባል ስረዓት ጋር ተዋውቆ ፤ ተንቀሳቃሽ እና ማዕከል የሌለው በመሆኑ የተለመደው የነገሥታቱ ጦር ሊደርስበት በእማይችልበት ኹኔታ ፤ አከባቢዎችን በድንገት በማጥቃት ፤ በገዳ ስረዓት የቦታዎችን ስም እና የሕዝቡን ስብጥር እየቀየረ ሐገር መውረሩን በደቡብ ገፋበት ።
ከላይ በአለው ዘገባም እንደ እምንረዳው ፤ ኦሮሞ ጉጂውን ቦረናውንም ኦሮሞ የአደረገው በእዚኽ አዲስ በተዋወቀው የገዳ ስረዓት አግባብ ነው ማለት ነው ።
ዖሮሞ በእዚኹ ዘመን ባስተዋወቀው ገዳ የእሚባል ስረዓቱ ፤ በእየደረሰባቸው ቦታዎች የእሚገኙ አከባቢዎችን ስም በመቀየር እና ሕዝቡንም በገዳ ስረዓት ማንነቱን በመቀየር ፤ ወረራ እና ጥቃት ብቻ ሰአይሆን የደረሰበትን ቦታ ፤ በገዳ ስረዓት ማደራጀት ውስጥ ገባ ። የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት መንግሥቱ ሐይለማሪያም፤ ስለገዳ ስረዓት ፖለቲካዊ እንደምታ ሲናገሩ ፦
“የኦሮሞ ማሕበረሰብ ወይም ነገድ ምናልባት አንድ ወጥ ደም ወይንም ዘር የነበረው ጥንት በቅድመ ገዳ ስረዓት እንጂ በድህረ ገዳ…የአንድ ቋንቋ ቤተሰብ እንጂ የአንድ ወጥ ዘር አይደለም ። [112]”
ተንቀሳቃሽ ከሆነ የከብት አርቢ ማሕበረሰብ ንቃት እና እድገት አካኼድ ውጭ በሆነ ኹኔታ የገዳን ስረዓት የተዋወቀው የዖሮሞ ሕዝብ ፤ አንዳንድ አጥኝዎች እንደ እሚሉት ፤ ኦሮሞ ይህን መሰሉን አካኼድ ያመጣው ፤ በዘላንነት ከብት አርቢ በነበረበት ኹኔታ የገጠመውን የግጦሽ መሬት እጥረት ለመቅረፍ ነው የእሚባለው ትንተና ትክክል አይመስልም ።
ለእዚኽ ኃሳብ መቃወሚያ ፤ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ፤ መንግሥቱ ኃይለማሪያም ዖሮሞን የግጦሽ መሬት ችግር ቢሆን ኖሮ ወራሪ እና ሰርጎ ገብ የአደረገው ፤ እጅግ ለምና እና ለግጦሽ አመቺ የነበረውን የደቡብ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ መሬት ትቶ ፤ ለብዙ መቶ ዓመታት የተኖረበት ከእዚኽም የተነሳ በተነፃፃሪነት የተፈጥሮ ኃብቱ የተራቆተበት እና የመሬት እጥረት ወደ አለበት ተራራማው ሸዋ እና አኹን ወሎ ወደተባለው አንጎት አይመጣም ነበር ይላሉ ።
ለእዚኽም መከራከሪያ ፤ ነፃ ፣ ሰፊ እና ለግጦሽ አመቺ መሬት ከሰሜኑ ይልቅ በደቡባዊ ኢትዮጵያ ፤ እንኳን የዛሬ 400 ዓመት ፤ ዛሬም በብዛት የእሚገኝ መሆኑንም በማስረጃነት ያቀርባሉ ፦
