በእዚኽ መጽሐፍ ውስጥ በሦሥት ምዕራፎች ፤ የተለያዩ ፖለቲከኞች ሐገርን የእሚረዱበትን አግባብ ፣ የዓለም ሕዝብ ፖለቲካዊ ዝግመት በጠቅላላው እና የኢትዮጲያ ፖለቲካዊ ዝግመት በልዩ ኹኔታ አይተናል።
ይኽንንም የአደረግንበት ምክንያት ፤ ሐገራችን ኢትዮጲያ ፤ በዓለማችን ላይ እንደ ነበረች አንዲት ጥንታዊት ሐገር ፤ ቢያንስ ከዛሬ 100 ዓመት አስቀድሞ በሕዝባዊ መንግሥት መርህ አንጻር ተዋቅራ ፤ ይኽን መሰሉም መዋቅር በእሚፈጥርላት አመቺ ማሕበረ ኢከነሚ ታግዛ ፤ በዛሬው ዘመን በዓለም ላይ ከአሉ፟ ፤ የበለጸጉ ሐገራት ተራታ ልትመደብ ሲገባት ፤ ገሚስ በታሪካዊ ሰነካላዎች ፤ ገሚስ ደግሞ እነ እዚኽ ታሪካዊ ሰንካላዎች በፈጠሩዋቸው የማሕበረ ኢከነሚ ድቀት ምክንያት ፤ ይኽንን ታሪካዊ እጣ ፈንታዋን ሳትጨብጠው ቀርታለች ።
ሳትጨብጠው ቀርታለችም ብቻ ሰአይሆን ፤ እስካ አሁን በአለው አካኼድ ፤ ወደ እዚኽ ታሪካዊ እጣ ፈንታዋ ሊያስወንጭፋት የእሚችለው ሕዝባዊ ሕገ መንግሥት ባለቤት መሆን አልቻለችም።
ስለ እዚኽ ፤ ሐገራችን ኢትዮጲያ ወደ እዚኽ ታሪካዊ እጣ ፈንታዋ እንድ ትወነጭፍ ወይንም ለእዚኽ ቅድመ ኹኔታ የሆነውን ፥ ሕዝባዊ ሕገመንግሥት ኢትዮጲያ እንደ አትይዝ ያደረጉዋትን ምክንያቶች ፣ እስከ አኹን የነበሩት ሕገመንግሥቶች ከሕዝባዊነት አንጻር የነበረባቸውን ችግሮች ማሳየት እና የአዲስ ሕዝባዊ ሕገ መንግሥት አስፈላጊነትን ለማስረዳት ነው ፤ የመጽሐፉ ዋና ግብ።
ነገር ግን ፤ ኢትዮጲያ ሕዝባዊ ሕገመንግሥት እንደ አትይዝ ያደረጉዋትን ምክንያቶች ፣ እስከ አኹን የነበሩት ሕገመንግሥቶች ከሕዝባዊነት አንጻር የነበረባቸውን ችግሮች ማሳየት እና የአዲስ ሕዝባዊ ሕገ መንግሥት አስፈላጊነትን ፤ ብቻ አይተን ወይንም ችግሩን ብቻ ዘርዝረን ብንጭርሰው ፤ መጽሐፉ ሙሉ አይሆንም።
በእዚኽም መሠረት ፤ በእዚኽ አራተኛው የመጽሐፍ ምዕራፍ የመጨረሻ ንዑስ በኹለት የንዑስ ንዑስ ክፍሎች ከፋፍለን፦
ሆኖ ቀርቧል።