“…እንኳንስ በ15ኛው እና በ16ኛው ምዕተ ዓመታት ቀርቶ ዛሬም በደቡብ ኢትዮጵያ ለጦርነት የእሚያዳዳ የግጦሽ መሬት ችግር አለመኖሩን ስለምናውቅ ነው ።…ችግሩ ይኼ (የቁጥር መብዛት እና የመሬት ጥበት) ቢሆን ኖሮ የግጦሽ መሬት ለማግኘት ከፍተኛ የሕዝብ ክምችት ባለበት እና የመሬት ጥበት ችግር ወዳለበት የመሐልና የሰሜናዊ የሐገሪቷ ክፍል መኼድ መፍትኼ ሊሆን አይችልም ። [112]”
ስለ እዚኽ ሶማሌዎች ኦሮሞን እንዲያሳድዱ የአደረገው ፤ በኋላም ኦሮሞ እና ሶማሌ መላው ሱማሊያን እንዲቆጣጠሩ ከእዛኽም የኦሮሞ እና የሶማሌ ሕዝብ በተለያየ ደረጃ እና ግዜ ወደ ኢትዮጲያ እንዲሰርጉ በማድረግ ውስጥ በመሐከላቸው የገቡት በኢትዮጲያ ላይ ጅኃድ የማወጅ ፍላጎት የአላቸው የአረብ ሱልጣኖች ከፍተኛ ሚና አለ ማለት ነው።
ይኽን መልክ የነብረው የዖሮሞ ሰፊ ሰርጎ ገብነት ፤ እንቅስቃሴው ሰላማዊ የሕዝብ ሰፈራ ጉዳይ ሰአይሆን ፤ የዖሮሞ ሕዝብ በታሪኩ የአዳበረውን የዘላን እና ጦረኝነት የህይወት ዘይቤ ፤ አዲስ በተዋወቀው ገዳ በእሚባል ስረዓት ወይንም ይኽንን የገዳ ስረዓት ባስተዋወቀው ምን አልባትም በውስጣቸው ሰርገው የገቡት የጸረ ኢትዮጵያ ሙስሊም ሱልጣኖች ኃይል አማካኝነት ፤ በብዙ አቅጣጫ የተወጠረው የወቅቱ የኢትዮጵያ ነዋሪ ላይ የፖለቲካ የበላይነቱን ለመጫን የኼደበት አኳኋን መሆኑ ግልፅ ነው ።
ከእዚኽም የተነሳ ፤ በቻለበት ቦታ ኹሉ ፤ የሰዎችን እና የአከባቢን ስም ኹሉም በመቀየር ፤ አከባቢውን በጦር ኃይል ራሱን ለማስመሰል ተንቀሳቅሷል ።
ይኽም ታሪካዊ ኃቅ ፤ በተለይ በእዚኽ በእኛ ዘመን በአንዳንዶች ሲባል እንደ እምንሰማው ፤ ይኽን የዖሮሞን ከሶማሊ ላንድ ጅምሮ በባሊ አድርጎ ወደ መሐል ኢትዮጵያ የተሰራጨብትን ታሪክ እንደ አልተፈጠረ በመካድ እና አጉል ተረት ተረት እየፈጠሩ ፤ አማራ እና ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኦሮሞ ቀድሞ እስከ ባሌ ባለው የኢትዮጵያ ክፍል ነዋሪ እንደ አልነበረ ለማስመሰል የእሚደረገው አካኼድ ታሪካዊ እውነታ የሌለው ተራ ፕሮፖጋንዳ ነው።
ስለ እዚኽ ፦ የኦሮሞ ሕዝብ በሱማሊያ ውስጥ ፤ ከ10ኛው ምዕተ ዓመት አንስቶ ፤ መጀመሪያ በእንግሊዝ ሱማሌ ፤ ከእዛም በደቡብ ምሥራቅ ሶማሌ ወደ ሞቃዲሾ አከባቢ በኋላም በቆላማው ቤናዲር ሲኖር ቆይቶ ፤ በ16ኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ ወደ ኢትዮጲያ እንደ ሕዝብ መስረግ እንደ ጀመረ በአግባቡ በታሪክ የተመዘገበ ነው።
ስለ እዚኽ ፦ የኦሮሞ ሕዝብ ከ10ኛው ክፍለ ዘመን እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን መኖሪያው የዛሬው ሶማሊያ እንደ ሆነ እና ከእዛም በሶማሊ እና በባንቱ ሕዝብ በደረሰበት ጦርነት እና የኦሮሞን የኢትዮጲያ ወረራ ለራሳቸው ፖለቲካዊ ጥቅም በፈለጉ አረብ ሱልጣኖች አማካኝነት ፤ ከግራኝ ጦርነት በኋላ ፤ ማለትም በ16ኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ ላይ ፤ በአረብ ሱልጣኖች ሴራ እንደ ሕዝብ ኢትዮጲያ ውስጥ መግባት እንደ ጀመረ ነው ታሪክ የእሚነግረን።
ይኽ የኦሮሞ ታላቁ ስርገት ፤ በወቅቱ በተለያየ ዘርፈ ብዙ ችግር ለተደቆሰችው ኢትዮጵያ ሌላ አንድ ተጨማሪ የመከራ ገፅ የነበረ በመሆኑ ፤ ይኽ ወረራ በጣም በፍጥነት በእሚስፋፋበት ወቅት ፤ በዝዋይ በነበሩት ገዳማት የነበሩት ፤ እጅግ በሳሉ አባ ባሕርይ ፤ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1593 ዓ.ም. ዜናኹ ለጋላ በእሚለው እና በግዕዝ ጽፈውት ከእዚያኽም ወደ ጀርመንኛ ፣ እንግሊዘኛ በኋላም በጌታቸው ሐይሌ (ፕሮፌሰር) ወደ አማርኛ የተመለሰው መጽሐፍ ላይ ፤ ለምን ይኽን ታሪክ እንደጻፉ እና የኦሮሞ ጦር ፤ ከክርስቲያኑ በመጠኑም በያዘውም የጦር መሳሪያ ዝቅተኛ ሆኖ ሳለ ፤ በክርስቲያኑ ላይ ይህን ኹሉ ድል በአጭር ግዜ እንዴት ሊያገኝ ቻለ ብለው ተመራምረው ፤ የድሉ ምንጭ ነው ብለው የአሰቡትን እንዲኽ አስቀምጠውታል ፦
“‘የክፉውን ዜና እንደ ደጎች ዜና ለምን ጻፈ?’ የእሚለኝ ከአለ፟ ፥ ‘በኃይማኖት ጠላቶቻችን ሆነው ሳለ፟ የመሐመድ ታሪክ እና የእስላሞች ነገሥታት ታሪክ እንደ ተጻፈ ታይ ዘንድ መጽሐፍትን መርምር’ ስል መልስ እሰጠዋለሁ ።
“ እነዚኽ ኹሉም ብዙዎች ስለ ሆኑ ቱለማ ይባላሉ ። አብረው ይዋጉ ነበረ ። ከብዙ ዘመን በኋላ ተጣሉ እና አብረሐምና ሎጥ ከብቶቻቸው በበዛ ግዜ ፥ ‘ወይ አንተ በቀኝ እኔ በግራ ፥ ወይንም እኔ በቀኝ አንተ በግራ እንለያይ’ እንደ ተባባሉና እንደ ተለያዩ እርስ በርሳቸው ተለያዩ …
አዋቂዎች (እንዲህ እያሉ) ብዙ ምርምር ይመረምራሉ ፤ ‘እኛ ብዙዎች ፥ የጦር መሳሪያችን ብዙ ሆኖ ሳለ ጋላ እንዴት ይአሸንፈናል?’ ይላሉ ።
‘በሐጢያታችን ምክንያት እግዚአብሔር ፈቀደለት’ የእሚሉ አሉ ።’
ሕዝባችን ከዓስር ፆታ ስለ ተከፈለ ነው ። ከእነርሱ ውስጥ ዘጠኙ ፆታ ከውጊያ አይቀርቡም ፤ በፍርኃታቸው አያፍሩም ። አስረኛው ፆታ ግን የተቻለውን ያህል ይዋጋል ፥ ይጋደላል’ የእሚልም አለ ።
ቁጥራችን ብዙ ይኹን እንጂ ውጊያ የእሚችሉ ጥቂቶች ፥ ወደ ውጊያ የእማይቀርቡ ብዙዎች ናቸው ።
ከእነ እርሱ ውስጥ አንዱ ፥ ቁጥር የሌላቸው የመነኮሳት ወገን ነው ። እንደ እዚኽ ታሪክ ጸሐፊና ብጤዎች በልጅነቱ በትምህርት ላይ ሳለ መነኩሴዎች ሲደልሉት የእሚመነኩስ አለ ፤ ውጊያ ፈርቶ የእሚመነኩስ አለ ።
ኹለተኛው ወገን ደብተራ ይባላሉ ። መጽሐፍቱን እና የክህነቱን ሥራ ኹሉ ይማራሉ ፤ በእጃቸው ያጨበጭባሉ በእግራቸው ያሸበሽባሉ ። ስለ ፍርኃታቸው አያፍሩም ። ምሳሌነትን የአሮን ልጆች ከሆኑት ከሌዋውያን ከካህናት ይወስዳሉ ።
ሦሥተኛው ወገን ዣን ሐፀና እና ዣን መዓሠሬ ይባላሉ ። ፍርድ ይጠብቃሉ ፤ ከውጊያም ይጠበቃሉ ።
አራተኛው ወገን የመኳንንት ሚስቶች እና ወይዛዝሮች ደጋፎች ናቸው ፤ ኃይለኛ ወንዶች ፥ ጠንካራ ጎልማሶች (ሆነው ሳለ) ወደ ውጊያ አይቀርቡም ። ‘የሴቶች ሎሌዎች ነን’ ይላሉ ።
አምስተኛው ወገን ሽማግሊ ፥ ገዜ ፥ ባለ ርስት ይባላሉ ፤ መሬታቸውን ለገበሬ አካፍለው ያዝዙታል ፤ በፍርኃት አያፍሩም ።
ስድስተኛው ወገን ገበሬዎች ናቸው ፤ እርሻ ላይ ይውላሉ ፤ ስለ ውጊያ አንዳችም ኃሳብ የላቸውም ።
ሰባተኛው ወገን በንግድ የእሚጠቀሙና ለእራሳቸው የእሚያተርፉ ናቸው ።
ስምንተኛው ወገን እንደ አንጥረኞች ፥ ጸኃፍት ፥ (ልብስ/ቆዳ) ሰፊዎች ፥ አናጢዎች የአሉ፟ እና እነዚኽን የእሚመስሉ ጥበበኞች ናቸው ፤ ውጊያ አያውቁም ።
ዘጠነኛው ፆታ ልመናን ሥራ የአደረጉ አዝማሪዎች ፥ ባለከበሮዎች ፥ ባለበገናዎች ናቸው ። የሰጣቸውን ይባርኩታል ፤ ብጡል ምስጋናና ውዳሴ ከንቱ ይሰጡታል ። ያልሰጣቸውን ሲራገሙት እዳ አይሆንባቸውም ፤ ሕጋችን ነው ይላሉ ።
ከውጊያ በረጅሙ ይርቃሉ ።
ዓስረኛው ፆታ ጦርና ጋሻ የእሚይዙ ፥ ውጊያ የእሚችሉ ፥ ‘ለሩጫ የንጉሡን ፈለግ’ የእሚከተሉ ናቸው ።
በእነዚኽ ጥቂትነት ምክንያት አገራችን ጠፋች ።
ጋላ ግን እነ እዚኽ ያነሳናቸው ዘጠኝ ወገኖች የሉበትም ። ኹሉም ከደቂቅ እስከ ሊቅ ለውጊያ የሰለጠኑ ናቸው ። ስለ እዚኽ ያጠፉናል ፥ ይፈጁናል ። [115]”
አባ ባሕርይ በመጽሐፋቸው ምዕራፍ 19 ላይ ያስቀመጡት ይኽ የወቅቱን ፖለቲካዊ ቀውስ ምክንያት ለመተንተን የኼዱበት መንገድ ፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተጠቃሽ የሆነው መጽሐፋቸው የወቅቱን ታሪካዊ ኺደት በጥሩ ኹኔታ የእሚዘግብ ነው።
በእዚኽ ስፍራ አባ ባሕሪ እየአንጸባረቁ የአሉ፟ት ፦ በወቅቱ ፤ ለመላው የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ አዋቂ ፈተና የሆነበት ጥያቄ ፤ በቁጥር ብዙ ሆነን እና የተሻለ የጦር መሳሪያ ታጥቀን ፤ ከእኛ በቁጥር በእሚያንሰው እና ደካማ ጦር መሳሪያ በታጠቀው የኦሮሞ ሕዝብ እንዴት ይህን መሰል ተደጋጋሚ ሽንፈት ይደርስብናል? የእሚለው ጥያቄ ነበር ።
የጦር ብዛት እና የበላይነት ኖሮን ከተሸንፈን ፤ ሐጥያታችን የእግዚአብሔርን ቁጣ አምጥቶ ነው ብለው መጽሐፍ ቅዱስ ያጣቀሱ ነበሩ ። በእዚኽ ያልተስማሙት መነኩሴው አባ ባህሬይ ፤ ራመድ ብለው ፤ እኛ ፦
መንኩሴ ፣ ደብተራ ፣ ዳኛ ፣ የቤተመንግሥት አገልጋይ ፣ ዣን (Senator) ወይንም ባለ ርስት ፣ ገበሬ ፣ ነጋዴ ፣ ሞያተኛ እና ተዋንያን በእሚሉ ሞያ የተከፋፈለ ሕዝብ ስለ ሆንን ፤ የሕዝባችን ቁጥር ብዙ ቢሆንም ፤ ከአስሩ ዘጠኙ ወታደር አይደለም ፤ የኦሮሞ ሕዝብ ግን ኹሉም ወታደር ነው ፤ እንዲኽ ዓይነት ማሕበራዊ ክፍፍል ስለ ሌለው ፤ በእዚኽ ምክንያት ፤ ሕዝባችን ብዙ ቢሆንም የጦር ሰራዊታችን ትንሽ ነው ፤ ለእዚኽ ነው የተሸነፍነው ነው የእሚሉት ።
አባ ባሕሪ የወቅቱ ተወዳጅ አሰላሳይ እና ታሪክ ጸሐፊ ቢሆንም ፤ አንዳንድ ሰዎች በእዚኽ ከእላይ በተቀመጠው ክፍል ላይ ያስቀመጡትን ትንታኔ በአልተገባ መልኩ ሲጠቀሙበት ስለ እሚታይ ፤ በእኔ እምነት ይኽ የአባ ባሕሪ ትንታኔ ፤ ትክክለኛ የሆነው ይኽ ሽንፈት የእግዚአብሔር ቁጣ ሰአይሆን የወታደራዊ ስልት ልዩነት ፤ እኛን ተጠቂ እነርሱን አጥቂ ስለ አደረጋቸው ነው የእሚለው ብቻ መሆኑን መጠቆም ተገቢ ይመስለኛል።
ከእዛኽ በስተቀረ ግን ፤ ሌላው ዝርዝር በወቅቱ ስለ ነበረው ታሪክ እና ማሕበራዊ አድረጃጀት ጥሩ ታሪካዊ እና በሳል ገለፃ ቢሰጠንም ፤ ትክክለኛውን የኃይል ሚዛን ምንጭ የእሚጠቁም አይመስልም ።
የማሕበረሰብ ሳይንስ እንደ እሚያስረዳን ፤ ማሕበረሰብ ውስጥ በሞያ መከፋፈል ወይንም በአባ ባህረይ ቋንቋ የፆታ መከፋፈል የእድገት እንጂ የደካማነት እና የኋላ ቀርነት መገለጫ አይደለም ። ስለ እዚኽ የኢትዮጵያ የወቅቱ ሠራዊት ፤ ከመላው ሕዝቡ አስር እጅ ብቻ ስለ ሆነ እንደ ሕዝብ ብዙ ብንሆንም ሰራዊታችን ጥቂት ነው እና ለእዚኽ ነው የእምንሸፈው የእሚለው ትንታኔ ልክ አይደለም ።
ዛሬን እንኳን ብንወስድ በየትኛውም ማሕበረሰብ ውስጥ ፤ ወታደሩ የመላው ሕዝብ ጥቂት እጅ ነው ። የወቅቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወራሪ ከነበረው የዖሮሞ ሕዝብ ይልቅ በተለያየ ፆታ መከፋፈሉ ፤ የአለበት የማሕበረሰባዊ የእድገት ደረጃ የበላይነት መገለጫ እንጂ የደካማነት መገለጫ አይደለም ።
የወቅቱ የዖሮሞ ሕዝብ ልሙጥ እና ይኽን መሰል መኃበራዊ አደረጃጀት የሌለው መሆን እና ከሊቅ እስከ ደቂቅ ተሰባስቦ የዘረፋ ጦርነት ባህል ይዞ ፤ ልክ ኋላ ቀር የነበሩት የጀርመን ቪስጎቶች ፤ ከእነርሱ በብዙ እጥፍ የሰለጠነችው ሮም ላይ የአደረሱትን ወረራ ዓይነት ፤ ከእነርሱ ይልቅ በሰለጠነው እና በደረጀው የዘመኑ የኢትዮጵያ መንደሮች ላይ ፤ በድንገት መጥቶ ፤ ዘርፎ ፣ ገድሎ ፣ ሰልቦ እና ሴቶችን ይዞ መኼድ ፤ የእዛኽን ወቅት ዖሮሞ እንደ ሕዝብ በጣም ኋላ ቀር የማሕበረሰብ የእድገት ደረጃ ላይ ለመገኘቱ ማሳያ እንጂ የጥንካሬው ማሳያ አይደለም ።
ይኽም ብቻ ሳይሆን ትንታኔያቸው የወቅቱ የኢትዮጲያን መንግሥት የእሚገኝበት ከአቅሙ በላይ የሆነ አጣብቂኝ ፣ የጂኃዲስት ሱልጣኖቹ ሴራ እና የጥቃቱን ይዘት ከግምት የአስገባ አይደለም።
የወቅቱን የጦርነት ታሪክ ስናይ ፤ ለነገሥታቱ ሠራዊት ዋና ፈተና የሆነባቸው ፤ ከእላይ በዘረዘርናቸው ማዕበሎች ከመናጣቸው በአሻገር ፤ ይኽ አደጋ ጣይ ወራሪ ኃይል ፤ ሕዝባዊ የሽምቅ ተዋጊ በመሆኑ ፤ በጦር ግንባር ተገኝቶ የእሚገጋጠሙት በአለመሆኑ ነው ።
ልክ እንደ ግራኝ ሠራዊት መጀመሪያ ላይ እንደ ነበረው እና የአብዛኞቹ የሙስሊም የወቅቱ አደጋ ጣዮች ፤ በጣም ተንቀሳቃሽ እና በዋናነት ፤ ዘረፋ ፣ ጠለፋ እና ግድያ ግቡ በመሆኑ ፤ የመንግሥት ጦር ሳሳ በአለበት አከባቢ ድንገት መጥቶ ፤ ከብት ዘርፎ ፣ መንደር አቃጥሎ ፣ ሴቶች ጠልፎ ፣ ወዘተ ፤ ስለ እሚመለስ ፤ የእየ መንደሩን ነዋሪ ቋሚ ስጋት ውስጥ ከመክተቱ በአሻገር የመንግሥትን ጦር ከስፍራ ስፍራ እንዲንቀሳቀስ በማድረግ ማዛሉ ነው ወይንም ኋላ ቀር ስልቱ ነው ለመደበኛው ጦር ፈታኝ የአደረገው ።
በእዛኽ ላይ ፤ በእዚኽ መልኩ በዖሮሞ ወራሪ ሰላም እና ፀጥታው በቋሚነት አደጋ ውስጥ የገባበት ሕዝብ ፤ ቀኼውን እየተወ ራሱን ወደ ሰሜን ወደ መንግሥት ሲያስጠጋ ፤ ወራሪው ኃይል መንደሩን ተዘርዝሮ እያገኘው ፤ በገዳ ስረዓቱ በቀላሉ ለመለወጥ ክፍተትን ይሰጠዋል ።
ስለ እዚኽ ፤ የወቅቱ የኢትዮጲያ መንግሥት የችግሩን ፖለቲካዊ ምንጭ በአግባቡ በተረዳ አኳኋን ራሱን አደራጅቶ ፤ ቀድሞ ማጥቃት (Preemptive strike) ማድረግ እና የአከባቢ ሚሊሻ ማደራጀት ከአልቻለ በስተቀር ፤ የሞያ ክፍፍል ውስጥ የገባውን ሰፊውን የኢትዮጲያ ሕዝብ እንደ ገና ይኽንን የደረስከበትን ስልጣኔ ትተኽ ፤ እንደ ገና ዘራፊ ወታደር ኹን ቢሉት የእማይቻል ነገር ነው። የታሪክን መንኮራኩር በሕዝብ ላይ እንደ ገና ወደ ኋላ ማንኮራኮር የእማይሆን ነገር ነው።
የወቅቱ የኢትዮጲያ መንግሥት ተከላካይ ከእሚሆን ይልቅ የችግሩ ምንጭ ከአፍሪካ ቀንድ የእሚገኙ ወደቦች መሆናቸውን አውቆ በእነ እዚኽ አከባቢ የበላይነቱን ለማረጋገጥ በትጋት ቢሰራ ኖሮ የግራኝ ጦርነት ራሱ እዚኽም አይደርስም ነበር።
ሲያምጹ እና ጥቃት ሲያደርሱ ብቻ የምላሽ ምት ለመስጠት ከመንቀሳቀስ የችግሩን ምንጭ ማድረቅ ላይ ቢሰራ ችግሩ እዚኽም አይደርስም ነበር።
አንድ ግዜ ግን አደጋ የመጣሉ የማመጹ ስልት በሽምቅ ውጊያ መንግሥትን አሳስቶ በስተመጨረሻ መናገሻውን እስከ ማስለቀቀ ከደረሰ በኋላ ግን ምን አልባት አከባቢያዊ ሚሊሻ መገንባት መልስ ሊሆን ይችል ይሆናል እንጂ ቄሱን ፣ አዝማሪውን ፣ ነጋዴዎን ነፍጥ አንሳ ማለት አስቸጋሪ ነው።
ከወቅቱ ታሪክ እንደ እሚታየውም በኋላ ላይ መንግሥት ማገገም ሲጀምር ችግሩን በቁጥጥር ስር ያስገባው እስኪያጠቁ ጠብቆ ምላሽ በመስጠት ሳይሆን ቅድመ ጥቃት በማድረግ ነው።
ይኽን መሰል ይዘት የነበረው የዖሮሞ ወረራ የወቅቱ አራተኛው የኢትዮጵያ ነገሥታት አራተኛ ፈተና ምንጭ ሆኖ የዖሮምን ሕዝብ ከመኖሪያው ሶማሊያ አውጥቶ ደቡባዊ ኢትዮጲያ ውስጥ አስገባው።
በእዚኽ መልኩ ለአንድ ሙሉ መቶ ዓመታት ፤ በአራት የሐገር ውስጥ እና የውጭ ኃይሎች በደረሰባት መጠነ ሰፊ ጥቃት ፤ በተዳከመችው ኢትዮጵያ ነው ፤ ዘመነ መሣፍንትን በገሐድ ያስጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት የጀመረው እና ስድስተኛው የታሪካችን ክፍል የአልኹት እና የፓርቲ ፖለቲካ ኢትዮጵያን ፖለቲካ የእሚያውክበት ዘመን የተጀመረው ።
አንዳንዶች ሣልሣዊ ዳዊት ወይንም ዳዊት ሦሥተኛ ነው ተብለው መጠራት ያለባቸው ይላሉ ፤ ለእዚኽም ምክንያት ሲያቀርቡ ፤ ቀዳማዊ ዳዊት የእሚለው ለእስራኤሉ ንጉሥ ዳዊት የተቀመጠ የክብር ስም ሆኖ ፤ ዳግማዊ ዳዊት ደግሞ የአጼ ዘራ ያቆብ አባት የሆነው ከ1375 . – 1404 ዓ.ም. የነገሠው አጼ ዳዊት ስም ነው ይላሉ ። ↑
እንደ እሚታወቀው በእዚኽ በ12ኛው እና በ13ኛው ምዕተ ዓመት በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ የነበሩት የዛግዌ ስርወ መንግሥት ነጋሢዎች ነበሩ ።ቀደም በአለው ክፍል ለማየት እንደ ሞከርነው ፤ የዛግዌ ስርወ መንግሥት ነጋሢዎች ደግሞ ፤ ከአክሱም ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕጋዊ ነጋሢዎች ንግሥት ሳባ ከንጉሥ ሰለሞን የወለደችው የቀዳማዊ ምንሊክ የልጅ ልጆች ናቸው የእሚለው እድሜ ጠገብ ሐገራዊ የፖለቲካ ትርክት ምክንያት ፤ በሐገር ውስጥ እንደ ሕገ ወጥ ነጋሢዎች የእሚታዩ የነበረ በመሆኑ ፤ በሐገር ውስጥ ተቀባይነት ከማጣጣት እና እርሱንም ተከትለው የእሚመጡ የተለያዩ ችግሮችም ለመቋቋም ለየ፟ት የአለ የውጭ ግንኙነት የመመሥረት ፍላጎት ስለ ነበራቸው ፤ የቀሲስ ዮሐንስን ንግርት አስጀምረውት ይኾናል በእሚል መላምት ጥናት ቢደረግ ፤ እስከ አኹን ለቀሲስ ዮሐንስ ንግርት እንደ መነሻ መላምት ተወሰደው የማጣሪያ ጥናት ሲደረግባቸው መና ከቀሩት ይልቅ የተሻለ ውጤት የእሚያስገኝ ይመስላል ።
ስለ እዚኽ የዛግዌው ስርወ መንግሥት የነበረበትን ውስጣዊ ችግር ለመቋቋም ፤ በወቅቱ አውሮፓን የአሰጋውን የእስልምና መንግሥት እኔ አሸንፍላችኋላሁ በእሚል ለቀሲስ ዮሐንስ ንግርት መጀመሪያ የሆነውን ደብዳቤ ጽፏል የእሚለው ግምት ወደ ፊት ትኩረት የእሚገባው ሰአይሆን አይቀርም ። ↑
ንግርቱ በውስጡ በጣም የተጋነኑ እንደ ኤልደራዶ ዓይነት የግነት ነገሮችም አሉበት ፤ ለምሳሌ ፦ አንድቀንዳ (Unicorn) በእኛ ሐገር አለ የእሚል ሐተታ አለበት ይባላል ፤ ምንም እንኳን አንዳንዶች ይኼ ግነት ሰአይሆን አውራሪስን አመላካች ነው የእሚሉ ቢሆንም። ↑
የአጼ ዘራ ያዕቆብ አባት ነው በእዚኽ ክፍል ላይ የተጠቀሰው አጼ ዳዊት ። ይኽም ማለት አጼ ልብነ ድንግል አይደለም ማለት ነው። ↑
ጎርጎርዮስ የካቶሊክ ዕምነት ተከታይ የነበረ ኢትዮጵያዊ ምኹር ሲሆን ፤ ከሰሶኒዎስ ጦርነት በኋላ ካቶሊኮች ከኢትዮጵያ ሲባረሩ ፤ አብሮ ወደ ህንድ ፥ ከእዛም ወደ እየሩሳሌም ፥ እንደ ገና ከእዛኽም በኋላ ወደ ሮም እና በስተመጨረሻ ሉዶልፍ ጋር ጀርመን ኼዶ ፤ ዛሬ በጀርመን ያለው የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል ከሉዶልፍ ጋር አብሮ የመሰረተ ነው። ↑
በኢየሩሳኤም የእሚገኘውን የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ የሦሥት ቀን መቃብር። ↑
በኢየሩሳሌም የእሚገኘው ኢየሱስ ክርስቶስ ለሦሥት ቀን ተቀብሮበት የነበረው መቃብር። ↑
አረማዊ ብዬ የተረጎምኩት እማያምኑ የእሚለውን ስለሆነ ፤ ሙስሊም ያልሆኑ ክርስቲያኖችን ሆነ ሌሎች በኃላዊ እምነት የእሚከተለቱን የእሚያካትት ነው ፤ ከሙስሊሞች አንጻር። ↑
ለመጀመሪያ ግዜ ፤ ከፖርቹጋል ፥ በኬፕታወን ከእዛያኽም በደቡብ ምስራቅ አፍሪካ አሳብሮ ህንድ የደረሰው የባህር ተጓዥ። ↑
ንግሥት ሰብለ ወንጌል ፤ የአጼ ልብነ ድንግል ባለቤት እና የአጼ ገላውዴዎስ እናት። ↑
ቀሲስ ይኋንስ ወይንም ፕሬስተር ጆን ፤ ልክ እንደ አጼ የኢትዮጵያ ነጋሢዎች መጠሪያ ስለ መሰለው ነው ቀሲሱ የእሚለው ፤ ልክ አጼው እንደ ማለት ልንረዳው እንችላለን። ↑
አኹን ሰሜን ሱዳን ውስጥ የእሚገኝ ቀይ ባሕር ላይ ያለ የወደብ ከተማ። ↑
ቤኔሮ በእዛኽን ወቅት እናሪያ የእሚባለው አውራጃ ግዢ ወይንም ሹም የእሚጠራበት ስም ነው ። ↑